አቶ በረከት ስምዖን መከላከያ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


እነአቶ በረከት ስምዖን በተከሰሱባቸው ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማዬት ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ መስከረም 30 ቀን 2012ዓ.ም በዋለው ችሎት ከፍርድ በፊት የሚቀርብ ማንኛውም ማስረጃ መርምሮ ትክክለኛ ብይን ለመስጠት አጋዥ ስለሚሆን ዐቃቤ ሕግ እንዲያዝለት ያቀረበውን 141 ገፅ ማስረጃ ከዚህ ቀደም የቀረበው የሰነድ ማስረጃ አካል እንዲሆን ሊያያዝ ይገባል ብሎ ነበር፤ ሰነዱን መርምሮ ብይን ለመስጠም ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በተከሰሱባቸው ጉዳዮች ላይ መከላከያ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ለሕዳር 24 ቀን 2012ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

(አብመድ)