በሳውዲ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሰብዓዊ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ተገለፀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በሳውዲ እስር ቤቶች የሚገኙ ስደተኞች ሁኔታ አሳሳቢ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የስደትድርጅት ገለፀ።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከጀኔቫ ትናንት ባወጣው ዘገባ በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት የታሰሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሰብዓዊ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱን አሳስቧል።
በቅርቡ በተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል የሰዎች መጨናነቅ ፣ ለሰዎች የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ዕቃዎች እጥረት እና የጤና እና የንፅህና አጠባበቅ ሁኔታዎችን እንዲሁም የእርዳታ ልመናዎች ድርጅቱ መመልከቱን ጠቅሷል። ስደተኞች በተለይም ለእስር የተዳረጉት ከሚያጋጥማቸው መድልዎ ፣ የውጭ ዜጎች ጥላቻ ፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የጉልበት ብዝበዛ አደጋ በተጨማሪ ከጎርጎሪያኑ 2020 መጀመሪያ ጀምሮ በድንገት ለተከሰተው የኮቪድ -19 በሽታ ተጋላጭነታቸውም ጨምሯል ሲል አይ ኦ ኤም ገልጿል።ስለሆነም ሀገራት ምንም ይሁን ምን በሁሉም ለህዝብ የጤና በሚሰጡ ምላሾች ስደተኞችን ማካተታቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርቧል ፡፡
No photo description available.በእንደዚህ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የስደተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ የአስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኙ ድርጅቱ ተማፅኗል ፡፡ ይህ ድጋፍ ከመጡበት ሀገር የሚደረግን ዘላቂ የመልሶ ማቋቋምንና በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው የመመለስ አማራጮችን እንደሚያጠቃልል አመልክቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ስደተኞችን በግዳጅ መመለስና በኮቪድ-19 ሰበብ በአንድ አካባቢ ማጎር እንዲገታ ዓለም አቀፉ የስደት ድርጅትና እና የተባበሩት መንግስታት የስደት ትስስር ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህ ይልቅ ለህፃናት፣ ለቤተሰብ አባላትና ተጋላጭ ለሆኑ ስደተኞች ቅድሚያ በመስጠት ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ አማራጮችን እንዲጠቀሙ መክረዋል። DW