የአንድነት ፓርክ የቤተመንግስቱ እድሳት ፕሮጀክት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሮጀክት ነው ተባለ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

የቤተመንግስቱ እድሳት ፕሮጀክት?

Image may contain: one or more people

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ “ በቤተ መንግሥት ውስጥ ሙዚየም ገንብተን የቀድሞ መሪዎችን መጠቀሚያ ቁሳቁስ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ጎብኝዎች እናሳያለን፣ የተንጣለለውን የቤተ መንግሥት ግቢ ቀንሰን አዲስ ፓርክ እንሰራበታለን” ሲል ብዙዎች አዲስ ሐሳብ ያፈለቀ ነበር የመሰላቸው፡፡ እርሱ ራሱ ሃሳቡን የግሉ አስመስሎ ሲያወራው ቆይቷል፡፡ ይሁንና ፓርኩንም ሆነ ሙዚየሙን የመሥራቱ ሐሳብ በጣም የቆየ ነው፡፡

ይህንን ሐሳብ በቅድሚያ ያፈለቁት የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሲሆኑ በወቅቱ ሀገሪቷን የሚመራው መንግሥትም ሐሳቡን ተቀብሎት ጥናት እንዲካሄድበት አድርጓል፡፡ ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሳይተገበር ቆይቷል፡፡ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከኢህአዴግ ጋር ተጣልተው የቤተ መንግሥቱን ግቢ ከለቀቁ በኋላ ዞር ብሎ ያየው ሰው ያለ አይመስልም፡፡

ታዲያ ዶክተር ነጋሶ በ2003 በታተመው ዳንዲ የተሰኘ ግለ-ታሪካቸው ጉዳዩን በዝርዝር አስረድተውታል፡፡ ዶክተር ዐቢይ ይህንን ሃሳብ ወስዶ ነው የተገበረው፡፡ ዶክተር ዐቢይ በጥናቱ ላይ የጨመረው ነገር ቢኖር የቀድሞ አፄዎችን ሃውልት መገንባት የሚለው ብቻ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ሊጠናቀቅ የቻለው ጥናቱ ቀደም ብሎ የተሰራ በመሆኑ ነው፡፡

የሌሎችን የፕሮጀክት ሐሳብ፣ ርዕዮተ ዓለምም ሆነ የሳይንስ ግኝት እየወሰዱ “የራሴ ነው” ብሎ መናገር በውጪው ዓለም ከባድ ቅጣት ያከናንባል፡፡ መሪዎች እንደዚህ አድርገው ከተገኙ ደግሞ ከስልጣን ከመነሳት ጀምሮ በየሀገራቱ ፓርላማና ኮንግሬስ ሌሎች ቅጣቶችን ያስከትላል፡፡ በሀገራችን ግን መሪው የሌላውን ሀሳብ እንደ ዘበት እየወሰደው የኔ ብሎ በአደባባይ ይናገራል፡፡
—–
እውነቱን መረዳት የሚፈልግ ሰው “ዳንዲ” የተሰኘውን መጽሐፍ ገጽ 201 መመልከት ይችላል፡፡ ከዚያ መጽሐፍ screenshot አድርጌ የወሰድኩትን ደግሞ እዚሁ ማንበብ ትችላላችሁ፡፡

አፈንዲ ሙተቂ