በውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በአሜሪካን የገንዘብ ሚንስትር ጋባዥነት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲያካሄድ የነበረውን ውይይት አጠናቀቀ::
የውይይቱን መጠናቀቅ አስመልክተው ሚንስትሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል::
በመግልጫቸውም ውይይቱ:-
1) የኢትዮጵያን ፍትሃዊ አቋም ለማስረዳት አመቺ ሁኔታ በመፍጠሩ:
2) የተጏተተውን የቴክኒክ ውይይት በተፋጠነ ሁኔታ ለማስቀጠል ከስምምነት በመደረሱ
ስኬታማ እንደነበር ገልጸዋል::
አያይዘውም:-
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ በቦታው በመገኘት ሪቫን አብረው በመቁረጥ ለመመረቅ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን ጠቁመዋል::