ባልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ የተሰጡ የትምህርት ማስረጃዎች ህጋዊነት የላቸውም ተባለ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ባልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ የተሰጡ የትምህርት ማስረጃዎች ህጋዊነት እንደማይኖራቸው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ።

እንደ ኤጀንሲው ገለጻ እያንዳንዱ ተቋም የየራሱ የደረጃ ስያሜ ያለው ሲሆን፥ ዩኒቨርሲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኮሌጅ እና ኢንስቲትዩት በሚል የሚገለጽ ነው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ደረጃ ስያሜ እንዲሁ በዘፈቀደ የሚሰጥ ሳይሆን፤ የራሱ የሆነ መመሪያ እና የመመዘኛ መስፈርቶች እንዳሉትም ነው ኤጀንሲይ ያስታወቀው።

ማንኛውም ተቋም በደረጃ ስያሜ መመሪያው መሰረት የሚፈልገውን የደረጃ ስያሜ ጥያቄ አቅርቦ በኤጀንሲው ተገምግሞ ለጠየቀው የደረጃ ስያሜ የተቀመጠውን የመመዘኛ መስፈቶችን አሟልቶ ሲገኝ እንደሚሰጠውም አስታውቋል።

እዚህ ላይ ከተጠቀሰው ውጪ ከደረጃ ስያሜ ውጪ ባልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ በሚዲያ ማስታወቂያ ማሰራት፣ በተለያዩ ሰነዶች እና ባነሮች ላይ መጠቀም፤ ማዕተም ማሰራት ወዘተ የተከለከለ ነው፡፡

ባልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ የተሰጠ የትምህርት ማስረጃም ህጋዊ እንዳልሆነም ኤጀንሲው ጨምሮ አስታውቋል።

በመሆኑም ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከዚህ በፊት ለምሩቃኖቻቸው በሰጡት የትምህርት ማስረጃ ላይ ያልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ ተጠቅመው ከሆነ ተቀባይነት ስለማይኖረው ከወዲሁ ማስተካከያ እንዲያደርጉ፤ ለወደፊቱም ለተመራቂዎቻቸው በሚሰጡት የትምህርት ማስረጃ ላይም ሆነ ማስታወቂያ ላይ የተፈቀደላቸውን የደረጃ ስያሜ ብቻ የመጠቀም ህጋዊ ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ኤጀንሲው አሳስቧል።

ተማሪዎችም በሚመረቁበት ወቅት ከተቋሙ የሚሰጣቸው የትምህርት ማስረጃ ላይ የሚሰፍረውን የተቋሙ የደረጃ ስያሜ የተፈቀደ ስለመሆኑ ማረጋገጥ እንዳለባቸውም አስታውቋል።

ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ እስከ ሰኔ 2011ዓ.ም. ድረስ ካሉት 191 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ዩኒቨርሲቲ የሚል የደረጃ ስያሜ ያላቸው 4፣ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ስያሜ ያላቸው 5፣ ኢንስቲትዩት የሚል ስያሜ ያላቸው 10፣ የቀሩት 172 ተቋማት ኮሌጅ የሚል ስያሜ ያላቸው ናቸው።

የተቋማቱ ዝርዝርም እንደሚከተለው ቀርቧል፦

 1. ኤ.ሲ.ቲ. አሜሪካን ኮሌጅ
 2. ኤም.ቲ.ዋይ. አቢሲኒያ ኮሌጅ
 3. አቢሲኒያ ኮሌጅ
 4. አዳማ ጀነራል ሆስፒታልና ሜዲካል ኮሌጅ
 5. አዲስ አበባ ሜዲካል እና ቢዝነስ ኮሌጅ
 6. አዲስ አምባ ኮሌጅ
 7. አዲስ ኮሌጅ
 8. አዲስ ኮንቲኔንታል የጤና አጠባበቅ ኢንስቲትዩት
 9. አድማስ ዩኒቨርሲቲ
 10. አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 11. አፍራን ቀሎ ኮሌጅ
 12. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ
 13. አፍሪካ የጤና ኮሌጅ
 14. አልካን የጤና ሳይንስ፣ ቢዝነስ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 15. አልፋ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ
 16. አንድነት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
 17. አርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒካል ኮሌጅ
 18. አትላስ ቢዘነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 19. አትላስ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 20. አየር ጤና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 21. ቢ.ኤስ.ቲ ኮሌጅ
 22. ቢ.ኤስ.ቲ.ኤል ኮሌጅ
 23. ባቢት ኤፍ ቢዝነስ ኤንድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 24. ቤካ ኮሌጅ
 25. በለስ ፓራዳይዝ ኮሌጅ
 26. ቤን መስከረም ፕራይም ኮሌጅ
 27. ብራና ኮሌጅ
 28. ብርሀን ኮሌጅ
 29. ብስራት ኮሌጅ
 30. ቤታ ሎጎ ኮሌጅ
 31. ቤተል ሜዲካል ኮሌጅ
 32. ብሉ ማርክ ኮሌጅ
 33. ብሉ ናይል ኮሌጅ
 34. ጭላሎ የጤናሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 35. ሲቲ ሜዲካል እና ቢዝነስ ኮሌጅ
 36. ሲፒዩ ቢዝነስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 37. ዳዲሞስ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ
 38. ዳማት የሆቴል እና ቱሪዝም ኮሌጅ
 39. ዳሞታ ቴክኖሎጂ ኤንድ ቢዝነስ ኮሌጅ
 40. ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ
 41. ዳንግላ አንድነት የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 42. ዲማ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 43. ድሪም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 44. ዱርማን ኮሌጅ
 45. ኤግል ኮሌጅ
 46. ኢስት አፍሪካ ኮሌጅ
 47. ኢኩስታ ከፍተኛ ትምህርት ኢንስቲትዩት
 48. ኢሊያስ ኮሌጅ
 49. እናት ኤች አት ኤች ኮሌጅ
 50. ኢንኮዶ ኮሌጅ
 51. እንጅባራ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ
 52. ኢትዮ ሌንስ ኮሌጅ
 53. ኢትዮጵያ አድቬንቲስት ኮሌጅ
 54. ኢትዮጵያ ኮሌጅ
 55. ኢትዮጲስ የርቀት ትምህርት ኮሌጅ
 56. ኢትዮ ስማርት ኮሌጅ
 57. ፋሆባ ኮሌጅ
 58. ፋም ኮሌጅ
 59. ፋና የጤና፣ ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 60. ፈቃደ እግዚእ ኮሌጅ
 61. ፉራ ኮሌጅ
 62. ጂቲ ኮሌጅ
 63. ጋብስት ኮሌጅ
 64. ጌጅ ኮሌጅ
 65. ጋምቢ የህክምና እና ቢዝነስ ኮሌጅ
 66. ገንፈል ኮሌጅ
 67. ጂኒየስ ላንድ ኮሌጅ
 68. ጊዮን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 69. ጀንትል ኮሌጅ
 70. ጊቤ ቫሊ ኮሌጅ
 71. ጅግዳን ኮሌጅ
 72. ግሎባል ኮሌጅ
 73. ግሎባል የጋዜጠኝነትና የኮሚዩኒኬሽን ኮሌጅ
 74. ጎፋ ዩንቨርሳል ኮሌጅ
 75. ጎልደን ስቴት ኦፍ ቢዝነስ ኤንድ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 76. ግራንድ ኮሌጅ
 77. ግሬት ኮሌጅ
 78. ግሪን የምርምርና የልማት ተቋም
 79. ሀጌ ኮሌጅ
 80. ሐይሉ አለሙ ኮሌጅ
 81. ሀምሊን ኮሌጅ ኦፍ ሚድዋይፈሪ
 82. ሀረር አግሮ ቴክኒካል እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 83. ሐራምቤ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ
 84. ሀረር የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 85. ሀረር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
 86. ሀርበር ቢዝነስ እና ሊደር ሺፕ ኮሌጅ
 87. ሃያት ሜዲካል ኮሌጅ
 88. ሕብረ ብሔር ኮሌጅ
 89. ሐይላንድ ኮሌጅ
 90. ሂልኮ የኮምፒዩተር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 91. ሆፕ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ
 92. ሆርን ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
 93. አይቤክስ ሆቴል እና ቱሪዝም ኮሌጅ
 94. ኢንፎሊንክኮሌጅ
 95. ኢንፎኔት ኮሌጅ
 96. ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት
 97. ጅግጅጋ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 98. ኬ.ቢ. ኢንተርናሽናል ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 99. ካኔኑስ ኮሌጅ
 100. ኪያ ሜድ ሜዲካል ኮሌጅ
 101. ኮቻ ኪድማስ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 102. ቆጋ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 103. ላሊዛግ ኮሌጅ
 104. ሊድስታር ኮሌጅ ኦፍ ቢዝነስ እና ሊደርሺፕ
 105. ሊባኖስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 106. ለደግ ሚድዋይፈሪ
 107. ላየን ኢትዮጵያ ቱሪዝም እና ሆቴል ኮሌጅ
 108. ሉሲ ኮሌጅ
 109. ኤም ኤ ኮሌጅ
 110. ማንኩል ኮሌጅ
 111. ማርቆስ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 112. ሜድኮ ባዮ ሜዲካል ኮሌጅ
 113. መካነ እየሱስ ማኔጅመንትና ሊደር ሺኘ ኢንስቲትዩት
 114. ማይክሮ ቢዝነስ ኮሌጅ
 115. ማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 116. ማይሎሚን ኮሌጅ
 117. ሚዩንግ ሳንግ ሜዲካል ኮሌጅ
 118. ናሽናል አቬይሽን ኮሌጅ
 119. ናሽናል ኮሌጅ
 120. ነገሌ አርሲ ጀነራል ሆስፒታልና ሜዲካል ኮሌጅ
 121. ኔት ወርክ ኮሌጅ
 122. ኒው አቢሲኒያ ኮሌጅ
 123. ኒው ዲፕሎማትስ ኮሌጅ
 124. ኒው ጄኔሬሽን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ
 125. ኒው ግሎባል ቪዥን ኮሌጅ
 126. ኒው ላይፍ ኮሌጅ
 127. ኒው ሚሊኒየም ኮሌጅ
 128. ኖብል ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
 129. ኖርዲክ ሜዲካል ሴንተር ሃየር ለርኒንግ ኢንስቲትዩት
 130. ኖርዝ ኢስት ኮሌጅ
 131. ኑር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
 132. ኦፕን 20 -20 ኮሌጅ
 133. ኦሮሚያ ኮሌጅ
 134. ጎቶኒያል ኮሌጅ
 135. ኦክስፎ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ
 136. ፓራሜድ ኮሌጅ
 137. ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ
 138. ፔንቴክ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 139. ፔስክ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ኮሌጅ
 140. ፋርማ ኮሌጅ
 141. ፖሊ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ
 142. ፕሪቶር ቢዝነስ ኮሌጅ
 143. ፕሪንስፓል ቢዝነስ እና የጤና ኮሌጅ
 144. ኪዊንስ ኮሌጅ
 145. ራዳ ኮሌጅ
 146. ሮሆቦት ሜዲካል ኮሌጅ
 147. ርሆሜድ ሜዲካል እና ቢዝነስ ሳይንስ ኮሌጅ
 148. ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ
 149. ሮያል ኮሌጅ
 150. ቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 151. ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርስቲ
 152. ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ
 153. ሳታ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 154. ሴባስቶፖል ሌጅ
 155. ሰላም የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
 156. ሰሌክት ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 157. ሰሊሆም የጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ
 158. ሸባ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ
 159. ሲምለስ የርቀት ትምህርት ኮሌጅ
 160. ሲንድባድ የአረብኛ ቋንቋ ኢንስቲትዩት
 161. ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ኮሌጅ
 162. ሶሎዳ የጤናና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 163. ሶርስ ኮሌጅ
 164. ስሪ ሳይ ኮሌጅ
 165. ስታንዳርድ ኮሌጅ
 166. ሰሚት ኮሌጅ
 167. ሰንዳዕሮ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 168. ጣና ሃይቅ ኮሌጅ
 169. ቴክኖ ሊንክ ኮሌጅ
 170. ቴክ ዞን ኢንጅነሪንግና ቢዝነስ ኮሌጅ
 171. ቶፕ ኮሌጅ
 172. ጦሳ የኢኮኖሚ ልማት ተቋም
 173. ትሪፕል ኮሌጅ
 174. ትሮፒካል ኮሌጅ ኦፍ ሜዲስን
 175. ዩ.ኤስ. ኮሌጅ
 176. ዩኒየን ኮሌጅ
 177. ዩኒክ ስታር ኮሌጅ
 178. ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ
 179. ዩኒቨርሳል ሜዲካል ኮሌጅ
 180. ዩኒቨርሳል ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
 181. ቪክትሪ ኮሌጅ
 182. ዋሸራ ቦርድ ቪው ኮሌጅ
 183. ዌስተርን ኮሌጅ
 184. ዎርልድ ብራይት ኮሌጅ
 185. ውቅያኖስ ኮሌጅ
 186. ያኔት ኮሌጅ
 187. ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል የርቀት ትምህርት ኮሌጅ
 188. የምስራቅ ጎህ ኮሌጅ
 189. ዮም ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢኮኖሚ ደቨሎፕመንት
 190. ዛክቦን ኮሌጅ
 191. ዛየን ቴክኖሎጂ ኤንድ ቢዝነስ ኮሌጅ