" /> ምህረት የተደረገላቸዉ ታራሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ይለቀቃሉ ተባለ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ምህረት የተደረገላቸዉ ታራሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ይለቀቃሉ ተባለ

DW : የኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ምክንያት በማድረግ ለአንድ ሺ ሰማንያ ሰባት የፌደራል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ። ታራሚዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ይለቀቃሉ ተብሏል። ይህ የተባለው ዛሬ የፌዴራል ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት በተለምዶ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለመገናኛ ብዙኃን ለጉብኝት ክፍት በተደረገበት ወቅት ነው።

ይህ ማረሚያ ቤት 7 ዞኖች ያሉት ሲሆን አንዱ የሴቶች መኖሪያ ነው። በሴቶች ማደሪያ እመጫቶችን ጨምሮ በርከት ያሉ ህጻናት ወላጆቻቸው ጋር አብረው ይኖራሉ ። ወጣት ሴቶች ግን ከላቀድን ቁጥር ይዘው ፍንደሚገኙ ተመልክተናል። በማረሚያ ቤቱ በአሁኑ ወቅት ከ3 ሽህ በላይ ታራሚዎች ይገኛሉ።

አያያዙ ላይ ለውጥ አለ የሚሉት ያነጋገርናቸው ታራሚዎች አሁንም ፍትህ እንደሚጠይቁና ፣ ይቅርታና ምህረትም እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ስርቆት ፣ ውንብድና ፣ አስገድዶ መድፈር እና ሙስና ይቅርታ ተደርጎላቸው በወጡ ታራሚዎች እየተፈጸሙ ያሉ ወንጀሎች መሆናቸውንና ለእነዚህ ወንጀሎች ይቅርታ እንደማይደረግ በጥቅሉ ግን የወንጀል ድርጊት እየተበራከተ ነው ብለዋል። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር እንዳለው ከሆነ አሁን ላይ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ጨለማ ቤት የሚባል ቤት የለም ብለዋል።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV