ሰበር ዜና፦ የገዛኸኝ ነብሮ ቤተሰቦች የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የገዛኸኝ ነብሮ ቤተሰብ ትናንት በተካሄደው የቀድሞው አየር ወለድ አመታዊ ክብረ በአል ላይ የታጋዩ ምስል ያለበት የክብር መታሰቢያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የነብሮ ቤተሰቦች ሽልማቱን ሲረከቡ


የገዛኸኝ ነብሮ በሰለጠነ ቅጥረኛ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ) ውስጥ ከተገደለ ሁለት ዓመቱ ሊመጣ ጥቂት ወራት ብቻ የቀሩት ሲሆን ወደ አገሩ አጽሙን አምጥቶ በክብር ለማሳረፍ የተገባው ቃል እስካሁን አእንዳልተተገበረ ቤተሰቦቹ በተለይ ለመረጃ ቲቪ ተናግረዋል፡፡

ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ሕዝብ በሚበዛበት ካርልና ፖሊ ጎዳና የነበረ ሲሆን ፖሊስ ግን የደረሰው ከአርባ ደቂቃ በላይ #ሆን ብሎ በመዘግየት እንደነበር ሁኔታውን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ። የምርመራው ሂደትም ሽስካሁን ሸልተጠናቀቀም መባሉ ቅሬታ እየፈጠረ ይገኛል፡፡

ጀግናው ከመገደሉ በፊት በነበረው ቀን በስፍራው በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በነበረ ዝግጅት ላይ ተጠርቶ ሳይሆን ለመቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንደተለመደው በተቃውሞ የአጋርነት ድምጹን ለማሰማት ተገኝቶ ነበር። በቀጣዩ ቀን መገደሉም ይታወሳል፡፡

ነብሮ የቀድሞው 102ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አባል ሲሆን በተገደለባት ደቡብ አፍሪካ ከሃያ አመታት በላይ መኖሩ የሚታወቅ ሲሆን የቀድሞውን አየር ወለድ በመወከል ሽልማቱን የሰጡት የ102ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጄ/ል ተስፋዬ ሃብተማርያም ናቸው፡፡