የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ባለስልጣናት ራሳቸዉ ያወጡትን ደንብ እየጣሱ ነው።

DW : መመሪያና ማስጠንቀቂያዉን የሚሰጡት በተለይ የአማራ ክልል የገዢዉ ፓርቲ (የብልፅግና) ባለስልጣናት፣ ራሳቸዉ ያወጡትን ደንብ እየጣሱ መሆናቸዉን ነዋሪዎች አጋለጡ

በፍጥነት የሚዛመተዉን የኮሮናተሕዋሲ ስርጭትን ለመግታት የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሁሉም ሐገራት መንግሥታት፣ ዜጎች አንዳቸዉ ከሌላቸዉ እንዲርቁ፣እጃቸዉን እንዲታጠቡና ሌሎች ጥንቅቄዎችን እንዲያደርጉ እየመከረ፤ እያሳሰበና እያስጠነቀቀ ነዉ።ይሁንና መመሪያና ማስጠንቀቂያዉን የሚሰጡት በተለይ የአማራ ክልል የገዢዉ ፓርቲ (የብልፅግና) ባለስልጣናት፣ ራሳቸዉ ያወጡትን ደንብ እየጣሱ መሆናቸዉን ነዋሪዎች አጋለጡ።የባሕርዳሩ DW ያነጋገራቸዉ የአማራ መስተዳድር ነዋሪዎች እንደሚሉት የብልፅግና ፓርቲ ባለስልጣናት ካለፈዉ ሮብ ጀምሮ በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ የፓርቲዉን አባላት በየአዳራሹ ሰብስበዉ «ሥልጠና» ያሉትን ዉይይት እያደረጉ ነዉ።የየአካባቢዉ ነዋሪም ቢሆን የአደገኛዉን ተሕዋሲ ስርጭት ለመከላከል ማድረግ የሚገባዉን ጥንቃቄ አያደርግም።