1 ሺህ 441ኛው የአረፋ በዓል ከነገ በስቲያ አርብ ይከበራል


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
1 ሺህ 441ኛው የአረፋ በዓል ከነገ በስቲያ አርብ ይከበራል
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እንድሪስ በዓሉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአረፋ በዓልን ሲያከብር የኮቪድ19 መከላከያ መንገዶችን እና የተቀመጡ ክልከላዎችን በመተግበር ሊሆን ይገባል – የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
(ኤፍ ቢ ሲ) ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአረፋ በዓልን ሲያከብር በእምነቱ የተቀመጡ የወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን ተግባራዊ በማድረግ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ።
Image may contain: 1 personየምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እንድሪስ በዓሉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብም ይሁን ሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ኮሮናን በመከላከል ረገድ ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የምናከብረው እንደ ቀደሙት አመታት በአንድ ላይ ተሰባስበን ሳይሆን ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በመከወን መሆን ይገባዋልም ነው ያሉት፡፡
ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአረፋ በዓል ላይ የተቸገሩትን በመርዳትና የታመሙትን በመጠየቅ ሰብአዊ ተግባር እንዲፈጽምም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም ሰብአዊነትን በተግባር በማሳየት እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በያለበት ቦታ ሁሉ የዱዓ ፀሎት በማድረግ በአሉን እንዲያከብርም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
1 ሺህ 441ኛው የአረፋ በዓል ከነገ በስቲያ አርብ የሚከበር ይሆናል፡፡