ያለፈው ዓመት ታላቅ ፈተና የተደቀነበት ግን ኢትዮጵያ በፈተና የማትወድቅ መሆኗን ዳግም ያስመሰከርንበት ዓመት ነበር – ዶ/ር አብይ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“ያለፈው አንድ ዓመት በአገሪቷ ላይ ለዘመናት ተጭኖ የነበረው የመብት ረገጣና የመበታተን አደጋ ተወግዷል”-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

አዲስ አበባ መስከረም 1/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያለፈው ዓመት ኢትዮጵያ በፈተና የማትወድቅ መሆኗን ዳግም ያስመሰከርንበት አጋጣሚ ነው አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በብሔራዊ ቤተመንግስት በተዘጋጀ ጳጉሜን በመደመር የብሔራዊ አንድነት ቀን በሚል በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ላይ ንግግር አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በለውጥ እርምጃዎች ታጅቦ ያለፈው ዓመት ከእድሜው ቁጥር በላይ ታላቅ ፈተና የተደቀነበት ግን ደግሞ ኢትዮጵያ በፈተና የማትወድቅ መሆኗን ዳግም ያስመሰከርንበት ዓመት ነበር ብለዋል።

ያለፈው አንድ ዓመት ኢትዮጵያዊያን ላይ ለዘመናት ተጭኖ የነበረው ድህነት የመብት ረገጣና የመበታተን አደጋ በዘላቂነት እንዲወገድ እንዲሁም የዘመናት የዴሞክራሲ ጉዞ ወደ ቁልቁለት እንዳይወርድ ለአንድ አመት ብቻ ሳይሆን የአስር ዓመት ውዝፍ እዳ የተጋፈጥንበት ዓመት ነበርም ብለዋል።

አዲስ ዘመን ማለት ምንም ያልተፃፈበት ባለ 365 ገጽ መጽሀፍ በመሆኑ በዚህ መጽሀፍ ላይ አኩሪም አሳፋሪም፣ ጠቃሚም ጎጂም፣ ታሪክ መፃፍ ይቻላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጀመሪያው ገጽ መስከረም አንድ የሚጀምር በመሆኑ አኩሪ ታሪክ በመፃፍ እንጀምር ብለዋል።https://www.ena.et/?p=60804