“የደሞዝተኛው ኑሮ እየከፋ ሂዷል” የምክር ቤት አባላት
👉 የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያው ሀገርን የታደገ ትልቅ እርምጃ ነው- ገንዘብ ሚኒስቴር
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ የቀረበለትን የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት አጽድቋል፡፡
የተጨማሪ በጀት ረቂቁን በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ የቀረበ ሲሆን አዋጁን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ እና አስተያየት ተነስቷል።
ከተነሱት ሀሳቦች ውስጥም የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሬ ተግባራዊ ባለመሆኑ እና የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የደሞዝተኛውን ማህበረሰብ አኗኗር እንዳከበደው የተገለጸው ዋነኛው ነው፡፡
በተጨማሪም በነጋዴው ላይ ያለው የታክስ ክፍያ የንግድ ዘርፉን አለመረጋጋት ውስጥ ሊከት እንደሚችል ያለውም ስጋት ተነስቷል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴም በጉዳዩ ላይ ከምክር ቤት አባላት በተነሱት ጥቄዎች ላይ በሰጡት ምላሽ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን እና ያለን ሀብት ለመጠቀም የሚረዳ ከመሆኑም በላይ ከማሻያው በፊት ባለው መቀጠል የሀገርን ኦኮኖሚ እያደሙ መቀጠል እና ወደ ለየለት የኢኮኖሚ ውድቀት የሚያመራ በመሆኑ ማስተካከያ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱም በተጨማሪ በጀቱ ላይ ከተወያየ በኋላ በሦስት ተቃውሞ እና በአምስት ድምጸ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ በጀቱን አጽድቆታል። “የደሞዝተኛው ኑሮ እየከፋ ሂዷል” የምክር ቤት አባላት
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ለፕላንና በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቷል፡፡