ስነ ቋንቋና ሕግ ማገናዘብ የጎደላቸው የኦሮሞ ብሄርተኞች ድንቁርና እና ቀውስ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ስነ ቋንቋና ሕግ ማገናዘብ የጎደላቸው የኦሮሞ ብሄርተኞች ድንቁርና እና ቀውስ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በሕገመንግሥቱ አማርኛ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ ነው። ኦሮምኛንም የፌዴራሉ ቋንቋ ለማድረግ የግድ ሕገመንግስቱ መሻሻል አለበት። ስለዚህ ለአንድ ክልል ሲባል ሕገ መንግስቱ አይሻሻልም የሚል መልስ ለአማራው ክልል እንደተሰጠ ሁሉ ለኦሮሚያ ክልልም መደገም አለበት። ሕገ መንግስቱ ካልተሻሻለ በስተቀር በፍፁም ኦሮሚኛ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ ሊሆን ካለመቻሉም በተጨማሪ ሕገመንግስቱ መሻሻል አለበት ብለው ካሁን ቀደም ጥያቄ ያቀረቡትም ክልሎች በጎ ምላሽን ይፈልጋሉ።

ኦሮሚኛ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆን የሚወተውቱ አካላት በኦሮሚያ ክልል ሌሎች ቋንቋዎች እንዳይኖሩ ጫና ለማድረግ እየተራወጡ ሲሆን፣ የሌላውን ቋንቋ እና ማንነት ሳያከብሩ የራስን በሌላው ላይ ለመጫን መሞከር ስኬትን ሳይሆን ውድቀትን ያመጣል። ለምሳሌ አማርኛ በኦሮሚያ ክልል ሁለተኛ የስራ ቋንቋ ሊሆን ይገባል ፤ይህም መሆን ያለበት ኦሮምኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋ ከመሆኑ በፊት መሆን አለበት።ይህ ካልሆነ በስተቀር የኦሮሞ ልሂቃን ድንቁርና ወሬ ሆኖ ይቀራል።

የኦሮሚኛ ቋንቋ በ አንድ ክልል የተወሰነና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በፍጹም የማያውቁት ቋንቋ ነው። እንደ አማርኛ በመላው ኢትዮጵያ የተስፋፋ አይደለም። አማርኛ በተለያዩ ቦታዎች ከመነገር አልፎ በሰሜን አሜሪካ የስራ ቋንቋ እስከመሆን ደርሷል። ስለዚህ መጀመሪያ ኦሮሚኛ ወደ ፌዴራል የስራ ቋንቋነት ከማደጉ በፊት በመላው ኢትዮጵያ ሊሰራጭና ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ሊማሩት ይገባል። ኢትዮጵያውያን በሚገባቸው መልኩ በፊደላቸው ተጽፎ ሊማሩት የሚገባ ሲሆን ከውጪው ተፅእኖ ተላቆ ኢትዮጵያዊ ማንነትን የተላበሰ ቋንቋ እንዲሆን ማድረግ ግዴታ ነው።

ከሕገ መንግስቱ መሻሻል ጋር ተዳምሮ ቢያንስ አስር ቋንቋዎች የፌዴራሉ የስራ ቋንቋ ሊሆኑ ይገባል። አማርኛ፣ ሶማሊኛ ፣ ኦሮሚኛ፣ ጉራጊኛ፣ ሲዳሚኛ ፣ አፋርኛ ፣ ትግሪኛ እና ሌሎች ተጨማሪ ቋንቋዎች የሃገሪቱ የስራ ቋንቋ ሊሆኑ ሲገባ በትምሕርት ቤት ደረጃም እንደ አንድ ትምሕርት ሊሰጡ ይገባል። በፍላጎት ላይ በተመሰረተ መልኩ ተማሪዎች እንዲማሩ ማበረታታትም ያስፈልጋል።

በሰለጠነ ዘመን በማንነት ቀውስና በዘረኝነት የሚሰቃዩ ደናቁርት የኦሮሞ ብሄርተኞች አብዛኛዎቹ ከሁለት ብሄር የተዳቀሉ መሆኑ ጉዞውን አደገኛ አድርጎታል። እንዲሁም አገሪቱን እንመራታለም የሚሉ ባለስልጣናት ልጆቻቸውን ፈረንጅ አገርና በውድ የግል ትምሕርት ቤቶች እያስተማሩ በቀሪው ደሐ ሕብረተሰብ ላይ በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የፖለቲካ ቁማራቸውን በመቆመር በመንደር የተከለለ ትውልድ በመፍጠር የትውልዱን እጣ ፋንታ እየቀበሩ ይገኛል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)