የአሜሪካን ፕሬዚዳንታዊ ሽልማት ያሸነፉት ኢትዮጵያዊው የሂሳብ ሊቅ 

ኢትዮጵያዊው ዶክተር ሙላቱ ለማ በአሜሪካ ጆርጂያ ግዛት የሳቫና ስቴት ዩንቨርስቲ የሂሳብ ፕሮፈሰር ናቸው። የዘንድሮውን አሜሪካ ከፍተኛ የፕሬዚዳንታዊ ሽልማት ካሸነፉ 12 ታላላቅ ሰዎች ውስጥም አንዱ ናቸው። ፕሮፈሰር ሙላቱ ተወልደው ያደጉት በአርሲ ዞን ሳቩሬ ከተማነዉ። የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አግኝተዋል።…