Home › View all posts by Getachew Shiferaw
Blog Archives
የትኛውን ሰንደቅ አላማ ነው የምታከብሩት?
አገዛዙ “የሰንደቅ አላማ ቀንን እያከበርኩ ነው” እያለ እየቀለደ ነው። ግን ምን እንደሚያከብር እንኳን አያውቅም!
አረንጓዴ፣ ቢጫ ፣ ቀይ ቀለሞቹን ስታዩ የሚያስደነግጣችሁን ሰንደቅ አላማ ነው እውነት የምታከብሩት?
ቀለሞቹን ልብስ ላይ ስታዩዋቸው ነጠላ ስትቀዱ የከረማችሁትን ነው የምታከብሩት? የህፃናትና አዛውንቶች አንገት ቀምታችሁ የቀደዳችሁትን ታከብራላችሁ?
ቀለማቱን የእጅ ማጌጫ፣ የቁልፍ መያዥያ ወዘተ ላይ ስታዩ ሰብስባችሁ ያቃጠላችሁትን ሰንደቅ አላማ ነው የምታከብሩት?
ፍተሻ ጣቢያ ላይ ቀለማቱ የታተሙባቸውን ቁሶች እየቀማችሁ የጣላችሁትን፤ ህዝብ ያንገላታችሁበትን፣ መንገድ ላይ ሰው ነጥላችሁ ያሰራችሁበትን ቀለም ነው የምታከብሩት?
የሰንደቁን ቀለሞች ያደረገ ኦርቶዶክስ፣ አማራ ወዘተ እያላችሁ ለይታችሁ ማጥቂያ ያደረጋችሁበትን ቀለሞች ውጤት የሆነውን ሰንደቅ አላማ እያከበራችሁ ነው?
የክልል ባንዲራ ላዩ ላይ የምታንጠለጥሉበትን፣ በዓል ሲኖር ከከተማው ሙልጭ አድረረጋችሁ የምታነሱትን ሰንደቅ አላማ እያከበራችሁ ነው?
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለምን ትጠሉታላችሁ እንጅ ታከብሩታላችሁ? ማሳደጃ፣ ማጥቂያ፣ ለይቶ መምቻችሁን እናከብረዋለን እያላችሁ ነው? መንገድ ላይ ቀምታችሁ የምትረግጡትን እንዴት ታከብሩታላችሁ?
በርካታ አገራት ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ቀለም ሲወስዱ እናንተ ከኢትዮጵያ ተፀይፋችሁ ከሌላ አገር የሰንደቅ አላማ ቀለም ወስዳችሁ እንዴት እንደምትጠሉት በተግባር ያሳያችሁትን ሰንደቅ አላማ ነው ቀን ቆርጣችሁ የምታከብሩት?
በሰንደቅ አላማው ቀለም ምክንያት የተንገላቱ፣ ተለይተው የተጠቁ፣ ነውሩን በአካልና በሚዲያ ሲመለከቱ የከረሙ፣ ያሸማቀቃችኋቸው ኢትዮጵያውያን እንኳን የሚታዘቡ፣ የሚያገናዝቡ አይመስላችሁም?
እገታ ይፋዊ ሆኖ መጥቷል!
በሰሞኑ የእስር ዘመቻ እገታ ይፋዊ ሆኖ መጥቷል። በበርካታ የአማራ ከተሞች ንፁሃን ታስረው ጠቀም ያለ ገንዘብ ከፍለው እየተለቀቁ ነው። ጉዳዩ “ወንጀል ሰርተዋል” በሚል አይደለም። ህጋዊ ሆኗል እገታም። “ህግ ማስከበር” ተብሎ ንፁሃን ታስረው ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ ነው። ይህ በርካታ ከተሞች ላይ እየተፈፀመ ያለ የአገዛዙ የይፋ እገታ ነው።
የታሰሩ ንፁሃን መካከል ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ የጭካኔ ድብደባና ግርፋት ሰለባ ሆነዋል። በርካታ ንፁሃን አካላቸው ጎድሏል።
ንፁሃኑ ብቻ ሳይሆኑ ካድሬው ታስሮ በቀናት ውስጥ የሚፈታው በአለቃዎቹ ውትወታ ነው። እስሩ አይደለም ለህዝብ ለአብይ አህመድ ታዛዥ የክልሉ ባለስልጣናት ግራ አጋብቷል። የእነሱ ሰዎች በየቦታው ታስረው ተለማምጠው እያስፈቱ ነው። ቀሪው ደግሞ ከንፁሃኑ ጋር ታስሮ ፍዳውን እያየ ነው። የተጠየቀውን ገንዘብ መክፈል የቻለ ካድሬ የአማራ ክልል ብልፅግና አመራር ፍቱት ሳይል ይፈታል። በእስር አቆዩት ቢልም ከገንዘብ አይበልጥም። በቅርብ መነጋገርያ የነበረው እገታ ላይ የአገዛዙ እጅ ከፍተኛ እንደሆነ የሰሞኑ ዘመቻ ጥሩ ማሳያ ነው።
የእስር ዘመቻ አስፈፃሚዎቹ ንፁሃን ለማሰር መጥተው ቤት ውስጥ ያገኙትን ገንዘብና ሌላ ንብረት እያጋበሱ ነው። ጥይትና መሳሪያም ቀምተውም የሚሸጡት ራሳቸው ናቸው።
“ኤርትራ ለጭፍጨፋ ተጠያቂ አይደለችም። ጭፍጨፋም አልፈፀመችም። ለደረሰ ጉዳት ተጠያቂው ህወሓት ነው!”
የጓዳ ውሉ አካል ብርሃኑ ጁላ
ከፕሪቶሪያው ስምምነት ማግስት ለእነ ታደሰ ወረደ የባጥ የቆጡን እየቀባጠረ “አማራና ኤርትራን እንምታ” እያለ ትብብር የጠየቀው ብርሃኑ ጁላ ነው። በተግባር ያሰቡት ጉዳይ አለ መሰል በሚዲያ እያስተባበለ ነው። በጓዳ ውሉ መሰረት ይህ በትህነግ ዘንድ እንደ ክህደት ይቆጠራል። ትህነግም ሰሞኑን ፈርገጥ ፈርገጥ እያለ ስለሆነ ይሆናል።
የታቀደበት ቃለ መጠይቅ ነው። ሲሳይ ወይ ኤርትራ ላይ ትርክት ፈልጓል። ወይንም ቀድመው ተነጋግረውበታል። የሆነ ሆኖ ብርሃኑ ኤርትራ ተጠያቂ አይደለችም ብሏል። ወይ ኤርትራን ማቀዝቀዝ ፈልገዋል። አሊያም የጓዳ ውሉ እየቀዘቀዘ ነው። ገና በጓዳ የተዋዋሏት ትሟሟለች።
ያ በአማራ ላይ የታወጀ ጦርነት መነሻ የሆነ “እንበላቸው” የጓዳ ውል በዚህም በዛም እየተሸራረፈ፣ “እንበትናቸዋለን፣ በትነናቸዋል።” እንዳልተባለ እንዳሰቡት አልቀናቸውም። “አማራና ኤርትራ ላይ እንዘምታለን” ያሉበት አሁን የኤርትራን ወደ ማስተባበል ገብተዋል። በጥላቻ ጦርነት የከፈቱበት አማራ ደግሞ ሲያሸንፍ የሚሉት ይኖራቸዋል።
የታቀደው ዘመቻ አማራውን አስርበን እናሸንፈዋለን የሚል ነው።
ብልፅግና በካድሬ እስር እንደጀመረው ተደርጎ የሚያስነግረው ዘመቻ ቀጣይ ኢላማ ህዝብ ነው። “እነሱንስ ይበላቸው” ተብሎ ወደ ህዝብ ነው ዋናው ዘመቻ። የመኸር ወቅት ነው። በእርግጥ ካድሬውንም ባያምነው ዋናው ኢላማ ግን ህዝብ ነው። በይፋ ፋኖን ህዝብ ደግፎታል ብለው ገምግመዋል።
አሁን አሳውን ለመያዝ ባህሩን ማድረቅ አለብን የሚል ዘመቻ ነው የቀጠለው። መረጃ ይሰጣሉ ያሏቸውንም ሌላውንም ካድሬ አስረው የፋኖ ደጋፊ ተብሎ የተፈረጀን ህዝብ ግን መመታት አለበት ብለው ወስነዋል። እስካሁን ቤት ለቤትም ሆነ መንገድ ላይ ሲገድሉት የከረሙት አማራ ላይ ነው ዘመቻው። ደግሞ በዚህ የመኸር ወቅት።
ወቅቱም የተመረጠበት አማራው ምርቱን ሳይሰበስብ ወደ ጦርነት ማስገባት፣ ማዋከብ፣ ማሰር፣ መግደል ነው። በዚህ ሂደት አመት የለፉበት መና ይቀራል የሚል ጠላትነት ነው። የተፈጥሮ አደጋና ጦርነት ሲፈራረቅበት የከረመ ህዝብ ለርሃብ ይዳረጋል። እርዳታ የሚሰበስበው ደግሞ አገዛዙ ነው።
አማራውን ያዘመረውን እንዳይሰበስብ አድርጎ የእርዳታ እስረኛ ማድረግና ማሸነፍ ነው። ጦርነቱ ህዝብ ላይ ከከረመው የባሰ ቀውስ እንዲያመጣ ነው ዕቅዱ።
ነገር ግን ህዝብን በዚህ መንገድ ማሸነፍ አይቻልም። ከአሁን ቀደምም በርካታ የጥላቻ ዘመቻዎች ተደርገው ውጤታቸው ታይቷል።
የፋኖ አመራሮች የሰሞኑን ወጥመድ በጥንቃቄ እለፉት!
የሶማሊያ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ቡድኖች አግዛለሁ የሚል ፕሮፖጋንዳ አሰራጭቶ ብልፅግና ደንበኛ ወጥመድ አድርጎታል። ሰሞኑን በርካታ ሚዲያዎች ወደ ፋኖ አመራሮች እንዲደውሉ ይደረጋሉ። የፋኖ አመራሮች ይህን ወጥመድ በጣም በጥንቃቄ ማለፍ አለባቸው።
1) በጣም ጠቃሚው አማራጭ ፋኖ በጉዳዩ ምንም መልስ ባይሰጥ ነው። አስፈላጊ አይደለም። የፋኖ ትኩረት ህዝቤን ነፃ ማውጣት ላይ ነው የሚል መሆን አለበት። የአማራ ህዝብ በርካታ ችግሮች ውስጥ በመሆኑ መፍታት ያለብን የራሳችን ጉዳይ አለ። ጊዜም ትኩረታችንም ለራሳችን አላማ ነው ማለት ያስፈልጋል።
2) ፋኖ እርዳታም፣ ድጋፍ ወዘተ የሚያገኘው ከህዝብ ነው። ስንቄና መጠለያዬ ህዝቤ፣ ትጥቅ የማገኘው ሰተት ብሎ ከመጣ ጠላት ነው ማለት በቂ ነው። ለድጋፍ ህዝብ፣ ለትጥቅ ጠላት በቂ ነው። አራት ነጥብ!
ማንም ተነስቶ አግዛለሁ ሊል ይችላል። ከእነ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የተኮራረፈ የብልፅግና ቡድን “ፋኖን አግዛለሁ” ቢል “አዎ ያግዘኝ” አይባልም። ማንም አግዛለሁ፣ አላግዝም ስላለ፣ መግለጫ ስለሰጠ ብቻ ፋኖ መልስ መስጠት የለበትም። ጫካ ያሉ አመራሮች ስለ ጉዳዩ ላይሰሙ ስለሚችሉም “አልሰማሁም” ማለት ጤነኛ መልስ ነች። ጫካ ውስጥ ያለ ኃይል የሶማሊያን ጉዳይ የግድ መስማት የለበትም። “አልሰማሁም” ምክንያታዊ መልስ ነው!
3) የግድ ከሆነ በገደምዳሜው ማለፍን መልመድ ያስፈልጋል። የሉአላዊነትም ሆነ ሌላ ጉዳይ ስልጣን ሲያዝ የሚፈታ ጉዳይ ነው። ከውጭ ኃይሎች ጋር ያለ ግንኙነት ስልጣን ስንይዝ የምንፈታው እንጅ አሁን ባለንበት ሁኔታ የሚቻል አይደለም የሚል መልስ በቂ ነው። ለዚህ ሲባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ አገዛዙን እንዲያስወግድ
ብልፅግና የማይችለውን አድርጋችሁ አሳዩ!
የፋኖ አመራሮች በዋነኛነት ማተኮር የሚገባቸው ብልፅግና ማድረግ የማይችለውን አድርጎ ማሳየት ነው። በፖለቲካ ድጋፍ የሚባለው ዘላለሙን አይኖርም። በጦርነትና ስቃይ ውስጥ ያለ ህዝብ ቀርቶ በተረጋጋ ሁኔታ ያለ ህዝብ ድጋፉን ይቀንሳል። ወይ ይተወዋል። ሲብስ ወደተቃርኖ ይገባል። እየተደረገ ያለው ጦርነት ነው። የካድሬም ሆነ የሚሊሻ ዘመድ ያለው ሞልቷል። ከዚህ አልፎ በፋኖዎች መካከል ጎራ ተለይቶ ጭቅጭቅ ሰንብቷል። በዚህ ምክንያት የድጋፍ መቀዝቀዝ ብቻ ሳይሆን መቃወምም ጭምር ሊመጣ ይችላል። ሆን ተብለውም ይሁን ሳይታወቁ የሚፈፀሙ ስህተቶችን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ለትችትም ለተቃውሞም ይዳርጋሉ። ፋኖ ጠንካራ ድጋፍ ከፈለገ ብልፅግና ማድረግ የማይችለውን ለህዝብ ማድረግ ነው። “የአማራ ህዝብ” እያሉ መግለጫ ማውጣት በቂ ድጋፍ አስይዞ አያስቀጥልም። ወታደራዊ ድልም ሆነ ሌላው የህዝብን ተስፋ የማይመልስባቸው ጉዳዮች ሊገጥሙ ይችላሉ። ቤተሰቡን ከመታገት ያልታደገ አባውራ፣ ህፃኗ የተገደለችባት እናት ወዘተ ወታደራዊ ድል መጣ አልመጣ ግዷ የማይሆንበት ደረጃ ልንደርስ እንችላለን። ከዚህ ሁሉ መዳን የሚቻለው፦
1) ፋኖ ብልፅግና ማስጠበቅ የማይችለውን ሰላም ማስጠበቅ ሲችል ነው። ለአብነት ያህል ፋኖ ለገጠሩም ሆነ ለከተማው ማህበረሰብ አዋጅ ማወጅ ይችላል። አነስ ባለ መንገድ የተከለከሉ ጉዳዮችን ያስቀመጠ ህግ አሰራጭቶ በሚችለው መዋቅር ማስፈፀም አቅም አለው። የአማራ ህዝብ ለህግ ቀናኢ ነው። ተግባር ታክሎበት ካየ ደግሞ በሳምንት ውስጥ በገበያ ቦታ፣ በኃይማኖት ተቋም ወዘተ የትም መዳረስ የሚችል ጉዳይ ነው። በዚህና በሌሎች መንገዶች ህግ ማስገበር ከቻለ ህዝብ ከዚህ የተሻለ የሚጠብቀው ነገር የለም። ብልፅግና ሰላም ማስከበር አይችልም። ይህን ፋኖ አድርጎ ካሳየ
የትግሉ መዳኛም መሞቻም ይሆናል! በአስቸኳይ መፍትሔ ይሻል!
ባለፈው ሳምንት አገዛዙ ፋኖን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት እየሰራ እንደሆነ በዝርዝር ፅፌያለሁ። አንደኛው የእገታ ጉዳይ ነው። በእገታው አገዛዙ ከፍተኛ እጅ አለበት። ነገር ግን የፋኖ አመራርም ጉዳዩን ትኩረት አልሰጠውም። እንዲያውም አገዛዙ ፋኖን ከማህበረሰቡ ጋር አጋጭቶ ትግሉን ለማኮላሸት የሚያደርገውን ጥረት የፋኖ አመራርም ሆነ አባላት በዝምታም ሆነ በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ተሳትፎ ሳያውቁት እያገዙት ነው።
በሁሉም የአማራ ክፍል እየተባባሰ የመጣው በጎንደር እየከፋ የመጣው እገታ ጉዳይ ላይ ፋኖ የአቅሙን መፍትሔ መስጠት፣ አቋሙን ማሳወቅ፣ አሊያም ከህዝብ ጋር ሆኖ ታግሎ ከፍተኛ የፖለቲካ ድል ማግኘት ሲችል እየታማበት ነው። አደገኛ ነው!
የጎንደሩን ሁኔታ አብነት እጠቅሳለሁ።
1) የፋኖ የቅርብ ዘመድና ወዳጆች ታግተው በነፃ ተለቅቀዋል። ይህ ጎንደር ውስጥ በስም ተጠቅሶ “የፋኖ እንትና እህት፣ የፋኖ እንትና ጎረቤት” ተብሎ እየተወራበት ያለው ጉዳይ ነው። ታጋቾች የተፈቱት የፋኖ አመራሮች በቀጥታ ደውለው ነው። ይህ ማለት የፋኖ አመራሮች ለራሳቸው ዘመድ ወዳጆች ያደረጉትን ለሌላው ሕዝብም ማድረግ ይችላሉ። የፋኖ አመራሮች አስፈራርተውም ቢሆን ያስለቀቁ፣ አፋኖችን ያውቃሉ ማለት ነው። የአገዛዙን ዋና ኃይሎች አሳድደው አዲስ አበባ ያስገቡ የፋኖ አመራሮች ከጫካ ወደ ከተማ እየመጣ ንፁሃንን የሚያግት ወንበዴ ልክ ማስገባት ሊያቅታቸው አይችልም። ትኩረት ስላልሰጡት ነው። ከህዝብ ጋር የበለጠ የሚያጋምድ የፖለቲካ ድል እንደሚያስገኝ ስላልገባቸው፣ ዋና አላማ ከሚሉት የሚያናጥብ ስለመሰላቸው ይሆናል። ግን ስህተት ነው። ህዝብህን ሳትይዝ ትግል የለም። ከወንበዴ ጋር ጎን ለጎን እየተላለፉ ድል አይመጣም። አሁን ጭራሽ ትግሉ እየታማበት ነው።
“ኦሮሞ በፌስቡክ የሚነዳ ህዝብ ነው” የእነ ደብረፅዮን ትህነግ/ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል።
ዝናቡ ገብረመድህን የሚባል ሰሞኑን እነ ደብረፅዮን ባደረጉት ጉባኤ የተመረጠ አመራር የኦሮሞን ህዝብ በፌስቡክ የሚነዳ ብሎታል። ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ከኦህዴድ ጋር የተደረገው ሽርሽር አለቀ ማለት ነው። የአማራን ህዝብ አብረን እናጥቃ ያሏቸዎ ሰዎች ዛሬ ኦሮሞን በዚህ ለክ ገልፀውታል።
አስፋው አብርሃ የተረጎመው ዋና ጭብጥ ከስር ተቀምጧል!
“የማይጨው ወጣት የእነ ደብረጽዮንን ልዑካን አትምጡብን አላቸው” እያሉ ፌስቡክ ላይ የሚፅፉ ሰዎች አሉ።እነዚህ ሰዎች የማይጨው ወጣት ልክ እንደ ኦሮሞ በፌስቡክ የሚታዘዝና የሚነዳ መስሏቸዋል። ዝናቡ ገብረመድህን (የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል)
እነ ሽመልስ አብዲሳ ያስገደሉት ዋና አስተዳዳሪ ጉዳይ!
ከሶስት ወር በፊት መከላከያ ባሕርዳር ላይ ሕዝባዊ ስብሰባ በሚል የተለያዩ አካላት ጋር ውይይት አደረገ። በዚህ ውይይት የኦሮሞ ብልፅግና አዲስ አበባና ናዝሬት ላይ እየሰበሰበ አማራ ክልል ውስጥ የክልልነት ጥያቄ እንዲያነሱ የሚደግፋቸው አካላት በይፋ “ክልል መሆን አለብን” የሚል ጥያቄ አነሱ።
ከከሚሴ ዞን የመጣው ግን ያልተጠበቀ ነበር። የከሚኬ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው አቶ አህመድ አሊ በመድረኩ “ሕዝባችን ቋንቋውን እየተጠቀመ፣ በልጆቹ እየተዳደረ ነው። ከአማራ ክልል ያጣነው፣ አሁን ካለው የተለየ የምንጠይቀው ነገር የለም።” ሲል ተናገረ። በሶስተኛው ቀን በጠራራ ፀሐይ ገደሉት።
ከቀናት በኋላ ገዳዩ “እጅ አልሰጥም ብሎ ተገደለ” ብለው ቀለዱ።
ገዳዩን መጀመሪያ ሸኔ ቀጥለው ደግሞ ግለሰብ አደረጉት። ተገድሏል ብለው ነገሩን “አለቀ ደቀቀ” አሉ።
ሰውየው የተገደለው በእነ ሽመልስ አብዲሳ ቀጥታ ትዕዛዝ ነው።
ብሔርተኝነቱን መስመር ጠብቁለት!
የአማራ ብሔርተኝነት በብዙ በኩል የሚወጋ መከረኛ አጀንዳ ነው። የሚጎዳው ግን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከውስጥ የሚመታው ነው። መስመር አለማስያዙ ደግሞ ትልቁ ችግር ይመስለኛል። በጊዜው መስመሩ ካልተጠበቀ የማንም መዘባበቻ እንዳይሆን ስጋት አለኝ።
1) ብሔርተኝነቱ ከምሁራን ወጥቶ እንደፈለገ የሚተረጉመው የማህበራዊ ሚዲያ ተሳታፊ እጅ እየገባ ይመስላል። ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ብሔርተኛ በሆነ ነገር ተደስቶ ወይንም ተናድዶ ፀረ አማራ ብሔርተኞች የሚፈሱበት ቦይ በኩል የአማራን ብሔርተኝነትም ላስኪደው እያለ ያለ ቀለሙ፣ ያለ ታሪኩ ሲያስጨንቀው፣ ለተቃርኖ ሲዳርገው እንመለከታለን። አማራውን አገር በመመስረት እንደ ጥፋት የሚቆጥሩበትን ኦነግና ትህነግ ኃይሎች መከራከሪያ የሚያጠናክሩ መከራከሪያዎችን ይዘው የሚሮጡ ወገኖችን አያለሁ። ይህ ተቃርኖ የአማራውን ምሁር እያራቀ፣ የአማራን ብሔርተኝነት ከገናና ታሪኩ እያኮሰመነ፣ ከአባቶቹ አበርክቶ እያሳነሰው ተገንጣይ የአማራ ጠላቶች ጋር የሆነ ስርቻ ውስጥ ሊከትተው የሚጥር ስህተት ይመስለኛል።
2) ባለማወቅ የአማራን ብሔርተኝነት አናት አናቱን እየቀጠቀጡ እናለመልመዋለን የሚሉም አያለሁ። አማራ መለያው ፀረ ቅኝ ግዛት ተጋድሎ ነው፣ ፓን አፍሪካኒዝም ነው፣ የአጤ ምኒልክ፣ የአጤ ቴዎድሮስ፣ የበላይ ዘለቀ፣ የፕሮፌሰር አስራት ፈለግ ነው። እነዚህ ዕንቁዎች ፀረ አማራ ብሔርተኞች “ነፍጠኛ፣ ትምክተኛ” ወዘተ ቢሏቸውም ሌላው ጭምር የሚያከብራቸው፣ በአህጉርም በአለምም ደረጃ ምልክት የሆኑ ናቸው። የእነዚህን ነፀብራቆች አላማ የአገር ባለቤትነት ነው። በተቃራኒው አንዳንዶች ሳይሞርዱ ወስደው ሊጠቀሙበት የሚፈልጉት የፀረ አማራ ብሔርተኞች ስልት አማራን አገር አልባ ያደረገ ነው። የአማራ ብሔርተኝነት ከቀለሙ፣ ከታሪኩ ሳይጣላ፣ ከጠላቶቹ ጋር የሆነ ስርቻ ውስጥ ሳይገባ መሄድ ካለበት መስመሩን፣ ልዕልናውን በአባቶቹ ታሪክና አላማ ልክ
አብይ ክፉኛ እየቃዠ ነው!
በየ አጋጣሚው ስለ መፈንቅለ መንግስት ያወራል። የዛሬው የከፋ ነው።
1) መፈንቅለ መንግስት የሚደረገው በመከላከያ አመራሮች፣ በደህንነትና ፀጥታ ሰዎች፣ በመዋቅሩ ነው። ከህዝብ አልፎ ይህ ኃይል ክዶኛል እያለ ነው።
2) አይደለም መፈንቅለ መንግስት ሌላ አነስ ያለ ነገርም ቢሆን አገዛዙ ከሰማ ተቆጣጥሮ ለማጥፋት ወዘተ ይጥራል እንጅ በአደባባይ ነቅቸባችኋለሁ እንደማይል ግልፅ ነበር። የዛሬው የአብይ “ነቅቸባችኋለሁ” የአቅም ማጣት ነው። “ተነቅቶብናል” ብለው እንዲተውለት ነው። በፀጥታው ኃይል ስላልቻለ በወሬ ቢበተኑ ብሎ ነው። አቅም ማነስን ካላሳየ ምንም ሊያሳይ አይችልም።
3) አቅሙ መቆጣጠር ካላመቻል ባለፈም ሆኖ ይሆናል። መረጃ አግኝቶ አለመቆጣጠር ብቻ አይደለም። መረጃ ሁሉ ሲያጣ በቃ እንዲሁ ላስደንግጥ ብሎ ይሆናል። ጭንቅ ሲለው ተንፍሸው ልሙት ይሆናል። የፀጥታ ተቋማቱ ፈራርሰዋል። አብዛኛው ካድሬም የእነ እዩ ጩፋ ትንቢትን ነው የሚጠብቅ። በዚህ መሃል መፈንቅለ መንግስት ሲያስፈራው በፓርላማ ወጥቶ “ጨነቀኝ ጠበበኝ” ይላል።
4) መካሪ አልባ መሆኑን ያሳየበት ነው። መፈንቅለ መንግስትን ቀላልና እንዲለመድ እያደረገው ነው። ጀኔራሉም ሌላውም የማይፈራው የተደጋገመ፣ እንሞክረው ብለው እንዲያብሰለስሉት የሚያደርግ ነው። የአብይ የመፈንቅለ መንግስት ስጋት ለወታደሮቹ ምርጥ ምልክት ነው። መፍራቱን ደጋግሞ እየነገራቸው ነው። ቢችሉ ስልጣኗን፣ ባይችሉ መደራደሪያ ብዙ ጥቅማጥቅም ይጠብቁበታል። ጥቅማጥቅም እየጎረፈላቸው ነው። ሲጠግቡ ስልጣኗን ያስቧላት። እንቅልፍ አጥቶ ብቻ አይቀራትም። የፈራን መከተልን ወታደር አይጠፋውም።
5) ምን አልባት የሚፀልዩነት የሀሰተኛ ፓስተሮች ነግረውትም ይሆናል። ዞሮ ዞሮ ሁሉም ውድቀት ነው። አብይም ክፉኛ እየቃዤ ነው! ለመፈንቅለ መንግስት ያደረሰ ውድቀት መኖሩን በአንደበቱ እየደጋጋው ነው!
ራሱ ትህነግ አደናቅፎታል
ትህነግ ሲፎክርበትና ሲያምታታበት የከረመውን በ’ተፈናቃይ’ ስም ታጣቂ የማስገባት ሂደት ራሱ አክሽፎታል።
በራያ ያደረገው ወረራ እየታወቀ ጠለምት ላይም ተፈናቃይ ልመልስ ሲል በጊዜው ተደናግረው የወጡ ወርቅ ቆፋሪዎችን ይሆናል በሚል የጠለምት አማራ በጊዜው ወደ ትግራይ የሄዱት እነማን እንደነበሩ ስለምናውቃቸው ከየቀበሌው ሰዎችን ወክለን እንለይ በሚል ሆደ ሰፊነት በርካታ የትግራይ ተወላጆችን ተቀብለው እያስተናገዱ ነበር።
ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ትክክለኛው የትህነግ ዓላማና ፍላጎት ተገልጧል። ከሁሉም ቀበሌዎች የተመረጡ ሽማግሌዎች እንዳረጋገጡት ትህነግ ሦስት አይነት ቡድኖችን ይዞ መጥቷል።
የመጀመሪያው በጠለምት ሽማግሌዎች ነዋሪ የነበሩ መሆናቸው የተመሰከረላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ እነዚህ ወደ ቀደመ ቀያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። ከተመለሰት መካከል ትጥቅ መፍታት የነበረባቸው ያልፈቱ በርካታ ሚሊሻዎች ይገኙበታል። ሆኖም ትህነግ በሁለተኛ ዙር ጠለምትን ወርረው የነበሩ የትህነግ አመራሮችን ከማቅረቡም በላይ በሦስተኛ ዙር የሚገቡ በሚል ጠለምትን በጦርነቱ ወቅት ብቻ የረገጡት የታወቁ ዲሽቃና ሞርታር ተኳሾችን ሳይቀር የያዘ የወራሪው ወታደራዊ አባላትን ለማስገባት አስተዋውቋል።
የጠለምት ሕዝብም የሁለተኛና የሦስተኛ ዙር ተመላሽ የተባሉትን ቡድኖች ማንነት በግልጽ ያስረዳ በመሆኑ ትህነግ ደግሞ የወረራ አላማውን የሚያስፈፅምባቸው አካላት የማይገቡ ከሆነ አጠቃላይ ሂደቱ ይቋረጥ በሚል በሕዝብ ፊት ወስኗል።
በሌላ በኩል በአገር ሽማግሌ ተለይተው የገቡት የትግራይ ተወላጆች እየተቧደኑ የጠለምት አማራዎችን ማጥቃት የጀመሩ ሲሆን ለአብነትም የጠለምት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሜቴ አባላትንና ንፁሃንን ከትላንት ጀምሮ ለማካሄድ ሲሞክሩ የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት የኮሚቴው ፀኃፊ የሆነው መብራት አዲስ ላይ አካላዊ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል። ይህ አይነት ጥቃት ህዝብ በጥቃቱ
ፋኖን በሌላ እቅድ “አጠፋዋለሁ” ብሎ የነበረው ብልፅግና “ህወሓት ያግዘኝ” ብሎ መጥቷል። ፋኖን ለመምታት በሚል በብልፅግና እና ትህነግ መካከል አዲስ የጓዳ ስምምነትም ተፈፅሟል። በዚህም መሰረት፦
1)ወደ ራያ ከገባው በተጨማሪ በቀጣይ ቀናት በጠለምት የታጠቀ የትህነግ ኃይል እንዲገባ ተወስኗል።
2) የሰላም ስምምነቱ አካልና የህዝብ ጥያቄ ነው እንዲባል በትግራይ ከተሞች ሰልፎች ተደርገዋል። ጠለምት ላይ የተጠራ ተቃውሞ በአገዛዙ ታፍኗል።
3) ህወሓት “ፋኖን ትደግፋለህ” በሚል በብልፅግና ሲታማ የነበረበትን አጠራለሁ በሚል ሰሞኑን በተደረገው ጉባኤው ወስኗል። “ከኤርትራ ጋር እንተባበር” የሚል አጀንዳ ውድቅ ተደርጎ “ከአብይ ጋር ተባብረን። የሚለንን ፈፅመን የድርጅታችን እውቅና እና ወልቃይትና ራያን እንረከባለን” ብለዋል።
4) በየጊዜው ከእቅድ ወደ እቅድ ሲሸጋገር የከረመው ብልፅግና ይህኛውን እቅድ ሰሞኑን ይጀምረዋል። ጉዳዩን የተቃወሙ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተጠርተዋል።
5) ከትህነግ ታጣቂ በተጨማሪ አዴን በሚል ከወራት በፊት ከብአዴን ጋር የተስማማ ታጣቂው ሰሞኑን በአገዛዙ ድጋፍ ስልጠናዬን ጨርሻለሁ ብሏል።
ወደ ላስታና አጎራባች አካባቢዎች አሰማራዋለሁ ብለው አስበዋል።
ፖለቲካው ሁሉንም እንዳያሳጣችሁ!
የኢትዮጵያ ፖለቲካ መገመት የማይቻል፣ የዱብ ዕዳ ፖለቲካ ከሆነ ቆይቷል። የማታው ደማቅ አጀንዳ ጠዋት በሌላ ይተካል። ጠዋት ስንነሳ የምንሰማው ያልተጠበቀውን ነው። ፖለቲካው ከአንደኛው ጫፍ ወደሌላኛው ጫፍ ተላግቶ፣ የሆኑ ያልሆኑ ኃይሎች ተጣልተው፣ ሌሎቹ ወዳጅ ሆነው እናገኛቸዋለን።
በዚህ በሚናጥ ፖለቲካ ውስጥ ብዙዎች እርስ በእርስ ይናከሳሉ። ከቀናት በፊት ፕሮፋይል ያደረጉትን ሰው ፎቶ ዘቅዝቀን ልታዩዋቸው ትችላላችሁ። ወዳጃቸውን አምርረው አውግዘው ጠላቴ ነው ያሉትን ይቅርታ ሲጠይቁ መመልከት እየተለመደ ነው። በዚህ አቅጣጫ ቢስ ፖለቲካ ታዲያ ሁሉንም ላለማጣት መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው።
ከድልም ከሽንፈትም በኋላ ዘወር ስትሉ የኃይማኖት አባት፣ ጓደኛ፣ ወዳጅ ወዘተ የሚባል ነገር አለ። ዞር ስንል ቢያንስ እንዳናፍር፣ ቢበዛ እንዳናጣቸው መጠንቀቅ የተሻለ ነው።
የፖለቲካውን ፍጥነት ያልተረዱ ሰዎች ድንገት ገብተው ከነፋሱ ጋር እንንጎድ ሲሉ ይታያሉ። በድሮ ጓደኛቸው ላይ ሚስጥር አወጣን ሲሉ፣ አርዓያችን ነበር የሚሉትን እያወገዙ፣ ሲጠሉት የነበረውን ሲያሞካሹ እናያለን። በሚቀያየረው ፖለቲካ ከነፋሱ ጋር ራስን ለማራመድ ብለው ወዳጃቸውን እያወገዙ፣ ከድሮ ባላንጣዎቻቸው ለመለጠፍ የሚሞክሩ በማህበራዊ ሚዲያም በሌላውም የምናያቸው ሰዎች በርክተዋል። ወዳጆቻቸውም ይታዘቧቸዋል። ባላንጣዎቻቸውም አያስጠጓቸው። በዚህ ውዥንብር የበዛበት ወቅት የሚያዝ የሚጨበጥ ነገር ያስፈልጋል። ካልሆነ ቀዝቀዝ ሲል የኃይማኖት አባት፣ ጓደኛ፣ ወዳጅ ዘመድ አይኖረንም።
መከራከር ጥሩ ነው፣ የራስን ወገን ለማሳመን ብዙ ርቀት መሄድ መልካም ነው። የማይጎዳውን ማለፍ፣ ቀሪውን መታዘብ፣ በሚያውቁት ሰው በኩል መነጋገር ወዘተ መልካም ነው።
አንድ ቀን ፀጥ ረጭ ሲል ብዙ ሰው ዞር ዞር ሲል የሚያጣው መአት ነው። የራስን ወገን ሳያሰባስቡ፣
“ጌታቸው ረዳን አግዙት” የሚሉ የ”አማራ” ጉዶች/ደላላዎች መጥተዋል!
ጌታቸው ረዳ “አማራ” ብሎ የሚያገኛቸው አርቲስቶች፣ ባለሀብቶች፣ የቀድሞ ጓደኞቹ፣ ባለስልጣናት፣ “ተፅዕኖ ፈጣሪዎች” አሉ። ከስምምነቱ ማግስት ጀምሮ አዲስ አበባ ሲመጣ የሚያገኛቸው ደላላዎችም አሉ። እነዚህ ሰዎች ታዲያ ሰሞኑን እየዞሩ “ተፅዕኖ ፈጣሪ” የሚባሉ ሰዎች ጋር “ጌታቸው ረዳ ከአማራ እገዛ ፈልጓል” እያሉ ነው። የሚገርመው ደግሞ ጌታቸው ረዳ እገዛ ፈለገ የተባለው ምክትል ከሆነበት ትህነግ/ህወሓት ጋር ለመታገል ነው። ቀልዳቸውኮ አይጠገብም። ሲያወሯቸውማ ጭራሽ “ከአድዋ ቡድን ጋር” እያሉ ነው። እውነታችሁን ነው?አንዳንዶቹ ይችን መረጃም እንደማጋለጥ ቆጥረዋት ይናደዱብኝ ይሆናል። ግን አማራን በዚህ እያደነዘዙ ሊቀጥሉ ስለማይገባቸው ነው። ለማንኛውም “ጌታቸው ለአድዋውን ቡድን ለመታገል ድጋፍ ፈልጓል” አይነት ጅልነትን ማሳመኛ ብለው እንደማሳመኛ የሚገልጿቸው ጉዳዮችም አሉ። ፍሬ ቢስ መሆኑን ለማሳየት እዘረዝራቸዋለሁ።1) የአድዋው ቡድን ለጦርነት እየተዘጋጀ ሲሆን ጌታቸው ረዳ ጉዳዩን በሰላም ስምምነት መሰረት መጨረስ ይፈልጋል የሚል ነው። እውነት ቢሆን ጥሩ ነበር። ነገር ግን ፍሬ ቢስ ማደንዘዣ ነው። ጌታቸው ረዳ በስምምነት ስም እየማለ ግዛቶቹን በኃይል እንዲያዙ አድርጓል። የአማራ ግዛቶችን በመያዝ ከአድዋው ቡድን ጋር ልዩነት የለውም። የትህነግ ታጣቂም፣ ጀኔራሎቹም፣ በአማራ ላይ ስልታቸውም ተመሳሳይ ነው።2) ሁለኛው “ጌታቸው ረዳ ከአማራ እገዛ ፈልጓልና ነጥለን እናግዘው” የሚለውን ማሳመኛ ተደርጎ የተነገረው በዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ዘንድ የተሻለ እድል የተሰጠው መሆኑን ነው። ይህም ግን ጅልነት ነው። ጌታቸው ለዲፕሎማቶቹ የሚናገረውም አማራ ወራሪ እንደሆነ አስመስሎ ነው። ትህነግ/ህወሓትን ወክሎ ነው የሚናገረው። በዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ፊት በሀሰት የሚከስህ፣ ትህነግን ወክሎ የሚናገረውን ለትህነግ ነጥለህ አግዘኝ
ትህነግ/ህወሓት አፋርን ወርሯል!
ትህነግ/ህወሓት አፋር ላይ ወረራ ፈፅሟል። ሰበብ ፈጥሮ ታጣቂውን ወደ አፋር ያስገባው ትህነግ በአክቲቪስቶቹ በኩል “ይህን ያህል ገድየባቸዋለሁ” እያስባለ ነው።
በሰላም ስምምነቱ መሰረት በግልፅ በ30 ቀን ትጥቅ ይፍታ የተባለው ትህነግ በጓዳ ስምምነት ትጥቅ ባለመፍታቱ አማራንና አፋር መልሶ እየወረረ ነው።
ትህነግ አፋር ላይ ወረራ የፈፀመው ከአፋር የመጡ ሰዎች “ወንጀል ፈፅመዋል” በሚል ሲሆን ያለ ወረራ ፈፅሞ ንፁሃንን መግደሉ ታውቋል።
ትህነግ አፋር ላይ የፈፀመውን ወረራ ምክንያታዊ ለማስመሰል የጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር መግለጫ አውጥቷል።
በሚሊዮን የሚቆጠር የራያና የወልቃይት መታወቂያ እየተሰራጨ ነው!
ብልፅግና በአማራ ግዛቶች አስተዳደሮችን አፍርሶ “በፌደራል ስር ሆነው ሕዝበ ውሳኔ ይሰጥባቸዋል” ብሎ ነበር። እውነታው ግን ለትህነግ አሳልፎ ሰጥቶ የትግራይ ወጣት ህገወጥ የራያና ወልቃይት መታወቂያ በገፍ እየታተመ እየታደለው እንዲሰፍር እየተደረገ ነው። የፈለገ የትግራይ ስራ አጥ ወጣት የራያ ይሁን የወልቃይት መታወቂያ ይታደለዋል። ትህነግ በሀሰት በሚሊዮን የሚቆጠር ተፈናቃይ አለኝ ባለው መሰረት በአማራ ግዛቶች ህዝብ ለማስፈር በሚሊዮን የሚቆጠር መታወቂያ ተዘጋጅቶ እየተሰራጨ ነው።
ብልፅግና በመከላከያ ስር ሆኖ ህዝበ ውሳኔ ይደረግበታል ቢልም አሳልፎ ሰጥቶ መታወቂያ እየታተመ የህዝብን አሰፋፈር ለመቀየር እየተሰራ ነው። በግልፅ “መታወቂያ ውሰዱ” እየተባለ እየተሰጠ ነው። የፕሪቶሪያ ስምምነት ሆነ ብልፅግና በየዕለቱ መከርኩበት የሚለው ይህን አይልም። ይህ የጓዳ ውሉ ውጤት ነው! እርባና ቢሱ ብአዴን ደግሞ ዝምታን መርጧል።
በአብይ አህመድ ትዕዛዝ ነው!
አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በያዘው በውጭ ኃይሎች የተደገፈ ፕሮጀክት ለማስፈፀም ከመረጣቸው ስልቶች አንደኛው ቤተ ክርስቲያንን መሪ ማሳጣት ነው። ባለፈው ቤተ ክርስቲያን ላይ በሞከረው ጥቃት ጠንከር ካሉበት አባቶች አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ናቸው።
ሰሞኑን ጥምቀትን ለማክበር ወደ ሀገረ ስብከታቸው እንደሚሄዱ ሲታወቅ ገና አውሮፕላኑ ሳይነሳ በሄዱበት ቀሩ ብለው የሀሰት መረጃ አሰራጩ። ወዲያው ገና ያልተሰራጨ መፅሐፋቸውን በዘመድኩን በቀለ ስም የታተመ አስመስለው በኢንተርኔት ለቀቁት። የሚያሸማቅቋቸው መስሏቸው ነው።
ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በአብይ አህመድ ቀጥታ ትዕዛዝ ነው። እንዳይመለሱ ለማድረግ ነው። ቤተ ክርስቲያኗን መሪ አልባ አስቀርቶ አብይ አህመድ በፕሮጀክት አስፈፃሚነት የያዘውን ኦርቶዶክስን ማመንፈቅ ማስፈፀሚያ መንገድ ነው። አይሆንም! (ጌታቸው ሽፈራው )
ጭፍጨፋ የሚፈፀመው በኦሮሚያ መዋቅር ነው!
ይህ ሰው የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ሰራተኛ ነው። የኦሮሞ ብልፅግና በተለይም የአብይን መልዕክት ሲያሰራጭ ነው የሚውለው። የአዲሱ አረጋ የቅርብ ሰው መሆኑ ተገልፆአል። ሌሎቹ ጋር አብሮ እንደሚውል በፎቶ ይታያል።
ይህ የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ሰራተኛ ታዲያ ኦርቶዶክሶች ከኦሮሚያ መፅዳት አለባቸው ብሎ በይፋ ፅፏል። ይህ ሰው በጥንቃቄ ሊሰራ ይችላል ተብሎ የሚታሰበው የክሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ሰራተኛ ሆኖ ነው የዘር ፍጅትን በግልፅ የሚሰብከው። የኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤቱ ላይ በዚህ ልክ ከተቀሰቀሰ ሌሎቹ ምን እንደሚያደርጉ ማሰብ ቀላል ነው። https://t.me/GetachewShiferaw/7327?single
የዚህ ሰው ቅስቀሳ ያረጋገጠው የዘር ፍጅቱ የሚፈፀመው በኦሮሚያ መዋቅር መሆኑን ነው። አውርተው፣ አሰማርተው የሚያስፈጁትን ለምደውትና አማራና ኦርቶዶክስን መፍጀት ህጋዊና ግዴታ አድርገውት በይፋ ይፃፋል። የፃፈው ከአለቆቹ የተነገረውን ነው። የፃፈው በመዋቅር የሚሰሩትን ነው!
አቡነ ሉቃስ አብይን ተቹ ብለው ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ያውጃሉ። የአቡነ ሉቃስ አጀንዳ ህዝብን ለመፍጀት ሰበብ ነው! በይፋ ህዝብን ከኦሮሚያ እናፀዳለን ብለው እየፃፉ ነው። ኦሮሚያ መዋቅሩ የሚያምነው ይህን ነው! እስካሁን የተፈፀመው ወንጀል እንዲህ በመዋቅር ተቀስቅሶ የተፈፀመ ስለመሆኑ ይህ አንድ ማስረጃ ነው! https://t.me/GetachewShiferaw/7327?single
ቤተ ክርስቲያንን የማጥቂያ ሰበብ!
ብልፅግና “ቤተ ክርስቲያን ታውግዝ” እያለ ጫና እያሳደረ ነው። ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል የሚጠቀምባቸው የብሔር “ሲኖዶሶች”ም ይህን የብልፅግና ዘመቻ ተቀላቅለዋል። እነ አብይ ዘመቻ ያስጀመሩት ቤተ ክርስቲያን የማውገዝ ግዴታ ስላለባት አይደለም። ሊያጠቋት ሰበብ ፍለጋ ነው። ለምንድን ነው ውግዘቱ?
1) አቡነ ሉቃስ የተናገሩት ሲፈፀም የከረመውን ነው። ሳይፈፀም የጨመሩት ወንጀል አለ?
2) ተታልያለሁ እንዳሉ አባት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ይህን አይደለም የኃይማኖት አባት ከአብይ ጎን የነበሩት እነ ታዬ ደንድኣ የተናገሩት ነው። አብይ ጨካኝ ነው ብሏል ታዬ። አቡነ ሉቃስ ምን ጨመሩ?
3) የግድያው ወሬ የተጋነነ ነው። አብይ ራሱ በየጊዜው ጓደኞቹን ጭምር ልታስገድሉኝ እንደሚናገር ይታወቃል። ባለፈው ወር የቤተ መንግስት ጥበቃዎች ደብረዘይት የተገመገሙት ተፈርተው አይደለም እንዴ? አብይ በግል ጠባቂዎቹን “ልትገድለኝ” ወዘተ እያለ እንደሚጠይቅ ይነገራል። አሁን እንደ አዲስ ምን አስደነገጣቸው? አቡነ ሉቃስ አብይ ዲያብሎስ ነው ሲሉ በዝርዝር ህፃን ከመግደል ጀምሮ ያለውን አሳይተዋል። የኃይማኖት አባት ለዲያብሎስ እንዲራራ ፈልጋችሁ ነው?
ይህ ሁሉ ጫጫታ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት ሰበብ ነው! ብልፅግና ቀሳውስትን ገድሎ ይቅርታ ጠየቀ? ንፁሃንን ጨፍጭፎ ይቅርታ ጠየቀ? አመራሮቹ በህዝብ ላይ ሲለፉደዱ አንዴ እንኳን ይቅርታ ጠይቆ ያውቃል? እና ቤተ ክርስቲያን አንድ አባት ደፈር ብለው የአገዛዙን ወንጀል ስላወገዙ ለምን ታወግዛለች? ቤተ ክርስቲያን የሚወገዝና የማይወገዘውን የምትወስነው በራሷ መንፈሳዊ አሰራር እንጅ በማህበራዊ ሚዲያና በስልክ እየተደወለ በሚደረግ ጫና አይደለም።
ብታወግዝ ማውገዝ የሚገባት ቤተ ክርስቲያን የሚያቃጥለውን፣ ምዕመናን የሚያርደውን፣ ማፍያ ቡድን አደራጅቶ ቤተ ክርስትያን የማከፍለውን ኃይል
ጌታቸው ሽፈራው ይህን እንኳን ባልፅፈው ደስ ይለኝ ነበር። ቢያንስ ከስነ ምግባር አንፃር ጭምር ትክክል የማይመስላቸው ታላላቆቻችን ቢያነቡት ወዘተ ሊወቅሱን ይችላሉ። አልተለመደም። እኔም በግል ደስ አይለኝም። ግን እየሆነ ያለ ጉዳይ ነው!
ካድሬው ዘርፎ ጥሬ ስጋ በልቶ ቢራ የሚገለብጥበት ብቻ የሚመስለው ብዙ ሰው ነው። ከዛ በላይ አልፈዋል። ዶላር የለም እያሉ ጠባሳቸውን ሁሉ በኢትዮጵያ ሀብት እያሳከሙ ነው። ስብሰባ ላይ ሲገናኙ በየሚዲያው ስለሚወራው ስለ በጋ ስንዴ ወዘተ ሳይሆን ስለ ልብስ ዲዛይንና ስላስከረከሙት ወይንም ስላስቀጠሉት የአካል ክፍል ማውራት ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ማስዋብ፣ ገበታ ለወዘተ ከሚሉት በላይ ለግል ውበት በውጭ አገር ጭምር የሚያጠፉት ገንዘብ ቀላል አይደለም። ቤት አሳደስንበት ከሚሉት በላይ ነው!
በትህነግ ዘመን እነ ጀኔራል ምግበ ኃይለ ያልተጎዳ የጀርባ አጥንት ሁሉ በብረት አስቀይረው ጉድ ተብሎ ነበር። እነ አዳነች ከዛ በላይ ከፍ አድርገውታል። እነ ታከለ ኡማ የራሳቸውን ልብስ ዲዛይን እያስተዋወቁ ነበር። የእነ ታከለ ኡማ ደጋፊዎች አሁን በእነ አዳነች አቤቤ እየተሳለቁ ነው። ቀደም ብዬ የብልፅግና ካድሬ በ30 ሚሊዮን ብር ቤቴን አሳድሻለሁ ማለቷን ፅፌ ነበር። ብልፅግና አዲስ አበባን ማስዋብ፣ ገበታ ለምናምን ከሚለው በላይ ቡግር ሲወጣባቸው ወደ ውጭ አገር እውቅ የህክምና ተቋማት የሚመላለሱ ካድሬዎችን አፍርቷል። ካድሬው የልብስ ዲዛይን ብቻ አይደለም። ከደቡብ ክልል መምህራንን ደሞዝ ከፍ ያለ በጀት አካል ለመቀያየር እየዋለ ነው። የአማራ ክልል ጤና ተቋማት በድሮን እየወደሙ ባለስልጣናት ገፅታቸውን ጭምር የሚቀያይር ቀዶ ጥገና እስከማድረግ ደርሰዋል። ከዚች ሴትዮ ጋር የሚዞረው አገኘሁ
በኦሮሞ ብልፅግና ፍላጎት ብቻ ነው የምንለው በምክንያት ነው!
ከትህነግ/ህወሓት ጋር ሆኖ ዋግኸምራና አካባቢው ላይ ጥቃት ሲፈፅም የነበረ ቡድን ስምምነት መፈራረሙ ተሰምቷል። ይህ ቡድን ከየት መጣ ብለው የሚገረሙ ሰዎች ይኖራሉ። እነ ብርሃኑ ጁላና ጌታቸው ጉዲና ሲሰሩት የከረሙትን ለማመን ነው የሚከብደው።
ከአንድ አመት በፊት ጎንደር ኤርፖርት ላይ ከፍተኛ የቅማንት ኮሚቴ አመራር ይያዛል። ሰውየው በግል ሳይሆን በእነ ብርሃኑ ጁላ ጋባዥነት ነበር ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው። በመከላከያ በግልፅ ደብዳቤ ፅፈው፣ ቀጥታ ሽፋን ሰጥተው እንዳይወስዱት ቡድኑ አልታረቀም። ከመከላከያ ጋር ጦርነት ላይ ነበር። ስለሆነም ባላቸው ትስስር ሊያግዙት ሲሞክሩ በአካባቢው ሰው ጥቆማ ተያዘ። ጥናት ሲደረግ ከዚህ ሰው በፊት የሄዱት ጦር ኃይሎች ግቢ እየተመላለሱ ነው የሚውሉት። በዚህ መሰረት አማራው ላይ የተደራጁ ቡድኖችን በሙሉ ወደ አዲስ አበባ ወስደው ያነጋግሯቸዋል። የሰሞኑ ስምምነት ላይ መከላከያ በማያገባው አደራዳሪ የተባለው አማራውን የሚወጉትን ወደ አዲስ አበባ ወስዶ የእነ ሽመልስ አብዲሳ ቡድን እንዲያደራጅ ስላደረገ ነው። የትኛውም አካል ስብሰባ በማይፈቀድለት ሁኔታ እነዚህ ቡድኖች ናዝሬትና አዲስ አበባ መግለጫ ሲሰጡ ነው የከረሙት።
ነባራዊ ሁኔታው ከሆነ ይህ ቡድን የሰቆጣ ወጣቶችም አንይህ የሚሉት ነው። ይህ ነው የሚባል አቅም የለውም። የኦሮሞ ብልፅግና ስለሚፈልገው ብቻ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራር ጋር ሲደራደር ሰንብቷል። በመላ አማራ ክልል የናጣቸውን ፋኖ ደግሞ በመንደር ሽማግሌ “እጅ ስጥ” ይሉታል።
ነባራዊ ሁኔታው ፋኖ መከላከያ ሲቆረጥ ጭምር ያዳነው፣ አብሮት የደማ ኃይል ነው። የትናንቱ ቡድን ደግሞ ከትህነግ ጋር ሆኖ የመታው ኃይል
መሬት ላይ ያለውን ንቅናቄ በሚዲያ አትውጉት!
መሬት ላይ ያለው የአማራ ንቅናቄ በልኩ የፖለቲካና የሚዲያ አጋዥ አላገኘም። በርካታ በጎ ነገር በአሉታዊ መንገድ ይዘገባል። ለረዥሙ የአማራ ትግል ከሚጠቅመው ይልቅ የዕለቱን እይታ የሚያስገኘው ገፅ ይጎላል። ለምሳሌ ሰሞኑን ከሽማግሌዎቹ አንፃር በርካታ ተቆርቋሪ ነን ያሉ ሚዲያዎች የሰሩት መሬት ላይ ከተደረገው የተለየ፣ ለቀጣይ የአማራ ፖለቲካ የማይጠቅም፣ የአማራን ንቅናቄ ያለ አግባብ ስም የሚያሰጥና ከጀርባ የሚወጋ ነው። የፋኖ መሪዎች የሽምግልና አካሄድ ብልሹነቱን፣ የአገዛዙን ንቀት ወዘተ አውግዘው፣ ሽማግሌዎቹን ግን በሚታየው መልኩ አክብረው፣ ጦርነቱ በዚህ የአካባቢ ሽምግልና እንደማይፈታ አስተምረው መልሰዋል። ለፍትሕ ከተነሳው የአማራ ንቅናቄ የሚጠበቀውን ክብር አድርገዋል።
ሚዲያውን ሁሉም በቆረጣ ገብቶበት ሲያበላሽ እንደታየው አይደለም። አብዛኛው ለአማራ ፖለቲካ በጣም አሉታዊ ነው!
1)የፋኖ አመራሮች ያላደረጉት በጣም በአሉታዊ መልኩ አገዛዙ የአማራውን ትግል በሚያጥላላበት ሁኔታ በሚዲያ ተሰርቷል። ይህ መሬት ላይ ያለውን የማይገልፅ፣ አገዛዙ ንቅናቄውን በሀሰት ጭቃ የሚቀባው ላይ የተጨመረ አሉታዊ የሚዲያ አሰራር ነው። ከግንዛቤ እጥረትም፣ ከስሜታዊነትም ወዘተ የመጣ የሚዲያ አሰራር ነው።
2) ለቀጣይ አማራ ፖለቲካም ይህ አይነት የሚዲያ አካሄድ አይጠቅምም። ከጦርነቱ በኋላም ፖለቲካ አለ። ትህነግ እሴቱን በሙሉ ንዶ አሁን ትግራይ ውስጥ የሀይማኖት አባት ቢል፣ ሽማግሌ የሚሰማ ጠፍቶ ሰው እየፋጀ ነው። ኦሮሚያ እሴቱን አጥፍተው አህያ እየበሉ፣ ሰው እየጨፈጨፉ ነው። አረመኔነቱ ማንንም አልምር ብሏል። አማራው አቅም የሆነው ግዙፍ ስነልቦናው፣ እምነቱ ነው። ይህ መሬት ላይ እያለ ሚዲያ ላይ እያንሻፈፉ መዘገብ በቀጣይ ትውልድ ላይ ጭምር የተቃጣ ጥቃት ነው።
የአዲሱ ኢህዴን ንቀት!
ይህ መግለጫ የተሰጠው ተጠንቶና ታስቦበት እንዳልሆነ ይዘቱ ይናገራል። ይህ መግለጫ የተሰጠው ለታዬ ደንድኣ እስር ማስቀየሻ ነው። የአማራ ህዝብ ለአንድ የኦሮሞ ብልፅግና ታሳሪ ማስቀየሻ ጥሪ ነው የሚደረግለት።
ጥሪ አደረግን የሚሉት ቀልድ ነው። መሳሪያ ማስረከብ ነው። አርሶ አደሩንም በዛው መሳሪያ ለመቀማት። ሰላም አይፈልጉም ተብለው ሲጋለጡ “ሰላም ፈላጊ” መስለው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚሰሩት በአማራ ህዝብ ላይ ነው። የሰላም ጥሪ ብለው አብይ አህመድ ያዘዛቸውን ንቀት አስተላልፈዋል። አማራ ክልል ችግር እንዳይፈታ ተንኳሽ መግለጫ እንጅ የሰላም ጥሪ አይደለም። ከባሕርዳር ወደ ቅርብ ከተማ በመኪና መሄድ የማይችለው የአማራ ክልል አዲሱ አመራር /የአብይ አህመድ ኢህዴን/ “ትጥቅ ፍቱ” ብሎ መግለጫ ያወጣል።
ይህ በትዕዛዝ የተሰጠ መግለጫ የታዬን አጀንዳ ለመሸፈን ነው። የአማራ ክልል አመራር የአንድ ሰው እስር ዜናን ለመሸፈን ብሎ በአማራ ህዝብ ላይ እንዲህ ያለ ንቀቱን ያቀረሻል።
አዲሱ የአማራ ክልል አመራር አማራ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን የሚንቅ አስመስሎ እንደነ ታምራት ላይኔ እየቀሰቀሰ ያለ፣ አማራው በድሮን ሲጨፈጨፍ የመከላከያ ደም ተመለሰ ብሎ የሚደሰት ጠላት ኃይል ነው። ይህ ኃይል በበረከት ስምኦን አማካሪነት፣ በሰማ ጥሩነህ መልማይነት አብይ አህመድ ያስቀመጠው አዲሱ ኢህዴን ነው!
አዲሱ ኢህዴን መሬት ላይ ያለውን ስለማይረዳ ትናንት እጅ ስጡ ብሎ መግለጫ ሰጥቶ ዛሬ የወሎ ዕዝ ፋኖ አደረጃጀት ተመስርቷል። አዲሱ ኢህዴን የአብይን ፍላጎት እንጅ መሬት ላይ ያለው ጉዳይ አያገባውም!
ይህ ኃይል እንደ ድሮው ኢህዴን አማራን ስሙን እያጠፋ፣ ክብሩን እያሳነሰ ማስገዛት ነው አላማው! ይህ ኃይል አማራን
ክብር አይሰጡትም!
ነገ ሰሜን ዕዝ የተመታበት ዕለት ነው። ጥቅምት 24!
ይሁንና አገዛዝ ለይምሰል እንጅ ለሰራዊቱ ክብር አይሰጥም። ትህነግ/ህወሓት በክልል ደረጃ ሶስት ቀን አውጆ ለታጣቂዎቹ “መከላከያን ማርኮ፣ ገድሎ” እያለ አስፎኮሮላቸዋል። ሰራዊቱን ነዳነው እያሉ ዘፍነዋል። በቅርቡ ነው።
የሰሜን ዕዝ መጠቃት ግን በአገዛዙ አይታወስም። ምክንያቱም ሰራዊቱን ሞቶ ስልጣን እንዲያስጠብቅላቸው እንደ ክብሪት እያነደዱ የሚጠቀሙበት እንጅ ክብር አይሰጡትም።
ሰሜን ዕዝን ቢያስታውሱ ለሰራዊቱ ክብር ከመስጠታቸው ባሻገር ማን አዳነው ሲባልም አማራና ኤርትራ ሊሆንባቸው ነው። እንዲጠቀስ አይፈልጉም።
ያን ያስመቱትንና ክብር የማይሰጡትን ሰራዊት በአማራ ላይ አዝምተውታል። ቢሞት ጉዳያቸው አይደለም። እንዲያውም ወደ ስልጣን እንዳያይ በጦርነት ማባከን አለባቸው። በሁለት አመቱ ጦርነት ወቅት ሰሜን ዕዝ የተመታበት ተከብሮ ነበር። አሁን እየረሱት ነው። ምክንያቱም ጊዜያዊ መቀስቀሻ እንጅ ሰራዊቱን በመርህ ስለማያከብሩት ነው።
ሰሜን ዕዝን ሲያጠቃ የተመታ የትህነግ/ህወሓት ታጣቂ ሰሞኑን በሰመአትነት ሲወደስ ሰንብቷል። የተጠቃው ሰራዊት ግን አስታዋሽ የለውም። ሰራዊቱ ያለ ማቋረጥ ጦርነት ውስጥ እንዲከርም እንጅ እንዲታወስ አይፈልጉም! የምታውቁትን የሰራዊት አባል “ይኸው በአገዛዙ ዘንድ ክብር የለህም” በሉት። ጠላቱ አገዛዙ እንደሆነ ድገሙለት። (ጌታቸው ሽፈራው)
እስካሁን የተሰማውን ሲያስተባብሉ ሌላ የከፋ አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል! የአስቸኳይ ጊዜያዊ አዋጁ አማራን በጅምላ አላሰርኩም ቢልም ከዛም የከፋ ነገር ተሰምቷል። የእስረኛ ቤተሰቦች ወገኖቻቸውን በገንዘብ እንዲያስፈቱ ሚሊዮን ብሮችን እየተጠየቁ ነው። በጅምላ አፍነው አማራን ለወገኑ በሚሊዮን ብር እያስከፈሉ ነው።
የአዲስ አበባ ሀኪሞች አይናችን ጉድ አይቷል ብለዋል።
አብይ አህመድ ለተመስገን ጥሩነህ የደመቀ መኮንንን ስልጣን ቃል ገብቶለታል።
ፋሽዝም እንዲህ ቅጡን አጥቷል! ከጌታቸው ሽፈራው
በመጀመርያው ፎቶ የሚታየው ጫላ ቡልቱሜ የሚባል ሙዚቀኛ ነው። ይህ ሰው በቅርቡ ሆቴል ውስጥ ንፁሃንን በጥይት መትቶ ማንም የጠየቀው የለም። ይልቁን በሀሰት ፋኖ አጠቃኝ ብሎ በአማራ ላይ የጅምላ ፍጅት እንዲደረግ በፌስቡክ ገፁ ቀስቅሶ ነበር። በጥይት ንፁሃንን መትቶ ምንም አልተባለም። ገዥዎቹ ቢያቆስልም፣ ቢገድልም የእኛ ሰው ነው ብለው ነው።
በአንፃሩ ህፃናቱ ምንም ሳያደርጉ ጫማ እየጠረጉ፣ ሎተሪ እያዞሩ፣ በዚህ እድሜያቸው ስራ ላይ እያሉ በአማራነታቸው ታፍነው የናዚ አይነት የጅምላ ማጎሪያ ውስጥ እየተሰቃዩ ነው። ህፃን፣ ንፁህ፣ ለስራቸው ደፋ ቀና የሚሉ ቢሆኑም አማራ እስከሆኑ ድረስ መታሰር አለባቸው ተብሎ ነው።
በዚህ ወቅት መሃል ከተማ ንፁሃንን በጥይት ከሚመታ ጥጋበኛ ይልቅ፣ ሎተሪ አዟሪ ምስኪን ህፃናት ወንጀለኞች ናቸው። ምክንያቱም ወንጀል የሆነው ማንነታቸው ነው። ገዥዎቹን እስከጠቀመ ድረስ ጫላ አቁስሎም፣ ገድሎም፣ በጥላቻ የዘር ፍጅት ቀስቅሶም የሚጠይቀው የለም። ታታሪዎቹ ህፃናት፣ የደካማ እናት አባቶቻቸውን ራት ገዝተው ለመግባት የሚሰሩ ህፃናት ግን አማራ እስከሆኑ ድረስ ወንጀለኞች ናቸው። ፋሽዝም እንዲህ ቅጥ አጥቷል። የወቅቱ ፖለቲካ መገለጫ ይህ አስጠሊታ ሀቅ ነው።
እነ ጌታቸው ጉዲና ማጀቴ ላይ በቀል ፈፅመዋል!
እነ ጌታቸው ጉዲና እና ብርሃኑ ጁላ ማጀቴ ላይ በቀል ፈፅመዋል። የማጀቴና አካባቢው ሕዝብ የኦሮሚያ ብልፅግና ያዋቀረው “ኦነግ ሸኔ” ከከሚሴ ተነስቶ ሸዋን ሲያጠቃ ከጥቃት ተከላክሎ ራሱን አስከብሮ ቆይቷል። ማጀቴና አካባቢው ጥቃት ሲቀለብስ እነ ጌታቸው ጉዲና በመከላከያ ሲያስመቱት ኖረዋል። አሁን ሌላ የበቀል ጊዜ አገኙ።
ዛሬ ከ7_8 ሰዓት ማጀቴ አካባቢ ጦርነት ነበር። ፋኖ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ያሉት እነ ብርሃኑ ጁላ ኃይላቸው ሲመታ በቀላቸውን ንፁሃን ላይ አድርገዋል። ያኔ በብሔር ስም ሲያስወርሩት የተከላከላቸውን ሕዝብ ዛሬ በሰላም ማስከበር ስም ተበቅለውታል።
ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ቤት ለቤት እየገቡ ሴት፣ ህፃን፣ ሽማግሌ ሳይሉ ረሽነዋል። ትልልቅ ሰዎች “እናንተ ናችሁ ፋኖን የምትቀልቡ” ተብለው ተገድለዋል። ይህ ያደረ፣ የከረመ በቀል ነው። የኦሮሚያ ብልፅግና አስታጥቆ የሚልከውን ኃይል የሸዋ አማራ ሲመክት እነ ጌታቸው ጉዲና፣ ብርሃኑ ጁላ ሲበሽቁ ኖረዋል። ዛሬ ሰበብ ፈልገው ንፁሃንን ቤት ለቤት እየዞሩ እየገደሉ ነው።
በአለቃቸው አብይ አህመድ በኩል የሰላም ጥሪ፣ በሚያዙት በኩል ደግሞ ጭፍጨፋ እያደረጉ ነው። ጦርነቱ የታወጀው በሕዝብ ላይ ነው። ይህ ለቡድናዊ ጥቅማቸው የሚያደርጉት ፀረ አማራ ተልዕኮ በሕዝብ ትግል ይከሽፋል።
አገዛዙ የተጋለጠበት!
በፎቶው የምትመለከቱት አገዛዙን በደንብ ያጋለጠ ሀቅ ነው። ዝም ብሎ ወታደር አይደለም። ቅጥረኛ ወታደር ነው። ከቀናት በፊት መረጃውን ፅፌው ነበር። በመላ ኢትዮጵያ ታስረው የነበሩትን የትግራይ ተወላጆች የሁለት አመት ደሞዝ ከፍለው ወደ ጦርነት አስገብተዋቸዋል። ከእነሱ በተጨማሪ እነ ሽመልስ ያዋቀሩት የኦነግ ሸኔ ክንፍም ተሳትፏል። ለተወሰነ ጊዜ እንዲዋጉላቸው ነው። ሕዝብን እያስፈጁ ያሉት ለአላማ፣ ለአገር ተብሎ በተመለመለ ሳይሆን ወንጀለኛ ተብሎ ታስሮ ተፈትቶ ጦርነትን በቀን ስራነት አይቶ በተቀጠረ ኃይል ነው። በቅጥረኛ ሰራዊት።
አገዛዙ ቢሸፋፍነውም እውነታው አፍጥጦ ታይቷል። በፎቶው የሚታየው ሀረር ታስሮ የነበረ የቀድሞ የመከላከያ አባል ነው። ለዚህ ጦርነት በገንዘብ ተገዝቶ የመጣ ነው። ይህ ሀይል ደግሞ በቀል እየፈፀመ ነው። ከተሞቹ በከባድ መሳርያ እየተደበደቡ፣ ሴቶች እየተደፈሩ፣ ወጣቶች እየተረሸኑ ነው።
ይህን ታስሮ የከረመ ኃይል ያመጡት አማራ ላይ ፍጅት እንዲፈፅምላቸው ነው። እየተጠቀሙበት ነው። ደብረማርቆስ፣ ሸዋሮቢት፣ ደብረታቦር፣ ቆቦ በርካታ ንፁሃን የተረሸኑት በዚህ የጦርነት ስልት ነው። አማራን ይጠላል ያሉትን ሁሉ መሳርያ አስይዘው አሰልፈውታል።
የዐብይ አህመድ ቅጥረኛ ወታደሮች!
አማራ ንፁሃን ላይ ከባድ መሳርያ እየተተኮሰ ንፁሃን በጅምላ እያለቁ ነው። ሸዋ (ለሚ)፣ ደብረማርቆስና ደብረታቦር በርካታ ንፁሃን በከባድ መሳርያ አልቀዋል። ተቋማት ወድመዋል። የአርሶ አደሩ ቤትና እንሰሳት በከባድ መሳርያ ሆን ተብሎ እየተመቱ ነው። ይህን የአማራ ሕዝብ ከቁስል አድኖ የላካቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጭምር ያማረረ ነው። ብዙዎች መሳርያቸውን እየሸጡ ጠፍተዋል። ይህን የሚያደርጉ የዐብይ ቅጥረኞች ግን ሞልተዋል። መደበኛ መከላከያ ሆነው በጥላቻ ከተሰበኩት ባሻገር ቅጥረኛ ሰራዊት ተሰማርቷል።
አንዱና የመጀመርያው ከህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያ ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ ናቸው። አብይ ሲያስገርፋቸው ከርሞ አሁን በገንዘብ ገዝቶ አማራ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈፅሙ እያደረገ ነው።
የትግራይ ተወላጆች የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አልተፈቱም ነበር። አማራውን ለመውጋት ሲል ፈትቷቸዋል። የታሰሩበት ሁለት አመት ስራ ላይ እንደነበሩ ተቆጥሮ የሁለት አመት ደሞዝ ተከፍሏቸዋል። እድገት ተጠብቆላቸው ስራ ላይ እንደነበሩ ተደርጎ በሁለት አመት ያገኙት ነበር የተባለው ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ይህ በግልፅ ቅጥረኝነት ነው።
በቅርቡ ደግሞ ወደ ትግራይ 20 ሺህ የሚደርስ የመከላከያ ዩኒፎርምና ጫማ ተልኳል። ትህነግ ያሰናበታቸውንም ሆነ በካምፕ ያሉትን ወደ አማራ ክልል ሊያመጣ እንደሆነ ተገምቷል።
ከኦነግ ሸኔ ተማረኩ እያሉ የሚያሳዩትን፣ በየ ክልሉ ጡረታ የወጡትን ሳይቀር የአመታት ደሞዝ ከፍለው አማራ ክልል ላይ አሰማርተዋል። እነ ሽመልስ የፈጠሩት የኦነግ ሸኔ ክንፍን እንደሚጠቀሙበት ይታወቃል።
የአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በገንዘብ በተገዙ ወታደሮች ጭምር ነው።
በአማራ ክልል ነገ የሚሰየመው የኦሮሚያ ብልፅግና አሻንጉሊት አስተዳደር ተሿማዎች ከመሸ በስልክ ተነግሯቸዋል። የብዙዎቹ ዞኖች ተወካዮች አሁን ባለው ሁኔታ የምክር ቤት አባሎቻቸው እንደማይገኙ ታውቀዋል።
አብይ አህመድ ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ ዶክተር ጌታቸው ጀምበርንና አቶ ስዩም መኮንን አዲስ አበባ በቁም እስር ያሰነበተ ሲሆን እነሱን በይፋ ባይሆንም ከስልጣን አንስቷቸው ሰንብቷል። ከስልጣን የተነሱትም ክልከላው ተነስቶላቸው ወደ ባህርዳር ሄደዋል።
እስካሁን ከነበረውና ለአብይ አቤት ወዴት ሲል ከከረመውም የከፋ አስተዳደር ለመመስረት ሲመከር ሰንብቷል። በብልፅግና አሰራር ተሿሚዎቹ ከሳምንት በፊት የትምህርት ዝግጅትና ልምድን የሚያሳዩ መረጃዎችን ይጠየቁ የነበር ሲሆን የሚሾሙ መሆኑ ቀድሞ ይታወቃል። የነገዎቹ ተሿሚዎች ግን የተነገራቸው ከመሸ ነው። ለሌላ ሳትናገሩ በአስቸኳይ በጠዋት ድረሱ ተብለዋል።
ይህን ጦርነት በቀዳሚነት መቃወም ያለበት የኦሮሞ ሕዝብ ነው!
1) የኦሮሚያ ብልፅግና በሀሰት አማራ ኦሮሞን ሊያጠፋ ንቅናቄ የጀመረ አስመስሎ በኦሮሞ ሕዝብ ስም ያወጀው ጦርነት ነው። የሕዝብ ጦርነት ለማድረግ ቅስቀሳዎች አሉ። በስሜ አይሆንም መባል አለበት። ከዚህም ከዛም ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ አስተያየቶች ተለምደዋል። እነዚህን ያልተገቡ አስተያየቶች በጋራ ማስቆም ነው። በዋነኛነት ግን እነዚህ አልፎ አልፎ የምናያቸው አሉታዊ በሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ አስተያየቶች ገዥዎቹ ለራሳቸው ስልጣን የሚጠቀሙባቸው እንጅ የሕዝብ ዋነኛ መገለጫዎች አይደሉም። ስለሆነም ሰበብ ሳያስፈልግ ጦርነቱ የእኛ አይደለም ማለት ያለበት የኦሮሞ ሕዝብ ጉዳይ ያገባኛል የሚለው፣ ሰፋ ሲልም ሕዝቡ ነው።
2) የአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመበት ያለውን በደል ከኦሮሞ ሕዝብ የተሻለ ሊገነዘብ የሚችል የለም። ኦሮሚያ ውስጥ በገዥዎቹ መዋቅር ጭምር የተፈፀመውን ያውቃል። “ተዋቸው” ሲል “ምን አገባህ አንተ ኦሮሞ ነህ!” ተብሎ ተወቅሶ ጭምር በአይኑም ያየው በደል ነው። የአማራ ሕዝብ ብቻውን መጮህ አልነበረበትም። ሲበደል ያየው የኦሮሞ ሕዝብም አብሮት መጮህ ነበረበት። ኦሮሞ በደል ሲደርስበት በአፈና ወቅት በአደባባይ ለኦሮሞ ሕዝብ አጋር የሆነው የአማራ ሕዝብ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ የአማራን ሕዝብ ትግል በይፋ ባይደግፍ እንኳ ከበደል የመጣ መሆኑን በየቀየው ከተፈፀመው ዘር ፍጅት ያውቀዋልና የፍትሕ ጥያቄ መሆኑን አውቆ በእኛ ስም የጀመራችሁትን ጦርነት አቁሙ ማለት አለበት።
3) የኦሮሞ ሕዝብ በወርድና ቁመቴ ልክ ውክልና ያስፈልገኛል፣ ስልጣን ይገባኛል ሲል እንደነበረው የአማራ ሕዝብ የፍትሕ፣ የእኩልነት፣ የውክልና ጥያቄ አለው። አሁን አደባባይ ላይ የሚታዩት እንቅስቃሴዎች ጥያቄዎች ስላልተመለሱ የመጣ ነው። ገዥዎቹ ይህን ጥያቄ
ገዱ አንዳርጋቸውም ይሁን አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ለፍትሕ ለሚታገል ሕዝብ ምስክርነት ከሰጡልህ በሚጠቅምህ መንገድ መውሰድ ነው።
ሽመልስ አብዲሳ በኦሮምኛ፣ ጌታቸው ረዳ በትግርኛ የሚናገሩትን መረጃ አድርገህ እንደምትጠቀመው ወደድከውም ጠላኸውም በአማርኛም ይናገር በምልክት ቋንቋ መጠቀም ነው!
የስሎቪኺያ ወይም የትሪንዳድ የሆነ ባለስልጣን ስለ አማራ ሁለት ቃል ቢናገር አጀንዳ ታደርገዋለህ። ትክክል ነው። ወንጀል ሰርተዋል ብለህ የምታስባቸውማ ራሳቸው የነበሩበትን፣ የሚያውቁትን፣ ሴራውን፣ በአገዛዡ ላይ የመጀመርያ ምስክር ሲሆኑ አንተን ሊጨንቅህ አይገባም።
አገዛዙ የአንተን ወገን ገርፎ በራሳቸው ወገን ላይ ሊያስመሰክር ይጥራል። አገዛዙ እርስ በእርሱ ሲመሰካከር አንተ የህዝብህን የፍትህ ጥያቄ ላማጎልመስ ተጠቀምበት። የአገዛዙና የእሱ ቅርብ ሰዎች በፈቃዳቸው ሲመሰክሩ ገዥዎቹ እንቅልፍ ይጡ። ሲመሰክሩ የተዛነፈ ነገር ካለህ “ይህን ማለት ጥሩ። ይህ ግን ውሸት ነው” ብለህ አስተካክል። የአገዛዙ ሰዎች፣ ለአገዛዙ ቅርብ የነበሩትን አባብለህ ጭምር የማይሰጡህን መረጃ በራሱ ምክር ቤት ሲመሰክሩ በሚገባው መንገድ ከመጠቀም ውጭ ልታቅማማ አይገባም።
እርግጠኛ መሆን ያለብህ የጨነቀው ብልፅግና በራሱ ፓርላማ በዚህ ልክ መጋለጥ አይፈልግም። በፍፁም! እንዲያስተባብልለት ተሳዳቢ ቲክቶከር እየገዛ የቅርቡ ሰው የነበረ እንዲያጋልጠው ሊያሴር? በዚህ ወቅት ምን ሊያተርፍበት?
ልትዘነጋው የማይገባ አንተም በሆነ አደረጃጀት ከወንድሞችህ ጋር እንደምትጣላው ገዥዎቹም የጥቅም የሌላም ግጭት አላቸው።
የገዥ ባለስልጣናትን ስም እየጠቀስን “እንዲህ ሊያደርግ ነው” ብለን እየተቸን፣ ከእነዛ ከምንወቅሳቸው ባሻገር የራሱን ፓርቲ እያወገዘ ከተናገረልህ ምን አገባህ? ይበለው!
ልጠይቅህ! እንኳን በፓርላማ፣ የአንተ ሰዎች ፌስቡክ ልጥፍ ስል በአስተያየት ሲወራረፉ አይጨንቅህም? ትግሉን ይጎዱታል አትልም?
ፖለቲካ ሁሉን ነገር መጠራጠር ማለት አይደለም!
“ትግሉን
ትህነግ በሰሞኑ ጦርነት ተሳትፏል። ለማሳያ ያህል ከተዋጊው ባሻገር ለፌደራል መንግስት መረጃ እያቀረቡ ያሉ የህወሓት ሰዎችን እንሆ!
በቀጥታ ከሰራዊቱ የተላከው ከስር ቀርቧል!
1ኛ ኮ/ል ተወልደ አጠቃላይ የሕወሐትን የመረጃ ዘርፍ እየመራ ያለ ነው። ይህ ሰው በድርድሩ ወቅት ተደራዳሪ የነበር ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአማራን ጉዳይ እያጠናቀረ ለፌደራል መንግስቱ ያቀርባል።
2ኛ ተከስተ የተባለ የህወሓት አባል ብሔራዊ መረጃ ሁመራ ተመድቦ የነበረ ነው። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ሲከበብ የሀምሌ አምስት ኦፕሬሽን ከመሩት መካከል ነው። ወልቃይት ጠገዴ ሰፍረው የሚኖሩ ትግሬዎችን መልምሎ የደህንነት ስራ ያሰራ ነበር። አሁን አማራ ላይ መረጃ አሰባሳቢ ሆኖ ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየሰራ ነው።
3ኛ ሲሳይ የተባለ በጌታቸው አሰፋ መዝገብ ተከስሶ የነበረ ሲሆን በጎንደር መተማ የህወሓትን ደህንነት ስራ ሲያከናውን የነበረ ነው። በአሁኑ ወቅትም ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሳምረ የተባለውን ቡድን እያስገባ ይገኛል። ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየሰራ ነው።
4ኛ ገበረ ዮሐንስ የውጭ መረጃ ዳሬክተር የነበረ የህወሓት አባል ነው። በህወሓት የድሮው የጫካ ትግል ጎንደር እና ሁመራ በስለላ የነበረ ሰው ነው። በአሁኑ ወቅት የአማራውን ጉዳይ እየተከታተለ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ይሰራል።
5ኛ ሜ/ር ጀነራል ገብሬ ዲላ የፌደራሊስት ሐይሎች በሚል በሐገር ደረጃ አዲስ ኃይል በማደራጀት እየመራ ያለ ሲሆን አማራን ይቃወማሉ የሚላቸውን አማራ ክልል የሚኖሩ አካላት እያገኘ ኃይል እያደራጀ ነው። በዚህ ዘመቻ ተሳታፊ ነው።
ይህ በመረጃ ብቻ ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየሰሩ የሚገኙትን ለምሳሌ ያህል ለማሳየት ነው። በጦርነቱ ወቅት ከመከላከያ ሰራዊቱ የተቀነሱት የህወሓት አባላት
ለጊዜው ነው የምታሳቅቋቸው!
አዲስ አበባ ላይ አፈናው ቀጥሏል። ግን ለጊዜው ነው የሚያሳቅቋቸው። አማራ ክልል የነበረውን ሙቀት ገዥዎቹ ወደ አዲስ አበባ ወስደውታል። ሲያስሩ፣ ሲፍኑ በጊዜው ሊያሳቅቋቸው ይችሉ ይሆናል። ግን ቤተሰባቸው፣ ጓደኞቻቸው፣ ጎረቤታቸው፣ ከርቀት የሚያውቃቸው በሙሉ የታሰሩትን ሲያስብ የሚመጣለት የአማራ ጉዳይ ነው። የታሰሩት በአማራ ጉዳይ፣ በማንነታቸው ተጠርጥረው ነዋ።
ወገኖቻችን ያለ አግባብ ታስረው መሰቃየታቸው የሚያሳዝን ነው። ነገር ግን መታፈናቸውን ዋጋ አልባ ማድረግ የለብንም። የወገኖቻችንን መታሰር ዋጋ እንሰጠዋለን። አጀንዳ መደረግ አለበት። ፌስቡክ ላይ ብቻ አይደለም። የአዲስ አበባ ህዝብ በሚገባ አጀንዳ እንዲያደርገው ማድረግ የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ።
የወገኖቻችን እስር ባልንፈልገውም አፈናውን በደንብ በማሳየት አዲስ አበባ ላይ መታገያ ማድረግ ይገባል። በርካታ መንገዶችም አሉ።
አማራ ላይ ሲሆን የማይጥሱት ህግ የለም።
ባለፈው አማራ ክልል ምክር ቤት “በውይይት ይፈታ” ብሎ ወስኖ በነጋታው መከላከያ ጣሰው።
አሁን ደግሞ ክርሰቲያን ታደለን ያለ መከሰስ መብቱ እንኳን ሳያስጨንቃቸው አስረውታል።
ይህ ሁሉ የሚያሳየው ለማጥቃት የቋመጡለት አማራ ላይ ሲሆን የትኛውንም ህግ ለመጣስ ወደኋላ እንደማይሉ ነው። በነገራችን ላይ ክርሰቲያን ላይ ዘመቻ የተጀመረው በ OMN ነው። የሀሰት ድምፅ አቀናብረው ዜና ሰርተዋል። አማራ ላይ ሲሆን ከማንም ጋር ቢሆን ቅንጅት ይፈጥራሉ።
ነገር ግን ይህ እስር ያጋልጣቸው ካልሆነ፣ የድንጋጤያቸውን መጠን እና አማራ ላይ ሲሆን የት ድረስ እንደሚሄዱ ካላሳየ በስተቀር የሚፈልጉትን ውጤት አያመጣላቸውም።
ከላይ ከፓርላማው ህግ እየጣሱ ህግ እናስከብራለን ሊሉ እንደማይችሉ ያሳዩበት እስር ነው።
ገዥዎቹ የመረጡት ስልት!
“በተበታተነ መንገድ አንችለውም። ስለዚህም ወደ ከተሞች ይሰብሰብ። በሮችን ዘግተን። የራሱ መሰረተ ልማት ሲወድም ህዝብ ያማርርበታል። ያኔ በድሮንም፣ በሰርጎ ገብሞ እንዋጋቸዋለን”
የሚል ነው። በከተሞች የሚደረገው ውጊያ አማራን ለማውደም ለሚፈልጉት ገዥዎች ዋና ስልታቸው ነው። የላኩት ሰራዊት ቢያልቅ ጉዳያቸው አይደለም። ጦርነቱ ወደ ከተሞች ሰብሰብ ማለቱን ገዥዎቹ ይፈልጉታል። የማያውቁት ተራራና ሸጥ ድረስ መከተል አይችሉም፣ ኃይል መበተን አይፈልጉም። ሰርጎ ገቦቻቸው በሚኖሩበት ከተማ ነው ውጊያውን ማድረግ የሚፈልጉት።
ዛሬ ጊዜያዊ አዋጅ ሊያውጁ ይችላሉ። ግን አይሳካም!
1) ግጭቱ ከዚህ በከፋ ቁጥር በግጭቱ የህዝብ ተሳትፎ የበለጠ ይሆናል እንጅ አይቀንስም።
2) በህዝብ በበርካታ ጉዳይ ተማርሯል። በኑሮ ተማርሯል። ስራ የለም። በዚህ ሂደት ግጭቱን ካላጦዘው በስተቀር በጊዜያዊ አዋጅ መፍትሄ የሚያመጡ ከመሰላቸው ተሳስተዋል።
3) ወደ ከተሞቹ ህዝብ ከየቦታው እየተጠራራ ነው እየመጣ ያለው። ይህን ጉዳይ ፖለቲካ መፍትሔ ካልተሰጠ፣ ውይይት ካልተደረገ በኃይል እፈታለሁ ቢባል ሁሉም ወደመጣበት አካባቢ ቢያስፋፋው እንጅ የሚቆም ከመሰላቸው ተሳስተዋል።
4) ፋኖዎቹ እንዳይዘረፍ፣ ካድሬ እንዳይጠቃ እያደረጉ ነው። በብዙ አካባቢዎች ስርዓት አስከብረዋል። ይህን ሁኔታ ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት ለመቀየር የሚደረገው አካሄድ ከተሞችን ለዘረፋ፣ መዋቅሩን ለበቀል፣ ተቋማትን ለውድመት የሚዳርግ በመሆኑ ኃላፊነቱን የሚወስደው በችኮላ የሰላሙን ሂደት የረገጠው መንግስት ነው።
5) በጦርነት የተፈናቀለ፣ የተራቆተ ህዝብ ላይ ሌላ ጦርነት፣ ጦርነት ከከረመበት ህዝብ ላይ ሌላ ዘመቻ የሚያመጣው መዘዝ የከፋ ነው። “የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም” እንደሚባለው ከባፈው የተለየ አይመጣም ብሎ እስከመጨረሻው መፋለሙ አይቀርም። ጊዜያዊ አዋጁ አማራ ክልልን ሊያደቅ ይችላል። ገዥዎቹም ግን አያተርፉበትም
ውይይቱ ይቀጥል። የፖለቲካ መፍትሄው ይቅደም! ጊዜያዊ አዋጅ መፍትሄ አይደለም።
አማራ ክልል ሰላም እንዳይሆን የሚፈልገው ራሱ “መንግስት” ነው። ለሌሎቹ ሲሆን ሰላም ሰላም የሚለው ፋኖ ላይ ፉከራው አልበረደም። ፋኖ ከተማ ሲገባ አይዘርፍ፣ ፅ/ቤት አያቃጥል። ዘራፊዎቹን፣ ሾፌር የሚያግቱት ላይ ምንም አይሉም።
አማራውን በራሱ ጉዳይ እንጠምደወዋለን ብለው ያሰቡት ኃይሎች አሁንም ፉከራ ላይ ናቸው። ሀያ አመት መወያየት ይመረጣል እንዳላሉ አማራ ላይ ምርጫቸው ጦርነት ነው።
የመተከል ንፁሃን ገዳዮች አዲስ አበባና ናዝሬት ነው ያሉት።
በመተከል ጥቃት እንደ አዲስ ተጀምሯል። ከሳምንት በፊት እነ ሽመልስ አብዲሳ በአማራ ላይ ታጣቂ እያደራጁ መሆኑን መረጃ አጋርቸ ነበር። የአማራን ህዝብ በየአቅጣጫው እረፍት ለመንሳት እንደገና የጀመሩት ፕሮጀክት መቀመጫው አዲስ አበባና ናዝሬት ነው። የገዳዮቹ አለቆች ተጠርተው በኦሮሚያ ክልል እየደገፉ ነው። ይህ አካሄድ በአስቸኳይ መቆም አለበት። በሌሎች አካባቢዎችም መሰል ምልክቶች እየታዩ ነው።
አንድ ክልል በሌላው የአገሩ ክልል ላይ፣ ገዥ ፓርቲ በአንድ ህዝብ ላይ የግድያና ብጥብጥ ፕሮጀክት ነድፎ የሚሰራበት ሰይጣናዊ አካሄድ በአስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል። መቆም አለበት።
በቅርቡ የታፈኑት ሾፌሮች ገንዘብ ሳይቀር ለእንደዚህ አይነት ፕሮጀክት ነው የሚውለው። ይህን ትህነግ ሰርቶበታል። የሚደፋቸውን ታጣቂዎች ጠላታችን የሚሉትን ህዝብ እያገቱ መግደያ በጀት እንዲያዋጣ ሲያደርጉት ቆይተዋል።
በተረጋገጠ መረጃ ኦሮሚያ ክልል በአማራው ላይ ታጣቂ እያዘመተ ንፁሃንን ለማስጨፍጨፍ እየሰራ ነው። ይህ 100% የተረጋገጠ መረጃ ነው። በአስቸኳይ መቆም አለበት።
የአማራ ንፁሃን የሚታገቱት፣ የሚገደሉት አዲስ አበባና ናዝሬት በሚሰጥ ትዕዛዝ ነው። በቅርቡ ቡድኖቹ ናዝሬትና አዲስ አበባ ሆነው መግለጫ እንዲሰጡ፣ ቅስቀሳ አድርገዋል። ዝርዝር መረጃው የሚታወቅ ጉዳይ ነው።
ይህ አገር አፍራሽ አካሄድ መቆም አለበት። እንደ ጠላት አገር አንዱ ክልል በሌላው ላይ ገዳይ ማዘጋጀት፣ ህዝብ ለሚጨፈጭፍ በጀት መመደብ እጅግ የታመመ ፖለቲካ ነው። የዘር ጭፍጨፋ በገዥዎች በጀት ተመድቦለት እየተፈፀመ ነው። ይህ አገር አፍራሽ አካሄድ ማንንም አይምርም። መፍትሄው በአስቸኳይ ማስቆም ነው።
አማራው ወገኖቹ ሲገደሉበት ገዳዩ የት እንዳለ ያውቃል። አዲስ አበባና ናዝሬት እንጅ
ቀይ ባህርም፣ አሰብም አሁን የግጭት ምንጭ ሊሆን አይችልም! ( ጌታቸው ሽፈራው )
“አዲስ አበባ የእኛ ብቻ ነው” ብለው ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ ከአፍሪካ መዲና ንፃሃንን እያፈናቀሉ ያሉት ገዥዎች “አሰብን በጦርነት እናስመልስ” እያሉ እየቀለዱ ነው!
ከሰላም ስምምነቱ በኋላም ትህነግ/ ህወሓት ሲፈነጭ ለአገር አደጋ ነውና አስቁሙት ሲባሉ “ጦርነት ናፋቂዎች፤ ሰላም የማይወዱ” ብለው የዘመቱት ኃይሎች ከጎረቤት አገር ጋር ጦርነት ካልገጠምን እያሉ ነው።
“ሸገር” ብለው ከሰየሙት ከተማ በራሱ አገር በመቶ ሺህ ህዝብ ያፈናቀሉ ነውረኞች፣ ወለጋ አገርህ አይደለም እንዳላሉን ስለ አሰብ የኢትዮጵያነት ሊቀሰቅሱ መጥተዋል።
ኧረ የፈጣሪ ያለህ!
ኤርትራና ኢትዮጵያ ሰላም ከፈጠሩ በኋላ የኤርትራን ወደቦች ለመጠቀም ንግግር ተደርጓል። ኤርትራ መንገድ ሰርታ ጨርሳ፣ የእናንተውን ክፈቱ ሲባል አይሆንም ያሉት የአራት ኪሎዎቹ ገዥዎቹ ናቸው። ምክንያቱ ደግሞ ለወደቦቹ በቅርብ ርቀት ያለው አፋርና አማራ ይጠቀማል በሚል ነው። በዚህ ጉዳይ ስብሰባ ተደርጎ “ይቅርብን” ያሉት ራሳቸው በቀጥታ ደንበር ስለሌላቸው ነው። አሁን አሰብ ወዘተ የሚሉት ለአገር አስበው እንዳልሆነ ማንም ያውቃል።
የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ወደብ ነው ችግሩ? በአገሩ እንዳይኖር አድርጋችሁ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳያልፍ መንገድ እየዘጋችሁ፣ ከቀየው እያፈናቀላችሁ፣ የእምነት ተቋሙን እያፈረሳችሁ…. ወደብ እናስመልስ ልትሉት?
ካለፈው ጦርነት ሳያገግም በየቀየው ዘምታችሁበት፣ አስራችሁት፣ ማዳበሪያ እንኳን ማቅረብ ተሶኗችሁ፣ ባንኩን ባዶ አድርጋችሁ በሌላ አገር ስር ያለን ወደብ እናስመልስ ብትሉት ሊያምናችሁ?
ቀይ ባህርም አሰብም ወቅታዊ የህዝብ ጥያቄ አይደለም። ጥያቄው ቢነሳ እንኳን በሰላማዊ መንገድ ይነሳል እንጅ ህዝብ ጦርነት አይፈልግም። የጦርነት ፍላጎት የውጭ ኃይል
የስራ ማቆም አድማዋን ገዥዎቹ ይፈልጓታል!
ብዙ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ ወዘተ ጥሪ ወረቀት ፌስቡክ ላይ አያለሁ። ገዥዎቹ ለይምሰል ይቃወሙት ይሆናል እንጅ የሚፈልጉት ነው። በተለይ ያልተደራጀና ያልተጠና ከሆነ።
1) ገዥዎቹ ራሳቸው ህዝብ ስራ እያስፈቱ ነው። ጉዳያቸው አይደለም ባይሰራ። መንገድ ዘግተው ወደስራ እንዳይሄድ ሲከለክሉ ከርመዋል። ማዳበሪያ አያቀርቡ፣ ሲሚንቶ ከነጋዴ ጋር ተመሳጥረው በህገወጥ እየሸጡ ሌላውን ስራ አጥ አድርገውታል። በሶስት አመት ያልቃል የተባለ ግድብ 12 አመት የሞላው አለ። ፋብሪካዎቹ ስራ አቁመዋል። በሚቀጥለው አመት ደግሞ ተመራቂ አንቀጥርም ብለዋል። መስርያ ቤት ስራ የለም። ሄደህ ማየት ነው።ገዥዎቹ በኢትዮጵያ ላይ የስራ ማቆም አድማ ካወጁ ቆይተዋል። ብትሰራ ባትሰራ ጉዳያቸው አይደለም።
2) ወደ አገር ቤት የምትላከውን ትንሽ ዶላር ለራሳቸው አድርገዋል። ገንዘብ ጠፍቷል። አቅርቦት የለም። ነዳጅ በለው ስኳር ማቅረብ እየቻሉ አይደለም። ዘይት በለው ዱቄት ከቀን ቀን እየተወደደ ነው። ሱቅ ብትዘጋላቸው፣ ሳምንትና ወር ፀጥ ረጭ ብትል እረፍት የሰጠሃቸው ነው የሚመስላቸው። ችግሩ አንተ ባወጅከው የመጣ አድርገው፣ የአቅርቦት ጉዳይ ሳያስጨንቃቸው እረፍት ነው የሚወስዱበት።
3) የስራ ማቆም አድማ ስታደርግ ከአደባባይ ትጠፋለህ። ገዥዎቹ የሚፈሩት አደባባይ መውጣትን እንጅ ቤት ከተቀመጥክማ ደስታቸው ነው። ህዝብ የቤት ቁልፍ ቢሰጣቸው ዘግተውበት ቢጠፉ በወደዱ።
4) የስራ ማቆም አድማ የሚጎዳው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ውስጥ ያለውን ነው። አብዛኛውን ህዝብ ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ህዝብ የስራ ማቆም አድማ የጠራውን ያማርራል ማለት ነው። አሊያም ገዥዎቹ አድማ የጠሩት እንዲጠሉ ያደርጋሉ። ለኢኮኖሚ ምስቅልቅል የዳረገው ገዥው
የሚጠቅመው ይውሰደው!
ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ብዙ አቅም ያላቸው ሰዎች ወደ ፖለቲካው እንዲመጡ ሲያደርግ፣ ፖለቲካው አካባቢ ያሉ አካላት የመጡትንም የሚያርቁበት አጋጣሚ ብዙ ነው። ይህ እንዳይሆን ጥረት ማድረግ ጥሩ ነው።
1) የመጣበትን ህዝብ በሚያስፈርጅ መልኩ ሌላ ህዝብ ወዘተን በቲክቶክ ይሁን በሌላ የሚሰድብን ማበረታታት፣ ስድቡን ወዘተ እንደ መዝናኛ መመልከት ሄዶ ሄዶ ለራስ ይተርፋል። ዛሬ ሌላ ሲሰድብ ተው ያልተባለ ነገ የራስክን ህዝብ በጎጥና በአደረጃጀት እየከፈለ ያዋርዳል። ሌላው ላይ የለመደውን ወደ ራስህ ህዝብ ያመጣዋል። እንደ ህዝብ ስድብ ነውር መሆኑን አውቆ አለማበረታታት ያዋጣል።
2) አንዳንድ የማያዋጡ አካሄዶችን አያለሁ። አንድ ድርጅት ሰሞኑን “ቄሶችና ሽማግሌዎች አርፋችሁ ተቀመጡ” የሚል መግለጫ አውጥቶ ተመልክቻለሁ። አክሳሪ ነው። አዎ! ገዥዎቹ በሽምግልና ሰበብ ትግል ማኮላሸት ይፈልጋሉ። ነገር ግን ትግል ላይ ያለ አካል “አትምጡብኝ” አይደለም የሚለው። ለገዥዎቹ ስልት አዋጭ አማራጭ ይፈልጋል። መጀመርያ በሽምግልና መልክ የሚመጡ አካላት ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ፣ ቢመጡ ምን መደረግ፣ ከማን ጋር መነጋገር፣ ምን መልስ መሰጠት እንዳለበት መወሰንን ይጠይቃል። ከሚመጣው ሽማግሌ የአገዛዙን መረጃ ታገኛለህ፣ ፍላጎቱን ታጠናለህ፣ አሳስቶ ከሆነ የላከው አንተ የሚፈፀመውን በደል በመረጃ ትግተዋለህ፣ ብልጥ ከሆንክ በስልታዊ መንገድ የአንተው የትግል አካል ታደርገዋለህ እንጅ አትገፋውም። ከገፋኸው “መንግስት ነው ትክክል፣ እነዚህ ናቁኝ፣ ችግራቸውን እንኳን ማስረዳት የማይችሉ” ይልሃል። የማትፈልግ ከሆነም ጊዜ ትገዛበታለህ። እንገናኛለን እያልክ ታራዝማለህ እንጅ ቃል በቃል “እንዳትመጣብኝ” አዋጭ አይደለም። ሽምግልና ላትቀመጥ ትችላለህ “እንዳላይህ” ግን አትለውም።
ፖለቲካን ግንባሩን ብቻ ካየኸው ይህ ሀሳብም ላይመችህ ይችላል።
ኦነግ ሽሜ!
1) አገር አቋሬጭ መንገድ ዘግቶ በርካታ ሾፌሮችን አግቶ ገንዘብ እየተቀበለ ነው። እንደ ቴሌቶን ወስደውት ይሆናል። የገዥው መግለጫ የለም። ማንም አላወገዘም።
2) በአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት ከተማ ገብቶ ይወጣል። “ፅንፈኛ” አይባል። ይዘመትበት አይባል። ዜና የለ። የጋራ ግብረኃይል ስሙን አይጠራ። ፀጥ ጭጭ።
3) የወረዳ አመራር አግቶ ይገድላል። “አገር ሊያፈርስ” አይባል። “የትግስታችን ልክን ተፈታተነ” ብለው የሚፎክሩት የሉ። ሰልፍ አይወጣበት። አዲሱ አረጋም ሆነ፣ ለገሰ ቱሉ ረዣዥም የፍረጃ ፅሁፍ ተሰጥቷቸው አይለጥፉ። ዝም።
4) ነገ አዲስ አበባ ቢገባም ዜና የሚሰሩ፣ መግለጫ የሚሰጡበት አይመስልም። ያሰማራው ኃይል ነው በሌላው ላይ መግለጫ የሚሰጠው።
ኦነግ ሽሜ ቢገድልም፣ ቢያፈናቅልም፣ ከተማ ቢያወድምም፣ መንገድ ቢዘጋም አገር ሰላም ነው። ስምሪት ተጥቶት ነዋ። አፈናቅለው ህጋዊ ድሃ እንደሚሉት፣ ንፁሃንን “ህጋዊ ሟች”ም አድርገዋል።
አንድ ቀበሌ ተቆጣጥሮ የማያውቅ ድርጅት ባለፉት አመታት ቀበሌም፣ ወረዳም፣ ዞንም የያዘው በገዥዎቹ ፍላጎት እና ስምሪት ነው።
የነገው ሶስተኛ ሙከራ!
ትህነግ ሰሞኑን ሁለት ሙከራ ከሽፎበታል። በሌሊት ኃይል አመጣ ተመለሰበት። ቀጥሎ የፌደራል መንግስቱን ይዞ “ራያና ወልቃይትን ይመልሱልኝ” አለ። እንዳሰበው አልሆነም። ሶስተኛ ሙከራ ነገ ይደረጋል። ጌታቸው ረዳ ወደ ባህርዳር ይመጣል። ያኔ በጦርነት ባህርዳርን አውድሞ በአማራ ቲቪ ቀርቦ “አሸነፍን” ማለት ባይችልም አሁንም የሚመጣው ለሌላ ጦርነት ነው።
ሰሞኑን ብቻ ግልፅ ያደረጓቸው ጉዳዮች አሉ።
1) እነ ተሾመ ቶጋ አዲስ አበባ ላይ በጠሩት ስብሰባ የትግራይ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የሆነው ፍስሃ ማንጁስ “መሬቶቻችን ሳናስመልስ ትጥቅ አንፈታም” ብሎ እንቅጩን ተናግሯል። የተወሰኑ የይምሰል ሂደቶችን አድርገው ዋናው አላማቸው ወደ ጦርነት መግባት ነው።
2) ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ትጥቅ አልፈታንም ብሏል።
3) ፃድቃን መሬታችን እናስመልሳለን ብሎ ዝቷል።
4) መሬት ላይ ብዙ ሙከራዎች አሉ። ትናንት እንኳን ለአርሚ 11 ሶስት ክፍሎች የተላከውን ሁሉ እናውቃለን።
ይህ በሆነበት ስለ ተፈናቃይም ስለ ሌላውም ማውራት አይቻልም። ድንገት ተፈናቃይ የሚባል 50ም 100ም ቢኖር እንኳ ከተከዜ ማዶ ኃይል እያደራጀ “ተፈናቃይ” ብሎ አስተኳሽ የሚቀበል የለም። ተፈናቃይ ኖረም አልኖረም መጀመርያ ትህነግ ትጥቅ መፍታት አለበት። የነገው ውይይትም ስለ ሌላ ጉዳይ ሳይሆን ስለ ትህነግ ትጥቅ መፍታት፣ በሚዲያ የሚያደርገውን ትንኮሳ ማቆምና ወዘተ መሆን ይገባዋል።
በነገራችን ላይ እነ ጌታቸው ረዳ ደቡብ አፍሪካ ሲሄዱ ስለ ራያና ወልቃይት ይዘውት የሄዱትን ተንኮል ነገር በሌላ መልኩ ይዘውት ይመጣሉ። የሚዲያ ጨዋታውን ሁሉ አስበውበት ነው የሚመጡት። በአጭሩ ሌላ ዙር ሙከራ ነው።
በማይካድራ፣ በጭና፣ ቆቦ፣ ጋይንት፣ ደሴ፣ አጣዬ የፈፀሙት ጭፍጨፋ
የገጠመን ይሄ ነው!
“መንግስት” በአንድ ወቅት በውጭም በአገር ቤትም ያሉ ምሁራንን አማክሩኝ ብሎ “አማካሪ ቦርድ” አዋቅሮ ነበር። ምክራቸውን ስለማይፈልግ አሁን እየሰሩ አይደለም። እንዲያውም ወደ ተቃውሞ ገብተዋል። ምሁራኑን ገፍቶ ይጠቅሙኛል ብሎ ያመጣቸው ግን ተሳዳቢ ቲክቶከሮችን ነው። ተሳዳቢዎቹን ከምሁራኑ ያስበለጠው ከራሱ ባህሪ ጋር ስለሚቀራረቡ ነው። “መንግስት” ራሱ ተሳዳቢ ነው። እንደጎረምሳ ዛቻና ለከፋ አመሉ ነው።
በአጭሩ እነ ዶክተር ዮናስ ብሩን ገፍቶ፣ እነ ዮናስ ሙሉነህ (ዮኒ ማኛን) አመጣ። አገር አስተዳድራለሁ ብሎ ያሰበው በእውቀት ሳይሆን በስድብ፣ በማወናበድ፣ አጀንዳ በማስቀየር፣ በማሸማቀቅ ነው። ህዝብን፣ ድርጅቶችን፣ ግለሰቦችን እያሰደበ፣ እያሸማቀቀ ነው።
“መንግስት” የፈለገው በማህበራዊ ሚዲያ የአጀንዳ ትርምስ እየፈጠሩ የህዝብን ጆሮ የሚይዙለትን እንጅ ፀጥ ብለው ፖሊሲ፣ የችግር መውጫ መፍትሄ የሚያመጡለትን አይደለም።
የኢኮኖሚ ውድቀትን ለመከላከል ተብሎ ስራ አጥ መፍጠርን እንደ መፍትሄ የሚወስደው ከምርጫው ነው። ምሁራኑ መፍትሄ ይሰጡት ነበር። “መንግስት” ግን በሚቀጥለው “እንዴት አትቅጥረንም” ለሚሉት የምሁር መፍትሄ ሳይሆን ስድብ አዘጋጅቷል። “ሰርተህ ብላ፣ ስራ ፈት። አብይ ለአንተ ስራ ሊያመጣ ነው የተቀመጠልህ?” እያለ ያስወርፋቸዋል። ቲክቶከሮቹ የሚሳደቡትን ከዚህ ላይ ላለመፃፍ ነው። ነውር ስለሆነ!
መፍትሄው የስድብ ምንቸት ውጣ፣ የእውቀት ምንቸት ግባ ማለት ነው። ስድብ እንደ ፖሊሲ፣ ስድብ እንደመፍትሄ፣ ስድብ እንደ ብቃት፣ ስድብን እንደምርምር ውጤት፣ ስድብ እንደ መሳርያ ተጠቅመህ አገር ልትመራ? የዓለም ባንክ ኢኮኖሚስቶችን እየገፋህ፣ በዓለም አለ የተባለ የስድብ አይነትን በህዝብ ላይ ሲደፋ የሚውልን እየመረጥክ ከዚህ አዘቅት መውጣት አይቻልም።
አይቻል!
(ሁለቱም ዮናሶች መገለጫ እንጅ ግለሰባዊ ሙገሳም ወቀሳም
የትህነግ የመጀመርያው ዕቅድ ከሽፏል! በቀጣይም ይሞክራል።
ለሰሚው የሚገርም ነው። ሰሞኑን ትህነግ በራያ፣ አበርገሌና ጠለምት ወረራ ሊፈፅም ነበር። ድንበር ላይ ተመልሷል። የሆነው እንዲህ ነው።
1) ከትህነግ ላይ ወ*ረ*ራና ዘረፋ ሲፈፅም የከረመውን፣ ያስቸገራቸውን ሌባ ሁሉ ሰብስበው “ተፈናቃይ” ከፊት አደረጉ። ቀጥሎ ሚሊሻውን አስከተለ። ቀጥሎ “ጊዜያዊ አስተዳደር” ያላቸውን አመራሮች አስከትሏል። ከዚህ ሁሉ በኋላ ተዋጊ ኃይል አሰልፏል።
2) የመጡበት ሰዓት የሚገርም ነው። ሌሊት አምስት ሰዓት። ርስትም እንደ ቁስ ሊሰርቁ በውድቅት ሌሊት። የመጀመርያው ዕቅዳቸው የመከላከያ ሰራዊቱንም ሸውደው ማለፍ ነበር። እየሰረጉ እንዲገቡት ካደረጉ በኋላ ጠዋት አላማጣና ማይጠምሪ ጥግ ደርሰው በሚዲያ ሊያወናብዱ ነበር። ለጊዜው አልተሳካም። መከላከያ ሰራዊት አስቁሟቸዋል። አንዳንድ የፌደራል አመራሮች ጭምር “ግጭት ይፈጠራል” ብለው የትህነግን ኃይል ያስመለሱትን የሰራዊት አመራሮች አቋም በመልካም አልተመለከቱትም።
3) ትህነግ አሁን በተፈናቃይ ስም ከኋላ ታጣቂ ይዞ የጀመረው ስልት ለጊዜው ከሽፏል። ቀጥሎ ግጭት ፈጥሮ የፌደራል መንግስቱ በገላጋይ ስም “አንተም ተው አንተም ተው።” የሚል ውሳኔ እንዲወስንለት ይፈልጋል። ከእኔ ያፈነገጡ ናቸው ጦርነት የከፈቱት ማለት ይፈልጋል። እንደ ሰሞኑ በአስፓልት ሳይሆን እንደ ጦርነቱ ወቅት በየሸለቆው አልፈው ከገቡ በኋላ “ተቆጣጠርነው” አይነት ፕሮፖጋንዳም ይቀጥላሉ።
4) እየሆነ ያለው ሁሉ ለአማራ ህዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት ነው። በሌሊት መጥተው ርስቱን ሊነጥቁ መሆኑ ነው። ነባሩ ህዝብ በፕሮፖጋንዳ ሸሽቶ ሌባና ቀማኛውን አካባቢው ላይ አስፍረው ርስት ሊቀሙ፣ ህዝብ ሊያፈናቅሉ፣ በቀል ሊፈፅሙ መሆኑ ነው። ይህ አይሆንም። ህዝብ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ አለበት። ማንም በሌሊት መጥቶ የሚዘግነው ርስት፣ የሚያፈናቅለው
እስክንድርን የሚፈልጉት ህግ ለማስከበር አይደለም!
እስክንድር በዓለም የታወቀ ሰላማዊ ታጋይ ነበር። እስክንድርን ለዚህ ያደረሰው አገዛዙ ነው። ፓርቲ መስርቶ በሰላማዊ መንገድ እየታገለ “ግልፅ ጦርነት እንገባለን” ያለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው። እስክንድር ይህን መንገድ ሳይመርጥ ጦርነት ታውጆበታል።
እስክንድር ለአመታት በእስር የተለያቸውን ቤተሰቦቹን ጥሎ ለአዲስ አበባ ለመታገል ነው የመጣው። አሁን የመረጠው መንገድ ትክክል ሆነ አልሆነ ገዥዎቹ የሚፈልጉት ህግ ለማስከበር አይደለም። ለማዋረድ ነው።
እስክንድር ሰሞኑን ነው ከአንድ ድርጅት ጋር ስሙ የተያያዘው። ኦነግ ሸኔ ላለፉት አመታት ፋብሪካ ሲያቃጥል፣ ንፁሃንን ሲያርድ ጃል መሮን ፍለጋ መውጣቱን አልሰማንም። የእስክንድር ድርጅት ነው የተባለው ስሙ በተጠራ በሳምንት ውስጥ ሙሉ ዘመቻ ተደርጓል። እስክንድር መሰረተው የተባለው ድርጅት ይህ ነው የተባለ ወንጀል ሰርቶ አይደለም። እስክንድርን ስለሚፈልጉት አጋጣሚው ተገኘ ተብሎ ነው።
ከሁለት አመት በፊት የፃፍኩትን እደግመዋለሁ። መንግስት እነ ጃዋርን ሊያስር የነበረው በእስክንድር ነው። ሀጫሉ ከመገደሉ በፊት እስክንድርን አስገድለው ጃዋር ገደለው ብለው እስክንድርን ቀብረው ጃዋርን ሊያስሩ ነበር። እስክንድር ሰላማዊ ትግል ላይ እያለ ይህን ያህል ይፈልጉት ነበር።
የአማራ ክልል አመራር አሁን ሌላ ክፉ ጊዜ መጥቶበታል። የኦህዴድ ሰዎች እስክንድርን አስረው ወይንም ገድለው እንዲጨፍሩ እገዛ ካደረጉ መቸም የማይታረቅ ቂም ማትረፋቸው የማይቀር ነው። እስክንድር ወንጀል አልሰራም። እስከዚህ የገፋው አገዛዙ ነው። ችግር እንኳን ቢኖር በክልሉ ማዕቀፍ በሰላምም የሚፈታበትን መንገድ መፈለግ ካልሆነ በስተቀር ኦህዴድ እስክንድርን ለማዋረድ የሚሄድበትን መንገድ ካገዙ ህዝብ ጋር እስከወዲያኛው መነጠላቸውን መርሳት የለባቸውም። መታወቅ ያለበት አይደለም ከእስክንድር አማራን ካወደመው ትህነግ፣
ብልፅግና ኢትዮጵያን እንዲህ ነው የሚፀየፋት፣ የሚጠላት፣ የሚንቃት!
የሚገልፃት በክፋት ነው!
የሚስላት በተንኮል ነው!
የሚፈርጃት በምቀኝነት ነው!
ግለሰቦች መሰል ነገር ሊገጥማቸው ወይንም ከራሳቸው ችግር ተነስተው በስህተት በጅምላ ሊፈርጁ ይችላሉ። ስልጣን ላይ ያለ አካል ይህን ሲል ግን ጠልቶ እንደሚገዛት ማሳያ ነው።
በየትኛውም አገር ምቀኝነት አለ። ተንኮል አለ። ክፋት አለ። በኢትዮጵያም ይኖራል። የህዝብ መገለጫ ግን አይደለም። ህዝብና አገር ግን በእነዚህ ባህሪያት አይጠራም። ደግሞ በገዥ ፓርቲ።
ኢትዮጵያ የስንት በጎዎች አገር ነች። የእነ አበበች ጎበና አገር ነች። ምስኪኖችን ከጎዳና የሚያነሱት የእነ ቢኒያም አገር ነች። በገዳም ስለ ህዝብና አገር እየፀለዩ የሚኖሩ አባቶች አገር ነች። የኃይማኖተኞች አገር ነች። ለአገሩ ሲል መስዋዕትነት የሚከፍል፣ በኢትዮጵያዊነት አምናለሁ እስካለ ድረስ ገዥውን ሳይቀር በርታ የሚል ህዝብ አገር ናት።
ብልፅግና ቂም እንዳለበት ተራ ግለሰብ ነው አገርና ህዝብን የሚፈርጀው። ደግሞስ ክፉትና ተንኮል ከራሱ በልጦ ነው? መጅሊስና ሲኖዶስን እየከፈለ ስለ ሌሎች ክፋት ሊያወራ? ንፁሃንን አልያችሁ እያለ እያፈናቀለ ሌላውን በምቀኝነት ሊፈርጅ?
ይህ ፍረጃ ብቻ አይደለም ችግሩ። መሸታ ቤት እንደሚውል ግለሰብ በጅምላ የሚፈርጅ ተራ አስተሳሰብ የተሸከመ ኃይል ነው ስልጣን ላይ ያለው። አገር የምትመራው በዚህ ውዳቂ አስተሳሰብ ነው።
ሲኖዶሱ ሰሞኑን ስብሰባ ላይ ሲሆን እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ ብርሃኑ ጁላ፣ደመላሽ ወልደሚካኤልን ጨምሮ በቀጥታ ጫና በማድረግ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ አመራሮች “ባሉት ቦታዎች ኦሮሞ ካልሾማችሁ የኦሮሞ ሲኖዶስ እንዲቀጥል ይደረጋል።” በሚል ጫና እያደረጉ ነው። የተጠቀሱትን ጨምሮ በፌደራልና ክልል አመራርነት ላይ ያሉ የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሮች ዋና ስራቸው ሲኖዶስ ላይ ማሾም ሆኖ ሰንብቷል።
የሲኖዶሱ አባላት በመንፈስ ቅዱስ እንጅ በትዕዛዝ ሹመት እንደማይሰጥ ሲናገሩ የቆዩ ሲሆን የኦህዴድ ወታደራዊ፣ የመከላከያና የፀጥታ አመራሮች ግን እንደ ወረዳና ዞር አመራር ምደባ ለቤተ ክርስቲያንም እኛው ነው የምንሾመው ብለዋል። ካሉት 24 ቦታዎች በሙሉ የተወገዘውውን ቡድን አባላት እንዲሾሙም የሲኖዶሱ አባላት ጫና እየተደረገባቸው ነው።
የኦሮሚያ ብልፅግና ኦርቶዶክስ መፈንቅለ መንግስት ልታደርግብን ነው ሲል የከረመ ሲሆን በጠላትነት የፈረጃትን ቤተ ክርስቲያን ለማፍረስ በሙሉ አቅሙ እየሰራ ነው ተብሏል። ኦሮሚያ ውስጥ የተወገዘው ቡድን አባላት በእነ ሽመልስ አብዲሳ ፍላጎት በየደብሩ በስራ ከአስኪያጅነት ጀምሮ እየተመደቡ ሲሆን ጥበቃ የሚያደርጋቸውና በክልሉ ፀጥታ ኃይል ነው። በአንፃሩ ሲኖዶሱ የሾማቸው አባቶች ኦሮሚያ ውስጥ አሁንም እየተሳደዱ ነው።
የኦሮሚያ ብልፅግና ስልጣኑን ለማስቀጠል የትርክ ለውጥ ማድረግ አለብኝ የሚል አቋም የያዘ ሲሆን ለኢትዮጵያ አንድነት እና አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ቀናኢ የሆነች፣ የኢትዮጵያን ነገስታት የምታከብር፣ የኦሮሚያ ብሌፅግና የሚያፈናቅላቸውን ዜጎች መጠለያ የምትሰጥን ቤተ ክርስቲያን ጠላታችን ነች ብለው ከፈረጇት ቆይተዋል። ቀደም ሲል እነ ሀጅ ሙፍቲንም በሚፈልጓቸው ሰዎች ተክተው መፈንቅለ መጅሊስ ካደረጉ በኋላ “ሸገር ሲቲ” ብለው በጀመሩት ፕሮጀክት 13 መስጊድ ሲያፈርሱ ተቃውሞ አልደረሰባቸውም። በመጂሊሱ
መረጃ!
ፋኖና ልዩ ኃይሎችን ለመወንጀል በአማራ ከተሞች ሆን ብለው ጥይት የሚተኮሱ አካላት እንደተመደቡ መረጃዎች አመላክተዋል። ከአሁን ቀደም በስሜትና ሌሎች ምክንያቶች ጥይት የሚተኩሱ አካላት የነበሩ ሲሆን ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው ጥይትና መሳርያ ሻጭዎችም መፈተኛ ሲያደርጉት ይስተዋላል።
ይህን እንደ ስልት በመውሰድ የአማራ ክልልን ትርምስ ውስጥ ማስገባት፣ ፋኖና ልዩ ኃይል ላይ ዘመቻ ማድረግ የፈለጉ ገዥዎች ጥይት ተኳሾችን አሰማርተዋል ተብሏል። ይህ የጥይት ተኩስ እንዲቀጥል በማድረግ ጥይት በመተኮስ ነውጥ እየፈጠረ የሚገኘው ፋኖና ልዩ ኃይል ነው በሚል ሰበብ መወንጀል እንደሆነ ታውቋል።
ስለሆነም በየከተሞቹ ጥይት የሚተኩሱ አካላት አብዛኛዎቹ በገዥዎች ለአላማ የተላኩ እና ጥይት በመተኮስ ፌኖና ልዩ ኃይልን ለማስወንጀል ለገዥዎቹ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ እንደሆኑ መታወቅ አለበት። በስሜት መሰል ተግባር ላይ የሚሳተፉ አካላት ለገዥዎቹ የልዩ ኃይልና ፋኖ መክሰሻ መሳርያ እንደሆኑ አውቀው መቆጠብ አለባቸው። ህዝብም በየአካባቢው ጥይት የሚተኩሱት የልዩ ኃይልና ፋኖን ስም ለማስጠፋት፣ ከዚህም ሲያልፍ ለቀጣይ ልዩ ኃይልና ፋኖን ለማስወንጀል ያለሙ መሆናቸውን አውቆ ማጋለጥና ማስቆም አለበት።
ኢትዮጵያ በአማራ ላይ ብቻ አትፈርስም፣ ለአማራው ብቻ አትድንም።
ከስር ያለው የትህነግ የስነ ልቦና ጦርነት፣ ከገዥዎቹ የልብ ልብ ስላገኘ ነው። በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት እነዚህ አካባቢዎች በአማራ ክልል እንዲቆዩ ተፈርሟል። ነገር ግን የፌደራል መንግስቱ ዓለም አቀፍ ህግ እየጣሰ ለትህነግ የሚጠቅመውን ማድረግ ስለቀጠለ አሁንም ሌላ የእሳት ወረዳ ድረስ እየመጡ ነው።
“ደቡብ ትግራይ” ወዘተ የሚለው የመዋቅር ገፅ የራያና የዋግ አካባቢዎችን በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚያጠቃልል የሚገልፅ ነው። ለሚዲያዎቹ ዜና እንዲሆን የተደረገውም ትህነግ “የጊዜያዊ አስተዳደር ሰራተኛ ነኝ” እያስባለ እያስወራ ስለሆነ ነው። በመዋቅር ደረጃ መሰል ስምምነት የሚያፈርስ ስራ ሲሰራ የፌደራል መንግስቱም ሆነ ሁሌ ከኋላ የሚጎተተው የአማራ ክልል መንግስት ምንም አላሉም። ይህ የትህነግ የስነ ልቦና ጦርነት ማራመጃም ጭምር ነው። ነገር ግን መቆም አለበት። አማራው ዓለም አቀፍ ህግ እየተጣሰ የሚጎዳበትን ሁኔታ እስከመቸውም እየታገሰ ሊቀጥል አይችልም። መሆን የለበትም።
ኢትዮጵያ በደምና በአጥንት የቆመች አገር ነች። አማራው አይኑን ጨፍኖ መዝሙሯን ይዘምራል ማለት ግ ትፈርሳለች ብሎ ማንም ስግብግብ የያዘውን እየነጠቀ ሲቀጥል ለኢትዮጵያ ሲባል ዝም ማለት አለበት ማለት አይደለም። የኢትዮጵያ መዳን ለሁሉም የሚጠቅም እንጅ የአማራ ብቻ ጥቅም፣ አይበለውና በክፉዎቹ ምክንያት ኢትዮጵያ ብትፈርስ ለሌላው እንደ ገነት ወንዙ ዳር ሁሉ ለምለም፣ ለአማራ ብቻ የቀን ጨለማ የሚሆንበት ምክንያት የለም። በጦርነቱ እንደታየው አማራው እንደተጓዳው ሁሉ ትግሬውም ካለው መካከል አንድ ሚሊዮን አለቀብኝ እያለ ነው፣ ቁስለኛ ከተማ ሞልቶ ተቃውሞ እየወጣ ነው። ኢትዮጵያ ስትድን አብረን የምንጠቀም፣ ኢትዮጵያ ስትፈርስ አብረን የምንጎዳ እንጅ
ኦሮሚያ ውስጥ ትናንት በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፅሟል።
በተጠና መልኩ ከወለንጭቲ ወደ መተሃራ በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥቃት ደርሶባቸዋል። ጥቃቱ በተጠና መልኩ የተደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን 50 ያህል የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገድለው፣ ከ40 ያላነሱ ቆስለዋል።
ከተገደሉት መካከል አመራሮችም እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን መሳርያዎቻቸው ተወስደዋል።
ኦነግ ሸኔ ተብሎ የሚነገርለት የክልሉ መዋቅር የሚደግፈው ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ ነው የሌሎቹ ክልሎች በተለይም የአማራ ልዩ ኃይል ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ይጠቃለል የሚሉን። (ጌታቸው ሽፈራው )
_
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ የቆቦ ቀበሌ ሊቀመንበር እና የባለቤታቸው እናት ሰኞ ሚያዚያ 2/2015 ምሽት ሦስት ሰዓት ገደማ መገደላቸውን መተሐራ የሚገኙ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ተናግረዋል።
ግድያው የተፈጸመው ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ በተፈረጀው በሸኔ ታጣቂዎች እንደሆነ የተናገሩት ምንጮች፤ ምሽቱን በከተማው ረዘም ያለ የተኩስ ልውውጥ ይሰማ እንደነበርም ገልጸዋል።
ሊቀመንበሩ ከመተሐራ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘዋ ቆቦ ቀበሌን የሚያስተዳድሩ ሲሆን፤ ባለባቸው የደኅንነት ስጋት ምክንያት ከቀበሌዋ ውጭ መተሐራ ከተማ ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ነው የተጠቀሰው።
በሊቀመንበሩ ላይ ተኩስ የተከፈተው በረንዳ ላይ ሆነው ከቤተሰቦቻቸው ላይ እራት በመመገብ ላይ እንደነበሩ ሲሆን፤ ጥቃቱ ከደረሰባቸው በኋላ ወደ ሕክምና ሳይደርሱ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
አሁንም በቆቦ ቀበሌ በስፋት ይንቀሳቀሳሉ የተባሉት የሸኔ ታጣቂዎች ሰኞ ዕለት በአካባቢው አሰሳ በማድረግ ላይ በነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይም ጥቃት
1) ትህነግ ትጥቅ እንዳይፈታ ያደረገው “መንግስት” ነው። በሰላም ስምምነት ትጥቅ ይፍታ የተባለን ኃይል ተደራደራሪ የነበረው ሬድዋን ሁሴን “ስጋት ስላለበት አይፈታም” ብሏል። ይህ አልበቃ ብሎ ሰራዊቱ ስጋት ካለባቸው አካባቢዎች እንዲወጣ ተደርጓል። “መንግስት” ትህነግ ትጥቅ እንዲፈታ ፍላጎት የለውም። “መንግስት” ነው ኃላፊነቱ ያልተወጣው። በአንድ ወር ይፈፀማል የተባለን ትጥቅ ማስፈታት ከ5 ወር በላይ የወሰደው በሴራ ነው። አሁን ከአምስት ወር በኋላ ችግር ሲፈጠር በመግለጫ መጥቶ “የራሱ ሂደት አለው” ብሎ ማጭበርበር መፍትሄ አያመጣም። በዚህ ሂደት ለህዝብ ዋስትና የሚሰጠው ልዩ ኃይሉ ነው።
2) በትናንትናው ዕለት ትጥቅ ወደ ግምጃ ቤት እንዲገባ የሚያዝ ደብዳቤ ወጥቷል። ብልፅግና ልዩ ኃይሉ የግሉ ሰራዊት እንደሆነ አድርጎ በህገወጥ መንገድ በስራ አስፈፃሚው ያስተላለፈው ውሳኔ አልበቃ ብሎ ህዝብ ሳያውቅ የተደረገው ድብብቆሽና ችኮላ ሌላው ችግር ነው። እነዚህን ስህተቶች እንኳን ስህተት ናቸው ያልተባለበት መግለጫ ነው ዛሬ የወጣው።
3) ልዩ ኃይሉ ትህነግ ከሰሜን ዕዝ የወሰደውን ከባድ መሳርያ ገና በጥቃቱ ሌሊት ማስመለስ የጀመረ፣ ለሰራዊቱ የደረሰ፣ በየትኛው ግዳጅ አገራዊ ግዴታ የተወጣ ሆኖ እያለ የሚገባው ክብር ሳይሰጠው ነው ይህ ግልፅነት የጎደለው ሂደት የተጀመረው።
4) በተደረጉት ውይይቶች ግልፅ ቅድመ ሁኔታዎች ተቀምጠዋል። ትህነግ በሱዳንም በትግራይም በኩል ለወረራ ዝግጅት ላይ ነው፣ የአማራ ህዝብ ተፈናቃይ ሆኗል እና ሌሎችም ቀርበዋል። እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ነው። በጦር ሜዳም በድርድርም ትጥቅ ከመፍታት ውጭ አማራጭ የሌለውን ኃይል “ስጋት አለበት” ብሎ እንዳይፈታ አድርጎ አማራን ስጋት የለበትም የሚል ማደናገሪያ መፍትሄ መሆን አይችልም።
ይህ ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘ መረጃ ነው!
1) ትህነግ እንደ አዲስ በርካታ ወጣቶችን ወደ ስልጠና እንዲገቡ ምልመላ ተጀምሯል።
2) በመከላከያ ሰራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ማንኛውም የመኮንንነት ምልመላ ሁለት አመት ያገለገ መሆን አለበት። ነገር ግን ከሰሞኑ ኦሮሚያ ገና አመት ያልሞላው እየተመለመለ ወደ እጩ መኮንን ማለትም በአስር አመት የሚገኝ ማዕረግን በ6 ወር ለመውሰድ በልዩ ሁኔታ ማሰልጠኛ እየገባ ይገኛል።
3) ባለፈው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ትህነግ ትጥቅ እንደሚፈታ አንዱ የስምምነት አካል ነበር። አብዛኛው የትህነግ ተዋጊዎች በስምምነቱ መሠረት ትጥቃቸውን ፈትተው በሚሰጣቸው ካሳ መሠረት ወደ መሀል ሀገር ለመምጣት ነበር ፍላጎታቸው። ነገር ግን ሰሞኑን ከፌደራል መንግሥቱ የመጣ ትዕዛዝ ባሉት መሠረት የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎች በእጃቸው እንዲቆይ ተነግሯቸው።
4) ትህነግ በሀሰት በጦርነቱ ምክንያት ከአማራ ክልል የተፈናቀሉ በሚል ቁጥር በመቶ ሺህ በማድረስ ሪፖርት ሲያቀርብ የነበር ሲሆን ከተለያዩ የትግራይ ክፍል በመሰብሰብ ተዋግተን ወልቃይትን ማስመለስ አለብን በሚል የጦርነት ዝግጅት ላይ ነው። ይህ በሆነበት ነው የአማራ ልዩ ኃይል ትጥብ ይፍታ እየተባለ የሚገኘው።
አማራን በስልጣን ልታሸማቅቁት አትችሉም!
አማራ ስልጣን እንደማይገባው አድርገው ራሳቸውን ካሳመኑ ቆይተዋል። አማራን ምኒልክ፣ አጤ ምኒልክን ደግሞ በሀሰት “ሂትለር” እያሉ ሙዚቃ ሁሉ እንዲወጣ አድርገዋል። አማራን በሀሰት እንደ ናዚ ቆጥረው ስልጣን የማይገባ ብለው ራሳቸውን በኦነግ ትርክት አለማምደዋል። አማራ ስልጣን ፈልጓል ብለው መወንጀያ፣ ማሸማቀቂያ እያደረጉት ነው። የሆነው ግን ሌላ ነው፥
1) ኦርቶዶክስ ከትርክታችን ጋር አትመችም ብለው የራሳቸውን ቡድን ሲያዋቅሩ ያልተጠበቁት ተቃውሞ ገጠማቸው። ይህን ተቃውሞ አቅጣጫ አስቀይረው “አማራ ወደ ስልጣን ሊመጣ ነው” ብለው ጫካም ውጭ አገር ያለውንም ተገንጣያቸውን አብረን እንስራ ብለው ለመሰባሰብ ጣሩ። አማራ፣ከኤርትራ ጋር ሆኖ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግብን ነው እንዳላሉ የኤርትራ ባለስልጣናት አዲስ አበባ ሰንብተዋል።
2) ይህ ፍረጃ የተለመደ ነው። ሀጫሉን ራሳቸው በኦሮሞ አስገድለው አማራን አስረዋል። ከአስራት ሚዲያ በህዳር የለቀቀን ሰራተኛ ሰኔ በተፈፀመ ወንጀል አስረውታል። ስራ ላይ ያልነበረን፣ ቀጥታ ስርጭት አስተላልፎ የማያውቅን አስራት ሚዲያ በቀጥታ ስርጭት ግጭት ቀሰቀሰ ብለው ጋዜጠኞቹን አስረዋል። በምርጫው ወቅት “ዐንድ አማራ የሚባህ ድርጅት ለሽብር ያሰማራቸው” ብለው ምንም የሌሉበትን ሰዎች ስም በዶክመንተሪ አንስተዋል። በወቅቱ ሀሰታቸውን በሚገባ አጋልጠናል። የራሳቸውን ደህንነት ሰራተኞች የሽብር ቡድን አባል ብለው በሚዲያ አቅርበዋል።
3) ሰሞኑን አማራን ከስልጣን ድርሽ ማለት የሌለበት ብለው በጥላቻ ለያዙት አቋም ሰበብ አግኝተዋል። ክርስቲያን ታደለ ከጥያቄው በፊት ከህዝብ ጋር እንዳያያይዙት፣ የመፈንቅለ መንግስት ወዘተ እንዳይሉት አስጠንቅቆ ያነሳውን ጥያቄ የስልጣን ንጥቂያ አድርገው አማራን ፈረጁበት። ቀሰቀሱበት። ይህ ግን አልበቃቸውም።
4) ዛሬ “ባለስልጣናትን ለመግደል” በሚል አዲስ ክስ አምጥተዋል።
አሸባሪ ትጥቅ ሳይፈታ አገር ያዳነ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ ማለት በህዝብ ላይ ጦርነት ከማወጅ አይተናነስም!
1) ትህነግ ትጥቅ እንዳይፈታ ያደረገው መንግስት ነው። አቶ ሬድዋን ሁሴን “ህወሓት ስጋት አለበት” ብሏል። ለትህነግ ደህንነት ብለው ነው ያን ወንጀለኛ ታጣቂው እንዳይፈታ ያደረጉት እንደማለት ነው። ነገር ግን ሱዳን ያለውም እንዳይፈታ ተደርጓል። ሱዳን የትግራይ አካል አይደለም። ሱዳን ስጋት ስላለበት አይደለም የሱዳኑ ኃይል ትጥቅ ያልፈታው። አላማው ህዝብን ለማስጠቃት ዝግጅት ነው።
2)ጌታቸው ረዳ ለቅሶ ቤት ተገኝቶ ወልቃይትን በኃይል እንይዛለን ማለቱ ተዘግበ፣ል። ከአውሮፓና አሜሪካ ሄደው ሰሞኑን ሱዳን ያለው የትህነግ ኃይል ጋር ስብሰባ ያደረጉ የትህነግ ሰዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ወልቃይትን በኃይል አስመልሳለሁ እንዳላቸው በመግለፅ “እንዘጋጅ” የሚል ቅስቀሳ አድርገዋል።
በሌላ ስብሰባ ትህነግ ለምን ትጥቅ እንደማይፈታ የተጠየቀው ጌታቸው ረዳ “ከእኛ ውጭ ሆነው ለጦርነት የሚዘጋጁ ኃይሎች አሉ።” ብሏል። ኃላፊነት ላለመውሰድ ነው። የትህነግን ኃይል ለጦርነት የሚያዘጋጁት እነ ጌታቸው ጋር የሚውሉት ጀኔራሎች ናቸው። ዋናው ግን ለጦርነት እየተዘጋጁ እንደሆነ አምኗል።
3) እነ አዲሱ አረጋ የዘር ፍጅት አውጀዋል። ይህን የዘር ፍጅት የሚፈፅሙት ደግሞ በኦነግ ሸኔ እና ኦነግ ሸኔ አስመስለው በሚያሰማሩት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነው። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አዲስ ምልምል እያሰለጠነ ነው። ኦነግ ሸኔም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ትጥቅ ሳይፈቱ ሌሎቹ እንዲፈቱ ማድረግ የዘር ፍጅቱን ለማስፈፀም ነው የሚሆነው።
4) በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትግራይን ይይዛል የተባለው መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ብቻ ሳይሆን ከትግራይ አዋሳኞች ወጥቷል። በዚህ አካባቢ የሚኖረው ህዝብ በትህነግ የዘር ፍጅት
የኦሮሚያው ሰልፍ!
1) ላይ ላዩን ስለ “ለውጡ” ቢመስልም በዋነኛነት ግን ሰልፉ የተደረገው በስጋት ነው። ገና በአምስት አመት “ልቀቁ አሉን” የሚል ፍርሃት ያስደረገው እንጅ ለውጡ መጣበት የተባለው ቀንም ተረስቶ ነበር። መቸ እናድርግ ሲሉ አጋጣሚ ተገጣጥሞላቸው ነው የሚመስለው። ስልጣንን በስራና በመርህ ማስቀጠል ሲያቅት በሰልፍ የሚደግፈን ህዝብኮ አለ የሚል ማስታወሻ ቢጤ ይመስላል። “መንግስቴ ተጠቃ ብሎ የሚመጣ ህዝብ አለ” እንዳሉት ነው። “ለውጡ” ጠብቦ ጠብቦ ጅማ ላይ ደመቅመቅ እያለ ነው።
2) የብልፅግና አባላት በየክልላቸው ማደረግ ያልቻሉት ሰልፍ የአንድ ክልል ብልፅግና የ”ለውጡ” ተጠቃሚ/ባለተራ እንደሆን የተገለፀበት ነው። ስልጣኑ፣ ከስልጣኑ የተገኘው ጥቅም የአንድ አካባቢ እንደሆነ ራሳቸው የመሰከሩበት ነው። የኦሮሚያ ክልል ሰልፉን ሲያደርግ ይህን ግልፅ አድርጎ እንደሚያሳይ እንኳን ረስቶት ይሆናል። አሊያም ምን ያመጣሉ ብሎ ይሆናል። ፈጣጣነቱን፣ ልዩ ጥቅምን፣ ባለተራነትን ለምደውት ይሆናል።
3) ስለ ኢትዮጵያዊነት የተወራበት ለውጥ የቡድንና የብሔርተኝነት ማስፈፀሚያ ስለመሆኑ ዛሬ የታዩ ምስሎች ይመሰክራሉ። የኦሮሚያ ሰልፎች የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ስለማይታይባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት ወደ ደቡብ ክልል ሲሄዱ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያሸበረቀ አቀባበልን የዛሬ ሰልፍ አስመስለው እነ ሽመልስ አብዲሳ ጭምር ተጠቅመውበታል።
4) የሰልፉ አላማ ያሉትና እውነታው የሰማይና የምድር ያህል ነው። ሰልፉ ስለህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም እንደሆነ አውርተዋል። ቀበሌ፣ ወረዳና ዞን ያልወሰዱበት ክልል ግን የለም። ሁሉም አቤቱታ እያቀረበ ነው። ስለ ወንድማማችነት እያወሩ ነው። በለውጡ ወቅት ከፊት የነበሩት የአማራና የኦሮሞ ብልፅግና እንኳን ፊት ተነሳስተዋል። ስለ ፍትህ አውርተዋል። እውነታው ግን ሸገር በሚሉት ከተማ
እየተጠቀሙበት ያለው በመርህ ደረጃ “ልዩ ኃይል ለአገር ደህንነት አስጊ ስለሆነ መፍረስ አለበት” የሚለውን ነው። አሁን እየሄዱበት ያለው ግን ከመርሁ አኳያ አይደለም። በበርካታ መርህ ጥሰትና ሴራ የታጀበ ነው። ጊዜ ያልጠበቀ፣ ቅድመ ሁኔታ ያላሟላ፣ ወቅቱን ያላገናዘበ፣ ያለው ህግ ጋርም ያልተስማማ ነው።
1) በዋነኛነት የትግራይ ልዩ ኃይል መከላከያ ሰራዊቱን መምታቱን መነሻ አድርገውታል። ይሁንና መከላከያን መጀመርያ ከመታ በኋላ እጅግ ዘግናኝ ወንጀል የፈፀመውን የትህነግ ኃይል አሁንም ከእነ ትጥቁ እንዲቀመጥ አድርገዋል። ተጨማሪ ኃይል እየመለመለ ነው። በቅርቡ በለተያዩ አካባቢዎች ጥቃት ፈፅሟል። በዓለም መድረክ በ10 ቀን ውስጥ ትጥቅ ይፍታ የተባለን፣ መከላከያ ሰራዊትን የመታን፣ ህዝብን ያጠቃን ኃይል እስካሁን ትጥቅ እንዳይፈታ አድርገዋል። ትጥቅ እንዲፈታ ፍላጎት የላቸውም! ለሚጠሉት ህዝብና ኃይል ሚዛን ማስጠበቂያ እንዲሆን ፈልገዋል።
2) መከላከያ ሰራዊት የመታው ኃይል ከሰላም ስምምነቱ በተቃራኒ ተጨማሪ ኃይል እንዲያሰባስብ ሲደረግ፣ ለመከላከያ የደረሰ፣ ከመከላከያ ጋር ሆኖ የአገር ዳር ድንበር ሲጠብቅ የከረመው ነው ትጥቅ ይፍታ እየተባለ ያለው። ክህደት ነው፣ ሴራ ነው።
3) የትህነግ ኃይል ለጦርነት እየተዘጋጀ ስለመሆኑ “መንግስት” ያውቃል። ትህነግም መስክሯል። ሰሞኑን በነበር ስብሰባ “ታጣቂያችሁን ትጥቅ አላስፈታችሁም።” የተባሉት እነ ጌታቸው ረዳ “ከእኛ አቅምና ፍላጎት ውጭ ሆኖ ለጦርነት እየተዘጋጀ ያለ ኃይል እንጅ የእኛ አይደለም። ከእኛ በተቃራኒ የቆሙና ጦርነት የሚፈልጉ ኃይሎች ናቸው ይህን እያደረጉ ያሉት” ብለዋል። ይህ ኃላፊነት ላለመሸከምና ሌላውን አዘናግተው ጦርነት ለመክፈት የሰጡት ምክንያት ነው። ለጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑን ግን በይፋ ተናግረዋል። እነ ጌታቸው ለጦርነት እየተዘጋጀ እንደሆነ የገለፁት የትህነግ
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ የክልል ልዩ ኃይሎች የቡድን መሣርያዎችን ለመከላከያ እንዲያስረክቡ እና ወደ መደበኛ ፖሊስና ወደ ማረሚያ ቤት ፖሊስ እንዲቀየሩ መወሰኑ ተሰምቷል። ይህ ውሳኔ ጊዜውን ያልጠበቀ፤ ፍፁም ኃላፊነት የጎደለው፤ በተለይም ጥቃት ያንዣበበበትን ሕዝብ ለማስመታት ያለመ አደገኛ ወሳኔ ነው።
1) ከምንም በፊት በውሳኔው ላይ የተሳተፈው አመራር በሙሉ በቀጣይ ለሚፈጠር አገራዊ ትርምስ እና የሕዝብ ጥቃት ተጠያቂ መሆኑ መታወቅ አለበት። በተለይ በማንነቱ ተለይቶ እየተጠቃ ያለው፤ በሐሰት ትርክት የተደራጁ ታጣቂዎች በየአቅጣጫው እያጠቁት የሚገኘው አማራን ወክያለሁ ብሎ በውሳኔው የተሳተፈ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራር ለዚህ ታሪካዊ ስህተት ተጠያቂ መሆን ይኖርበታል።
2) ውሳኔው የተወሰነው በሽብተኝነት ተፈርጀው የነበሩ ታጣቂዎች መሣርያ ሳያወርዱ፤ ይልቁንም እንደ ትህነግ ያሉት የጥፋት ኃይሎች ተጨማሪ ሠራዊት እያሰለጠኑ እና በየአካባቢው እነዚህ ታጣቂዎች ጥቃት እየፈፀሙ ባሉበት ወቅት መሆኑ ሕዝብን ያለ ፀጥታ ኃይል ከለላ ለጥቃት የሚያጋልጥ እጅግ አደገኛ ውሳኔ ነው። ለአገር ህልውናና ዘላቂ ሰላም ቢታሰብ ኖሮ ከማንም በፊት ትጥቅ መፍታት የሚገባቸው በአገርና በሕዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ ጥፋት የፈፀሙትና እየፈፀሙ ያሉት ትህነግና ኦነግ-ሸኔ ነበሩ፡፡ ሆኖም እየሆነ ያለው ከዚህ ተቃራኒ በመሆኑ እንዳይኖሩ የተፈለጉት አገርና ሕዝብን የታደጉት እንደ አማራ ልዩ ኃይል ያሉት ናቸው፡፡ ውሳኔውን ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና አደገኛ የሚያደርገው ይህ ነው፡፡
3) በሰላም ስምምነቱ መሠረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የትግራይ አካባቢዎችን ይቆጣጠራል ሲባል ጥሎ በወጣበት፣ ትህነግ ትጥቅ እንዳይፈታ በተደረገበት፣ ኦነግ-ሸኔ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ እየገባ ያልተቋረጠ ጥቃት እየፈፀመ ባለበት እና የፌደራል ፀጥታ ኃይል ለሕዝብ
የአማራ ክልል አመራር ሰሞኑን በመግለጫ መጣሁ ሄድኩ እያለ ነበር። ከዛ ደግሞ ዝም ጭጭ ነው።
አማራው ከትህነግ ዘመን የቀጠለ ሌላ ብዝበዛና በደል ሲደርስበት አብዛኛው አመራር የሚመርጠው የራሱን ጥቅምና ስልጣን ማስጠበቅን ነው። የየራሱ የቡድን ወዘተ ጥቅምን አሳልፎ አይሰጥም። ለህዝብ ሲባል ግን ጉዳዩ አይደለም።
ከተወሰኑ አመታት በፊት የመተማ ደረቅ ወደብ እንዲታጠፍ ተደረገ። ከዛም የወረታ ደረቅ ወደብ እንዲሁ እንዲቀር ተደረገ። አሁን ደግሞ የኮምቦልቻው ደረቅ ወደብ ወደ ጅማ ተዛውሯል ተባለ። ድሮ ትግራይ ላይ እርከን ሲሰራ ያን አይተው መጥተው ነበር እንሰራለን የሚሉት። አሁን ለመስራት የግድ ኦሮሚያ ሊጀምርላቸው ይገባል። ስንዴም ችግኝም የሚወስዱት ከኦሮሚያ “ተሞክሮ” ነው።
ኢንዱስትሪዎቹ በመብራት ምክንያት ቆመዋል። ባለሀብቱ ዶላር አያገኝም። የሌላው የግል ባለሀብት ዶላር ሲመቻችለት አማራ ክልል ላይ ግን የመንግስት ፕሮጀክቶች እንኳን ዶላር አያገኙም። በአምስት አመት ይጠናቀቃሉ የተባሉ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሶስት እጥፍ ጊዜ ወስደው አሁንም አልተጠናቀቁም። የኢንዱስትሪ ፓርክ ወዘተ ተብሎ የሚገባው ስራ እየተሰራበት አይደለም።
ባለሀብቱን ለቀናት በቢሮክራሲ አስመርረው ወደ ሌላ ክልል ይልኩታል። መሬት ለአርሶ አደሩ ሳይሆን የአስመጭና ላኪ ንብረት ሆኗል። በግልፅ መሬት በጉቦ ይሸጣል።
አርሶ አደሩ ማዳበሪያ ሆነ ሌላ ግብአት በአግባቡ አያገኝም። አምርቶ ደላላ ነው የሚጫወትበት። ለምሳሌ ጥጥ ሱዳን ውስጥ 8 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው። ሌላ ክልል 5 ሺህ ብር ነው። የአማራ ገበሬ ከስሮ እንዲሸጥ እየተደረገ ነው። ሱዳን ልግዛችሁ እያለ አርሶ አደሩ አልፎ እንዳይሸጥ እየተደረገ ነው። ገበያ መፈለግ ወዘተ ተብሎ ስራ የሚሰራ የለም።
በአንፃሩ ተፈናቃይ
ጋምቤላ ምን ተፈጥሮ ነው?
ባለፈው ኦነግ ሸኔ የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማን ወርሮ ተመትቶ መመለሱ ይታወሳል። ትናንት በዛ የኦነግ ሸኔ ወረራ ወቅት ህግ ሲያስከብሩ ተሳስተዋል የተባሉ ፖሊስ አዛዦች ተይዘዋል ተብሎ መግለጫ ተሰጠ።
በጋምቤላም በንፁሃን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ደርሷል። ይሁንና ህግ ሲያስከብሩ ስህተት ተፈፅሟል የተባለው ንፁሃን በተገደሉበት አይደለም። ኦነግ ሸኔ በተመታበት ነው። እውነት ነው ኦነግ ሸኔን በድንጋንም በዱላም ቀጥቅጠውታል። የተያዙት ሲገደሉ የሚያሳይ ምስል አለ።
በክልሉ ንፁሃን ላይ ጥቃት ሲፈፀም የተጠየቀ የለም። የታሰሩት የኦነግ ሸኔን አባላት በጭካኔ ገደላችሁ ተብለው ነው።
ተመልከቱ! ጋምቤላም ሆነ ሌላ ክልል ንፁሃን ሲገደሉ የሚጠየቅ የለም። ጋምቤላ ላይ ኦነግ ሸኔ ላይ በተደረገው ህግ ማስከበር ስህተት ተፈፅሟል ተብሎ ለመጀመርያ ጊዜ የህግ ጉዳይ የተነሳው ለምንድን ነው? ለንፁሃን አዝኖ ገዳዮችን የሚያስር መንግስት እንደሌለ ይታወቃል።
የሆነው እንዲህ ነው። ኦነግ ሸኔ ጋምቤላን ወርሮ ከረመ። የባለሀብቶችን ሀብት ንብረት ወረሰ። ከ50 በላይ ባለሀብቶችን አግቶ ገንዘብ ተቀበለ። እስከ ዋና ከተማው ወረራ ፈፀመ። ይህ ሲሆን የሚያግዙት አካላት ነበሩ። በአጭሩ የኦሮሚያ ባለስልጣናት አግዘውታል።
ኦነግ ሸኔ ከሌላ ክልል ገብቶ ቦታ ይይዛል። የኦሮሚያ ፖሊስ ህግ ላስከብር ነው ይላል። ኦነግ ሸኔ ይለቃል። የኦሮሚያ ፖሊስ ይንዘዋል። ወደ ኦሮሚያ ይጠቃለላል። የጋምቤላ ክልል ሰዎች ይህን አሻፈረኝ ብለዋል። ኦነግ ተመትቷል። ንፁሃንን በገደሉት ሳይሆን ኦነግን በመቱት በርካቶች ታስረዋል።
ይህ የመስፋፋትና በወረራ የመጠቅለል ፖሊሲ በርካታ የጋምቤላ ተወላጆችን አስቆጥቷል። በኦነግ ስም ክልሉን የያዘው ኦሮሚያ ክልል ይውጣልን እያሉ ነው። መከላከያ ሰራዊቱ
ከፈረሱ አፍ! ጌታቸው ሽፈራው
በቀደም ሬድዋን ሁሴን ለትህነግ መረጃ እየሰጠ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን እንዴት እንዳስመታው ፅፌ ነበር። ትናንት Asfaw Abreha ከፈረሱ አፍ መረጃውን ይዞት መጣ። የትህነግ ታጣቂ አመራር የሆነው ገ/እግዚአብሔር በየነ (ወዲ አንጥሩ) እንዲህ አለ፦
“ዓቢይና ኢሳያስ እኛን ለማጥቃት ስምምነት ሲያደርጉ በቦታው የነበረ ሰው ደውሎ ነገረኝ። እነሱ ጥቅምት 28 ጥቃት ሊከፍቱብን እንደሆነ መረጃ ደረሰን። መረጃው እንደደረሰን ተሰብስበን መከርን። ቢያንስ ባካባቢያችን ያሉትን የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እንቀንሳቸው ብለን ወሰንን። እናም ቀነስናቸው!
በወቅቱ አቢይና ኢሳያስ እኛን ለመምታት ሲመክሩ በቦታው ተገኝቶ የነበረውና መረጃውን አሾልኮ የሰጠን ባለስልጣን ምናልባት ወደፊት በሚዲያ ቀርቦ ይመሰክር ይሆናል።”
መሰል መረጃዎችን ያደርስ የነበረው ሬድዋን ስለመሆኑ ቀደም ብሎ መረጃዎች ወጥተዋል። እኔ በበኩሌ በደረሰኝ መረጃ መሰረት ከወራት በፊት ፍትሕ መፅሔት ላይ ሰራዊቱን ከትግራይ ሲወጣ (ሁለተኛው ዙር ጥቃት) ያስመቱት ከ”መንግስት” የወጡ መረጃዎች እንደሆኑ ፅፌያለሁ። ሬድዋን ይህን ስለማድረጉ የሚያውቁ አካላት አሉ።
የሰሜን ዕዝ ሲመታም ሆኖ፣ በሁለተኛው ዙር ሰራዊቱ ከትግራይ ሲወጣ የተመታው በእነ ሬድዋን መረጃ ነው። ትህነግ አሸንፎ አዲስ አበባ ገብቶ ቢሆን የመጀመርያ ጉምቱ ባለስልጣን ይሆን የነበረው ሬድዋን ነበር። ምን አልባትም ሊላይ ኃይለማርያም በደርግ ዘመን አዲስ አበባ ሆኖ ይሰራው የነበረው ከተናገረበት እጅግ ከፍ ባለ መንገድ ሬድዋን የውስጥ አርበኝነቱን ይገልፅ ነበር። ዶክመንተሪ፣ ፊልም ይሰራለት ነበር።
የዛ ሁሉ ሰራዊት ደም የዚህ ሰውዬ እጅ ላይ አለ። በሰሜን ዕዝም ሆነ ከዛ በኋላ ለተገደሉት የሰራዊት አባላት አንድ ቀን ይጠየቅበታል።
ከሰላም ስምምነቱ
ሰራዊቱ እንዲመታ የሆነው በትህነግ ጥንካሬ ሳይሆን በውስጥ መረጃ ነው። አንዱና ዋነኛው የትህነግ የውስጥ መረጃ የነበረው ሬድዋን ሁሴን ነው።
በትህነግ የስልጣን ዘመን የሬድዋን እናት ታስረው ነበር። ወዲያው ተፈቱ። ፖሊስ ግን 53 የመሬት ካርታ ይዞባቸው ነበር። ይህ በእናቱ ብቻ ነው። በዘመድ አዝማዱ የያዘው “ሬድዋን ሰፈር” የሚባል ነበር።
ታዲያ ይህ በትህነግ ስልጣን የራሱን ክፍለ ከተማ ሊመሰርት ምንም ያልቀረው ሰው ከለውጥ በኋላ ወደ ኤርትራ በአምባሳደርነት ይላካል። ኤርትራ ደግሞ “የህወሓትን አፈቀላጤ አልቀበልም” ብላ አንድ አመት ሙሉ እውቅና ሳትሰጠው ዝም ብሎ ከረመ። ኤርትራ ስለነቃችበት ተኮርፎ ነበር።
የሰላም ስምምነቱ ሲመጣ ከተማ እንዲዘርፍ ካደረጉት ሰዎች ጋር መታረቅ ለእሱ አስደሳች ነበር። በስምምነቱ ወቅት ከእነ ጌታቸው ረዳ ጋር አንድ ሆቴል ሲዝናና እንደነበር ይታወቃል።
ዛሬ የትህነግ ፍረጃ ሲነሳ እንደ ሬድዋን የተደሰተ የለም። ትህነግ በጦርነቱ ወቅት አዲስ አበባ ቢገባ የተሻለ ስልጣን ሊሰጣቸው ከሚችላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ሬድዋን ሁሴን ነው።
ሬድዋን የፖለቲካ ተሳትፎውን የጀመረው የተቃዋሚ ፓርቲ ስም ነው። በተቃዋሚ ስም ሰርጎ ገብ ሆኖ ከሰራ በኋላ፣ ስራውን ሲጨርስ ደግሞ ፓርቲውን አፍርሶ ኢህአዴግን ተቀላቀለ።
ወደ አስመራ በአምባሳደርነት በሄደበት ወቅት የኤርትራ መንግስት እውቅና ያልሰጠው የትህነግ ኤጀንት እንደሆነ ስለሚያውቅ ነበር። በጦርነቱ ወቅትም በሚዲያ እያስመሰለ፣ በእውኑ ግን የትህነግ መረጃ አቀባይ ጭምር ነበር።
ሰራዊቱ ድንገት ከትግራይ እየወጣ ነው ተብሎ የተመታ ወቅት ለሰራዊቱ መመታት ተጠያቂ ከሆኑት መካከል አንዱ ሬድዋን ሁሴን ነው። ሰራዊቱ ከትግራይ ከመውጣቱ ከአንድ ወር በፊት ለሬድዋንና ለሌሎች ባለስልጣት
2000 አባውራዎች በማንነታቸው ምክንያት ከአዲስ አበባ ሊፈናቀሉ ነው!
አዲስ አበባ “የአርሶ አደር ልጅ” እየተባለ ከኦሮሚያ በርካታ ህዝብ ቤትና መሬት ተሰጥቶታል።
ኮንዶሚኒየም ታድሏል።
–
አገር አፍራሽ ለነበረው ሁሉ መታሰቢያ ወተዘ እየተባለ መስርያ ቤት ተሰጥቶታል። ዋቆ ጉቱ የሚባለው ከዚያድባሬ ጋር ሆኖ አገር ሲወጋ ጀኔራል ጃገማ ኬሎ አንቆ ያመጣው ሰው ስቴዲዬም አካባቢ “ዋቆ ጉቱ ፋውንዴሽን” ተብሎ አንድ ግቢ ተሰጥቶታል። ቦታ ለመያዝ ነው።
–
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ቤት ተሰጥቷቸዋል።
በርካታ ሺህ መምራን ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደርጓል።
የሀሰት መታወቂያ የተሰራለት ሁሉ ቦታና ቤት ተሰጥቷቸዋል።
የፈለጉትን ሁሉ አድርገው የቀረውን የህፃናት ኳስ መጫዎቻ ሜዳ ሳይቀር አርሶ አደሩ ገብቶ እንዲያርሰው አድርገዋል።
ከተማ ውስጥ የፈለጉትን ሲሰገስጉ ህገወጥነት አልተባሉም። አርሶ አደሩን እግር ኳስ ሜዳ እረስ ሲሉት ህገወጥ አልተባለው። ኮንዶሚኒዬም በአጣና ሲቀሙ ህገወጥ አልተባለም። ህዝብ በቁጠባ የሰራውን ቤት ለራሳቸው ሰው ሲያድሉ ህገወጥ አልተባለም። አማራዎች በገንዘባቸው የሰሩት ህጋዊ ቤት ግን ህገወጥ ተብሎ እየፈረሰ ነው። ህገወጥ ያስባላቸው ማንነታቸው ብቻ ነው። በአፍሪካ መዲና የዘር ማፅዳት በዚህ መጠን እየተፈፀመ ነው።
–
ሁለቱ ፎቶዎች የሰማይና የምድር ያህል ርቀት አላቸው። የመጀመርያው አዲስ አበባ ላይ ከሚፈርሱት የ2000 አማራዎች ቤት መካከል ነው። ሁለተኛው ፎቶ መሃል አዲስ አበባ አርሶ አደሩ የእግር ኳስ ሜዳንም ሳይቀር አርሰህ ዝራው ተብሎ ሜዳውን ሲያርሰው ነው። አሁን ያለውን ሁኔታ በደንብ የሚገልፅ ነው። አማራው የኖረበት ህጋዊ ቤት በሌሊት እየፈረሰ ይፈናቀላል። ኦህዴድ አርሶ አደሩ ከተማ ውስጥ
ሰራዊቱ መውጣት የለበትም የምንለው ከአቅም አንፃር አይደለም። ህገወጥ፤ አገር አፍራሽ ስለሆነ ነው!
መከላከያ ሰራዊት ከግንባር መውጣት የለበትም ሲባል አማራው አቅም ስለሚያንሰው አስመስለው የሚስሉት አሉ። ይህ ፈፅሞ ስህተት ነው። አማራው ራሱን ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ሰራዊቱንም አገርንም ታድጓል። መከላከያ ሰራዊቱ መውጣት የለበትም እየተባለ ያለው ከአገር ጥቅምና ከህጋዊነቱ አንፃር ነው።
1) የደም ዋጋ የተከፈለበት የሰላም ስምምነት ሰራዊቱ ከአማራ ክልል እንዲወጣ ሳይሆን ትግራይን እንዲቆጣጠር ነው የሚያዝዘው። የሚጠበቀውም። በዋነኛነት ስምምነቱ እየተጣሰ ነው። ይህ ደግሞ ለሌላ ትርምስ ይዳርጋል።
2) መከላከያ ሰራዊቱ እየወጣ ያለው ትህነግ ትጥቅ ባልፈታበትና ሌላ ወ*ረ*ራ ለመፈፀም እየተዘጋጀ ባለበት ሁኔታ ነው። የመከላከያ ሰራዊቱ አመራሮች ይህን ሁኔታ ለባለስልጣናቱ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ይህን አገራዊ ሁኔታ እየታወቀ ሰራዊት እንዲወጣ መደረጉ የአገር አንድነትና ሰላም ላይ የሚመጣውን ችግር ያለማሰብ ብቻ ሳይሆን ችግር እንዲፈጠር እገዛ ማድረግም ጭምር ነው። አገር እንዲፈርስ ማገዝ ነው።
3) ሰራዊቱ ሲወጣ በርካታ ደባዎችና ማጭበርበሪያዎች ተደርገዋል። የሰራዊቱ አመራሮች በርካታ መረጃዎችን አቅርበው “መውጣት የለብንም” በማለታቸው ስልጣን ላይ ባሉት ተፈርጀዋል። ተገምግመዋል። “መውጣት አልነበረብንም ብላችሁ ለህዝብ ተናግራችኋል” በሚል ተገምግመዋል። ይህ አልበቃ ብሎ ህዝብን ለማወናበድ ተሞክሯል። ሰሞኑን ከግንባር የሚወጣው ኃይል ምዕራብ ዕዝ ሆኖ እያለ የሚወጣው ሰራዊት “ምስራቅ ዕዝ” የሚል ባነር ለጥፎ ነው የወጣው። መጀመርያ ነገር ለደህንነቱ ሲባል ሰራዊት የዕዙን ስም በባነር ሰቅሎ እያሳየ አይወጣም። ተደርጎ አያውቅም። ህዝብን ለማወናበድ ምዕራብ እዝ ምስራቅ ዕዝ ተብሎ ተፅፎበት ወጥቷል። ይህ ውንብድና ነው። ለምን ማጭበርበር አስፈለገ?
በጣም
ከመከላከያ ሰራዊቱ አመራር ፍላጎት ውጭ ሰራዊቱ እንዲወጣ እየተደረገ ነው።
በሰላም ስምምነቱ መሰረት የመከላከያ ሰራዊቱ የትግራይ አካባቢዎችንም መቆጣጠር ነበረበት። ይሁንና ከትግራይ ብቻ ሳይሆን ከወልቃይት ጠገዴ አካባቢም ሰራዊቱ እንዲወጣ እየተደረገ ነው።
ህዝብ የጠላትን ከፍተኛ የወረራ ዝግጅት በየቀኑ ስለሚታዘብ፤ “ከአካባቢው ሠራዊት ሊጨመር እንጂ ሊቀነስ አይገባም” በማለት ለፌደራል መንግሥትና ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ተደጋግሚ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ የመከለካያ መኮንነኖች ሳይቀሩ የህህነግን የወረራ እንቅስቃሴ ስለሚያውቁት ሠራዊቱ መቀነስ እንደሌለበት ለፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች አመልክተዋል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትም እንዲሁ በተደጋጋሚ አሳስቧል፡፡ ሆኖም በጠ/ሚው ውሳኔ ሠራዊቱ ከወልቃይት ጠገዴና ከሰሜን ጎንደር እንዲወጣ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይህ እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ትህነግ እድል ተሰጥቶት ሌላ ወረራ እንዲፈፅም እየተደረገ ነው። ቀጣዩ ግጭት አገርም እንዲያፈርስ የሚያደርግ ዕብደት ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡
ይህ ነገር አሁንም መቆም ይኖርበታል፡፡ ሕዝቡ ሰራዊቱ እንዳይወጣ እየጠየቀ ነው፡፡ መታወቅ ያለበት ሰራዊቱ ከትግራይም ሆነ ከአማራ ክልል መውጣትን ተቃውሞ ነበር። ይህ ውሳኔ የውጮቹን ለማስደሰት ሲባል በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረገ ነው። የአማራ ህዝብና ፀጥታ ኃይል ራሱን ቀርቶ አገር የጠበቀ ነው። ይጠብቃልም። የመከላከያ ሰራዊቱንም ከጥቃት ያዳነ ነው። ለትህነግ የሚያንስ አይደለም። እሳቤው ግን አደገኛ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ህዝብን ከጥቃት የመከላከል ግዴታ አለበት። በስምምነቱ መሰረት ከወልቃይት ቀርቶ ከትግራይ መውጣት የለበትም። ህዝብ ሰራዊቱ እንዳይወጣ በሚያደርግበት ወቅትም ችግሮች ቢፈጠሩ ተጠያቂው መንግስት መሆኑ መታወቅ አለበት።
እንዲፈጠር የተፈለገው ሌላ ጦርነት አገር ያፈርሳል እንጅ የአማራ ህዝብ የራሱን ወገን አሳልፎ የሚረጥበት ሁኔታ
ትህነግ ከሽብርተኝነት መዝገብ መነሳት የለበትም!
ብሊንከን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የትህነግንና የፌደራል “መንግስት” አመራሮች አግኝቶ እንደሚያወያይ ይጠበቃል። አጀንዳ ይሆናሉ ከተባሉት መካከል አንደኛው የትህነግ ከሽብርተኝነት መዝገብ መነሳት ነው። ነገር ግን ይህ ጉዳይ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል።
1) አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የፀጥታ ተቋማትን መረጃ ተጠቅሞ በሚመስል በተደራጀ መልኩ ባጋራው መረጃ እንዳስረዳው 7000 ያህል የትህነግ ነፍሰ ገዳይ አሸባሪዎች ወደ መሃል ኢትዮጵያ ስምሪት ተሰጥቷቸዋል። ይህ ትህነግ የሽብር ተግባሩን ካለፈውም በባሰ ሊሰራ እንደሆነ ማሳያ ነው። የአቶ አንዳርጋቸው መረጃ የግለሰብ አስተያየት እንዳልሆነ ይታወቃል።
2) ትህነግ በተለያዩ ግንባሮች ስልጠና እየሰጠ፣ ወደ ኤርትራ፣ አማራና አፋር ክልሎች ኃይል እያስጠጋ ነው። በሱዳን በኩልም በተመሳሳይ። ስለሆነው ትህነግ በሽብር የተፈረጀበትን ተግባሩን እንደገና ሊጀምር እንጅ አልተወም።
3) የሰላም ስምምነቱ በሚያዘው መልኩ ትህነግ /ህወሓት ትጥቅ አልፈታም። በስምምነቱ መሰረት ትጥቅ ሲፈታና ሌሎች ግዴታዎቹን ሲወጣ ነው ከሽብር መዝገብ ይነሳል የተባለው። በሰላም ስምምነቱ መሰረት እንኳን ከሽብር መዝገብ እንዲፋቅ ቅድመ ሁኔታዎቹ አልተሟሉም።
4) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትህነግ የተያዙ ቦታዎችን ተረክቦ እያስተዳደረ አይደለም። ትህነግ ትጥቅ ባላወረደበት፣ እንደባለፈው በተለያዩ አካባቢ ያለውን ሰራዊት መምታትን ጨምሮ፣ የሽብር ዝግጅትና እንቅስቃሴ የማድረግ እድሉ ሰፊ ነው። እያደረገም ነው።
5) ትህነግ ለፈፀመው ወንጀል ተጠያቂነት አልሰፈነም። የሽግግር ፍትሕ የሚባለው ገና አልተሄደበትም። ለፈፀማቸው ዘግናኝ ወንጀሎች ሳይጠየቅ ከሽብር መዝገብ ሊነሳ አይችልም። ይህ በንፁሃን ቁስል ላይ መቀለድ ነው። ለቀጣይ የኢትዮጵያ ሰላምም መልካም ተሞክሮ አይሆንም።
6) ይህ ሁሉ በሆነበት ትህነግ ከሽብር መዝገብ ተነስቶ
አርሶ አደሩ ጤፍ አልሸጥም አላለም!
የአማራ አርሶ አደር ወደ አዲስ አበባ እንዳይሄድ በመንግስት የፀጥታ ኃይል ስለተከለከለ ነው ጤፍ የተወደደው እንጅ አርሶ አደሩ አልሸጥም አላለም። አዲስ አበባ ከተማው ነች። የአዲስ አበባ ህዝብ የራሱ ወገን ነው። አርሶ አደሩ አይደለም ለሚሸጠው ስታልፍም ካልበላህ ብሎ የሚያስቸግር ነው። ችግሩ የተፈጠረው በገዥዎቹ ክልከላ እንጅ አርሶ አደሩ ወገኑ ላይ አድሞ አይደለም።
በዚሁ አጋጣሚ እየተነሱ ያሉ የቢዝነስ ሀሳቦች ግን ምርጥ ናቸው። አርሶ አደሩ ተደራጅቶ ተጠቃሚ መሆን አለበት። ይህ ትናንት የመጣ ሳይሆን የቆየ ሀሳብ ነው። የአዲስ አበባም ሆነ የሌላው ከተማ ህዝብም አርሶ አደሩ ተደራጅቶ ምርት ቢያቀርብ ተጠቃሚ ይሆናል እንጅ አይጎዳም። በቂ አቅርቦት ያገኛል። በመሃል ደላላ አያስወድድበትም። እንዲያውም ከተሞች ይህ የቢዝነስ ሀሳብ እውን እንዲሆን ማገዝ ነው ያለባቸው።
መታወቅ ያለበት ግን አርሶ አደሩ ጤፍ እንዳይሸጥ የተደረገው በመንግስት ነው። መንገድ እየተዘጋበት በተደጋጋሚ እየተመለሰ ነው። ሾፌሮች ታግተዋል። በጥይት ተመትተዋል። የጫኑት እህል ተዘርፏል። ዋስትና አጥቷል። በዚህ ምክንያት በቂ አቅርቦት ወደ አዲስ አበባ እየገባ አይደለም። ይህ አሰራር አዲስ አበባን በማስራብ፣ ህዝቡን በማሳቀቅ የራስን አላማ የማሳካት ስልጣን የያዙት አካላት አካሄድ ነው። የኦሮሚያ ክልል አርሶ አደርም ምርቱን “ሸገር” በሚባለው ከተማ ብቻ እንዲሸጥ እየተደረገ ነው።
ከዚህ ባሻገር “መንግስት” በግዳጅና በርካሽ ከአርሶ አደሩ ስንዴ እየገዛ ነው። በመላ ኢትዮጵያ አርሶ አደሩ ስንዴ በጎተራው እንዳያከርም እያደረጉ ነው። በዚህ ምክንያት አርሶ አደሩም ስንዴ በርካሽ ሸጦ ሌላ እህል ለመግዛት ተገድዷል። ይህም የጤፍን ዋጋ
የሰላም ስምምነቱ ተጥሶ የወረራ ዝግጅት እየተደረገ ነው!
በሰላም ስምምነቱ መሰረት እስካሁን የትግራይ አካባቢዎች በመከላከያ መያዝ ነበረባቸው። ጭራሽ ሰራዊቱ ህይዎት ገብሮ ከያዛቸው ቦታዎች እንዲወጣ ተደርጓል።
የትህነግ ታጣቂ መሳርያ መፍታት ነበረበት። አስረከበው የተባለው ከባድ መሳርያ ቀለም የቀባ የማይሰራ መሳርያ ነው። ቀሪው ትህነግ እጅ ነው። የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳርያን ጭራሽ ለይምሰልም አላስረከበም። ትህነግ በዋግምኸራ በኩል በቅርቡ ጥቃት የፈፀመው በቡድን መሳርያ ጭምር ነው። በጠለምት፣ ራያ አዋሳኝ አካባቢዎች የትህነግ ታጣቂ ስልጠና ላይ ነው። በሁሉም አካባቢዎች ለወረራ ተዘጋጅቷል።
ከሱዳን መንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት ሱዳን ውስጥ እየንቀሳቀሱ ኢትዮጵያን ሲያጠቁ የነበሩ ታጣቂዎችን አልደግፍም ብላ ስታስወጣ፣ ትህነግ ግን አሁንም ስልጠና ላይ ነው። በቅርቡ ካርቱም በተከበረ የካቲት 11 በዓል በሱዳን ለሚገኘው የትህነግ ታጣቂ ገንዘብ ተዋጥቶ፣ ተጨማሪ ኃይል እንዲመለምልና እንዲያሰለጥን ተደርጓል። ሱዳን ሆነው የትህነግ ታጣቂን የሚያደራጁ አዲስ አበባ ደርሰው ወደ ሱዳን ተመልሰዋል። ትግራይ የነበሩ የታጣቂው አመራሮች ከትግራይ አዲስ አበባ መጥተው ወደ ሱዳን እንዲሄዱ ተደርገዋል።
የትህነግ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኞች በአማራና አፋር ላይ አዲስ ዘመቻ ከፍተዋል። ከስምምነቱ ውጭ ትህነግ ለወረራ እንዲዘጋጅ እድል ተሰጥቶት እየተዘጋጀ ነው።
ያላወቁት ግን የአማራና የአፋር ህዝብ ራሱን መከላከል ብቻ ሳይሆን ሰራዊትና አገርን ያዳነ ህዝብ ነው። በእንዝላልነት ያስመቱትን ሰራዊት ከትህነግ ጥቃት አትርፎ ወረራ የቀለበሰው የአማራ ህዝብ ነው።
–
ከታሽ የተቀመጡት ቪዲዮ እና ፎቶዎች ከቤተክርስቲያን ጀርባ እነማን እንዳሉ በቂ ማሳያ ነው። ቪዲዮው ላይ ከጀርባ የሚታዩት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጠቅላይ ምክር ቤት ( መጅሊስ) ምክትል ሊቀመንበር ሲሆኑ በአንደኛው ጎን ያለው ደሞ ራያ አባሜጫ የድምፃችን ይሰማ አስተባባሪ የነበረው ሰው ነው። ሌሎቹ የሚታዩት ደሞ እነ አወሉ አብዱና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት እና በሕገወጥ መንገድ ጳጳስ ከሆነ ግለሰብ ጋር ነው።
ውሃብያ ይበልጥ ተገለጠ! ፟ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው
ባለጊዜዎቹ በእነ ሙፍቲ ላይ መፈንቅለ መጅሊስ አድርገው ያመጡት ውሃብያው ቡድን ቤተ ክርስቲያን ውግዘቱን ካላነሳችለት ቡድን ጋር ታይቷል። የውሃብያው ቡድን መጅሊስ ዋና መሪና ምክትል የተባሉት ናቸው የሚታዩት። የተወገዘውን ቡድን አባላት በአቻነት እንደ ዋነኛ ሲኖዶስ አይተው መሆኑ ነው።
ሰሞኑን የተወገዘው ቡድን አባላት ሌላ ችግር እየፈጠረ ነው። ውሃብያም ከኦህዴድ ጋር ሆኖ እያገዛቸው ነው። አስተባባሪያቸው የኦህዴዱ አወሉ አብዲ ከውሃብያው መሪ ጋር ይታያል።
ሲኖዶሱና ሌሎች አባቶች እያሉ የውሃብያው ቡድን ግን እስካሁን ውግዘቱ ካልተነሳለት ጋር ነው ግንኙነቱን ያደረገው። በዚህ እንቅስቃሴ ውሃብያው ቡድን ሙሉ እጁ አለበት። በዚህ ምስል ይበልጥ ተገልጦ ነው የመጣው።
አላሁ ወክበር አላለም ?? pic.twitter.com/Ptgv4Hv9F8
— ምኒልክ (@Menellik_Shewa) March 6, 2023
በነገራችን ላይ በየመድረኩ ከሚለፈልፉት የሀሰት ምስክሮች በላይ የውሃብያው ቡድን ቤተ ክርስቲያን ለማፍረስ ከመንግስት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ የሚያሳዩ በርካታ መረጃዎች አሉ። ይህ ቡድን በነባሩ ሙስሊም፣ አሊያም በቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ የመጣ አይደለም። በኢትዮጵያ ላይ ነው። በቅርብ አመታት እዳው የሚታይ ይሆናል።
“ከአሸባሪው ቡድን የሚፈፀምብንን ጥቃት እንዳመጣጡ ለመመለስና ህልውናችንን ለማስከበር እንሠራለን”
“የሕግ ማሕቀፎች እና ሌሎች አስፈላጊ ሐቆችን ተቀብሎ ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ እስከመጨረሻው የምንታገል መሆኑን እናረጋግጣለን! ”
“የትግራይ ወ*ራ*ሪ* ኃይል ነባሩን የወልቃይት ጠገዴ አማራ አፈናቅሎ ያሰፈራቸውና በሕዝባችን ላይ የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ አካላት የሚመጡት ለፍርድ ካልሆነ በስተቀር፤ ወንጀለኞች በተፈናቃይ ስም ተመልሰው ዳግም ሕዝባችንን እንዲጨፈጭፉ የማንፈቅድ መሆናችንን እንገልጻለን!”
*****
እኛ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ፣ የካቲት 17 ቀን፣ 2015 ዓ.ም. በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማችን ተሰባስበን “በፈተና እንፀናለን፤ በሥራ እንገለጣለን፡- ዘላቂ የሕግ አሸናፊነት” በሚል ርእስ ከመከርን በኋላ፤ የሚከተለውን ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡-
1) የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍፁም ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መሆኑን በማመን፤ እስከመጨረሻው ከወገኖቻችን ጋር ፀንተን ለመቆም ተስማምተናል!
2) ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ሁሉ፤ ከዚህ በኋላም ለሚደረገው የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ትግል የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ እና ማንኛውንም ተልዕኮ ለመቀበል ቃል እንገባለን!
3) የወልቃይት ጠገዴ ትግል ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ሰማዕት የሆኑበት መሆኑን በመረዳት፤ የትግሉን ሰማዕታት አደራ ለመጠበቅ እንተጋለን!
4) የማንነት ትግሉ ፍፁም ፍትሐዊ እና ሕጋዊ በመሆኑ፤ ሌሎች ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የጥያቄው ተጋሪ እንዲሆኑ እና ከፍትሕ ጎን እንዲቆሙ እውነታውን ለማስገንዘብ እንሠራለን!
5) የማንነት ትግሉ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ በመሆኑ፤ ሌሎች አገር ዐቀፍና ዓለም ዐቀፍ ተቋማት እንዲሁም የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እውነታውን ተገንዝበው ከፍትሕና ከእውነት ጎን እንዲቆሙ እንሠራለን!
6) ትግሉ ለጥቂት ግለሰቦች
ለእውነት በመወገኑ 33 ጠበቆች ቆሙለት፤ ሕገወጡን ሲኖዶስ የሚመሩት ፓስተሮችና ደሕንነቶች ናቸው ሲል ያጋለጠው ፓስተር ቢኒያም
ለእውነት ተሟጋቹ ፓስተር ቢኒያም 33 የህግ ጠበቆች ቆመውለታል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ የፍርድ ቤት ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑ ተነግሯል፡፡ ፓስተር ቢኒያም በኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ላይ እየደረሰ ያለውን ፖለቲካዊ ሴራ በመቃወም በይፋ ድምጹን በማሰማቱ ለእስር መዳረጉ ይታወቃል፡፡ የጠበቆች ቡድን ክርክር ፓስተር ቢኒያም በ5000 ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ተወስኗል። ሌላው አስገራሚ የተባለው ነገር ለዋስትና ለሚከፈለው ብር በፈቃደኝነት ግለሰቦች ከግል ኪሳቸው ለማሰባሰብ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተሰምቷል። (AsharaM)
እውነት እጥፍ ድርብ አድርጋ ትከፍላለች። ፓስተር ቢኒያም በዓይኑ ያየውን እውነት ተናገረ። የተናገረው ግልፅ ነው። የተወገዘውን ቡድን የሚመሩት የእነ ዮናታንና እዩ ጩፋ ፓስተሮችና የመንግስት ደህንነቶች መሆናቸውን በአካል ያየውን መሰከረ። እውነት በመናገሩ ታሰረ።
ግን እውነት ትከፍላለች። ለአንድ እስረኛ አንድ ጠበቃ በቂ ነበር። ነገር ግን ለእውነት በመወገኑ 33 ጠበቆች ቆሙለት። ከእነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ ለመናገር እድል አያገኙም። ከሰዓትም ከሌላውም አንፃር ክርክር የሚያደርጉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው። ሌላ ገንዘብ የሚያገኙበትን የፍርድ ቤት ቀጠሯቸውን ትተው ለማይከራከሩበት ጉዳይ በነፃ የቆሙት ስለ እውነት ነው። አጋር ለመሆን ነው።
ለእውነት የቆመ መልካም ዋጋውን አያጣውም። እውነት ለያዘችው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቆመው ፓስተር ቢኒያም ምስክር ነው። 33 የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ጠበቆች ጥብቅና ቆመውለታል። ስላልተመቸው፣ በቦታው ስላልተገኘ “ጥብቅና ሳልቆምለት” የሚል እንደሚኖር ግልፅ ነው።
ይህን አይነት አጋርነት ጥቁር ለበሱ ተብለው ከስራ ለተባረሩ ሰራተኞችም መድገም ያስፈልጋል።
ጠበቆች ሆይ! ለእውነት ስለቆማችሁ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይኮሩባችኋል!
የውጭ አገር ዩኒቨርስቲዎች ለኢትዮጵያ 30 የፒኤችዲ ትምህርት እድል ይሰጣሉ። የምልመላና የስፖንሰርሺፕ ሂደቱ እና ስምምነቱ በትምህርት ሚኒስቴር እና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኩል ነው የሚከናወነው።
የዘንድሮው ስኮላርሽፕ የተሰጠው በሙሉ ለኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ሲሆን የሁለቱ መስርያ ቤት ዋና ኃላፊዎች ሳያውቁ በምክትሎቹ የተፈፀመ ነው። ከኦሮሞ ብልፅግና ሰዎች ውጭ ማንም እንዳያውቀው ተደርጓል። “የኦሮሞና ብሔር ብሔረሰብ ሲኖዶስ” ብለው ያዋቀሩት ከዚህ አንፃር ትንሽ ለማስመሰል ሞክረዋል።
የትምህርት እድል የሰጡት አንድም የሌላ ብሔር ተወላጅ የለም። በአደባባይ ለማይወጣው አይናቸውን በጨው ያጠቡ ስግብግቦች ናቸው። አንድም ከሌላ አያሳትፉም። አንድም!
ብሔር ብሔረሰብ እንጅሩ!
ኬኛ ብቻ!
ሰነዱ የሁለቱ ተቋማት ምክትል የሆኑ የኦሮሞ ብልፅግና አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የተፈራረሙት ነው።
ጌታቸው ሽፈራው እንደዘገበው !
ሌላውን ጨርሰው ነው ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጡት!
እነ አዳነች አቤቤ አንድ አውቶቡስ በ19 ሚሊየን ብር ገዝተው እንዳመጡ አድርገው ዜና እያሰራጩ ነው። ኮንትራት ወስዶ ያመጣው የተባለው የአንድ ኦሮሞ ባለሀብት ንብረት የሆነ ብራይተን ትሬዲን የሚባል ነው። ከእጥፍ በላይ እንዲያተርፍ አድርገው ሀብት ይፈጥሩለታል። ለአላማቸው ገንዘብ ያዋጣል። ይሄ ለእነሱ እጅግ ቀላሉ ነገር ነው። ከስር ያሉት ሌሎች የራሳቸው የዘረፋ ማስረጃዎች ናቸው።
1) መሬት እንዳይሸጥ የሚል እግድ በአደባባይ ይወጣል። በውስጥ ይወያዩና የእነሱ ሰዎች ተዘጋጁ ይባላሉ። እግዱ በውስጥ ደብዳቤ ይነሳል። እግዱ የተነሳበት ደብዳቤ በአደባባይ እንዳይታወቅ ይደረጋል። የእነሱ ሰዎች መሬት በውድ ይሸጣሉ። ሸጠው ሲጨርሱ ሌላ “መሬት እንዳይሸጥ” የሚል እግድ በአደባባይ ይወጣል። “እንዴ የባለፈው እግድ መቸ ተነሳ? ብለው የጠየቁ ቢሮ ደብዳቤ ያሳዩዋቸዋል። እንዲህ አድርገው ከተማውን ሸጠውታል።
2) ከወራት በፊት መኪናን ጨምሮ ከውጭ የሚመጡ ቁሳቁሶች ታግደው ነበር። የመኪና ዋጋ ጣራ ሲነካ “አሁን ነው ሀብት መፍጠር” ብለው በውስጥ ተነጋግረው የእነሱን ሰዎች ተዘጋጁ ብለው፣ የውጭ ምንዛሬ በጓዳ ፈቅደውላቸው ለተወሰነ ጊዜ ከፈቱት። መኪና አመጡ። ከቀረጥ ነፃ አስገብተው አተረፉበት። እንደገና እግድ ጣሉ። በእጥፍ ከሸጡ በኋላ።
3) ሲሚንቶ በህገወጥ መንገድ ተሸጠ ወዘተ እየተባለ በመንግስትም ደረጃ እየተለፈፈ ነበር። ዋናዎቹ ግን ራሳቸው ናቸው። ወጣቶችን አደራጁ፣ ፖሊስ፣ ደህንነት ወዘተ እንዲያግዛቸው ተደርጎ በጥቁር ገበያ እንዲሸጡ ተፈቀደላቸው። ሀብት ፈጠሩበት።
4) ኬኛ የሚባል የአልኮል ፋብሪካ እያቋቋሙ ነው። 7 ቢሊዮን ብር የተበደሩት ከአንድ የመንግስት ባንክ ነው።
5) ሻሸመኔ የትራክተር መገጣጠሚያን ያቆሙት ከልማት
የተወገዙት ይቅርታ ጠይቀው እንዳይመለሱ እያደረገ ያለው መንግስት ነው!
የተወገዘው ቡድን አባላት ይቅርታ ጠይቀው ለመመረስ ሲሞክሩ የሚያፍን ቡድን መኖሩ ታውቋል። ባለፈው ይቅርታ ጠይቀው የተመለሱት የታሰሩት ለቀሪዎቹ ለማስፈራራያ ሲሆን ከዛ በኋላም ይቅርታ ጠይቀው እንዳይመለሱ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል። ማስፈራሪያ የደረሰባቸው እንዳሉም ተሰሞቷል።
የህዝብ ቁጣ አስደንግጧቸው ይቅርታ ጠይቀው ለመመለስ ፍላጎት አሳይተዋል የተባሉትን “አዲስ አበባን ከሁሉም አቅጣጫ ዘግተን የአዲስ አበባንና የሌሎችን ክልሎች ሕዝብ ጩኸት እናበርደዋለን እናንተ በያዛችሁት መንገድ ግፉ” እየተባሉ ከፍተኛ ተጽዕኖ እየተደረገባቸው እንደሆነም ምንጮች ገልፀዋል።
መንግስት ኃይማኖት ለማስቀየር ነድፎ ቀብድ የበላበት ፕሮጀክት ይመክንብኛል ብሎ እየሰራ ነው። ዛሬ ህዝብን የሚያስፈራራበት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ የነበር ሲሆን እስካሁን የተሰማ ነገር የለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “መልካም ወጣት” በሚል ፕሮጀክት ነድፎ ለሚሰራው ዮናታን የገንዘብ እርዳታ ማድረጋቸው ይታወቃል። “መልካም ወጣት” የተባለው ለአሁኑ የተወገዘ ኃይል እንደ ዲያቆንና ቄስ አድርገው ሊያመጡት እንደሆነ መረጃዎች ከወጡ ቆይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የበላይ ጠባቂ ሆነው የሚሰሩት ፕሮጀክት ፍሬ አፍርቶላቸው እነ ዮናታን በሀሰት ነብይነት የሚያሰለጥኑት ወጣት ለተወገዘው ቡድን “ዲያቆንና ቄስ” ሆኖ ውጤታቸውን እያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ይህን የውጭ ድጋፍ ያገኙበታል።
ችግሩ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጉዳይ ሳይሆን ውጫዊ ነው የምንለው ለዚህ ነው!
ጥቃቱ መንግስታዊ ኃይማኖት የማስቀየር ነው የምንለው በምክንያት ነው!
ሽምግልና ቀልድ ነው!
1) “መንግስት” የተወገዘ ቡድን ብቻ አይደለም የደገፈው። የቤተ ክርስቲያንን ክብር ያወርዳሉ ያላቸውን ሰዎች ሰብስቦ ነው ፕሮጀክቱን እያስኬደ ያለው። የቤተ ክርስቲያንን ህግና ስርዓት መናድ ብቻ አይደለም። የመጨረሻውን ንቀት፣ ጥላቻ ያሳየበት ነው።
2) ሲኖዶሱ ለምኗል። በመንግስት ደረጃ ጥቃት ታውጆበት እንኳን የማሰቢያ ጊዜ ሰጥቷል። መንግስት የተወገዘውን ቡድን ደግፎ የቤተ ክርስቲያን በር ሰብሮ ሲገባ ነው ሰልፍ የጠራው።
3) ቤተ ክርስቲያን የቀራት ነገር የለም። ህጓ ተጥሷል። ተንቃለች። ተጠቅታለች። ልጆቿ ተገድለዋል። ለሽምግልና የሚሆን ክፍተት አልቀራትም። እያንዳንዱን እየሄደችበት ያለው በህጓ መሰረት ነው።
4) መንግስት የተወገዘውን ቡድን የማስቆም ሙሉ አቅም እያለው ሽምግልና ሊጠይቅ አይችልም። መሆን ካለበት የተወገዘው ቡድን በሰራው ወንጀል ተጠይቆ፣ መንግስት ለፈፀመው ወንጀል ተጠያቂ ሆኖ፣ ቤተ ክርስቲያንንና የህዝብን ቁስል የሚያሽሩ እርምጃዎች ቢወሰዱ ነበር። አያደርጉትም! ማዘናጊያ ብቻ ነው። የትግሉን ርቀት መለኪያ ነው!
ሽምግልና ቀልድ ነው። የቤተ ክርስቲያን በርን እየሰበረ ለሚገባ የተወገዘ ቡድን ድጋፍ የሚሰጥ ኃይል ስለ ሽምግልና ለመጠየቅ ሞራል የለውም። አያምንበትምም። ቤተ ክርስቲያንን ያዋርዱልኛል ያላቸውን ሰዎች ከየትም ለቃቅሞ የማፍረስ ስራ እየመራ ያለ ኃይል ስለ ሽምግልና የሚያወራው ስለጨነቀውና ስላላዋጣው ብቻ እንጅ ሊያምንበት አይችልም።
ቤተ ክርስቲያንንና ህዝብን እናዋርድበታለን ያሉበትን የመጨረሻውን ርቀት ሄደዋል። የቤተ ክርስቲያንንና ህዝብን ክብርና ህልውና የሚያስጠብቀውን የመጨረሻው ርቀት ድረስ መሄድ ያስፈልጋል። በአንድ በኩል የቤተ ክርስቲያን በር እየሰበረ በሌላ በኩል ሽምግልና እየላከ የሚያወናብድ አካል ማወናበጃው እንደማይሰራ ማሳየት የሚቻለው ጥቃቱን ለማስቆም የሚቻለውን የመጨረሻ ርቀት መሄድ ሲቻል ነው።
ጎንደር የሚገባቸውን ተናግራለች!
“መንግስት ነባሩን ሙስሊም ለማጥፋት በእኛ ላይ ያደረገውን ነው በኦርቶዶክስ ላይ እየፈፀመ ያለው።”
አንድ ሙስሊም አባት የተናገሩት።
እነ አዲሱ አረጋና ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የመሩት ስብሰባ ጎንደር ላይ ተደርጓል። ስብሰባው ላይ ወጣቶች እንዳይናገሩ እድል ተነፍጓቸዋል። ከጎንደር ችግር ባሻገር ህዝብ ለሰብሳቢዎቹ የሚገባቸውን ተናግሯል!
ሙስሊም አባቶች ሰሞኑን በኦርቶዶክስ ላይ ይፋ የወጣውን ጥቃት አውግዘዋል። ጥቃቱ መንግስት መር መሆኑን ተናግረዋል። “መንግስት ነባሩን ሙስሊም ለማጥፋት የጀመረው በእኛ ነው። በእኛ ላይ ያደረገውን ነው በኦርቶዶክስ ላይ እየፈፀመ ያለው።” ብለዋል።
የተወገዘውን ቡድን እየደገፈ ያለው መንግስት እንደሆነ ተነግሯቸዋል። የመንግስት ፕሮጀክት ነው ተብለዋል።
የዋግኸምራ በተለይም የአበርገሌ ወገናችን በርሃብ እያለቀ መንግስት እርዳታ እያደረሰ አይደለም ተብሏል። የስብሰባው ተሳታፊዎች ወደ ትግራይ እርዳታ እንደሚሄደው ሁሉ ለዋግኸምራ በተለይም የአበርገሌ ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል ብለዋል።
ሰራዊቱን እንዳታስመቱት!
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሁለት ጊዜ የተመታው በካድሬው እንዝላልነት ነው። አሁንም የሞቀ ሽርሽር ላይ ሆነው ሰራዊቱን እንዲመታ እያመቻቹት ነው።
1) ትህነግ የሚሰሩትን ከባድ መሳርያዎች ደብቆ የማይሰሩትን ጠጋግኖና ቀለም ቀባብቶ ነው ያስረከበው። አስረክብ ተብሎ የዘገየው መሳርያ እየደበቀ፣ እየጠገነና ቀለም እየቀባ ነው።
2) የሰላም ስምምነት አንፈልግም ያሉት የትግራይ ተቃዋሚዎች በጦርነቱ ተሳትፈዋል። ታጥቀዋል። የእነሱን ሀሳብ የሚሸከም የታጠቀና ትጥቅ አልፈታም የሚል ወጣት አለ። አይደለም ዛሬ በጦርነቱ መሃል ከትህነግ ታጣቂ አፈንግጠው መሳርያቸውን ይዘው ዝርፊያ የተሰማሩ በርካታ ወጣቶች ነበሩ። ትጥቅ አንፈታም የሚል የታጣቂ አመራር ብዙ ነው። ይህ ሁሉ ሲታይ ትግራይ ውስጥ ከሰራዊቱ ጋር ቂም ያለው በርካታ ባለመሳርያ እንደሚኖር ግልፅ ነው። ይህን ኃይል ትህነግ መቀሌ ሆኖ አዲስ አበባ እየተመላለሰም ቢሆን ያግዘዋል።
3)ትግራይ ውስጥ ባለው የኢኮኖሚ ችግር ዝርፊያና ስርቆት ዋና ወንጀል ከሆነ ቆይቷል። የመሳርያ ዝውውር በሰፊው አለ። ሰራዊቱን የሚጠላ፣ ትህነግ ትጥቃችን ከጠላታችን እያለ ሲያስተምረው የከረመው ወጣት ከሞባይል ባሻገር በየጉራንጉሩ ሰራዊት ገድሎ መሳርያ መቀማትን ነው አላማው የሚያደርገው። በየተራራው ተደብቆ የከረመው ደግሞ የሰራዊት ሰፈር አጥቅቶ ሌላ “የወያኔ ትግል ምዕራፍ” ተከፈተ ለማለት ይፈልጋል።
4) እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች አዲስ ምልምል እያስገባ ነበር። የተወሰኑ ጀኔራሎች በየቦታው የተበተነ ኃይልን እንደገና እያደራጁ ነው። ዲያስፖራው “ትጥቅ አንፈታም” እያለ ከአሁን ቀደም በተለያየ መንገድ ያገኘውን መስመር ተከትሎ እያገዘ ነው። አሁን ዳያስፖራው ቁጥሩ ይብዛም ይነስም የሚያግዘው የሰፈር ታጣቂ አለው። ባንክ ሲከፈት እገዛ የሚደረግለትና በየአካባቢው ኃይል
የትግሬ ወራሪ የጦርነት አዋጅ አውጥቷል! ጠላት ተብለው የተፈረጁ የኤርትራ መንግስት፣ የኢትዮጵያ መንግስትና አማራ።
ወንጀል ተብለው ከተዘረዘሩት መካከል አብዛኛዎቹ ለእነዚህ አካላት መሰለል፣ ወታደር ሁን ሲባል አሻፈረኝ ማለት፣ የትግሬ ወራሪ ቡድን አባላትን ማስኮብለል፣ የኮበለሉትን ማስጠለል፣ ትግሬን በብሔርና በእምነት መከፋፈል፣ የትግሬ ወራሪን መተቸት ወዘተ
የትግሬ ወራሪ የጦርነት አዋጅ አካል ነው! ያልታገለ ይታሰራል፣ ገንዘብ ተቀጥቶ በግዳጅ ወደ አሸባሪው ሰራዊት ይገባል። ካልተገኘ ቤተሰብ ገንዘብ ተቀጥቶ ይታሰራል። አመልጣለሁ ካለ በጥይት ይገደላል። ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ያጋለጠችውን ይህን የትግሬ ወራሪ የጦርነት አዋጅ ሕግ ነው። የአሸባሪውን ሰራዊት መቀላቀል ግዳጅ ነው። ካልተቀላቀለ ቤተሰቡም እሱም ይታሰራል። ገንዘብ ይቀጣል። ህፃን ሽማግሌ የሚባል ነገር የለም።
“We were forced to fight. #TPLF leaders needed one soldier per family. If we didn’t join the army, they would have imprisoned our parents”. Inside #Semera hospital talking with two #childsoldiers from #Tigray#Ethiopia #Etiopia pic.twitter.com/O0cn379FTl
— francesca ronchin (@francescaronch) July 13, 2022
በሚገርም ሁኔታ የትግሬ ወራሪ ኢትዮጵያን ለመበተን የሚጠቀምባቸውን ስልቶች ትግራይ ውስጥ በስቅላት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ጭምር አድርጓቸዋል። የሀሰት ወሬ ማስወራት፣ በሕዝብ ስነ ልቦና ላይ ሽብር መፍጠር፣ የትግሬ ወራሪ ሳይፈልግ ልንወረር ነው፣ እሳት ተቃጠለ፣ ሰራዊት ወደዚህ ሄደ ማለት ከባድ ወንጀል ሆኗል። ሸቀጣሸቀጥ መደበቅ፣ ኮንትሮባንድ ከባድ ወንጀል ነው። እነዚህን ወንጀሎችኮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፈፀሙ እየሰራ ያለው ራሱ የትግሬ ወራሪ በዲጅታል ወያነ በኩል ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ በየማሕበራዊ ሚዲያው በዲጅታል ወያነ በኩል የሚፈጥረው ትርምስ
የትግራይ ተቃዋሚዎች ትህነግ የትግራይን ሕዝብ አይወክልም ሲሉ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ አስታውቀዋል። ሳልሳዊ ወያነ፣ነፃነት ትግራይና ባይቶና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ በፃፉት ደብዳቤ ትህነግ በድርድሩ የትግራይን ሕዝብ ሊወክል አይችልም ብለዋል። ሶስቱም ፓርቲዎች በፃፉት ደብዳቤ ትህነግ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ሕጋዊ ውክልና እንደሌለው ገልፀዋል። ድርድሩን በመልካም ጎን እንቀበላለን ቢሉት ትህነግ የትግራይ ሕዝብ ወኪል ተደርጎ የቀረበበትን መንገድ ግን እንደማይቀበሉት ገልፀዋል።
፟
ወለጋ ላይ ሲሆን ከሟች ገዳይ ይቀርባቸዋል!
ጎንደር ላይ ችግር ተፈጥሮ ሙስሊምና ክርስትያን ወገኖቻችን ተጎዱ። የግጭት ነጋዴው የውሃብያ ቡድን ግን ሙስሊሞች ብቻ የተገደሉ አድርጎ አጮኸው። በየመስጊዱ ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከ ስልጤ ጎንደር እንደከተማ፣ አማራ እንደሕዝብ ተወገዘ።
በርካታ ሙስሊም አማራዎች ወለጋ ላይ ተጨፈጨፉ። ያኔ ከጣሪያ በላይ የጮኸው ኃይል ድምፁ አይሰማም። ምክንያቱም ችግሩ የተፈጠረው አማራ ክልል ላይ አይደለም። የሞቱትም አማራ ሙስሊሞች ናቸው። አማራ ሙስሊሞች የሚጮህላቸው ለውሃብያው ቡድን የፖለቲካ ትርፍ የሚያስገኝ ከሆነ ብቻ ነው።
ሞጣና ጎንደር ከሆነ ከልክ በላይ ይጮሃል። የጎንደሩን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰልፍ አስወጥተውበታል። ቱርክ መግለጫ እንድትሰጥ አድርገዋል። ወለጋ ላይ ሲሆን ግን ከሟች ይልቅ ገዳይ ይቀርባቸዋል። የግጭት፣ የደም ነጋዴዎች!
ትህነግ በአፋርና አማራ ክልሎች ሙስሊሙን ሲያሰቃይ ዝም። ኦነግ ሙስሊም ሲገድል ዝም። ራሳቸው በሰሩት ሴራ አማራ ክልል ችግር ሲፈጠር ፋኖን ያለስራው ማውገዝ! የውሃብያ ፖለቲካ ሸቀጥ!
በቀብር ወቅት ጀምሮ በንፁሃንና በመከላከያ ሰራዊቲ ላይ ተኩስ ከፍተው የዋሉ አሸባሪዎች ከእነ መሳርያቸው ተይዘዋል። መከላከያ ሰራዊቱና የአማራ ልዩ ኃይል ሕግ ሲያስከብሩ የዋሉ ሲሆን አሸባሪዎቹን የላኩ አካላት በሀሰት መከላከያ ሰራዊቱ ጎንደርን ጥሎ እንደወጣ፣ እንዲሁም በሙስሊሞች ላይ ግድያና ድብደባ እየፈፀመ ነው በሚል በሀሰት መረጃ ሲያሰራጩ ውለዋል። መከላከያ ሰራዊቱ በአሁኑ ወቅት በህንፃዎችና ቤት ውስጥ ሆነው ተኩስ የከፈቱበትን አሸባሪዎች ለሕግ እያቀረበ ይገኛል። አሸባሪዎቹ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳርያ ጋር መያዛቸው ታውቋል።
አላማው ግልፅ ሆኗል! አሸባሪዎቹ ከመከላከያ ጋር ገጥመዋል! ጎንደር ላይ ነዋሪውን የጎንደር ሙስሊም የማይወክሉ አሸባሪዎች ቤትና ህንፃ ውስጥ ሆነው ንፁሃን ላይና የፀጥታ ኃይሉ ላይ ተኩስ ከፍተው ውለዋል። ቤት ውስጥና መስጊድ አካባቢ ሆነው በንፁሃንና በመከላከያ ላይ ተኩስ ከከፈቱት መካከል ሶስቱ ተይዘዋል። በአሁኑ ወቅት ልደታ አካባቢ አንድ ህንፃ ውስጥ ሆነው መከላከያ ሰራዊቱ ላይ የሚተኩሱ አሉ። አንደኛው ከሌላ ክልል የመጣ ሲሆን ሌላኛው ከዚሁ የሚኖር ተላላኪ መሆኑ ታውቋል። መከላከያ ሰራዊቱ ህግ በማስከበር ላይ ይገኛል። በሙስሊምና ክርስትያን መካከል የተፈጠረ ፀብ የለም። አላማው ግልፅ ሆኗል። አሸባሪዎች ከመንግስት ፀጥታ ኃይል ላይ በመተኮስ ላይ ናቸው። የሰሞኑን ጉዳይ ይዘው ግጭት ለመፍጠር ሲሰሩ የከረሙ ይህን ኃላፊነት መውሰድ ይገባቸዋል። ከመንግስትና ሕዝብ ጋር የገጠሙት አህመዴ ሱቅ ሆነው ጥይት የሚተኩሱት አይደሉም። ይህን አላማ በሀሰት ሲያራግቡ የሰነበቱት፣ የጎንደርንና የአማራን ስም ሲያጠፉ የከረሙት ናቸው።
ደባርቅ ላይ ፓትሮል ላይ ሆነው ሕግ ሲያስከብሩ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን መስጊድ ውስጥ ሆነው ተኩሰው ገድለዋል።
መስጊድ የሚያቃጥል ክርስትያን አማራ፣ ቤተ ክርስትያን የሚያቃጥል ሙስሊም አማራ የለም። የፖለቲካ ፍልጎት ያላቸው እንጅ አማኞች የሌላውን ቤተ እምነት አያቃጥሉም። የሆነው እንዲህ ነው:_
1) በብሔር ግጭት ሲንጡን ኖሩ፣ ሕዝብን በማንነት ግጭት እረፍት ነሱት። ሆኖም የብሔር ግጭቱ እየተነቃባቸው፣ ያልተነቃውም አልበቃ ብሏቸው ወደ በእምነት ሰበብ ወደማጋጫት ዞሩ። ከአሁን ቀደም በእምነት ሰበብ የተደረጉ ግጭቶችን ደም አፋሳሽነታቸውን አይተዋል።
2) ጦርነት ከመጀመራቸው በፊት ሕዝቡን ማዳከም አለባቸው። ኃይል መበተን፣ ሕዝብን ማደረጋር አለባቸው። ቢችሉ “ህወሃት ይሻላል” የሚል ኃይል መፍጠር ፈልገዋል። ለዚህም ከብሔር በተጨማሪ የእምነት ግጭት አዋጭ ሆኖ አገኙት። በዋነኛነት ደግሞ ጠላት ያሉት አማራን መረጡ።
3) ወሎን አውድመውታል። ሸዋን በከፊል አውድመውታል። ቀሪውን ኦነግ በየቀኑ ይተነኩስላቸዋል። የቀረው ጎጃምና ጎንደር ነው። የቀጣይ አላማቸው ወልቃይትን ይዘው ወደ ሱዳን ማስከፈት ነው። ለዚህ ደግሞ ቀድመው የጎንደርና ጎጃም አማራን መምታት አለባቸው። አማራ ክልልን ማተራመስ አለባቸው። ለዚህም ከጦርነት የተረፈውን ሰርጎ ገባቸውን ተጠቀሙበት። ሙስሊም አስመስለው ተጠቀሙበት። ክርስትያን አስመስለው ተጠቀሙበት።
4) መጋቢት 27 ለ 28 / 2014 አጥቢያ እኩለ ሌሊት በባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ትልቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተቋም ውስጥ አንዱ የኃይማኖት ትምህርት ተቋም የሆነው የሠላም አርጊው ማርያም ቤ/ክ የአብነት ት/ት ቤት ሙሉ በሙሉ እንዲወድም ተደረገ። ከ 250 በላይ የቆሎ ተማሪ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ወድሟል። ብዙዎች ሊቃውንት የተማሩበት የቅድስት ማሪያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ከ 3,000 በላይ ተማሪዎችን የሚያስተምር የሊቃውንት ቤት ነበር። ሆኖም ወደ ግጭት ሳይገባ አለፈ። ሌላ
የግጭት ነጋዴዎች አማራ ላይ ሲሆን ሙስሊም ቢሞት ትርፋቸው ነው። አጀንዳ ካገኙ ደስታቸው ነው። አማራን፣ ጎንደርን ሰበብ ፈልገው ሲያወግዙ የከረሙ የግጭት ነጋዴዎች ሰበብ አገኘን ብለው ውግዘታቸውን ቀጥለዋል። በሀሰት ፎቶ ጭምር አጀንዳቸውን ቀጥለዋል።
ለአብነት ያህል ከስር የሚታየው የተቃጠለ ቅዱስ ቁርዓን ከሶስት አመት በፊት ፌስቡክ ላይ ሲዘዋወር የነበረ ነው። ጉዳዩን ለማጦዝ ብለው የሀሰት ምስል እያመጡ ሳይቀር ተጨማሪ ግጭት እንዲፈጠር እየሰሩ ነው። እነዚህ የሀሰት አጀንዳ ይዘው፣ ግጭት የሚነግዱ ክፉዎች አጋጣሚ ተጠቅመው፣ በሚጠሏቸው የአማራ ሙስሊሞች መረማመዳቸውን ማቆም አለባቸው።
ትናንት የተጎዱት የአንድ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው። ከምንም በላይ ለጎንደር ለአማራ ይቀርባሉ። ስለሆነም:_
የጎንደር ከተማ ሕዝብ ችግር ሲፈጥር ያየውን በእምነት ይምሰለው አይምሰለው፣ ይዘመደው አይዘመደው አሳልፎ ለሕግ መስጠት አለበት። ነገ ራሱን የሚያስጎዳው እንዲህ አይነት ነውረኛ ነው። በትናንቱ ችግር ሙስሊም ክርስትያኖች ተጎድተዋል። ጎንደር እንደ ከተማ ተጎድታለች። ስለሆነም የትኛውንም ነውረኛ ለሕግ አሳልፎ መስጠት ያስፈልጋል።
በሌላ በኩል ግን ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ፖለቲካ ለመስራት የተዘጋጀ ኃይል እጁን ቢሰበስብ ይሻለዋል! ትህነግ ደረሳዎችን ሲጨፈጭፍ አንድም ቃል፣ አንድም ቃል ትንፍሽ ያላለ በአማራ ክልል፣ በጎንደር ከተማ ሲሆን ለማባባስ የሚሰራ የፖለቲካ ነጋዴ ተው ማለት ያስፈልጋል። በትህነግ መስጊዶች ሲቃጠሉ፣ ቅዱስ ቁራን ሲቀደድና መፀዳጃ ሲያደርጉት፣ ሸኮችን በግዳጅ አልኮል ሲያስጠጡ፣ መስጊድ ውስጥ ሴቶችን ሲደፍሩ፣ መስጊድ ውስጥ መጠጥ ይዘው ሲጨፍሩ ሲያድሩ እያወቀ አንድም ነገር ትንፍሽ ያላለ አሁን ወንድማማቾች መካከል የተፈጠረንና ጎንደር የምትፈታውን ጉዳይ አጋጣሚ ተጠቅሞ ለማጦዝ የሚጥፈው እረፍ ሊባል ይገባዋል። ወንጀሉን የሚያባብስ፣
ስለፋኖ በግልፅ መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች!
1) ፋኖን ከኦነግ ሸኔ ጋር ማመጣጠኛ ለማድረግ የሚኬድበት ክፉ ፖለቲካ መቆም አለበት:_
ፋኖ የራሱን መሳርያና ስንቅ ይዞ ከጠላት ጋር ሲተናነቅ የከረመ ኃይል ነው። በርካቶች በዚህ ሂደት ሕይወታቸውን ገብረዋል። አካላቸው ጎድሏል። ቤተሰባቸው ተበትኗል። በርካቶቹ ቀድሞ እንደጠፋው አንዳንድ ባለሀብት፣ አሊያም እንደሸሸው ባለስልጣናት አገር ሸሽተው አገር ቤትም ውጭ አገርም መኖር የሚችሉ ናቸው። እነ ምሬ ወዳጆ ሀብት ንብረታቸውን ጥለው ነው ትግል የገቡት። ሌሎች በርካቶች ተመሳሳይ ዋጋ ከፍለው ነው ለአገር የቆሙት። ፋኖዎች ላበረከቱት መከበር እያለባቸው ግን የሚጠሏቸው አካላት አሉ። ለአብነት ያህል አንድ የለመድነው ክፉ ፖለቲካ አለ። የኦሮሞ ብልፅግና የሆነ አጥፊ ኃይል ላይ ሕግ አስከብር ሲባል አማራ ክልል ላይ ማመጣጠኛ ይፈልጋል። የኦሮሞ ፅንፈኞችን ግፊት በፈራ ቁጥር አማራ ክልል ውስጥ አሊያም አማራ ኀይል ያለው ላይ የጦስ ዶሮ ይፈልጋል። እነ ጃዋር ሞሃመድ ሲታሰሩ እስክንድርና ሌሎችን አማራ ናቸው ብለው በማመጣጠኛነት አሰሩ። ኦ ኤም ኤን በቀጥታ ስርጭት ሕዝብን እርስ በእርስ የሚያጋጭ ዘገባ ሰርቶ ይጠየቅ ሲባል ምንም ያላደረገውን አሥራትን አሽገው ሰራተኞቹን አሰሩ። ኦነግ አጣዬን ያቃጠለ ሰሞን ሽፋን ተሰጥቶታል። ለሕግ ይቅረብ ሲባል ማመጣጠኛ አማራ ተፈለገ። ወለጋ ላይ ኦነግ ሸኔ በንፁሃን አማራዎች ላይ ጭፍጨፋ ሲፈፅም አማራ ታጣቂ ተብሎ በሀሰት አማራ ስሙ ተነስቷል። መምቻ ነበር። ይሄ የተለመደ ነው። ምንም ይሁን ኦሮሚያ ክልል ውስጥ አንድ እርምጃ ይወሰድ ሲባል ዘወር ዘወር ብለው ንፁሃ አማራን የጦስ ዶሮ የማድረግ ክፉ አባዜ ተለምዷል።
ሰሞኑን
አዲስ አበባ ወዲህ፣ ፖለቲካው ወዲያ!
ጌታቸው ሽፈራው (ፍትሕ መፅሔት ላይ የታተመ)
ከመሬት ወረራ ወደ ማንነት ጥያቄ
በዘመነ ትሕነግ፣ የኦሕዴድ ካድሬ አዲስ አበባ እና ዙርያው ላይ ያለውን መሬት በመቀራመት ፊት-አውራሪ እንደነበረ አይዘነጋም። ሁላችንም እንደምናስታወሰው፣ ድርጅቱ ላይ የተለጠፉ ካድሬዎች ከራሳቸው አልፈው ተርፈው፣ ለሌላው መሬት በማደልም ሆነ በመቸብቸቡ ረገድ የሚስተካከላቸው አልነበረም። በርግጥ፣ ይኽን የዐደባባይ እውነት እነሱም ክደውት አያውቁም። ከ8 ዐመት በፊት፣ በእነ አባዱላ ገመዳ መሬት የተሰጠው አንድ የምቀርበው ኦሮሞ ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ያጫወተኝን አስታውሰዋለሁ። መምህራን ተሰብስበው አለን የሚሉትን ጥያቄ ያቀርባሉ። እነ አባዱላም መሬት እንደሚሰጧቸው ቃል ገብተው አፋቸውን ያስይዟቸዋል። በሌላ ጊዜ፣ የድርጅቱ ካድሬዎች እነዚያኑ መምህራን ሰብስበው፣ የተሰጣቸውን መሬት ምን እንዳደረጉት ሲጠይቋቸው፣ “ቤት እንዳንሠራበት ገንዘብ የለንም፤” የሚል አጭር ምላሽ ይሰጧቸዋል። በወቅቱ፣ ኦሕዴዶች ለዚህ ችግር መፍትሔ አድርገው ያቀረቡት ሌላ ተጨማሪ መሬት በመስጠት አንዱን ሸጠው፣ በሌላኛው ቤት እንዲሠሩ ነበር። ይህን ያደረጉት ለመምህራኑ አዝነው አይደለም። መሬቱ ከአርሶ ዐደሩ የተቀማ እንጂ፤ ከሰማይ የወረደ እንዳልሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። በወቅቱ፣ የድርጅቱ አመራሮች ይህን እርምጃ የወሰዱበት ዋናው ምክንያት ከመምህራን የተነሳባቸውን ተቃውሞ አቀዝቅዘው፣ ለጊዜውም ቢሆን ድጋፍ ለማግኘት ነበር። የዘመኑ ተቃውሞ ማብረጃ መላ ይህ እንደነበረ በታሪክ እንዳይረሳ ሆኖ ተመዝግቧል።
እዚህ ጋ ልብ መባል ያለበት፣ ለመምህራን ሁለት ሁለት መሬት የሚያድል ካድሬ፤ ለራሱ ምን ያህል ሊቀራመት እንደሚችል መገመቱ ቀላል አለመሆኑን ነው። ሦስት? አራት? ዐሥር? ወይስ ከዚያ በላይ?
ዘግይቶ የመጣው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ደግሞ ኦሕዴድ በግለሰብ፣
የትግሬ ወራሪ ከውጭ የተላከ መሳርያ ደርሶታል!
ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያውያን ገብቷቸውም ይሁን ሳይገባቸው ኢትዮጵያ መሳርያ እንዳታገኝ የሚከለክላትን ማዕቀብ እየደገፉ ነው። ይህን ማዕቀብ ለማፅደቅ እየሰሩ ያሉ አገራት ግን ለአሸባሪው ትህነግ በርካታ መሳርያ አድርሰውታል። ከቀናት በፊት ከፖርት ሱዳን በኩል የመጣ አራት መኪና መሳርያ ገዳሪፍ ኬላ ላይ ተይዞ ነበር።
ይሁንና “ልቀቁላቸው” ተብሎ ተለቅቋል። ይህን ያህል መሳርያ የሱዳን መንግስትን ቢወርሰው ያዋጣው ነበር። ይሁንና ትዕዛዙ አቅም ካለው አካል ስለሆነ ለቅቆታል። የምዕራባውያን የደሕንነት ተቋማት ከሌሉበት በስተቀር ይህን የሚያህል መጠን ያለው መሳርያ በፖርት ሱዳን ገብቶ፣ አገር አቋርጦ ጉምሩክ ላይ ሊለቀቅ አይችልም።
ያ መሳርያ ከተያዘበት ኬላ ተለቅቆ በሱዳን በኩል ኢትዮጵያን እየወጋ ለሚገኘው የትግሬ ወራሪ ደርሶታል። የትግሬ ወራሪ በሱዳን በኩል ባደረገው ወረራ ተመትቷል። ይሁንና ደጋፊዎቹ ከውጭ የደረሳቸውን መሳርያ ከኢትዮጵያ የማረኩት አስመስለው ፎቶውን ሲያሰራጩ ሰንብተዋል። ]
ከውጭ መሳርያ ሲገባላቸው አላስችላቸው ስላለ ነው። ምዕራባውያኑ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ደፋ ቀና እያሉ በሌላ በኩል ለትግሬ ወራሪ እያስታጠቁት ነው። ብዙ ኢትዮጵያውያንም ይህን ሀቅ አልተረዱም። ኢትዮጵያን መሳርያ የሚያሳጣ ሕግ እየደገፉ አሸባሪው ከውጭ መሳርያ እየታጠቀ ነው።
ሰሞኑን ጥቃት ያሰጋል!
1) የትግሬ ወራሪ ለወረራ ዝግጅት ላይ ነው። የትግሬ ወራሪ ከትግራይ በኩል ብቻ አያጠቃም። በመሃል አገር በአጋሮቹ በኩል ጥቃት ይጀምራል። ይህም ኃይል ይበትንለታል። የሕዝብን ትኩረትና አቋም ይከፋፍልለታል። በተለይ በርካታ አባላቱ ከየክልሉ መፈታታቸው እድል ይሰጠዋል። በቤንሻንጉል በተደረገው ጥቃት ከእስር የተፈቱ አባላቱ ዋናዎቹ አጥቂዎች እንደሆኑ አምነዋል።
2) የሳይበር ጥቃት ሌላኛው ስልታቸው ይሆናል። ትህነግን በማጋለጥ የሚፅፉ ገፆች ላይ ጥቃት ያደረሳሉ። የተቋማትን መረጃ መረቦች በዳያስፖራዎቻቸው በተገዙ የግል ተቋማት በኩል ያጠቃሉ።
3) የሀሰት መረጃ ስርጭት ይቀጥላል። ዘመቻ በጀመሩበት አማራ፣ ሶማሊ፣ ሲዳማ፣ አፋር፣ ወዘተ በየክልላቸው ችግር እንዲፈጠር ይሰራሉ። እርስ በእርስ ለማጋጨት ጥረት ይደረጋል። በአማራው መሃል አጀንዳ እየጣሉ ለማናቆር ጥረት ያደርጋሉ።
4) የሀሰት ሪፖርቶች ይወጣሉ። የተቀነባበሩ መረጃዎች ተለቅቀው መቀስቀሻ ይሆናሉ። የርሃብ፣ የሀሰት ግድያና ጭፍጨፋ ዜናዎችን ለዓለም እያደረሱ ከመሃል ኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ደረጃ ሊወጉን ይሞክራሉ።
ጦርነቱ አይቀሬ ነው እያሉ ነው። ትግራይ ውስጥ መፈክር በዝቷል። “ከበባ እንሰብራለን፣ ሱዳንና ባሕርዳር እንገናኝ” እየተባለ ነው። ጎንደርና ባሕርዳርን ባለፈውም ለመዝረፍ ቋምጠው ነበር። በወልቃይት ከሱዳን ጋር ከመገናኘት ባሻገር ጎንደርና ባሕርዳርን ዘርፈው ስንቅ መያዝ ሌላ እቅዳቸው ነው።
የተማሪዎችን ውጤት አበላሽቶ ምላሽ መስጠት የተሳነው መንግስት ደግሞ ምቹ አጋጣሚ ሰጥቷቸዋል። የቀጣዩን ትውልድ እጣ ፈንታ በደባ ሊያኮላሹ የሚሞክሩ ክፉዎች የተማሪ ውጤት ላይ እንድንጠመድ አድርገዋል። የክፋታቸው ክፋት ደግሞ በጦርነት የተጠቁትን አካባቢዎች ዳግመኛ ማጥቃታቸው ነው። በተማሪዎች ውጤት ላይ የደረሰው ብልሹነት ለትህነግ አጋዥ ነው። ትህነግን ሲፋለም የከረመ ሕዝብ ላይ
ለአማራ ሕዝብ እናስባለን ለምትሉ ወገኖች:_ አብንን አታባክኑት! Getachew shiferaw,
1) ድርጅት ሂደት አለው። በመሃል ውጣ ውረድ ይገጥመዋል። ይሄ በድርጅቶች ዘንድ እንደ ተፈጥሯዊ ሂደት የሚቆጠር ነው። አንድ ሰሞን በደንብ ሰርቶ፣ ሌላ ጊዜ የሚዳከምበት፣ በመጀመርያው ወቅት በደንብ ታግሎ ቀጥሎ የሚቀዘቅዝበት፣ በጥቂት አመራሮቹ ተናባቢ ሆኖ፣ ቀጥሎ የአባላትን ብዛት፣ የአመራሩን ድክመት መቆጣጠር የሚሳንበት ጊዜዎች አሉ። ይህን የድርጅት ተፈጥሯዊ አካሄድ፣ ፈተናና ድከመቶች ተረድቶ መፍትሄ ማምጣት ነው የሚያዋጣው። በአገራችን በርካታ ድርጅቶች ፈርሰዋል። ብዙዎቹ አቅማቸውን አጥተው በተወሰነ ኃይል አሉም የሉም የሚያስብል አጠራጣሪ ሁኔታ ላይ ናቸው። የፈረሱትት በተቀናቃኝ ኃይል ብቻ አይደለም። አባላቱና አመራሩ አቅል ማጣት፣ የአመራሩ ችግር፣ የድርጅት እድገትና ክፍተቶችን ባለመረዳት ነው። የኢህአፓ አባላትና አመራሮች የድርጅታቸው መፍረስ አሁንም ድረስ ይቆጫቸዋል። ያኔ ግን አንዱ አንዱን ጎንትሏል። ዛሬ ያተረፉት ውድቀትና ፀፀት ነው። እንትና ነው ያፈረሰው፣ አይ እንትና ነው የሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ለሕዝብ አይፈይድም። የአንድነት፣ የሰማያዊ ወዘተ አባላትና አመራሮች ድክመትና ደረጃውን ሳይረዱ አባክነው አፍርሰዋቸዋል። መኢአድ ብዙ ጊዜ ተጎትቶ ያን ግዙፍ አቅሙን አጥቷል። የእነ ፕሮፌሰር አስራትን መአህድ ጠላት ከውጭ፣ ብዙ የጠበቀበት ደጋፊና አባል ከውስጥ ብዙ ተፈታትነውታል።
አንድ መኪና ነዳጅ ጨርሶ፣ ሞተር ወይንም ሌላ ክፍሉ ተበላሽቶበት፣ አሊያም ሾፌሩ ከፊት የሆነ አደጋ አይቶ፣ ወይ ደክሞት፣ አሊያም ለግሞ ሊቆም ይችላል። ተሳፋሪዎቹ “ዝም ብለህ ካልሄድክ” ካሉት ገደል ነው የሚገባው። ተሳፋሪዎቹም ጭምር ወርደው አሊያም ጠይቀው መኪናው የቆመበትን ምክንያት ማጣራት አለባቸው። ካጣደፉት መኪናውም እነሱም አይተርፉም። አብን ምን
“የአማራው” ፌስቡከኛ ለምን ይወቀሳል? – Getachew Shiferaw
አክቲቪስቲም ፖለቲከኞቹም በፌስቡከኛው እያማረሩ ነው። ብዙዎቹ እየተሳቀቁ ነው። በርካቶች እየታዘቡ ነው። ቀሪው ግራ ይጋባል። ለምን ግን ይሄ ሆነ? ለምን በአማራ ስም የሚፅፈው ፌስቡከኛ ይህን ያህል ወቀሳ በዛበት? አንዳንድ ጉዳዮች መጤን ያለባቸው ይመስለኛል።
1) ማሕበራዊ ሚዲያ አናንቋል:_
ፌስቡክ መልካም ነገር የፈጠረውን ያህል ብዙ ችግር አምጥቷል። “ለውጥ” ከመባሉ በፊት ደፍረው የሚፅፉትን ሰዎች ፅሁፍ በስህተት “like” ላለማድረግ የሚጠነቀቀው አሁን የቻለውን ይፅፋል። ከድሮው በበለጠ ከመሪዎቹ ጋር ይገናኛል። ድሮ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በመፅሐፍ ወይ በጋዜጣ ያየው የነበረውን “መሪዬ” ብሎ የሚያከብረውን ሰው፣ አሊያም የተሻለ ሀሳብ የሚያቀርበውን አሁን ፌስቡክ ላይ ጓደኛው ነው። ቢፈልግ ከፍ ዝቅ አድርጎ ከስር አስተያየት ይፅፍለታል፣ በሜሴንጀር ይደውልለታል። መረጃ ይለዋወጣል። እዛው ፌስቡክ ላይ መልስ ይሰጠዋል። ወዘተ። አብረው ይውላሉ። ፌስቡክ ላይ “ጓድነት” አይከበርም። ዲስፕሊን የለም። መርህና ሕግ የለም። ሲፈልግ ሕዝብ ትክሻ ላይ ይሰቅለዋል። ሲፈልግ ይፈጠፍጠዋል። የፌስቡክ ጓድነት ሀሜት እንጅ መወያየት አይበዛውም። መነቋቆር እንጅ መማማር ብዙም አይደለም። “ትግላችን እልህ አስጨራሽ ነው” የሚል መፈክር ፌስቡክ ላይ እየደጋገመ ወቅታዊ ፖለቲካን የሚያስረዳ ረዥም ፅሁፍ ለማንበብ ወገቤን የሚል ይበዛል። የትግልን መራራነት እያወራ የራሱ ወገን ያጠፋ ሲመስለው “ምን ሆነህ ነው?” ብሎ በዝግ ለመጠየቅ አቅል አጥቶ ባለ በሌለው መረጃ ያወርድበታል። ጠላትም፣ ወዳጅም የሚውልበት ፌስቡክ ላይ። በዚህ ምክንያት ይህ መድረክ ለትግል ቀርቶ ለማሕበራዊ ሕይወትም ድብልቅልቁ የወጣ፣ አብዛኛው አጠቃቀሙንም የማያውቅበት ነው። ስለሆነም መናናቅ በዛው፣ አብሮ መዋል ጓድነትን አላልቶታል።
የወልቃይት ጠገዴ ህፃናት፣ ነፃ ወጣን ሲሉ ከእነ ጭራሹ ትምህርት ተቋርጦባቸዋል! የወልቃይት ትምህርት ቤቶች በበጀት ችግር እየተዘጉ ነው!
በወልቃይት ጠገዴ ሲቲት ሁመራ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለመምህራን ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ እየተዘጉ እንደሆነ ነዋሪዎች አስታወቁ።
ላለፉት ሶስት አመታት በአካባቢው ትምህርት በአግባቡ እየተሰጠ እንዳልነበር የገለፁት ነዋሪዎቹ በቅርብ ግን ከተለያዮ አካባቢዎች 406 መምህራን ተቀጥረው ትምህርት መሰጠት ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም ላለፉት አራት ወራት ለመምህራን ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ ትምህርት ቤቶች እየተዘጉ እንደሆነ ገልፀዋል።
–
ችግሩ የተፈጠረው ወልቃይት ጠገዴ ዞን በጀት ያልተመደበለት በመሆኑ የገለፁት ነዋሪዎቹ የፌደራልም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት ችግሩን ተገንዝቦ በጀት በመመደብ ትምህርት ቤቶች ስራ እንዲጀምሩልን ሲሉ ጠይቀዋል። የወልቃይት ጠገዴ ዞን በአማራ ክልልም ሆነ በፌደራል መንግስት መደበኛ የመንግስት በጀት እንዳልተለቀቀለት ይታወቃል።
የትግሬ ወራሪ ወልቃይት ጠገዴን በሚገዛበት ወቅት የወልቃይት ህፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዳይማሩ ተደርገዋል። አብዛኛዎቹ ለስደት ተዳርገዋል። ቀሪዎቹ በትግሬ መምህራን ምክንያት ትምህርት መማር አልቻሉም ነበር።
ወልቃይት ጠገዴ ከትህነግ ነፃ ከወጣ በኋላ የወልቃይት ጠገዴ ህፃናት መልካም ጊዜ መጣላቸው ተብሎ ነበር። ያቋረጡትን ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይማራሉ ሲባል መምህራኑ ደሞዝ ተቋረጠባቸው። ትምህርት ቤቶቹ ከእነ አካቴው ተዘግተዋል።
ይሄ የሚሆነው የትግሬ ወራሪ ጋር የተቀላቀለ የሆነ መስርያ ቤት ሰራተኛ ደሞዝ እየገባለት ነው። ይህ የሚሆነው መንግስት ፈቅዶ ለትግሬ ክልል እርዳታ በሚያልፍበት ወቅት ነው። ይህ የሚሆነው የወልቃይት ጠገዴ ሰሊጥና ማሾ ለውጭ ምንዛሬ በሚላክበት ወቅት ነው። ይህ የሚሆነው በርካታ የቀንድ ከብትና ጥጥ ለውጭ
ወደ አማራ ክልል የሚመጡት የትግሬ ስደተኞች ጉዳይ! – “እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም”
ወደ አማራ ክልል የሚጎርፈው የትግሬ ስደተኛ ያለ ትህነግ ፈቃድ አይመጣም። ትህነግ ካልፈቀደ ሊያሳልፈው አይችልም። ወደ አማራ ክልል የሚመጣው ትግሬ ስደተኛ በትግሬ ወራሪ ውሳኔ የሚመጣ ነው!
1) ከሚሰጣቸው የእርዳታ እህል በተጨማሪ በየከተማው በሴተኛ አዳሪነት መሰማራታቸውን መቀሌ ያሉ ሰዎች ሳይቀር ፅፈውታል። ሱዳን መጠለያ ካምፖች ውስጥ የሚኖሩትም በዚሁ ስለተሰማሩ ሱዳናውያን ከሶስት ጊዜ በላይ ካምፖቻቸውን አቃጥለውባቸዋል። በትግራይ ከተሞች የሚኖሩት እርዳታ ፈላጊዎችንም ትህነግ “ወደመጣችሁበት ሂዱ” ብሎ ወደ ትግራይ ክልል ወረዳና ዞኖች አባርሯቸዋል። በዋነኛነት የሚሄድላቸውን እርዳታ ትህነግ ለራሱ ተጠቅሞበታል። በሁለተኛ ደረጃ ኮሚቴ ወዘተ እያደራጀ የእነሱ ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረግ አልፈለገም። ስለሆነም ወደመጣችሁበት የትግሬ አካባቢ ወይንም ወደአማራ ክልል ሂዱ ብሎ ወስኗል። በ17 አመቱ የጫካ ቆይታውም እርዳታውን ቅርጥፍ አድርጎ በልቶ ስደተኛውን ወደሱዳንና አማራ ክልል እንደላከው እናስታውሳለን። ያኔ ደሴ ተጠልለው ያደጉት ናቸው መልሰው ደሴን የወጓት። ለምሳሌ ፕሮፌሰር ክንድያ ያኔ ስደተኛ ሆነው ወደ ደሴ ከመጡት መካከል ነበር። አድጎ ከአፈናቃዩ ጋር ሆኖ ደሴን ወግቷታል። ታቅፎ የመጣው ህፃን ሁሉ ተመልሶ ከአፈናቃዩ ጋር ሆኖ ወግቶናል።
2) ጦርነት ላይ ትኩረት ማድረግ ፈልጓል። ስለሆነም ስደተኛ ካምፕ ያለው ወጣት ሁለት አማራጭ ተሰጥቶታል። ወደመጣህበት የትግሬ አካባቢ፣ አሊያም ወደአማራ ክልል ሂድ ይሉታል። ወደመጣበት ሰፈር አይሄድም። እርዳታ ይዞ ለመሄድ ነው ወደ ከተማ የመጣው። ወደ አማራ ክልል ለመምጣት ይፈራል። የሰሩበት የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ አለ። ሁለቱን አልፈልግም ሲል ሶስተኛና
ጉዳዩ የምኒልክ አደባባይ ጉዳይ ብቻ አይደለም! ጌታቸው ሽፈራው
ለእቴጌ ጣይቱ አዲስ አበባ ላይ ማስታወሻ ይኑራት ሲባል በባለስልጣናት ደረጃ ከለከሉ። ለገሃር ብትሄዱ ግን ጉድ ታያላችሁ። ኢትዮጵያን ለዚያድባሬ ሊያስረክብ የነበር ዋቆ ጉቱ የሚባል ጀኔራል ጃገማ ኬሎ አንጠልጥሎ ያመጣው ሽፍታ ተቋም ተሰጥቶታል። አምባሳደር ልብስ ስፌት ጥግ፣ አንድ ግቢ “ዋቆ ጉቱ ፋውንዴሽን” የሚል ተፅፎበታል። ሰውዬው አዲስ አበባ ላይ ሊታወስ የሚያስችል ስራ ሰርቶ አይደለም። አዲስ አበባን ሳይንቁ ግቢም፣ ዛኒጋባም፣ አደባባይም የራሳቸው አድርገው በሕገወጥ መንገድ የተጀመረውን የባለቤትነት ጥያቄ ለማረጋገጥ ነው። አሁን እየሄዱበት እንዳለው የግለሰብ ግቢ ውስጥ ገብተው ግቢ ውስጥ ጠዋት ፀሐይ የሚሞቅበትን ደረጃ ሁሉ መከልከልና በራሳቸው መሰየም ነው የቀራቸው።
ሰሞኑን በመስቀል አደባባይ ጉዳይ አንድ ነውረኛ ስራ ጀመረዋል። የዋቄ ፈና እምነት ተከታዮች ነን የሚሉ አደባባዩን እንዲጠይቁ አድርገዋል። ከአሁን ቀደምም “ኢድ አደባባይ” የሚሉ ፅንፈኞችን ጥያቄን ያስነሱት የ”ፊንፊኔ ኬኛ” ሰዎች ናቸው እንጅ ሙስሊሙ አይደለም። አደባባዩ የዋቄ ፈና ነው ብለው ያነሱት ማበሳበሻ ጥያቄ ከአሁን ቀደምም የተገበሩት የሚታወቅ ስልት ነው። ባልደራስን ለማጣጣል አንድ የፓርቲዬ ቢሮ ጫት ቤት ውስጥ ነው የሚል ልጅ ፓርቲ መሰረትኩ ብሎ እውቅና ሰጡት። መቸም ይህ ሰው ሀምሳ ሰው እንኳን የፓርቲ አባል አድርጎ ሊያስፈርም አይችልም። ባልደራስን በጩልሌ ፓርቲ ለማበሳበስ እንደጣሩት፣ የመስቀል አደባባይን ጉዳይ የዋቄ ፈና ጥያቄ አመጡበት። ማሰላቸት፣ ጥያቄውን ማበሳበስ ነው።
አድዋ ድልድይ አካባቢ የጀግኖች ማስታወሻ ይሰራ ሲባል ደስተኛ አይደሉም። ዘንድሮ ግን ምኒልክ አደባባይን ለማስናቅ አድዋ ድልድይን መረጡት። ይህ
ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ብድር መቀበያ፣ መደራደሪያ፣ ፕሮፖዛል ማቅረቢያም መሆን የለበትም።
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የማይመጥን ምክንያት :- ጌታቸው ሽፈራው
የትናንቱ ፓርላማ ውሎ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ መልካም ጉዳይ ነግረውናል። የረመዳንን በዓል በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ብለውኛል። በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እምነት ሳይለያቸው በዓሉን እንዲያከብሩ ይሰራል ብለውናል። ይህ አስደሳች ዜና ነው። አስደሳችነቱ ደግሞ ለረመዳን ብቻ አይደለም። ባለፈው ልደትና ጥምቀት ይሄ ተሞክሮ ውጤታማ ነበር። ኢትዮጵያውያን በረመዳንም፣ በኢሬቻም፣ በጨምበላላም፣ በጥምቀት፣ መስቀል፣ ሻደይና ሶለል፣ ልደትና እየደመቁ በመጡት የፈረስ ጉግስ በዓላት ላይ ከውጭ እየመጡ እንዲያከብሩ ማድረግ ብዙ ጥቅም አለው።
ትናንትና የተነገረን ችግሩ ምክንያቱ ነው። በዓሉ በድምቀት እንዲከበር መታሰቡን ደስ ብሎን ሳንጨርስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ በዓል ያነሳሳቸው የሚመስል አድርገው ያቀረቡት ምክንያትን ለሰማ ጆሮን የሚያጮልና ለታሪክ ጠገቦቹ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም ክርስትያኖችም ክብረ ነክ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አረብ አገራት በቂ ሙስሊም ያለን አይመስላቸውም። የላችሁም ይሉናል” ብለዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አነጋገር “ለምሳሌ” ተብሎ አልተነገረም እንጅ ሚስጥር ነው። እነ አብይ አህመድ ወደ አረብ አገራት ተመላልሰዋል። ብድርም ሌላም ሲጠይቁ ታዲያ አገራት የራሳቸውን ፍላጎት ይጭናሉ። አንደኛው የእምነት ጉዳይ ነው።
ራሳቸውን ሚዛን አድርገው እስልምናን እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጡ አገራት እንዳሉ እናውቃለን። ታዲያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እንደተረዳነው “በቂ ሙስሊም የላችሁም” የሚለውን የአንዳንድ አገራት ጫና ለመቀነስ ረመዳንን ደመቅ አድርጎ አክብሮ ማሳየት እንደ እቅድ ተይዟል ማለት ነው። ይህ ጉዳይ ከብዙ መልኩ ክብረነክ ነው። ታሪክ ጠገቡን የኢትዮጵያ ሙስሊም ትናንት ነዳጅ ስላገኙ
አሸባሪ ለመሸገባት ትግራይ መቶ ቢሊዮን፣ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን ለቆመው ወልቃይት ጠገዴ ምንም! – ጌታቸው ሽፈራው
ትህነግ ምርጫ አደርጋለሁ ካለ በኋላ የፌደራል መንግስቱ ለትግራይ በጀት መድቧል። “እንዴት ለፌደራል መንግስቱ እውቅና ለማይሰጥ ትህነግ በጀት ይላካል?” ሲባል ለወረዳና ዞኖች እልካለሁ ብሎ ነበር። የሆነ ሆኖ ትህነግ ጫካ ገብቶም ትግራይ በጀት ተልኮላታል። ከታቀደላት በጀት አስር እጥፍ ( መቶ ቢሊዮን ) ተሰጥቷት አብዛኛውን ትህነግ ተጠቅሞበታል። በአንፃሩ ለወልቃይትና ራያ የተደረገ ነገር የለም። የተወሰኑ ወጭዎቻቸውን የሸፈነው የአማራ ክልል መንግስት ነው። ያውም ተጨማሪ በጀት ሳያገኝ፣ እንዲያውም ከጥቅምት 24 በኋላ መከላከያ መኪናዎቹንና ነዳጁን ተነጥቆ ሲመለስ አብዛኛውን አማራ ክልል ችሎ።
ባለፉት ወራት ራያ በትህነግ ስር ስለሆነ እንጅ ወልቃይት ላይ እያየነው እንዳለው የፌደራል መንግስቱ ምንም እንደማያደርግለት ግልፅ ነው። ወልቃይት በአማራ መንግስት ስር ቢሆንም የፌደራል መንግስቱ የትግራይ አካል አስመስሎ ከመሳል ያለፈ አመለካከት የለውም። ይሁንና ስለ ትግራይ በጀት ሲጠየቅ “በዞንና በወረዳዎቹ በኩል አደርሳለሁ” ያለው መንግስት በትህነግ ስር ለሚገኙ ወረዳዎች አደርሳለሁ እንዳላለ ከመንግስት ጎን ሆኖ አሸባሪ ለሚታገለው ዞን ግን በጀት ለማድረስ አልፈለገም። ወልቃይትን በወታደራዊ አፈፃፀም ይሸልሙታል ለበጀት ሲሆን ይረሱታል። ለወልቃይት ጠገዴ በጀት ለመላክ የሚያስቸግር ጉዳይ አልነበረም። ለትግራይ ተልኳል። ያውም አስር እጥፍ። ቀጠናው እጅግ ጠቃሚ፣ ኢትዮጵያ በብዙ ጉዳይ እየተጠቀመችበት ያለ ቀጠና ነው። በተደጋጋሚ በተደረጉ ስብሰባዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የመንግስት ባለስልጣናት “በጀት ይለቀቃል” እያሉ ሲሸነግሩ ከአመት በላይ ሆኗቸዋል። መጀመርያ አካባቢ የወልቃይት ጠገዴን ወጭ የቻለው አማራ ክልል ነው።
ሰው ምን ይለናል አይባልም!
በርካታ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ መብራት አልባ ናቸው። ዋግኸምራ መብራት የለውም። ራያ መብራት የለውም። ወልቃይት ጠገዴ ነፃ ከሆነ ጀምሮ መብራት የለውም። ሽማግሌዎች “ኧረ የመብራት ያለህ” እያሉ ይመላለሳሉ። የሚሰማቸው የለም። እነሱ ለአውሮፓ እንሸጣለን እያሉ ይቀልዳሉ።
ቢያንስ መብራት አስገቡልን ብለው ከወልቃይት ጠገዴ፣ ከዋግኸምራ፣ ከራያ የሚመላለሱት ሽማግሌዎችም ይታዘባሉ አይሉም። ሰው ይታዘባል ተብሎ ነገር የለም። በሚዲያ መደንፋት ነው።
መብራት የሌላቸው አካባቢዎች ሰራዊቱን እየቀለቡ ነው። ግብር ይከፍላሉ። ለአገር እየተዋደቁ ነው።
ለእነሱ ሲባል አገልግሎት አልገባም። አገልግሎት ባይገባ እንኳን እንደ ሕዝብ የሞራል ጉዳይ እንኳን አይታሰብላቸውም። በሚዲያ የህልም ዓለም ያወራሉ። ለሕዝብ ጥያቄ ግን መልስ የለም።
ኦሮሚያ ውስጥ ነውር ራሷ መንግስት መስርታለች፣ ጭካኔ መንግስት መስርታለች!
~የኦሮሚያ ክልል ካድሬ በፈደራል ፓርላማ የተፈረጀን ኦነግ ሸኔ ከተማ ዳር ያለ የቆሻሻ መጣያ ጫካ ውስጥ ወጣቱን ዱላ አስይዞ ዘመቻ ላይ ነኝ እያለ ሲቀልድ የከረመ ነው። በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት የአፋርና አማራ ሕዝብ፣ መከላከያው ከሌላኛው አሸባሪ ትህነግ ጋር የምር ጦርነት ላይ ነበር።
~የኦሮሚያ ክልል ካድሬ ድሮ ትህነግ ከአማራ ቀምቶ አስቀምጡት ያለውን የማገዶ እንጨት የመሰለ ቁመህ ጠብቀኝ መሳርያ ( አብዛኛውን በዚህ ወቅት አርሶ አደሩም አይዘው) ከኦነግ ሸኔ የቀማሁት ነው ብሎ በሚዲያ የሚቀልድ ነውረኛ ነው። ኦነግ ሸኔ የቡድን መሳርያ የታጠቀ ኃይል እንደሆነ እየታወቀ ከጓንዴም ያነሰ መሳርያ ከመሳርያ ግምጃቤት አውጥቶ በንፁሃን ሕይወት የሚቀልድ ነውረኛ ነው።
~ወጣቶች የኦነግ ሸኔ አባል ነን እንዲሉ ዊግ አስቀጥሎ በሚዲያ እንዳቀረበ ዘገባ ወጥቷል። እንደ ኮሌጅ ተማሪ ተቃቅፈው ፎቶ የተነሱ ወጣቶች የተማረኩ ተብሎ በሕዝብ የጅምላ ቀብር ላይ ቀልድ የሚሰራ ስብስብ ነው።
~ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስፓልት ዳር የተተከለ ችግኝ ተጎዳብኝ ብለው እሪ ያሉትን ያህል ኦሮሚያ ውስጥ ሺህ አማራ ቢገደል ጉዳያቸው አይደለም። በሴራ ሆን ተብሎ የተቃጠለው መስጊድ ላይ በማሕበራዊ ሚዲያ የተረባረበብን የኦህዴድ ካድሬ የአማራን ሞት ከቅጠል መቀጠፍ ያሳንሰዋል።
~ኦሮሚያ ውስጥ የአማራ መገደል ቀልድ ሆኗል። እስካሁን በይፋ በስራ አፈፃፀም አለማቅረባቸው ብቻ ነው። ብዙው ወንጀል በካድሬው ከለላ የሚፈፀም ነው። ብዙው ወንጀል በካድሬው ዝምታ የሚፈፀም ነው። ብዙው ወንጀል የሚሸፋፈነው በካድሬው ትዕዛዝና ስምምነት ነው። ከሁለት አመት በፊት ደብረ ብርሃን ላይ
እንደ ተራ ነገር የሚወሰድ አይደለም! በየተቋማቱ አይኑን ያፈጠጠ እውነታ ነው! የፌደሬሽን ምክር ቤቱ ገፅ ያጋራው ገፅ ሲፅፋቸው የሚውላቸው የኦነግና የትግሬ ወራሪ ቡድን ፕሮፖጋንዳዎች ናቸው!
ፌስቡክ ላይ ስህተት ይፈጠራል። ይህኛው ግን ቀላል ስህተት አይደለም። እንደ ተራ ነገር ገፁ በሌላ እጅ ገብቶ ወዘተ አይሉንም።
የፌደሬሽን ምክር ቤቱ ገፅ ያጋራው የጤነኛ ሰው ገፅ አይደለም። ጤነኛ ሀሳብም አይደለም። ግጭቶችን እፈታለሁ የሚል ተቋም መሰል አወዛጋቢ ጉዳይ ማጋራቱ እንደ ቀላል ስህተት መታየት የለበትም።
የፌደሬሽን ገፅ ያጋራው ሰው ገፅ እልም ያለ የኦነግ ደጋፊ ነው። የኦነግ ሸኔና የትግሬ ወራሪን ዜና ሲሰራ የሚውል ገፅ ነው። ሕዝብ ሲሰድብ የሚውል ገፅ ነው። የዚህ ገፅ አስተዳዳሪ ሳውዲ አረቢያ እንደሚኖር ይገልፃል። ሊሆን የሚችለው እንዲህ ነው:_
1) የፌደሬሽን ምክር ቤት ገፅን የሚያስተዳድሩት መካከል ይህን አመለካከት የሚጋሩ ሰዎች አሉበት። በራሳቸው ስም የተከፈተም፣ የሀሰት አካውንትም ሊኖራቸው ይችላል። በራሳቸው አካውንት እናጋራለን ብለው በፌደሬሽን ምክር ቤት ገፅ አጋርተውት ሊሆን ይችላል።
2) የዛ የኦነግ ገፅ ፀሀፊ ሳውዲ የሚኖር አስመስሎ ነገር ግን አገር ቤት የሚኖር እንዲያውም የፌደሬሽን ምክር ቤቱን ገፅ ላይ የሚሰሩት መካከል የዛ ገፅ ባለቤት ይኖራል። በሌሎች ገፆች አጋራሁ ብሎም ይሁን፣ ሆን ብሎ አጋርቶታል።
3) የፌደሬሽን ምክር ቤቱን ገፅ የሚያዙበት ሰዎች ስራ ለቀውም ይሁን በስራ ላይ እያሉ የዛን ሆን ብለው የዛን የኦነግ ገፅና ሀሳብ አጋርተውታል።
ሁሉም የሚያሳዩት የተቋማትን መበስበስ ነው። እንደ ቀላል ሊታዩ የሚገባቸው አይደሉም። በአደባባይ እንዲህ ከመንፀባረቃቸው በፊት