የአገዛዙ ኃይል በምስራቅ ደምቢያና በአከባቢው እየፈፀመ ያለው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተባብሶ መቀጠሉ ተሰምቷል።

የአገዛዙ ኃይል በምስራቅ ደምቢያና በአከባቢው እየፈፀመ ያለው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተባብሶ መቀጠሉ ተሰምቷል።

የአገዛዙ ወታደሮች ምስራቅ ደምቢያ ስር የሚገኙ አከባቢዎችን ጨምሮ በወገራ፣ በሊቦ ከምከም እንዲሁም በላይ ጋይንት ወረዳና በሌሎች የቀጠናው አካባቢዎች በንፁኋን ወገኖች ላይ ከጅምላ እስርና ግድያ ጀምሮ የሚፈፅሙት ከባድ የሆነ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተባብሶ መቀጠሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ተናግረዋል።

በተለይ የፋኖ ቤተሰብ ናቸው በተባሉና ለወታደሩ እሬሽን መግዣ የሚሆን ገንዘብ አላዋጡም እንዲሁም ብልፅግናን በገንዘብ አይደገፉም ተብለው በተጠረጠሩ ንፁኋኖች ላይ የሚፈፀመው የጅምላ እስርና እስከ ግድያ የደረሰ ድብደባ ተባብሶ ቀጥሏል።

ወታደሮቹ ከሚፈፅሙት የጅምላ እስርና ድብደባ እንዲሁም ወከባ በተጨማሪ ማንነት ተኮር ፀያፍ ስድቦችን በመሳደብ በአከባቢው ነዋሪዎች ላይ የስነ ልቦና ጉዳት እያደረሱ ነው ሲሉ ስለሁኔታው ለመረብ ሚዲያ የተናገሩ እማኞች ገልፀዋል።

በተጨማሪም ነዋሪዎቹ በየመኖሪያ ቤታቸው ምሽግ ተቆፍሮ መግቢያ መውጫ ማጣታቸውንም ተናግረዋል።