በምላሱ፣ በአገጩ እና በእግሩ ጣቶች ኮምፕዩተር የሚጠግነውን ሁለት እጆች የሌሉት ኢትዮጵያዊ

ሸገር ልዩ ወሬ – በምላሱ፣ በአገጩ እና በእግሩ ጣቶች ኮምፕዩተር የሚጠግነውን ሁለት እጆች የሌሉትን ግርማን እናስተዋውቃችሁ…

የ22 ዓመቱ ግርማ መኮንን ሲወለድ ጀምሮ ሁለት እጆች አልነበሩትም፡፡ ይህ ግን ከምንም ነገር እንዳልገደበው ነው የሚናገረው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በኮምፕዩተር ሳይንስ የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ግርማ በትርፍ ጊዜው በየተፈለገበት ቦታ እየሄደ ኮምፕዩተር ይጠግናል፣ ሶፍትዌር ይጭናል፡፡

ግርማ በእግሩ ጣሮች የኮምፕዩተር ማውዝ ይጠቀማል፣ ምላሱን ተጠቅሞም ይፅፋል፡፡

“የአእምሮ ጉዳት እንጂ አካላዊ ጉዳት ምንም ማለት አይደለም፣ እችላለሁ ብለህ ራስህን ካሳመንከው የማይቻል ነገር የለም” የሚለው ግርማ በወርልድ ቴኳንዶም ኢትዮጵያን ወክሎ ተወዳድሯል – በሞሮኮው ውድድሩ ወርቅ ሲያገኝ ከቱርክ ውድድሩ ደግሞ ብር ማግኘቱን ይናገራል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ፣ በሸገር ልዩ ወሬ መሰናዶው ወደ 4 ኪሎ ጎራ ብሎ ግርማ መኮንንን ያነጋገረውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል


► መረጃ ፎረም - JOIN US