ለ10 የሬድዮ ጣቢያዎች ፍቃድ ሊሰጥ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለተጨማሪ 10 የሬድዮ ጣቢያዎች ፍቃድ ሊሰጥ ነው።

የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱዓለም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በዚህ ዓመት ለ10 የንግድ ሬድዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ለመስጠት ባለስልጣኑ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

እስካሁን 12 የሚሆኑ ድርጅቶች የንግድ የሬድዮ ጣቢያ እንዲሰጣቸዉ መጠየቃቸዉን የተናገሩት ምክትል ዳይሬክተሩ፣ ለ5 የንግድ ሬድዮ ጣቢያዎች ጨራታ ወጥቶ ፍቃድ ለመስጠት በሂደት ላይ ይገኛሉ ብለዉናል፡፡

በቀጣይም መስፈርቱን ለሚያሟሉ ድርጅቶች ፍቃዱ ይሰጣቸዋል ነዉ ያሉት፡፡

ባለስልጣኑ ለክልል የንግድ የሬዲዮ ፍቃድ ለመስጠት ፍላጎት ቢኖረዉም፣ እስካሁን ጥያቄዎች እየቀረቡ ያለዉ ግን ለአዲስ አበባ ነዉ ብለዋል አቶ ወንድወሰን፡፡

በተለይም የራሳቸዉ የሬድዮ ጣቢያ የሌላቸዉ እንደ ሲዳማ፣አፋር፣ቤንሻንጉል እና ጋምቤላ ክልሎች ጥያቄዉ እንደቀረበ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዉ፣ጥያቄ ግን እስካሁን አለመቅረቡን ጠቁመዋል፡፡

ፈቃድ ለመዉሰድ በሂደት ላይ ያሉት አምስቱም የንግድ ሬድዮ ጣቢያዎች አዲስ አበባ ዉስጥ መሆናቸዉን የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሩ፣ እስካሁን ግን ፈቃዱን ወስዶ ወደ ስራ እንዲገባ የተፈቀደት ድርጅት የለም ብለዋል፡፡