የአማራ ሳታለያት ቴሌቭዥንና (አስራት) ራዲዮ ጋዜጠኞች ታሰሩ

የአሥራት ሚዲያ አስተባባሪና መስራች አቶ በሪሁን አዳነ “የመፈንቅለ መንግስት” ተሳታፊ ነህ በሚል ዛሬ በአራዳ ፍርድ ቤት ችሎት ክስ እንደተመሰረተባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከአቶ በሪሁን ጋር ወጣት ጌታቸው አምባቸውም ለእስር እንደተዳረገ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ሁለቱም የአስራት ሜዲያ ባልደረቦች በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በጨለማ ቤት ውስጥ እንደታሰሩና ጠያቂም እንደተከለከሉ አስራት ሜዲያ ዘግቧል።

ሰኔ አስራ አምስት ቀን ተፈጸመ ያሉትን “መንፈቀለ መንግስትን” ተከትሎ ፣ ከመንግስት ከሚሰጡ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑና የተዘበራረቁ መግለጫዎች ውጭ፣ ምን አይነት ገለልተኛ ሆነ ከዚያ ወገኝ የሚሰጥ መግለጫ የሌለ ሲሆን፣ በኦህዴድ/ኦዴፓ የሚመራው ገዢው ፓርቲ ልክ ህወሃት ሲያደርግ እንደነበረው ህዝብ እነርሱ ከሚሰጡት መረጃ ውጭ ሌላ ምንም አይነት መረጃ እንዳያገኝ ኢንተርኔቱን ጠርቅሞ በተለይም በአማራ ክልል ዘግቷል።