የኮቪድ86 እና የኮቪድ97 ያልተቀደሰ ጋብቻ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ተቃዋሚ ነን ባዮች የከሰሩ ፖለቲከኞች ሕገ መንግስታዊ ቀውስ ለመፍጠር መንግስትን ጠልፎ በመጣል ሰላምና ደሕንነትን ለማደፍረስ ኮቪድ 19ን ሰበብ አድርጎ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ እየተራወጡ ይገኛሉ

የኮቪድ86 እና የኮቪድ97 ያልተቀደሰ ጋብቻ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያልተቀደሰ ጋብቻ ፣ አደርባይነት፣ አስመሳይነት፣ ሴራ፣ የአቋራጭ ሳቦታጅ ወዘተ በተደጋጋሚ ስለሚደራረብ በክሕደት የተሞላና ወረት የደለለው ነው። ተቃዋሚ ነን ባዮች የከሰሩ ፖለቲከኞች ሕገ መንግስታዊ ቀውስ ለመፍጠር መንግስትን ጠልፎ በመጣል ሰላምና ደሕንነትን ለማደፍረስ እየተራወጡ ይገኛሉ

ኮቪድ 19ን ሰበብ አድርጎ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ ያሰፈሰፉት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በጋራ ሀገር መምራት ይቅርና ተስማምተው አንዲት ስራ ለመስራት የሚያስችላቸው አሰራር፣ ባህልም ሆነ የስነ ልቦና ዝግጁነት የላቸውም። የጋራ ግንዛቤን መፍጠር አለመቻል፣ ግትርነትና የስልጣን ጥመኝነት ዋነኛ ችግሮቻቸው ናቸው።

በሽግ ግር መንግስት ስም የስልጣን ጥምን ብቻ ለማርካት የሚደረግ ሩጫ በፍጹም አይሳካም። ሕዝቡም ተቃዋሚዎች ቢወቅጣቸው እንቦጭ ስለሆኑ ሕዝቡ አይፈልጋቸውም። መንግስት ከመስከረም በኃላ ለሚከሰተው ችግር አራት አማራጮች እስካቀረበ ድረስ በአማራጮቹ ዙሪያ ተወያይቶ መፍትሔ ከማምጣት ይልቅ የኛ ሽግ ግር መንግስት ካልሆነ የሚል ግትርነት ተቀባይነት የለውም። #MinilikSalsawi