በምስራቅ በለሳ ግንባር ፋኖ የአገዛዙን አከርካሪ የሰበረበት ትንቅንቅ!

በምስራቅ በለሳ ግንባር ፋኖ የአገዛዙን አከርካሪ የሰበረበት ትንቅንቅ!

በአፋብኃ ሰሜን ዐምሓራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር ስር ከሚገኙት ከኮሩ ተወርዋሪ ኃይል፣ ከአፄ እያሱ ክ/ጦር፣ ከዞዝ አምባ ክ/ጦርና ከንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር እንዲሁም ከጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በጋራ በመሆን ትናንት ጥር 01/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በወሰዱት እርምጃ የጠላትን አከርካሪ በመስበር ታላቅ ድል ተቀዳጅተው መዋላቸውን መረብ ሚዲያ ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።

ውጊያው የተደረገው በምስራቅ በለሳ ጣይመን ከተማ ሲሆን፡ በዚህም የፋኖ አባላቱ በከተማ ውስጥ የሚገኘውን የአገዛዙ ወታደራዊ ካምፕን ጥሰው ገብተው በሦስት አቅጣጫ ተኩስ በመክፈትና ሁለት ትላልቅ ምሽጎችን በመስበር ነው በጠላት ላይ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራ ማድረስ የቻሉት።

በውጊያው 37 የብልፅግና መከላከያ ሠራዊት አባላት ሲገደሉ 35 የአገዛዙ ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል ያለው ኮሩ፡ በለስ የቀናቸው 25 ወታደሮች ደግሞ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መማረካቸውን አሳውቋል።

ከንጋት ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን በዘለቀው አማራዊ ጀግንነትን ከጦር ሣይንስ እውቀት ጋር ያጣመረ ነው በተባለው በዚህ ከባድ ተጋድሎ ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ ከተደረጉት በተጨማሪ፡ ሦስት ብሬን፣ 55 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 1ሺ የብሬን ተተኳሽ፣ 2ሺ የክላሽ ተተኳሽ፣ 100 የእጅ ቦምብ እና ሁለት ወታደራዊ መገናኛ ራዲዮ በፋኖ መማረኩን መረብ ሚዲያ ከዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።

ቁስለኛ ወታደሮች ለሕክምና ወደ ጓህላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና ወደ አርባያ ሆስፒታል ተወስደዋል ነው ያለው ኮሩ ባወጣው መረጃ።

በውጊያው፡ ፋኖ የማጥቃት አቅሙ ምን ያህል እንዳደገ ያሳየ ሲሆን፡ በአንፃሩ የአገዛዙ ወታደሮች ደግሞ እራሳቸውን ተከላክለው ማዳን የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው በገሀድ ታይቶበታል ተብሏል።