Blog Archives

በርካታ ሰራዊት የያዘው የሱዳን ሰራዊት በኮርሁመር በኩል አዲስ ወረራ ጀምሯል።

ሕዝብ በሁለት አቅጣጫ እየተወጋ ነው! መቀሌ ቢሮ የተከፈተላቸው የቅማንት ኮሚቴ ነን የሚሉት ትዕዛዝ ዛሬ መንገድ ተዘግቶ ውሏል። ወደ መተማ ሲያልፉ የነበሩ አስራ አራት መኪናዎች ተሰባብረዋል። የዜጎች ቤት እየተመታ ነው። መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሀይል አካባቢውን ማረጋጋት አልቻለም። በሌላ በኩል ደግሞ ዛሬ የሱዳን ሰራዊት እንደ አዲስ ወረራ ጀምሯል። በርካታ ሰራዊት የያዘው የሱዳን ሰራዊት በኮርሁመር በኩል መግባቱ ተገልፆአል። ሕዝብ ከፊትና ከጀርባ እየተወጋ ነው። ወደመተማ የሚወስደው መንገድ ባለፉት ሳምንታትም ተጓዦችን ለአደጋ ያጋለጠ የነበር ሲሆን ዛሬ የባሰ ሆኗል። የመተማ ወረዳ ነዋሪዎችም “መንግስት ችግሩን ማብረድ ካልቻለ አማራጭ እንወስዳለን” በማለታቸው እስከ ነገ አራት ሰዓት ታገሱ መባላቸው ታውቋል። የሱዳን ወረራ ዛሬ ሀምሌ 25/ 2010 ዓም ከቀኑ 7 ሰዓት በሆሩመር ምድርያ በኩል የሱዳን ሰራዊት የአማራ ገበሬዎችን ወርሯል። ማሳቸው ላይ የነበሩት ገበሬዎች ላይ ወረራ የፈፀመው የሱዳን ሰራዊት ከወንድሙ ማሳ የነበረውን አንድ ተማሪ አቁስሏል። የአማራ ገበሬዎች ከባድ መሳርያ የታጠቀውና በርካታ ሰራዊት ያለው የሱዳን ጦርን የተከላከሉ ሲሆን አንድ ትራክተር፣ አንድ 3 ኤፍ መኪና እና አንድ ዲሽቃን ጨምሮ መማረካቸው ታውቋል። የሱዳን ሰራዊት ኃይል አጠናክሮ ሲመጣ ከተማረኩት መካከል 3 ኤፍ መኪና እና ዲሽቃውን ገበሬዎቹ አውድመዋል። ትራክተሩ ወደ ሆሩመር ከተማ ተወስዷል። የተወሰነ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው ቢኖርም የአማራ ገበሬዎችን አላገዘም።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰሜን ሱዳን ሰራዊት በድጋሚ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቷል።

የሱዳን ሰራዊት ዛሬም ወረራ ፈፅሟል ተስፋፊው የሰሜን ሱዳን ሰራዊት ዛሬ ሐምሌ 3/2010 ዓም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቷል። በትናንትናው ዕለት በአማራ ገበሬዎችና በአካባቢው ሚሊሻ ወደመጣበት የተመለሰው የሱዳን ጦር ራሱን አጠናክሮ ዛሬ ሐምሌ 3/2010 ዓም ከቀኑ 8: 30 አካባቢ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቷል ተብሏል። በትናንትናው ዕለት በርካታ ሚሊሻ አባላት ድንበሩን በመጠበቅ ላይ የነበሩ ቢሆንም ዛሬ ከ12 የማይበልጡ የሚሊሻ አባላት ብቻ እንደሚገኙ ገበሬዎቹ ገልፀውልኛል። የሱዳን ሰራዊት አባላትና የአማራ ገበሬዎች ኮር ሁመር የሚባል ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ ቦታ ላይ ቦታ ይዘው እንደሚገኙ ገበሬዎቹ በስልክ ገልፀውልኛል። በአካባቢው ገበሬዎችን የሚያግዝ ሌላ የመንግስት ሀይል እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል። ትናንት ሀምሌ 2/2010 ዓም የሱዳን ጦር በከባድ መሳርያ የታገዘ ወረራ ፈፅሞ በገበሬዎቹና በሚሊሻው ወደመጣበት እንዲመለስ ተደርጓል። በወቅቱም 3 አባላቱ ቆስለውበታል። በዛሬው እለትም በከባድ መሳርያ ታግዞ ድንበር እንደተሻገረ ገበሬዎቹ ገልፀዋል።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ገበሬ የሱዳንን ዳግም ወረራ አሳፍሮ መልሷል

የአማራ ገበሬ የሱዳንን ዳግም ወረራ አሳፍሮ መልሷል ትናንት የሱዳን ጦር በአብደራፊና በኮረደም አጠገብ ኮር ሁመርደ የተሰኘች ከተማ አቅራቢ ወደከውሊ የተባለ የኢትዮጵያ ግዛት ወርሯል። ሆኖም ሕዝብና ሚሊሻ ባደረጉት መከላከል የሱዳን ጦር ተሸንፎ ተመልሷል። የሱዳን ጦር 6 የአር ፒጅ ከባድ መሳርያዎችን በሕዝብ ላይ ተኩሷል። ሆኖም ጉዳት እንዳላደረሰ ለማወቅ ተችሏል። በሌላ በኩል ግን ሶስት የሱዳን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከገበሬውና ሚሊሻ በተተኮሰ ጥይት መቁሰላቸው ተገልፆአል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአቅራቢያው የነበር ቢሆንም “ትዕዛዝ አልተሰጠኝም” ብሎ የሱዳንን ዳግም ወረራ ዳር ቆሞ ተመልክቷል። የአማራ ልዩ ሀይል ዘግይቶ የደረሰ ሲሆን “ተመለስ” ተብሎ መመለሱን ምንጮች ገልፀዋል። በድንበር አካባቢ ገበሬውን እያገዙ የሚገኙት ሚሊሻ ሲሆኑ ትናንት ከ1000 በላይ የሚሊሻ አባላት በድንበር አካባቢ እንደነበሩና የአማራ ገበሬዎች የሱዳንን ጦር ወደመጣበት ሲመልሱ ትልቅ እገዛ ማድረጋቸው ተገልፆአል። የፌደራልም ሆነ የክልሉ መንግስት ሉአላዊነት ማስከበሩን ግዴታ አሁንም ለአማራ ገበሬዎች እንደጣሉት ነው።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሽር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የተላከላቸውን መልእክት ተቀበሉ።

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሽር በድንበር አካባቢ የፀጥታ ችግር መከሰቱን ተከትሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የተላከላቸውን መልእክት ተቀበሉ። የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ሰሞኑን በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ተስተውሎ የነበረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከላቸውን መልእክት ተቀብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት የላኩትን መልክእትም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ናቸው ያደረሱት። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በዚሁ ወቅትም ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋር ሰሞኑን በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በተስተዋለው የፀጥታ ችግር ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተከሰተው ግጭት የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የማይጎዳ መሆኑን እና ግንኙነቱም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው ኤል ዲልደሪ ሞሃመድ አህመድ ጋርም ተገናኝተው ተወያይተዋል። ውይይቱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንዳለ በመጥቀስ ኢትዮጵያ ከድንበር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን በሙሉ ለመቅረፍ ትሰራለች ብለዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ የሚነሱ ችግሮች እንዲፈቱ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ መግለፃቸውንም ዶክተር ወርቅነህ ተናግረዋል። የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርም በድንበር አካባቢ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ተፅእኖ በማይፈጥር መልኩ ለመፍታት እንደሚሰሩ አስታውቀዋልም ብለዋል። የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤል ዲልደሪ ሞሃመድ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና የሱዳኑ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመተማና ወልቃይት የጦር ሰራዊቱ ድንበር መጠበቁን አቁሟል።

የሀገር አልባዎች ዜና! (በጌታቸው ሽፈራው) ትህነግ/ኢህአዴግ የቋራን፣ የመተማና ወልቃይትን መሬት ለሱዳን ከሰጠ በኋላ የጦር ሰራዊቱ ድንበር መጠበቁን አቁሟል። የአማራ ገበሬ መከላከያ ሰራዊቱን ተክቶ ዳር ድንበር እያስከበረ ይገኛል። ዳር ድንበር ሲያስከብሩ ከነበሩት መካከል እውቁ ባሻ ጥጋቡ ይጠቀሳል። የመከላከያ ሰራዊቱ አልፎ አልፎ ብቅ ሲል ሱዳኖቹ የመለስ ጦር መጣ ይላሉ። የባሻን ጦር ደግሞ ያውቁታል። ሱዳኖቹ ከገዥዎቹ ጋር ቅርበት ያላቸውን ባለሀብቶች ሰብል ሲያቃጥሉ ወይንም ከብት ሲነዱ አልፎ አልፎ መከላከያ ሰራዊቱ ለሱዳን ወደተሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ይዘልቃል። ሱዳኖቹም የመለስ ጦር መጣ ይባላል። ጥጋብ ሲሰማቸው ” እንኳን የመለስ ጦር ባሻ ጥጋቡም ይምጣ” ብለው ይፎክራሉ። ከመለስ በላይ ባሻ ጥጋቡ ነበር ድንበር ጠባቂው። ባሻ ጥጋቡ በአነጋጋሪ ሁኔታ ህይወቱ አለፈ። ባሻ አለኝታው የነበረው ገበሬ መንግስት ነው የገደለው ብሎ ያምናል። በማግስቱ የኢትዮጵያ ገበሬዎች ማሳ በእሳይ ጋየ። የሱዳን ጦር የገበሬውን ቤት ሁሉ አቃጠለ። አሁንም ሌሎች ባሻ ጥጋቡዎች ድንበሩን ይጠብቃሉ። ሆኖም የኢትዮጵያ ጦር ነው የሚባለው የራሱን ሕዝብ እየወጋ ለሱዳን ያግዛል። የሱዳን ከብት ጠፋ ከተባለ ከሱዳን ወታደር ጋር በመሆን ገበሬዎቹን ይወጋል። የሱዳን ጦር ኢትዮጵያ መሬት ላይ ተቀማጭ ሲሆን የኢትዮጵያው ጦር ወደኋላ አፈግፍጎ ሕዝብ ለጠላት ጦር አስረክቧል። የሱዳን ጦር ደስ ባለው ጊዜ ገበሬውን እያገተ ይወስዳል። ይገድላል። ንብቱን ያቃጥላል። ልጆችና ሚስቱን አፍኖ ይወስዳል። የሚደርስ የኢትዮጵ የሚባል ጦር የለም። ገበሬው በቻለው መንገድ ይከላከላል። ዛሬም አፈናው ቀጥላል። ትናንት ሰኔ 14/2010 ዓም ደጉ ማሞ፣ ጌጤ ክብረትና ሌላ አንድ ገበሬ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook