ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃትና ግፊት እየተደረገባቸዉ ነዉ

ከዚሕ ቀደም የተበታተነና የወርሮ በሎች የነበረዉ ጥቃት፣ዘረፋና ጫና አሁን የተደረጃ መልክና ባሕሪ እየያዘ፣ በዉጪ ሰዎች ጥላቻና ከሐገር በማስወጣት ላይ ያነጣጠረ ነዉ።አርቲስ በላይ አዳነ የተባበሩት የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ እንዳለዉ ጥቃቱ በመላዉ ደቡብ አፍሪቃ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ላይ በተደጋጋሚ ይሠነዘራል።…