ፖለቲከኞች በሐገራችን ላይ ስርዓት አልበኝነትን በማስፈን ሰላም እየነሳችሁን ስለሆነ ከድርጊታቹህ ተቆጠቡ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ፖለቲከኞች በሐገራችን ላይ ስርዓት አልበኝነትን በማስፈን ሰላም እየነሳችሁን ስለሆነ ከድርጊታቹህ ተቆጠቡ።ዝምታን የመረጡ ሐገር ወዳድና ቅን ዜጎች ዝምታቸውን ሊሰብሩ ይገባል። ወጣቱ በሚማገድበት እሳት ፖለቲከኞች መሞቃቸውን ሊያቆሙ ይገባል።
ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምእራብ አንድ ጊዜ በብሔር ሌላ ጊዜ በሐይማኖት ጦርነትንና ግጭትን በመደገስ ለቦዘኔዎች ገንዘብ በመርጫትና በፈጠራ ፕሮፓጋንዳ በመደለል የደሐውን ልጅ ለሞት ማገዶ በማድረግ ረገድ ለስልጣን ጥማታቸው ሲሉ ግንባር ቀደም ሚናውን እየተጫወቱ የሚገኙት ፖለቲከኞች ናቸው።
ፖለቲከኞቹ በሐገራችን የለውጥ ጭላንጭል መጥቷል ተስፋ አለ በተባለበት ወቅት የመንግስትን መዋቅርና ቅጥረኞችን እንዲሁን በየጉሮኖው ያሰለጠኗቸውን ገዳዮችንና በጥባጮችን በማሰማራት የወጣቱን ደም ደመ ከልብ ከማድረግ ባለፈ ባለፉት ሁለት አመታት ፊታቸውን ወደ ልማት መልሰው ለወጣቱ አንድም መልካም ነገር ካለማድረጋቸውም በላይ ይብሱኑ ትውልዱ በትምሕርት እንዳይደረጅ በየከፍተኛ ትምሕርት ተቋማቱ ብጥብጥ በማስነሳት ወጣቱን ከትምሕርት ገበታው በግድያና በሁከት አፈናቅለውታል።
ወደ መሬት ሕዝብ መሐል ሲወረድ ሕዝቡ በሰላም ሰርቶ መኖርን እንደሚፈልቅ ምስክር አያሻውም። ሆኖም ፖለቲከኞች ከሌሎች አከባቢዎች የተደራጁ የሁከት ቡድኖችን ሰርጎ በማስገባት የሕዝቡን ሰላም በማደፍረስ በገዛ ሐገሩ ተዘዋውሮ የመስራት ሕልውናውን በማደፍረስ ለመፈናቀልና ለሞት ዳርገውታል።በተለያየ መንገድ የሰበሰቡትን ገንዘብ እየዘረፉና ለግጭት እያዋሉት እርስ በእርሳቸው እየተናከሱ መርዛቸውን ወደ ሕዝብ በመርጨት የደም ፖለቲካ በሽታቸውን በማስፋፋት ሐገርን ለውድቀት የሚዳርጉት ምረጡን የሚሉ ፖለቲከኞች ናቸው።
ፖለቲከኞቹ በሐይማኖቶች መሐል ጣልቃ በመግባት የሕዝብን የማምለክ መብት በመጋፋት፣ በመከፋፈል፣ ብጥብጥ በማደራጀት፣ ቤተክርስቲያንና መስጂዶችን በማቃጠል በሕዝብ መሐል መተማመን እንዳይኖር የሐሰት ትርክቶችንና መረጃዎችን በማሰራጫት የሐገርን ሰላምና የሕዝብን ደሕንነት አደጋ ውስጥ ጥለውታል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ለሁከትና ለብጥብጥ ተባባሪ ያልሆኑትን የመንግስት መዋቅር ባለስልጣናትን በመግደልና በማሳደድ በዛቻና በማስፈራራት ሽብር እየፈጠሩ ይገኛሉ።
በአጠቃላይ በሐገሪቱ ለሰላም መደፍረስ፣ ለዜጎች ደሕንነት ስጋት፣ ለስርዓት አልበኞች መፈጠርና ለሕገወጥ የመንግስት መዋቅር መስፋፋት ከፍተኛውን ሽብር እያራቡ የሚገኙት ፖለቲከኞች በተለይ ራሳቸውን ብሔርተኛ እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት ደም መጣጭ ፖለቲከኞች ከሴራና ከግድያ ፖለቲካ ከብጥብጥና ሁከት ፖለቲካ ራሳቸውን ለማግለል ፈቃደኛ ካለመሆናቸውም በላይ ብሶባቸው ሐገሪቱን በብሔርና ሐይማኖት ግጭት እያመሷት ይገኛሉ።
ሕዝቡ ጠላቶቹ ፖለቲካውን እያሽከረከሩ የሚገኙት ፖለቲከኞችና ቅጥረኞቻቸው መሆናቸውን አውቆ በንቃት የሐገሩን ሰላምና የራሱን ደሕንነት ሊጠብቅ ይገባል። በተለይ ዝምታን የመረጡ ሐገር ወዳድና ቅን ዜጎች ዝምታቸውን ሊሰብሩ ይገባል። ፖለቲከኞች በሐገራችን ላይ ስርዓት አልበኝነትን በማስፈን ሰላም እየነሳችሁን ስለሆነ ከድርጊታቹህ ተቆጠቡ እንላለን። #MinilikSalsawi
Cartoon – Addis Fortune