የህወሓት ህልም የሞንጆሪኖ ቅዠት

የህወሓት ህልም የሞንጆሪኖ ቅዠት ፦

” ኢትዮጵያ የአብዮታዊ ዲሞክራሲን አቅጣጫ ስታ በውድቀት ቁልቁለት ላይ ተቀምጣለች ፤ … መፍትሄው ደግሞ ወደ ቦታችን መመለስ ነው ። ”
.
ታጋይ ወ/ሮ ፈትለወርቅ/ሞንጆሪኖ/ በ6ኛው የመለስ ሙት አመት የተናገሩት ።
.
.

ለመሆኑ ወ/ሮ ሞንጆሪኖ በማን ፈቃድ ነው እንደገና ወደ ቦታቹ የምትመለሱት ?….ከዚያ ከደደቢት የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጨለማ የወጣው ሕዝብ ዳግም ወደዚያ ገሃነም ለመግባት እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ ይመስሎታል ? … ለማነኛውም ይህ ሐሳብዎ ቅዠት ስለመሆንና አለመሆኑ እስቲ በተመስጦ ቁጭ ብለው ያብሰልስሉት ።
.
አብዮታዊ ዲሞክራሲያቹ ሞቷል ፤ የመተ ደግሞ ሲነሳ አላየንም ።
.
” አንሰራርተን ዳግም በቤተመንግስት እንከሰታለን ። ” ብሎ የማመን መንፈስ ካላቹ ፤ … ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ” መለስን ከሞት አስነሳለሁ ። ” በማለት ሲያውጅ የነበረውን እስራኤል ዳንሳም እመኑት ።

ሜሮን ፋሲል