“የተኙትን ፓትርያርክ እንቀስቅሳቸው” እና “ልፋፈ ጽድቅ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“የተኙትን ፓትርያርክ እንቀስቅሳቸው” እና “ልፋፈ ጽድቅ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

እያንዳንዱ የትግራይ ጳጳስ 180, 000 ብር ደመወዝ በወር እንደሚከፈለው የአባ ሠረቀን ስም ጠቅሶ “የትግራይ ሲኖዶስ” በማለት እራሱን የሚጠራውን ስብስብ ቅሌት ከሁለት ሳምንት በፊት “አዲስ ኮምፓስ” የተባለ ዩቱብ አቅርቦት ነበር፡፡ በቀጠለው ሳምንት “ኢትዮጵያ ወዴት ሚድያ” ቀሲስ አስተርአየ ለአባ ሠረቀ የካቲት 12 ቀን 2015 የጻፉላቸውን ጦማር ከድረ ገጽ መዞ አውጥቶ ቀሲስን ጠይቋቸው በሰጡት ሰፊ ማብራሪያ የጠቅላላውን ሲኖዶስ ቅሌት አቅርበውት ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ቀሲስ አስተርአየ በሚድያው ያቀረቡትን “የትግራይ ሲኖዶስ” ቅሌት የሰሙ ሰወች ቀሲስ አስተርአየ የተኙትን ፓትርያርክ እንቀስቅሳቸውበሚል ጥር 2 ቀን 2017 ያቀረቡትን ጦማር ያነበቡ ሰወች እንደገና ብናቀርበው ላናነቡ ሰዎች ግንዛቤ ለማዳበር ይረዳል እንዲሁም ከወያኔው ሲኖዲስ ቅሌት ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጠየቁን፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ጠበቃ መስለው ዩቱብ ከፍተው የየራሳቸውን ጎራ አበጅተው በግል የሚጠሉትን እየነቀፉ በአንጻሩም የሚወዱት ወንጀል ቢኖርበት እንኳን እየደገፉ ግራ የሚያጋቡና ሀሰት የሚያሰራጩ ጩሉሌዎች የቀሲስን ጽሑፎች አንብበው እየተረዱ ከቀኖናዋና ከስነ መለኮት ሳይወጡ በከሐሰት ትርክት ሳይጠለፉ ራሳቸውን እያስተማሩ ህዝቡንም በማስተማር የቤተ ክርስቲያናችንን ቅድስናና ውለታ በመመሰከር ነቃፊወችን ማሳፈርና ቤተ ክርስቲያናችንንም ማገዝ ይችሉ ነበር፡፡ቀሲስ አስተራየን ያንጊዜ የጻፉት ምን ተሰምተዎት ጻፉት? አሁንስ በዚያው በጻፉት ቤተ ክህነቱን ሲመለከተቱ ምን የተለየ ነገር አዩ? ችግሩ ባሰ ወይስ እየተሻሻለ ነው? እንዴት ይመለከቱታል? ብለው መጠየቅና ምሁራኑም እንዲነጋገሩባት ምድረግ ይገባቸው ነበር፡፡

እርስ በርሳቸው እየተቀናኑና የሚያዳምጣቸውን ስሜት እየቀሰቀሱ ባበዙት አድማጭ ቁጥር በሚለቅሙት ገንዘብ ላይ ስለሚያተኩሩ መሠረታዊ የሆነውን ለህዝብ ማቅረብ አይፈልጉም፡፡ ሰውም እንዲያውቅ አይፈልጉም፡፡ ቀሲስ የጻፏቸውን እየተቀባበለ የሚያነበውን እንደኔ የመሰለው ምእመኑ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ መሰለው ዩቱብ ክፍተው ሕዝቡን ግራ የሚያጋባቱ ሰወች “ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያና አገር ናት” ብለው ጠ/ሚኒስቴሩ መጀመሪያ ሲመጡ የመላ ሕዝበ ክርስቲያንኑ ቀልብ የሳቡበትን ንግግር መነሻና መሠረት እየደረጉ የቤተ ክርስቲያንን ውለታ በመመስከር ህዝቡን ለዘላቂ ጥቅም የሚያዘጋጅ ከችግር የሚያወጣ ጠቃሚ ሐሳብ ማቅረብ ይገባቸው ነበር፡፡

ሐምሌ 18 ቀን 2015 ልፋፈ ጽድቅ በሚል ርዕስ ጽፈው ፓትርያርክ ከራሱ እስከ ጥፍሩ የለበሰው የክብር ልብስ የሕዝበ ክርስቲያናኑ አጋጣሚወች ለማንጸባርቀ እንጅ ፓትርያክ ሆኖ ከመንበሩ ላይ የሚቀመጠው አባት የራሱን ሰውነት ለማሳየት እንዳልሆነ አቅርበውልን ነበር፡፡ በሌላ ወቅትም ፓትርያርኩ የለበሱት ለምን እንደለበሱትና አላማው ምን እንደሆነ ገልጸውት ነበር፡፡ የተኙትን ፓትርያርክ እንቀስቅሳቸው ብለው ያቀረቡትን መልሰን ብናቀርብላችሁ ምናልባት እናንተንም ከእንቅልፋችሁ ይቀስቅሳችሁ ይሆናል፡፡ ህዝቡንም እንድታስተምሩበትና ፓትርያርኩንም ከተኙበት ለመቀስቀስ ደግሜ “የተኙትን ፓትርያርክ እንቀስቅሳቸው” በሚል ጥር 2 ቀን 2017 የጻፏትን አቀረብንላችሁ፡፡   ልፋፈ ጽድቅ በቀሲስ አስተርአየ

የተኙትን አቡነ ማቲያስን እንቀስቅስ