በትግራይ ክልል ምርጫ እናደርጋለን የሚለው ነገር ከጸጥታም ከህግም አኳያ በአግባቡ መታየት አለበት – ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
«ያለ ጦርነት ሀሳቤን ወደ መድረክ ማቅረብ አልችልም የሚለው ባህሪ በሶማሊያ የነበሩ የጦር አበጋዞች ነው» -ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ
Image may contain: 1 person, sitting, eyeglasses and indoor(ኢፕድ) – በጦርነት ካልሆነ በስተቀር ሀሳቤን ወደ መድረክ ማቅረብ አልችልም የሚለው ባህሪ ከፖለቲከኞች የሚጠበቅ ሳይሆን በሶማሊያ የነበሩ የጦር አበጋዞች መሆኑን ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ አስታወቁ። በትግራይ ክልል ምርጫ እናደርጋለን የሚለው ነገር ከጸጥታም ከህግም አኳያ በአግባቡ መታየት እንዳለበትም ጠቁመዋል።
ሌተናል ጄነራል ባጫ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በጦርነት ካልሆነ በስተቀር ሀሳቤን ወደ መድረክ ማቅረብ አልችልም የሚለው የፖለቲከኛ ባህሪ አይደለም። ይልቁንም የዚህ አይነቱ ባህሪ በሶማሊያ የነበሩ የጦር አበጋዞች ባህሪ ነው። ይህ ባህሪ ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ብዙ ዋጋ ከማስከፈል ባለፈ ያመጣው መፍትሔ አልነበረም።
«200ሺ ይሁን 400ሺ ወጣቶችን ሰብስቦ ጠመንጃ ማሸከም ዋጋ የለውም» ያሉት ሌተናል ጄነራል ባጫ ጦርነትን ማሸነፍ የሚቻለው መሳሪያ በመከመር፣ የሰው ኃይል በማብዛት እና ዘራፍ በማለት አለመሆኑንም ጠቅሰዋል። ከጦርነት ውጭ ይህን ነገር ላገኝ አልችልም ብለህ ህዝቡን የምታሳምንበት በቂ ምክንያት ሊኖርህ ይገባል። አሁን ባለው የሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚወስድ ምንም ነገር እንደሌለም አስረድተዋል።
መንግሥት ከማንኛውም ክልል ጋር ጦርነት ሊገጥም እንደማይችል ያስገነዘቡት ሌተናል ጄነራል ባጫ፣ የትኛውም ክልል የፌዴራል መንግሥትን ጦርነት ሊገጥም እንደማይችልና ይህን የሚያደርግ ከሆነ አላማውን እንደሚስት አስረድተዋል። «እንደዛ አይነት ነገር ይመጣል ብዬም አላስብም» ያሉት ጄኔራሉ ፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ግን ጦርነት ሊኖር ይችላል የሚሉ አስተሳሰቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
“በኢትዮጵያ ጦርነት ሊኖር አይችልም። ምክንያቱም የፌዴራል መንግሥቱን የሚዋጋ አካል ካለ ከሁሉም ክልሎች ጋር ይዋጋል ማለት ነው» በማለት ገልፀዋል። የፌዴራል መንግሥትን መዋጋት ማለት ሉዓላዊነትን መጣስ ወይም መፈንቅለ መንግሥት ማድረግ እንደሆነም አብራርተዋል። በመሆኑም ጦርነት የሚባለው ነገር ፈፅሞ ሊሆን የሚችል ጉዳይ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።
እንደ ጄነራሉ ገለፃ፤ አንደኛ ማንኛውም ክልል የፌዴራል መንግሥቱን መግጠም የሚችል አቅም የለውም። ክላሽን አሸክመህ ከታንክና ከምሳኤሎች ጋር የምታጋጥመው ሰው አይኖርም።እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ የሚገባ ወጣትም አይኖርም። ይህን አደርጋለው የሚል ካለ ሞኝ ነው። ማንም ሰው ከእንደዚህ አይነት ራስን የማጥፋት እርምጃ ይወስዳል ተብሎም አይታመንም።
አንድ ክልል ተነስቶ የፌዴራል መንግስትን በጦርነት አፈሙዝ አሸንፊ የሆነ ነገር አደርጋለሁ ብሎ ካሰበ የእሳት ራት እንደሚሆን አስገንዝበዋል። ጦርነት ሰውን፣ ኢኮኖሚ አውዳሚና ድህነትን የሚያባብስ በመሆኑ በየትኛውም መመዘኛ የሚመከር እንዳልሆነም አመልክተዋል።
በሌላ በኩልም “በትግራይ ክልል ምርጫ እናደርጋለን የሚለው ነገር ከጸጥታም ከህግም አኳያ በአግባቡ መታየት አለበት» በማለት ተናግረዋል። ምርጫን የሚመራው በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የምርጫ ቦርድ እንጂ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲ አለመሆኑን ጠቅሰው ማንኛውም ተወዳዳሪ ፓርቲ ምርጫ ማዘጋጀት እንደማይችል አመልክተዋል።
ምርጫን የሚያዘጋጀው ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ የሆነ በፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቋቋም በአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን መሆኑን አስታውሰዋል። «ምርጫ እናዘጋጃለን የሚሉት ወንድሞቻችን እነሱ የፖለቲካ ፓርቲ እንጂ ምርጫ ኮሚሽን አይደሉም፤ የረሱትና ያላወቁት ነገር የፖለቲካ ፓርቲ መሆናቸውን ነው» ያሉት ሌተናል ጄነራሉ በክልል አሸናፊ ፓርቲ ቢሆኑም ምርጫን የማዘጋጀት ስልጣን እንደሌላቸው ተናግረዋል።ይህ አንድ የጸጥታ መደፍረስ ምንጭ ሊሆን ስለሚችል ቢታሰብበት መልካም እንደሆነ መክረዋል ።
መንግስት በአንዳንድ ጉዳዮች ትእግስት ማድረጉ ትክክል ቢሆንም ወንጀል ላይ በተለይም ሊታለፍ በማይገባ ወንጀል ትእግስት ማድረግ እንደማይገባው አስገንዝበዋል። «ከመጋቢት 24 ቀን 2010ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ወንጀል የሚፈጸመው በተመሳሳይ ቡድን ነው ያሉት ሌተናል ጄነራሉ፤ መንግስት ይህን ቡድን ከያለበት መልቀም እንደሚገባው አሳስበዋል። ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብም ከሰሜን ትግራይ ጀምሮ እስከ ደቡብ ዶሎ ድረስ፣ ከምስራቅ ዋርዴር እስከ ጋምቤላ ድረስ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚተባበር ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።