እረፍት ላይ ያሉ ተማሪዎች ከአስተማሪዎቻችን የሚላኩልንን የጥናት ጽሁፎችና መጽሃፍት በኢንተርኔት ችግር ልንጠቀም አልቻልንም አሉ

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

DW : የኮሮና ተኅዋሲን መዛመት ለመግታት ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ተማሪዎች በቤታቸው እንዲቆዩ ከተወሰነ ጀምሮ በበጎ ተግባር ላይ ተሰማርተው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ዴቼ ቬለ ያነጋገራቸው ተማሪዎች ገለጹ።
ከአስተማሪዎቻቸው በቴሌ ግራም የጥናት ጽሁፎችና መጽሃፍት አልፎ አልፎ ይደርሰናል የሚሉት ተማሪዎቹ የተሳለጠ የኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት ለማንበብና ጊዜያቸውን በአግባቡ ለመጠቀም እንደተቸገሩም ተናግረዋል።
ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የጠቅላላ ትምህርት ተማሪዎች በእጃቸው ያሉ የሚነበቡ መጽሃፍትን እንዲያነቡ ፣ ትምህርት በሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንዲከታተሉ ጥረት እየተደረገ ነው ያለው ህምህርት ሚኒስቴር ፣ ይህ ማለህ ግን ተማሪዎቹ ከመምህሮቻቸውና ትምህርት ቤት ያገኙት የነበረውን እውቀት ቤታቸው ሆነው እንዲጨብጡ ይጠበቃል ማለት አይደለም ብሏል።