Blog Archives

ጠ/ሚ አብይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠ/ሚ አብይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ውይይት አደረጉ፡፡ በውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 100ኛውን የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሜሪካ ታሪካዊውን የለውጥ ሂደት እንደምትደግፍ ጠቅሰው፥ በአሜሪካና ኢትዮጵያ መካከል ስላለው ጠንካራ ወዳጅነት አስፈላጊኒት አንስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ማይክ ፓምፒዮ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ እንዲሁም ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መወያየታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡ በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነትና የጥምር መንግስቱ ተግባራዊ እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማይክ ፖምፒዮ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ Source (ኤፍ.ቢ.ሲ)
Posted in Amharic News, Funny

ኦሮምኛን ጨምሮ ተጨማሪ ቋንቋዎችን የፌደራል የሥራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠ/ሚ ዐብይ ተናገሩ

BBC Amharic : ኦሮምኛን ጨምሮ ተጨማሪ ቋንቋዎችን የፌደራል የሥራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ኦሮምኛን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው። ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ ሌላ ቋንቋ የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ ማድረግ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ካሉና ያላቸውን አመለካከት የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሰጡት መልስ “በዚህ ረገድ ምንም ችግር የለውም” ሲሉ በአፅንኦት መልሰዋል። አክለውም “ሁለት፤ ሦስት ቋንቋዎች መጠቀም ሰውን ይጠቅማል እንጂ ምንም ዓይነት ጉዳት የለውም” ሲሉ አብራርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ተጨማሪ የፌደራል የሥራ ቋንቋዎች ለመጨመር እየተሰራ መሆኑን ተናግረው፤ ለዚህም ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ ይህ ሊሆን የሚችለው በስሜትና በኩርፊያ ሳይሆን በእውቀትና በተረጋጋ አኳዃን ነው ብለዋል። ስለሆነም በቅርብ ጊዜ ሌሎች ቋንቋዎችን የፌደራል የሥራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንና ጥናቱም ሲጠናቀቅ “ከኦሮምኛ በተጨማሪ ሶማልኛ እና ሌሎች ቋንቋዎች የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ቢሆኑ የምንጎዳው ነገር የለም” ሲሉ ተናግረዋል። ተጨማሪ ቋንቋዎችን የሚጠቀሙ ሀገራትን እንደ ምሳሌ በማንሳት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከዚህ ኤርትራ ቢኬድ፣ ኬኒያ ቢኬድ፣ ጅቡቲ ቢኬድ እንዲህ አይነት ነገር የተለመደ ነው” በማለት ችግር እንደማይኖረው አብራርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ስለ መደመር፣ ስለ እሬቻ፣ ሪፎርምና እና ስለ ቤተ መንግሥት እድሳት ዘርዘር ያለ
Posted in Amharic News, Funny

“ልጃችሁን ምን መሆን ትፈልጋለህ ብላችሁ አትጠይቁ?” ፌቨን ሰይፉ

Posted in Ethiopian News, Funny, Music, Psychology

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከትናንት ምሽት ጀምሮ የእሳት አደጋ አጋጥሞታል፡፡

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከትናንት ምሽት ጀምሮ የእሳት አደጋ አጋጥሞታል፡፡ ከፓርኩ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሳው እሳት በጨለማውና ነፋሱ እንዲሁም በአካባቢው መልክአ ምድርና ተቀጣጣይ ነገሮች መብዛት ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኖ አድሯል፡፡ወደ ስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከክልልና ፌዴራል ቡድን ተንቀሳቅሷል፡፡ የአርግንና አምባራስ አካባቢ አርሶ አደሮች፣ የፓርኩ የጥበቃ ሠራተኞችና አስጎብኝዎች እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት ቢያድርጉም መቆጣጠር አልቻሉም፡፡ ከደባርቅ ተጨማሪ ኃይል ለመሄድ በመኪና እጥረት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አልተሳካም ነበር፡፡ አብመድ ደባርቅ ከሚገኙ የፓርኩ ጽሕፈት ቤት ባለስልጣናትና ከደባርቅ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች ሌሊቱን ባገኘው መረጃ መሠረት እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ተሽከርካሪ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡Image may contain: one or more people, night and fire የአማራ ክልል የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በላይነህ አየለ ለአብመድ በስልክ እንደገለጹት እሳቱን ለመቆጣጠርና የአደጋውን መንስኤና ጉዳት ለማጣራት ከክልልና ፌዴራል የተደራጀ ቡድን ወደ አካባቢው አቅንቷል፡፡ አሁን ላይ እሳቱ ያለበትን ደረጃ ለማዎቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ የጋዜጠኞች ቡድን በቦታው እንደደረሰ ዝርዝር መረጃዎችን የምናደርስ ይሆል፡፡  (አብመድ)
Posted in Amharic News, Funny

“ማብረርን ወደላቀ ደረጃ የማድረስ ህልም ነበረው”የረዳት አብራሪው አህመድ ኑር ጓደኛ

BBC Amharic በቅርቡ የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ረዳት አብራሪ የነበረው አህመድ ኑር ፓይለት ከመሆኑ በፊት በልደታ ህንፃ ኮሌጅ በአርክቴክቸር የትምህርት ክፍለ ዘርፍ እንደተመረቀ የሚናገረው በተቋሙ ሲማር በነበረበት ወቅት የዩኒቨርስቲ ጓደኛው ፈክሩዲን ጀማል ይናገራል። ከጓደኝነት በተጨማሪ በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ለሶስት አመታት ያህል በአንድ ዶርም ውስጥ አድረዋል። አህመድ ኑርን ለመግለፅ ቃላት ያጠረው ፈክሩዲን “አህመድ ኑርን ለመግለፅ ይከብዳል። በጣም የተረጋጋ ሰው ነበር። ምንም ነገር ሲያደርግ በጣም ተረጋግቶ ነው። ትዕግስተኛ ነው” ይላል። ፈክሩዲን እንደሚናገረው የአርክቴክቸር ትምህርት ፈታኝ ቢሆንም “አህመድ ኑር በተረጋጋ መንፈስ ነገሮችን ስለሚያከናውን እንደፈተነው መገመት ይከብዳል።” ይላል። ለጓደኞቹ ፈጥኖ ደራሽ ነበር የሚለው ከሰባት አመት በላይ ጓደኛው ፈክሩዲን “ማብረርን እንደ ጥናት ሳይሆን ወደላቀ ደረጃ የማድረስም ህልም ነበረው” ብሏል። አብዛኛውን ጊዜም ስለበረራ ሲያስረዳቸው በአይነ ህሊናቸው እንዲታያቸው አድርጎ በጥልቀት እንደሚተነትንም ያስታውሳል። “በሕይወቱ አቋራጭ ነገር ሲጠቀም አይቼው አላውቅም” ሁልጊዜም በአንድ ጉዳይ ላይ የጠለቀ እውቀት እንዲኖረው ስለሚፈልግም ጊዜውን እንደሚሰጥ ይናገራል። ልደታ በነበረበትም ወቅት ለማብረር ከፍተኛ ፍቅር እንደነበረው የሚናገረው ፈክሩዲን በህይወቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች አትኩሮት ሰጥቶም እንደሚከታተል ይገልፃል። በማያጠናበት ወቅት እግር ኳስ ይጫወት የነበረ ሲሆን፤ ለቀድሞ የአማርኛ ሙዚቃዎች ለየት ያለ ፍቅር ነበረው። ” እኩል እድሜ ላይ ብንሆንም እኛ የማናውቀውን ሙዚቃ ይዘፍንና ይሄ ልጅ ግን መቸ ነው የተወለደው ያስብለን ነበር።” በማለት ፈክሩዲን ይናገራል። ድሬዳዋ ተወልዶ ያደገው የ26 አመቱ አህመድረ ኑር ወደ አዲስ አበባ የመጣውም በዩኒቨርስቲ ድልደላ በምህንድስና የትምህርት ዘርፍ አዲስ
Posted in Amharic News, Funny

ተንኳሹ ዝንጀሮ – ቪዲዮ

$bp("Brid_15099_1", {"id":"12272","video":"228884","width":"550","height":"309"}); ለፈገግታ ያህል
Posted in Funny
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook