ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ መምሪያ ለወራት የሰለጠኑ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን አስመረቀ

::

ምኒልክ ዕዝ የልዩ ዘመቻ መምሪያ አሃድ ከሆኑት መካከል ለወራት የሰለጠኑ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች የዕዝ የኮርና የክፍለጦሩ አመራሮች በተገኙበትና መልክት ባስተላለፉበት ሁኔታ ተመርቀዋል::

ከፍተኛ የዕዙ አመራሮችም የተጀመረውን የፖለቲካ ትጥቅ ትግል ከግብ ለማድረስና የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ብሎም ቀጣይነት ያለው ነፃነት ለመጎናፀፍና የሃገራችን ባለቤት ለመሆን በፅናትና ቁርጠኝነት መታገል ብቻኛ አማራጭ መሆኑን ለተመራቂዎች አስገንዝበዋል::

ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን ያስመረቁት በልዩ ዘመቻ መምሪያው ስር የሆነው አሃድ ወታደራዊ አዛዥና ምክትል ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት አርበኞችም ለተመራቂዎች መልክታቸውን አስተላልፈዋል::

የልዩ ዘመቻ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ዛሬ የተመረቃችሁ ምኒልክ ዕዝ የልዩ ዘመቻ እንደስማችሁ ልዩ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ለበርካታ ወራት ፀሀዩን:ብርዱን:ቁሩን በርካታ ውጣውረዱ ሳይበግራችሁ ባልተመቻቸ ሁኔታ ተቋቁማችሁ ለዚህች ልዩ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ የናንተ ስልጠና ለየት የሚያደርገው ያኔ በጣት በምንቆጠረበት ጊዜ ሳይሆን አሁን በሺዎች ብሎም በሚልዮኖች በትጥቅም ይሁን በሰው ኃይል አቅማችን እንዲሁም የማድረግ አቅማችን ትልቅ የስኬት ጫፍ ላይ ባለንበት ጊዜ መቀላቀላችሁ በተጨማሪም  የዚህን አንባገነን ስርዓት ግፍ በደል እና ሰቆቃ አድራሽነት ማንም ሳይጎተጉታችሁ እያንዳንዳችሁ ቤት አንኳኩቶ የገባ በመሆኑ ያለማንም ቀስቃሽ በቃኝ አሻፈረኝ ብላችሁ ይህን ትልቅ የትጥቅ ትግል የተቀላቀላችሁ መሆኑ ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ለየት ያደርገዋል።

እንሰባሰባለን እንደራጃለን እንሰለጥናለን እንታጠቃለን ተዋግተን ይህን አንባገነን ፀረ_አማራ ስርዓት ከትክሻችን ላይ አሽቀንጥረን እንጥላለን።
የአማራ ተጋድሎ አካሄድ እና መስመር⚡️:-
👉 የተጋድሏችን
መነሻ:-የአማራ ህልውና አደጋ ነው።
መዳረሻው:- አደጋውን ቀልብሶ ህዝቡን ከባርነት አውጥቶ ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር የሃገሪቱን በትረ ስልጣን መልሶ መቆጣጠር ነው::
👉የተጋድሎው ርዮት አማራ ብሔርተኝነት ነው!
👉የተጋድሎው አካሄድ የትጥቅ ትግል ነው!
👉የአማራ ብሔርተኝነት የህልውናችን ዘላለማዊ ዋስትናም ነው!
👉የአማራ ብሎም ኢትዮጵያ ህልውና በሀገር መስራቹ በታላቁ አማራና በተባባሪ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ትብብር ዳግም ይፀናል።እናሸንፋለን!

በመቀጠልም የዚህ ስርዓት አካሄድና የህዝባችን ግፍና ሰቆቃ ለኛ ብቻ ሳይሆን እንደአማራ አማራን ለማጥፋት እየተሄደበት ያለው እርቀት  መላው ዓለም እየተረዳው ያለ ሀቅ ነው  ።እሄ ሆኖ ሳለ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ያልገባችሁ በተለያየ የፀጥታ ዘርፍ በመከላከያ :በፌደራል :ፖሊስ :በአድማ ብተናና ብሎም ሚኒሻ ውስጥ ሆናችሁ ስርዓቱን እያገለገላችሁ ያላችሁ ትውልደ አማራውያን በሙሉ በቃኝ በማለት የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ህዝባችሁን ከባርነት ቀንበር ነፃ ታወጡት ዘንድ ታላቅ የተጋድሎ ጥሪየን አስተላልፋለሁ።

በመጨረሻም አማራ በወርቃማ ልጆቹ መስዋትነት አራሱን ነፃ ያወጣል እናሸንፋለን።መ/አለቃ ግርማው አብየ
የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ የክፍለ ጦር አዛዥ

ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ተመራቂዎች   እንኳን ለዚች ቀን በሰላም አደረሳችሁ
ከዚህ በመቀጠል ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ እንኳን ለዚች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

ተመራቂወች የአማራ ህዝብ የተቃጣበት የማንነት ተኮር ጥቃት ከመገደል ወደ መከላከል ከመከላከል ወደ ሺምቅ ከሺምቅ ወደ ማጥቃት ገብተናል።

ሰለዚህ የአማራ ህዝብ መዳኛው መሰልጠን  መታጠቅ እንዲሁም በአድነት ቁመን  የአማራን ህዝብ የታወጀበትን ዘር ማጥፋት  በአድነት በመተባበር ወደፊት እንሄዳለን::

አንድነት ሃይል ነው በአንድነታችን የማንሻገረው ወንዝ የማንወጣው ተራራ የማንወርደው ቁልቁለት የለም:: እኛ አማራዎች ጀምረን ያልጨረስነው ትግል የለም:: ምክንያቱም  የአባቶቻችን ልጆች ነን የአማራን ህዝብ ለማዳን እስካሁን መሰዋትነት እየከፈሉ የመጡ ጎዶቻችነን  ትግል የማስቀጠል ግዴታችንን እደምንወጣ አልጠራጠርም:: አማራ ያሸንፋል!   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አርበኛ አሻግሬ ሙሉ /ቦምበኛው/

ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ