የጅቡቲ መንግስት የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ በመግባት በፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ሦስት ንፁኋኖች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ታወቀ!

የጅቡቲ መንግስት የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ በመግባት በፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ሦስት ንፁኋኖች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ታወቀ!

ዐብይ አህመድ ሀገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ የሚገኙ ድንበሮቿን ክፍት በማድረግ ከተራ ታጣቂዎች እስከ ጎረቤት ሀገራት መንግስታት እንደፈለጉ በመግባት ኢትዮጵያውያን ላይ ያሻየውን ጥቃት የሚፈፅሙባት ሀገር ካደረጋት ዋል አደር ብሏል።

የጅቡቲ መንግስት ንብረት እንደሆነ የተነገረለት አንድ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥር 05/2018 ዓ/ም የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ በመግባት በአፋር ክልል ጥቃት መፈፀሙን ታማኝ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችሏል።

የድሮን ጥቃቱ የተፈፀመው በአፋር ክልል ኤሊዳዕር ወረዳ ስር በሚገኝ በአንድ የገጠር መንደር ላይ ሲሆን፡ በዚህም ሦስት ንፁኋኖች ሲገደሉ በርካታ ንፁኋኖች ደግሞ መቁሰላቸውን ምንጮቻቸን አክለው ገልፀዋል።

በጥቃቱ ከሞቱትና ከቆሰሉት መካከል ሴቶችና ህፃናት እንዲሁም አረጋውያን እንደሚገኙበት ነው ምንጮች የገለፁት።

በዚኸው አፋር ክልል ከወራት በፊትም በተመሣሣይ መነሻውን ከጅቡቲ ያደረገ የሰው አልባ አውሮፕላን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በቀብር ስነ ስርዓት ላይ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈፀመው ጥቃት የሀይማኖት አባቶችና አዛውንቶችን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸውን ጣቢያችን በወቅቱ መዘገቡ አይዘነጋም።

በሁሉም አቅጣጫ የሚገኙ የሀገሪቱን ድንበሮች ክፍት በማድረግ፡ ድንበር ሲጠብቁ የነበሩ ወታደሮችን ጨምሮ ሀገሪቱ አለኝ የምትለውን ጦር ድሮንና ጀት እንዲሁም ሌሎች ከባባድ መሣሪያዎችን አስታጥቆ ወደ አማራ ክልል አስገብቶ በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀው ኦህዴድ መሩ የብልፅግና አገዛዝ፡ ከወደ ፋኖ የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ወታደራዊ ኃይሉ የተመናመነበት ሲሆን፡ በአንፃሩ ደግሞ ፋኖ የአገዛዙ ወታደሮችን መሣሪያ ማርኮ እራሱንና አደረጃጀቱን በማዘመን የድል አጥቢያ ላይ ይገኛል።