በፌዴራል ደረጃ ከተመዘገቡት 470ሺ የንግድ አና አገልግሎት ሰጪ የግል ድርጅቶች ውስጥ 370ሺ ስራ አቁመዋል ….. አስደንጋጩን ሪፖርት እነሆ

በፌዴራል ደረጃ ከተመዘገቡት 470ሺ የንግድ አና አገልግሎት ሰጪ የግል ድርጅቶች ውስጥ 370ሺ ስራ አቁመዋል ….. አስደንጋጩን ሪፖርት እነሆ
…  የድርጅቶች በዚህ ደረጃ መዘጋት የመንግስት ገቢን በመቀነሱ ምክንያትም በቀሩት ጥቂት ድርጅቶች ላይ የሚያሳድረው የግብር ጫና በሂደት ቀሪዎችንም ከገበያ ሊያሰወጣ የሚችል ክስተት መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድበት የሚገባ ነው። ……..በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ኤክስፐርቶች ተጠንቶ የቀረበን ሪፖርት በመንተራስ ቅዳሜ የወጣው የእንግሊዘኛ ሪፖርተር ሳምንታዊ ጋዜጣ በፌደራል ደረጃ ተመዝግበው ከሚገኙና በተለያየ ሙያና ዘርፍ ከተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች መካከል 80% የሚሆኑት እንደተዘጉና በአሁኑ ጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ቁጥር ከ100 ሺህ እንደማይበልጡ ዘግቧል።…… ለረጅም ዓመታት ፈጣን እድገት በማሳያት 470 ሺህ ደረሰው ከነበሩት በፌደራል ደረጃ የተመዘገቡ የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች መካከል 370 ሺዎቹ በ2025 መዘጋታቸውን በዘገባው ላይ አክሏል። ….. ሪፓርተር መሰረት ባደረገው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ኤክስፐርቶች ጥናት መሰረት በ2025 ከ370 ሺህ በላይ ድርጅቶች ከፌደራል መዝገብ ተሰርዘዋል ማለት ምን ያህል የስራ እድል፣ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የመንግስት ገቢዎችን እንደሚቀንስና ከአገልግሎት አሰጣጥና ከአቅርቦት አኳያም በምን ያህል ደረጃ የምርት አቅርቦትና ስርጭት ሚዛንን እንደሚያዛባ መረዳት ይቻላል። #MinilikSalsawi