በአገዛዙ በድሮንና በመድፍ የታገዙ ሁለት የኮማንዶ ክፍለጦሮችንና የሁለት ዕዝ ሰራዊትን ከሚኒሻና አድማ ብተና አባላት ጋር አጣምሮ አስልፎ የተዋጋበትና፡ ይህ ሁሉ ግትልትል ሰራዊት የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት “ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም” የተባለበትን ሽንፈት የተከናነበበት አውደ ውጊያ!
ከላላ ወረዳን ጨምሮ በበርካታ የምዕራብ ወረዳዎች ላይ ታህሳስ 28/2018 ዓ/ ም ከንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት ከባድ ውጊያ መደረጉን በእለቱ መረብ ሚዲያ በሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገፆቹ መዘገቡ ይታወቃል።
በውጊያው፡ አገዛዙ ከድሮን ጀምሮ በመድፍና በቢኤም እንዲሁም በሞርተርና በዙ23 የታገዙ ሁለት የኮማንዶ ክፍለጦሮችን እና ከሁለት ዕዝ የተወጣጣ ሰራዊትን አሰልፎ የነበረ ቢሆንም፡ ነገር ግን “ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ” የተባለው አባባል ደርሶበት በጥቂት የፋኖ አሃዶች የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋምም ባለመቻሉ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራን ተከናቧል።
ውጊያው የተካሄደው በጃማ፣ በከላላ፣ በልጓማ፣ በደብረዘይት፣ በለገሂዳ፣ ገነቴ፣ በመኃል ሳይንት ደንሳ ከተማ፣ በተንታ አጅባር፣ በመቅደላ ማሻ፣ በጉጉፍቱ፣ ካቤ እና በሰኞ ገበያ ላይ ነው።
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከሶስት ኮሮች ማለትም ከንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ ከልጅ እያሱ ኮር እና ከደጋው መብረቅ ኮር፣ እንዲሁም የዕዙ ልዩ ዘመቻ አሃድ ከሆነችው ከበላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች እና ከአፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝና ከወሎ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ጥምረት በመፍጠር ነው በጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ላይ ጥቃት የከፈቱት።
በአገዛዙ በኩል በአየር ወለድ ኮማንዶ መምሪያ የ105ኛ እና የ107ኛ ክ/ጦር ኮማንዶዎችን ጨምሮ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ801ኛ ኮር ሰራዊትና የ11ኛ ዕዝ ወታደሮች እንዲሁም የደቡብ ወሎ ዞን “መከታዎቼ” ሲል የሚመካባቸው <ፓራ ኮማንዶ> የሚል መጠሪያ ያላቸው የሚኒሻ አባላትና የአድማ ብተና አባላት በወረዳ ካድሬዎች መንገድ መሪነት የድሮንና የመድፍ፣ የዙ23ና የሞርተር እንዲሁም የቢኤም ሽፋን እየሰጠ ያሰለፈ ቢሆንም፡ ነገር ግን “ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም” ነውና ነገሩ ይህ ሁሉ ግትልትል ሰራዊት የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ከባድ ሽንፈትን ተከናንቦ ውሏል።
በውጊያው አራት ብሬን፣ አንድ ስናይፐር እና 170 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ ሁለት ወታደራዊ ኦራል ተሽከርካሪዎች ከነጫኑት ሬሽንና ተተኳሽ እና 146 ወታደሮችና በርካታ ወታደራዊ መገንኛ ራዲዮኖች በፋኖ መማረካቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በተጨማሪም የጠላት ብልፅግና ቡድን ከላላ ወረዳ ውስጥ ለገና በዓል ለእርድ አዘጋጅቷቸው የነበሩ አራት ሰንጋ በሬዎችና በርካታ ኩንታል የምግብ እህል በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል።
በዚህ ውጊያ ከተገደሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የሚኒሻ እንዲሁም የአድማ ብተና አባላት በተጨማሪ መንገድ ሲመሩ የነበሩ በርካታ የወረዳ አመራሮችም ተገድለዋል፡ከፊሎቹም በከባድ ሁኔታ ቆስለዋል።
መከላከያን መንገድ ሲመሩ ተገኝተው ከተገደሉ የወረዳ አመራሮች መካከል የከላላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ሃላፊ አቶ አሚኑ አህመድ፣ የወረዳው ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አሊ አህመድ የሱፍ፣ እንዲሁም የወረዳው ሚልሻ ፅ/ቤት የሰላም አስከባሪ ሂደት ኃላፊ ሳጅን አልዩ አህመድ አብዲን ጨምሮ ሌሎች የወረዳው ፀጥታ ቢሮ አመራሮችና አባላት እንደሚገኙበት ታውቋል።
ይሄንን ተከትሎ የከላላ ወረዳ አስተዳደር ከታህሳስ 28/2018 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ እስከ ትናንት ታህሳስ 30/2018 ዓ/ም ለአምስተኛ ጊዜ የሐዘን መግለጫ ማውጣቱን መረብ ሚዲያ ከወረዳው ይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክቷል።
ወረዳው በመግለጫው፡ ከአመራሮቼ መካከል አንዳንዶቹ በተኙበት ነው የተገደሉት ያለ ሲሆን፡ ሌሎቹ ደግሞ በውጊያ መኃል የተገደሉብኝ ናቸው ማለቱን ነው መረብ ሚዲያ የተመለከተው።
(ምስል፦ በእለቱ በፋኖ ከተማረኩ የጦር መሣሪያዎች መካከል ጥቂቱ)