በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የባላደራውን ስብሰባ ሕጋዊ አይደለም ማለቱ ተሰማ

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

የባላደራው ምክር ቤት በአገር ውስጥ ሰላማዊ የሆነ እንቅስቅሴዉን እንዳያደረግ በኦህዴድ/ኦዴፓ በሚመራው አገዛዝ እመሰናክሎች እየገጠሙት እንደሆነ ይታወቃል። በቅርቡም ሰኔ 15 የተፈጠረው የባለስልጣናት ግድያን እንደ ሰበብ በመዉሰድ . በርካታ አመራር አባላቱ በሽብርተኝነት ክስ ታስረዋል። በጀርመን የኢትዮጵያ መንግስት ተጠሪ የሆነው በበርሊን የኢትዮጵያ እምባሲ ባለስልጣናት ባላደራው በአውሮፓ ለማድረግ ያሰበውን እንቅስቃሴ በመቃወም ሕግ ወጥ ብለዉታል። “የባለአደራ ምክር ቤት በጀርመን የሚያደርገው ስብሰባ ተቀባይነት የለውም” ሲል በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ባላአደራው ም/ቤት በበኩሉ ቅስቀሳው “በሀገር ውስጥ ያለውን ጭቆና የሚያሳይ ነው” ብሎታል።

የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአምስት የአውሮፓ ከተሞች ስብሰባ ለማድረግ ያሰበው የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት እንቅስቃሴው ህጋዊ አይደለም በማለት በጀርመን ያኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ የባለአደራው ም/ቤት በበኩሉ አስተያየቱ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ጭቆና የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡

በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራ እና ኮንሱላር ክፍል አንደኛ ሚኒስተር አቶ ከበደ በየነ ባስተላለፉት መልእክት “የአዲስ አበባ ባለ አደራ ም/ቤት በአገር ቤትም ይሁን በውጭ አገር የሚያካሄደውን እንቅስቃሴ ኢ-ህገመንግስታዊ ፤ በኢትዮጵያ ሥርዓት አልበኝነትን የሚያስፋፋ እና የአገሪቱን ሰላም የሚያደፈርስ ስለሆነ ኢትዮጵያን የምንወድ በሙሉ ከህገወጥ ድርጊት መቆጠብ ይኖርብናል።” የሚለው የሃላፊውን አስተያየት ተከትሎ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት ዋና ሰብሳቢ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለኢትዮ ታይምስ እንደገለፀው “አስተያየቱ ከእውነት የራቀ እና የሚያሳዝን ነው፡፡ ሀጋዊ መሆናችንን እና በሰላሚዊ መንገድ መነቀሳቀሳችን በምነሰጠው መግለጫና የራሳችን ቢሮ እንዳለን ይታወቃል፡፡ አስተያየቱ ሃገር ውስጥ ያለውን ጭቆና የሚያሳይ ሲሆን ሰዎች በሰላማዊ መንገድ የመንቀሳቀስ መብታቸውን የሚጋፋም ነው” ሲል የአፀፋ ምላሽ ስጥቷል፡፡

አቶ ከበደ አስተያየታቸውን ሲቀጠሉም “በአሁኑ ወቅት በዶ/ር አብይ የሚመራውን የኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካ ስልጣን መያዝ የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ፤ ፓርቲ መስርቶ እና ፕሮግራም ነድፎ በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ እንዲችል፤ የዴሞክራሲ እና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የሚያስችሉ ለውጦችን እተካሄደ ባለበት ወቅት፤ ህገወጥ እንቅስቃሴ ማድረግ የኢትዮጵያን ሰላም ማደፍረስ እና ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር መተባበር ነው።” ብለዋል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር በበኩሉ “በጀርመን ለሚደረግ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስትን ይሁንታ አንጠብቅም ፤ የተሰጠው አስተያየት የሚታዳሙትን ኢትዮጵያውያን ለመቀነስ ያለመ ነው፡፡ ከሃላፊውም ሆን ከቆስላ ፅ/ቤቱ ማስተባበያ እንጠበቃለን፡፡ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን የመሰብሰብና የመደራጅት መብታቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግም ይጠበቅባቸዋል፡፡” ሲል ምላሹን ሰጥቷል፡፡

ስበሰባው በጀርመን ፤ ኔዝርላንድ ፤ ስዊዘርልንድ እና ስዊድን ከተሞች ይደረጋል ተበሎ ይጠበቃል ፤ የባለአደራው መ/ቤት ም/ሰብሳቢ ኤርሚያስ ለገሰም እንደሚገኝ የገለፀዋል።