በጎንደር የጎበዝ አለቆችን ለመያዝ በሕወሓት ሰራዊት ጦርነት ተከፍቷል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በደቡብ ጎንደር ሊቦ ከምከም ወረዳ የሚገኘው የጎበዝ አለቃ ጀግናው አረጋ በ 03/11/2010 ወደ አመሻሹ ላይ የጎበዝ አለቃውን አረጋን ለማፈን የመከላከያ ልብስ የለበሱ የህዋሐት ቅጥረኛ ወታደሮች በአካባቢው ተኩስ ከፍተዋል ።

ማምሻውን ከወታደሮች ጋር እየተደረገ ባለው የተኩስ ልውውጥ የጎበዝ አለቃውን አረጋን አሳልፈን አንሰጥም ያሉት የጀግናው አረጋ ግብረ አበሮች ሶስቱ መስዋአት ሆነዋል።

በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ገበሬ የይድረሱልን ጥሪውን አስተላልፋልን በማለት ከወታደሩ ጋር እየተፋለመ ይገኛል።

መልዕክቱ በፍጥነት ለመላው የአካባቢው አማራ ህዝብ እንዲደርስ ይተባበሩን ።
የጎበዝ አለቆችን ፎቶ አታውጡ አትቸኩሉ ግዜው ገና ነው ሲባሉ ያልሰሙ አክተቪስቶች እነሆ ትርፉ ይህ ነው። ስርዓቱ ሲፈልጋቸው የቆዩ ጀግና አርብኛ የጎበዝ አለቆች ፎቷቸው በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ምክንያት ለህዝብ ይፋ ከሆነበት ግዜ አንስቶ ወያኔ አደኑን ውስጥ ውስጡን መጀመሩን መረጃዎች እየደረሱን ነው።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በድጋፉ ሰልፉ ላይ ለህዝብ ፎቷቸውና ማንነታቸው ይፋ የሆኑት ብሎም ማንነታቸው በአደባባይ የተገለፁት ጀግና አርብኞች /የጎበዝ አለቆች በወያኔ ደህንነቶች እየታደኑ መሆኑን ይህ ጥብቅ መረጃ ከበቂ በላይ ነው ።

ምንጭ ኢትዮጵያን ዲጄ