እጃችን ላይ የቀረው የሰኔ 15ቱ ጉዳይ ነው – አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ

“እኛ ወንጀል ተሰርቷል ወይስ አልተሰራም የሚለውን እንጂ ፈጻሚው ብሔሩ ምንድን ነው? ኃይማኖቱ ምንድን ነው? ትውልዱ ከወዴት ነው? የት አካባቢ ነው? የየትኛው ቡድን አባል ነው? የሚለው ነገር የኛ ጉዳይ አይደለም” አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
******************************************
(ኢፕድ)

• ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ጥሩ ተሰርቷል ብለን የምናነሳው የመጀመሪያውና ዋናው ጉዳይ በፍትህ ሥርዓት ውስጥ ያለው ችግር ምንድን ነው የሚለውን ነገር መለየታችን ነው።

• ባለፈው አንድ ዓመት የምህረት አዋጅ በማውጣት ከ45 ሺ በላይ ታራሚዎች እንዲፈቱ ተደርገዋል። በተጨማሪም በይቅርታ እንዲሁም ክስ በማቋረጥ ደግሞ በጣም በርካታ ሰው እንዲፈታ ተደርጓል።

• ሌላው ደግሞ ሮሮ ሲሰማባቸውና ጥያቄ ሲቀርብባቸው የነበሩ ሕጎች ነበሩ። እነዚህን ሕጎችም ማሻሻል መቻል በራሱ ትልቅ ጉዳይ ነው።

• ተጠርጣሪዎች በተቻለ መጠን ረጅም ጊዜ እስር ቤት እንዳይቆዩ ማስረጃዎችን ሰብስበን ምንም እንኳ መቶ በመቶ ነው ባንልም እርግጠኛ ሆነን ልናስከስስ የምንችላቸውን ሰዎች ለመያዝ የሚያስችል ደረጃ ላይ ነው ያለው።

• መረጃውን ሰብስበን ወደ ማስረጃ ቀይረን ነው ሰዎች የያዝነው። በዚህ መልኩ ሰው ከተያዘ በኋላ ደግሞ ቃሉን መስጠት ይኖርበታል። በተለይ ደግሞ ሙስና ከሆነ ንብረቱ መጣራት አለበት። ሌሎች ሰነዶችም ሊኖሩ ስለሚችሉ እነዚህ ሁሉ ማጣራትን የሚጠይቁ ጉዳዮች ናቸው። ስለዚህም በተወሰነ መልኩ ይህ ሁሉ የሚወስደው ጊዜ አለ፤ ይሁንና እነዚህን ሁሉ እንኳ አድርገን ክሱ የተመሰረተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው።

• ሜቴክን በተመለከተ የመጣው ጥቆማ ከ58 በላይ ነው። አብዛኛው በሚያስብል መልኩ ክስ ተመስርቶ በተወሰኑት ላይ ተከላከሉ ተብለው በመከላከል ላይ ናቸው። ስለዚህ በዚህ ሂደት ረጅም ጊዜ የወሰደ ጉዳይ የለም ማለት ይቻላል።

• በአሁኑ ሰዓት እጃችን ላይ የቀረው የሰኔ 15ቱ ጉዳይ ነው። እሱ ደግሞ የወንጀል አፈፃፀሙ በመንግሥት ውስጥ ያሉት አካላት የመንግሥት ሥልጣን ላይ ሆነው ወንጀሉ የተፈፀመ ስለሆነ ምርመራውን ውስብስብ ያደርገዋል ማለት ነው።

• እኛ የምናየው ነገር ወንጀል ተሰርቷል አልተሰራም? ወንጀሉ ውስጥ ያለው ማነው? የሚለውን ነገር ነው እንጂ ብሔሩ ምንድን ነው? ኃይማኖቱ ምንድን ነው? ትውልዱ ከወዴት ነው? የት አካባቢ ነው ያለው? የትኛው ቡድን ነው? የሚለውን ነገር አይደለም።

• ወንጀለኛ ከሕግ ለማምለጥ ይደበቃል፤ ይሸሻል፤ ራሱን በተለያየ መልኩ በመለወጥም ከሕግ ለማምለጥ ጥረት ያደርጋል። ዘመዱን ወይም ጓደኛውን ለሕግ እንዳይቀርብ የተለያየ ሽፋን የሚሰጥ ግለሰብ አሊያም ቡድን ሊኖር ሊኖር ይችላል።

• በአንድ አገር ውስጥ ሆነን አሳልፎ መስጠት የሚባል ነገርም ሊኖር አይችልም የፌዴራል ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዞ በአገሪቱ የትኛውም ቦታ ሄዶ ተፈላጊውን መያዝ መብት አለው፤ በዚህ ላይ ብዙም ችግር የለም።

• የሕግ የበላይነት በአገራችን ተከብሮ አገራችን ወደ ብልፅግና፣ ወደ እድገት፣ ወደልማት እንድትሸጋገር ትልቁ ክንድና ጉልበት ሕዝብ ነው። ከእኛ የሚጠበቀው ያንን የሕዝብ ጉልበትና አቅም አስተባብረን ሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ጉዳይ ነው። ከዚህ አንጻር መንግሥት ማለት ከሌላ ቦታ የመጣ አካል ሳይሆን ከሕዝቡ የወጣ ነውና በአገራችን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በተለይ ኅብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ ከእኛ ጋር ሆኖ እንዲወጣ ነው ጥሪዬን የማስተላልፈው።

አዲስ ዘመን በጷጉሜን 05 ቀን 2011 ዓ.ም ዕትም በፖለቲካ አምድ ከፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከአቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ጋር አዲስ ዓመትን በማስመልከት የተደረገን ቃለምልልስ ይዛለች። ያንብቧት!

ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/Ama/?p=17574