የጠቅላይ ምኒስትሩ ተቀባይነት የት ደረሰ?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ውይይት — የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ መንግሥት ተቀባይነት እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ

DW : ባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያ ከተሞች ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና መንግሥታቸው ላይ ያነጣጠሩ ተቃውሞዎች ታይተዋል። ሥልጣን ሲይዙ ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉባቸው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና መንግሥታቸው በስራዎቻቸው የበረታ ትችት ሲገጥማቸው ነበር። የጠቅላይ ምኒስትሩ ተቀባይነት የት ደረሰ?

ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች በተደረጉ ተቃውሞዎች ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተቃውሞ ቀርቦባቸዋል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ከከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር ወደ አምቦ ባቀኑበት ወቅት ወጣቶች የሚበዙበት ሌላ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። በእርግጥ ጠቅላይ ምኒስትሩ እና መንግሥታቸው ኢትዮጵያውያን የጣሉባቸው ተስፋ ተሟጠጠ? ባለፈው አንድ አመት ከስድስት ወር ገደማ የጠቅላይ ምኒስትሩ መንግሥት ሳይሰራቸው የቀራቸው የቤት ስራዎችስ የትኞቹ ናቸው? አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ተቀባይነት ማጣት መቃቃር በበረታበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ያሳድራል?

በዚህ ውይይት ወሰናዶ በኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ የሚሳተፈው ኬቤኪ ባጫ፤ የሕግ ባለሙያው አቶ ኪያ ጸጋዬ እና የፖለቲካ ተንታኝ እና አክቲቪስ መስፍን አማን በዚህ ውይይት ተሳትፈዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደሚሉት መልስ ያላገኙ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እና የከረረ የልሒቃን ልዩነት ዜጎች በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ መንግሥት ላይ ያላቸውን እምነት እንዲሸረሸር ያደረጉ መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው።

ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የሚከተለውን መስፈንጠሪያ ይጫኑ