በተከለከበት አዳራሽ ህዝብ አክብሮት ፍቅርን አቀነቀነ – ብሩክ ሰይፉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“የምንሊክ አምላክ የሃይለሥላሴ አምላክ የበላይ ዘለቀ አምላክ የዘርአይ ደረስ የአብዲሳ አጋ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን”።
ቴዲ አፍሮ።


ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ከተደረጉ አስገራሚ ክንውኖች ውስጥ አንዱ ገራሚ ነገር የፕሬዚዳንት ኢሳያስ በአማርኛ መናገር ብቻ ሳይሆን ተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ የኤርትራ ታሪክ እና ኢሳያስ አምርረው የሚጠሏቸውን ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን በድፍረት ጠርቶ ማመስገኑ ነው። አፄ ምኒልክ ከጣልያን ጋር አብረው የነበሩትን የሃማሴንን ተወላጆች የቀጡብን ከመረብ ምላሽ ብለው ያገለሉን ብለው ለነፃነት ትግላቸው ምክንያት የሚያረጉትን ንጉስ ነው በመሪያቸው ፊት ያመሰገነው። አፄ ሃይለሥላሴንም ፌዴሬሽኑን አፍርሰው በዩንየን ደባለቁን ብለው የሚከሷቸው ናቸው። በላይ ዘለቀም ጣልያንን ከነኤርትራዊ አስካሪዎቻቸው የደመሰሰ ታላቅ አማራ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ነበር ።

ከሁሉም ለየት ባለ መልኩ ደግሞ ዘርአይ ደረስ ኤርትራዊ ሲሆን በሮም አደባባይ ያን ጀግንነት የፈፀመው የኢትዮጵያን የንጉሳዊ መንግስት መለያ ሞአ አንበሳ ሃውልትን በምርኮኝነት አይቶ በመበሳጨቱ ነበር። ቴዲ አፍሮም ይህንን ጠንቅቆ ያውቃል። ግን በድፍረት ይህንን ተናግሮ በመደመር መሃልም በእርቅ መሃልም ኢትዮጵያውያን ጅግኖቻችንን እንደማንረሳ አሳይቷል።
ግን በሚያሳዝን ሁኔታ በማህበራዊ ሚድያ እንደምናየው ብዙዎች ለምን በደንብ አልዘፈነም ብለው ስለኢትዮጵያ ምክንያት ለሃያ አመታት ጥርስ እንዳልተነከሰበት ስንትስ ገንዘብ ከእነ አላሙዲ አልፈልግም ብሎ እንዳልተወ አሁን ገንዘብ ስላልተከፈለው ነው ብሎ መስደብ እጅግ በጣም ከስልጣኔ የራቀ ብልግና ነው። ቴዲ አፍሮ አርቲስት ቢሆንም ሰው ነው። ከረጅም ጉዞ እንደመምጣቱ ድካም ግዜያዊ የጤንነት እክል እና ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። በዛ ላይ ዘፋኝ የሆነ የክብር እንግዳ ሁሉ ተነስቶ መዝፈን የለበትም። እንደቴዲ ለሃገሩ ብዙ ያቀነቀነ ሰው የክብር እንግዳ ሆኖ ሲጠራ መስተናገድ እንጂ ማስተናገድም አይጠበቅበትም። 


ጥፋትስ ቢኖር የሃያ አመት ውለታ በአንድ ምሽት አለመዝፈን መሻር ያስተዛዝባል። እኔም በግሌ ቴዲ አፍሮ እዚህ በአትላንታ ከተማ በተደረገ ኮንሰርት ላይ ለኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ታዳሚዎቹ አንድ ነን እያለ ስዘፍን እና በቃላትም ሲሰብክ ከብዙ አመታት በፊት ሰምቼዋለሁ። ይህ ህልሙ ተሳክቶለታል። አርፎ በክብር እንግድነት ቁጭ ብሎ እንዳትደርስ በተባለበት አዳራሽ ፈጣሪውን ያመስግንበት።