የዴሞክራሲ ቀን በመላ ሃገሪቱ እየተከበረ ነው።

የዴሞክራሲ ቀን በመላ ሃገሪቱ እየተከበረ ነው።

ቀኑ በተለይም በሸራተን አዲስ ሆቴል “በመደመር እሳቤ ጠንካራ እና ዘላቂ ዴሞክራሲን ለመገንባት እንነሳ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ ይገኛል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ፥ አሁን ላይ የፍትህና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለማጠናከር ማሻሻያዎች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋማቱ ገለልተኛ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው ምክትል አፈ ጉባኤዋ የተናገሩት።

አያይዘውም መንግስት እየወሰደ ያለውን ማሻሻያ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና መጠናከር መስራት ይገባልም ነው ያሉት።

ምክትል አፈ ጉባኤዋ የሁሉም የሆነች ሃገር ለመገንባትና የዜጎችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለዚህ ስኬት ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ ይገባል ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ ሁሉም ህብረተሰብ ለዴሞክራሲ ስርዓት መጎልበት የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

FBC


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE