ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል እና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መሪዎች ጋር ውይይት አደረጉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከክልል እና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ጠንካራ እና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ባህልን ለመገንባት በምንንደረደርበት በዚህ ወቅት፣ ባለፉት ሳምንታት የተካሄዱት የፖለቲካ የውይይት መድረኮች ጠቀሜታቸው የላቀ ነው። ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ዛሬ ባደረግነው ውይይት፣ በልዩ ልዩ ጭብጦች ላይ በማተኮር ተመሳሳይ የውይይት መድረኮችን ለማስቀጠል ተስማምተናል። – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ውይይቱ በዋናነት በሀገራዊ መግባባት ላይ የተደረገውን ውይይት ምን እንደሚመስል መገምገም እና ቀጣይ በምን ሁኔታ ውይይቶች ይካሄዱ የሚለውን ለመወያየት ነው።
አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደገለጹት የተደረጉ ውይይቶች በፓርቲዎች መካከል ፉክክር እንዲደረግ በር የከፈተ እና መቀራረብ የፈጠረ ነው ብለዋል።ታይተው የነበሩ ችግሮች እየተቀረፉ መምጣታቸውንም አንስተዋል።

በሚቀጥለው ጊዜ ምን ይደረግ በሚለው ጉዳይ ላይም አራት ርእሰ ጉዳዮችን መርጠዋል።
እነዚህም
• ህገ መንግስት እና ህግ መንግስታዊነት ስር በኢትዮጵያ የቅራኔ ምንጭ ላይ ውይይት፣
• የፖለቲካ አደረጃጀቶች ምን መምሰል አለበት፣
• የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሰባሰብ በሚመለከት እና
• ትክክለኛ ምርጫ ምን ማለት ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲደረጉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫው ስርዓቱ ምን ይሁን እንዲሁም በምን መልኩ ምርጫውን ማከናውን አለበት በሚሉ ጉዳይ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው ።