ባልደራስና መኢአድ ቅንጅት ለመመስረት ሊፈራረሙ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ባልደራስና መኢአድ ቅንጅት ሊመሰርቱ ነው፡፡ ቅንጅቱ ባልደራስ መኢአድ ይባላል፡፡

ድርጅቶቹ በነገው እለት በመኢ አድ ቢሮ ውስጥ የቅንጅት የፊርማ ስነ ስርዓት እንደሚያደርጉ ለሚዲያ ተቋማት ባሰራጩት ጥሪ አስታውቀዋል።

ሁለቱ ድርጅቶች ቅንጅት መመስረት ያስፈለገን ምርጫ ቦርድ የካቲት 30፣ 2012 ዓም ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት፣
በሚቀጥለው ምርጫ ለገዢው ፓርቲ ሀገር አቀፍ አማራጭ ለማቅረብ፣ ሌሎች ድርጅቶች በሂደት የሚቀላቀሉትን ስብስብ በሕጋዊ መንገድ ለመፍጠር የመጀመሪያ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሲሉ ገልጸዋል።