ስምንት የትግራይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዲስ ጥምረት ፈጠሩ።

ስምንት የትግራይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዲስ ጥምረት ፈጠሩ። ስምረት፣ አረና ትግራይ፣ ባይቶና፣ ውድብ ወለዶ ትግራይ፣ ቃንጫ ሃቂ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ትንሳኤ 70 እንደርታ እና ራያ ራዩማ፤ ትግራይን ወክለው በአገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ ያስችላል ያሉትን አዲስ ጥምረት መፍጠራቸውን ዋዜማ ከጥምረቱ አባል ፓርቲዎች አመራሮች ሠምታለች። ከክልሉ 96 ወረዳዎች በ86ቱ አገራዊ ምክክሩን ማካሄድ እንደሚቻል የገለጹት አመራሮቹ፤ አስቻይ ሁኔታ በሌለባቸው ወረዳዎች ደሞ በዞን ደረጃም ቢሆን ምክክር መደረግ አለበት ሲሉ አቋማቸውን ነግረውናል። በትግራይ ውስጥ ሊደረግ የታቀደው የምክክር ሂደት በሕወሃት ይሁንታ ላይ የተመሠረተ መሆን እንደሌለበት በመግለፅ፤ በክልሉ የሚደረጉ ምክክሮች በአዲሱ ጥምረት በኩል እንዲደረጉ ለምክክር ኮሚሽኑ ሃሳብ ማቅረባቸውንም አመራሮቹ ገልጸዋል።