ሁለት የቱርኪዬ ዜጎች እና አንድ ኢትዮጵያዊ አሽከርካሪ ማንነታቸዉ ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ በጉብኝት ላይ የነበሩ ሁለት የቱርኪዬ ዜጎች የሆኑ ጎብኝዎች እና አንድ ኢትዮጵያዊ አሽከርካሪ ዛሬ ከጧቱ 2 ሰዓት ከ20 ላይ “ማንነታቸዉ ባልታወቁ” ታጣቂዎች ተገደሉ።

ጥቃቱን የፈጸሙት “የአርብቶ አደር ሽፍቶች” መኾናቸውን ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ የጠቀሠው የክልሉ መንግሥት፣ ጥቃቱን ተከትሎ ጸጥታ ኃይሎች የተቀናጀ የሕግ ማስከበር ዘመቻ መጀመራቸውን ገልጧል።

የክልሉ መንግሥት፣ ሽፍቶቹ በጎብኝዎቹ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት “ለዝርፊያ” ሲሉ ነው ብሏል።