በሃሰት የኮሮና ቫይረስ አለብኝ ያለች ሴት በቁጥጥር ስር ዋለች

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

በሃሰት የኮሮና ቫይረስ አለብኝ ያለች ሴት በቁጥጥር ስር ዋለች
በሃሰት የኮሮና ተኅዋሲ አለብኝ በማለት ወደ 8335 የደወለችው የጎንደር ከተማ ነዋሪ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለች። ወጣቷ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 16 በግል ስራ ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን ከአረብ ሃገር በቅርቡ እንደመጣች በመግለጽ የበሽታው ምልክት እንደታየባትና እርዳታ እንደምትሻ ተናግራ ነበር ብሏል የከተማዋ ፖሊስ።
ይህንን ተከትሎ የክልልና የዞን የጤና ባለሙያዎች ተነጋግረው ልጅቷን ሲያፈላልጉ ስልኳን በመዝጋት ተደብቃ የነበር ቢሆንም ፣ በ ጂ ፒ ኤስ ተፈልጋ ተገኝታለች ተብሏል። በከተማዋ ፖሊስ መምሪያ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊው ረዳት ኢንስፔክተር ወንድምሁነኝ ተሻገር ለ ዶቼ ቬለ እንዳሉት፣ ወጣቷ ያለችበት ታውቆ በጤና ባለሙያዎቹ የሙቀት ልኬት ሲደረግላት ሙሉ ጤነኛነቷ ተረጋግጧል፣ የበሽታው ምልክትም አልተገኜባትም ብለዋል።
ወጣቷ ተፈልጋ እንደተገኘች መደወሏን ክዳ የነበረ ሲሆን ያንን ለምን እንዳደረገች ስትጠየቅ ምናልባት በሽታው ካለብኝ ወደ ማግለያ ክፍል ልወሰድ ስለምችል ያንን በመፍራት ነዉ ብላለች ብለዋል ኃላፊው።
ከአረብ ነገር ነው የመጣሁት በማለት የተሳሳተ መረጃ ለምን እንደሰጠችም በ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ሆና እየተጠየቀች መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል። DW