ህወሓት አማራንና ኦሮሞን ለማጣላት የተቀነባበረ የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ በአዲስ መልክ ጀምሯል

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

የህወሓት ካድሬዎች ለጸረ-ለውጥ የሶሻል ሚዲያ ዘመቻቸው ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱ የኦሮሞና የአማራ በሚመስሉ ስሞች ብዙ ሺህ የፌስቡክና የትዊተር አካውንቶች ከፍተው በመርዝ የተለወሱ አስተያየቶችን በመጻፍ ጠብ መጫር ነው። የኦሮሞንና አማራ ህዝብን ለማጣላት ህወሓት የማያደርገው ነገር አይኖርም። አጼ ምኒሊክ የኦሮሞ ሴቶችን ጡት ቆርጠዋል የሚል የውሸት አፈታሪክ በመንዛት አርሲ ውስጥ በሃያ ሚሊዮን ብር የተቆረጠ ጡት ሃ ውልት ያቆመ መሰሪ ድርጅት መሆኑን አንርሳ።

ሰሞኑን ኦህዴድ የኢትዮጵያን መንግስት ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል የሚል አሳሳች ወሬ በስፋት በሶሻል ሚዲያ እየተነዛ ነው። የዚህ ወሬ ምንጭ እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ከባድ አይደለም። እንደገዢ ፓርቲ ቁልፍ ቦታዎችን ኦህዴድ ሊቆጣጠር ይገባል። በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሌሎቹ ድርጅቶች እራሳቸውን ከወያኔ ሰላዮችና ካድሬዎች ሳያጠሩ ለእነሱ ቁልፍ የመንግስት ቦታዎች መስጠት ለለውጡ እንቅስቃሴ አደገኛ ነው። የመረጃና ደህንነት ሚኒስቴር፣ ለምሳሌ፣ በኦህዴድ ስር መሆን ሲገባው አቋሙ ገና በእርግጠኝነት ያልታወቀው የብአዴን አባል ጄኔራል አደም መሃመድ እጅ ነው ያለው።

ኦህዴድ ሀገሪቱን በአግባቡ እስካስተዳደረና ወደ ዴሞክራሲ ጎዳና እስከመራ ድረስ ለጊዜው መንግስትን ሙሉ በሙሉ ቢቆጣጠር ምን ክፋት አለው? ቁልፍ ከሆኑ የሀገር ጸጥታ ሃላፊነት ቦታዎች ውጭ የተለያዩ ድርጅቶች አባላት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ተመድበዋል። ለምሳሌ የፓርላማ አፈጉባኤ፣ የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የንግድ ሚኒስቴር፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የፋይናንስ ሚኒስቴር፣ የመረጃና ደህንነት፣ የኢንሳ፣ እና ሌሎችም በርካታ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን መስርያ ቤቶች ሃላፊዎች የኦህዴድ አባላት አይደሉም።

ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህን ህወሓት ከአንዳንድ የስልጣን ጥማት ከተጠናወታቸው በአቋራጭ ስልጣን ላይ መውጣት ከሚከጅሉ የከሰሩ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የከፈተውን የፕሮፕጋንዳ ዘመቻ ለመቁቋምና የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመደገፍ እንስራ።