ሳፋሪኮምና ቮዳኮም የቴሌኮም ካምፓኒዎች ወደ ኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ ለመግባት እየሰሩ ነው ተባለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Safaricom Plc and parent Vodacom Group Ltd. plan a joint bid for an Ethiopian telecommunications license that they expect to cost as much as $1 billion.

የኬንያ ትልቁ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ ሳፋሪኮም፤ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ቮዳኮም ጋር በመሆን ኢትዮጵያ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ልትሰጥ ካሰበቻቸው ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃዶች ውስጥ አንዱን ለማግኘት እየሠራ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።

የሳፋሪኮም ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚው ማይክል ጆሴፍ እንዳሉት፤ በቮዳኮምና በብሪታኒያው ቮዳፎን በከፊል ባለቤትነት ሥር ያለው ኩባንያ፤ በመንግሥት የሚተዳደረው ኢትዮ-ቴሌኮምን በከፊል በመግዛት፤ ከፍተኛ ትርፍ ወደሚያስገኘው የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለመቀላቀል ከውሳኔ አልደረሰም።

የቴሌኮም ሞገዱን ለማግኘት ከፍተኛ ወጪ እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ጆሴፍ፤ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ፈቃዱን ለማግኘት የሚፈልጉ ተቋማት የደለበ የገንዘብ ምንጭ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።

“ለአየር ሞገዱ በጨረታ መወዳደር ያስፈልጋል። ፈቃዱን ለማግኘት በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ እንደሚጠየቅ እየተነገረ ነው” ሲሉ ተቋሙ ያገኘውን የመጀመሪያውን ግማሽ ውጤት ይፋ ካደረጉ በኋላ ተናግረዋል።

“Ethiopia is the biggest prize left in Africa” Safaricom’s CEO Michael Joseph speaks on expansion plans to Ethiopia.”

Sources :

https://www.bloomberg.com/news/articles/2019-11-01/safaricom-sees-1-billion-price-tag-for-ethiopian-license

https://www.reuters.com/article/kenya-safaricom-ethiopia/kenyas-safaricom-plans-joint-bid-with-vodacom-for-ethiopia-licence-idUSL8N27H1Q9

Kenya’s Safaricom plans joint bid with Vodacom for Ethiopia license