Blog Archives

ለአዲስ አበባ ሞተር ሳይክሎች የመቆጣጠሪያ ዘመናዊ የጂፒኤስ ሥርዓት ተገጥሞላቸው ወደ ስራ ሊገቡ ነው ተባለ

የታገዱት የአዲስ አበባ ሞተር ሳይክሎች የመቆጣጠሪያ ዘመናዊ የጂፒኤስ ሥርዓት ተገጥሞላቸው ወደ ስራ ሊገቡ ነው ተባለ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የታገዱት የአዲስ አበባ ሞተር ሳይክሎች የመቆጣጠሪያ ዘመናዊ የጂፒኤስ ሥርዓት ተገጥሞላቸው ወደ ስራ ሊገቡ ነው ። በከተማዋ ውስጥ ሞተር ሳይክሎች እንዳይንቀሳቀሱ የተጣለውን እገዳን በተመለከተም የተጠየቁት ም/ከንቲባው እዚህ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት በየአንዳንዱ ቀን አዲስ አበባ ውስጥ በሞተር ሳይክሎች አማካይነት ዝርፊያ ይፈጸም ነበር ብለው፤ በዚህ ምክንያትም ሞተር ሳይክሎች ላይ በተጠና መልኩ ክልከላ መጣሉን ይናገራሉ። እስካሁን የነበረው ሁኔታ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡትን ሞተር ሳይክሎች ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ነገሮች እንዳልነበሩና በዚህም ምክንያት ዝርፊያና የደህንነት ስጋት እንደተፈጠረ በመግለጽ “በቀጣይ ሞተር ሳይክሎቹ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችል ሕግና ደንብ ይዘጋጃል” ብለዋል። የከተማው አስተዳደር ሞተር ሳይክሎች ላይ እገዳውን ከጣለበት ዕለት ጀምሮ “በሚያስደንቅ ሁኔታ በከተማዋ ውስጥ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ያጋጥሙ የነበሩ የጸጥታ ችግሮች ከግማሽ በላይ በሆነ ሁኔታ ለመቀነስ አስችሏል” ሲሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል። ስለሞተር ሳይክሎቹ ዝርዝር መረጃ እንኳን እንደሌለ እገዳውም ያሉት ችግሮች እስኪፈቱ ድረስ እንደሚቆይ የሚናገሩት ምክትል ከንቲባው አስፈላጊው ህጋዊ የቁጥጥር ሥርዓት ከተዘረጋ በኋላ ግን ወደ ሥራቸው እንደሚመለሱ ገልጸዋል። ም/ከንቲባው አክለውም ሞተር ሳይክሎቹን የመቆጣጠሪያ ዘመናዊ የጂፒኤስ ሥርዓት እንደሚዘረጋ አመልክተው፤ ከሚዘረጋው ሥርዓትና ደንብ ውጪ ማንም በከተማዋ ውስጥ እንዲሰራ አይፈቀድለትም ብለዋል።
Tagged with: ,
Posted in Ethiopian News

የ”ብሄሮች” ጠላት ማን ነው? ሞጋሳ ወይስ ምኒሊክ? የገዳ ስርአት እርግጥ የዲሞክራሲና የእኩልነት ስርአት ነበርን?

Posted in Ethiopian News

“ትላንት የወደደ ያመነ ሰው ሲበዛ በቃኝ አይልም ወይ??” መስከረም አበራ

Posted in Ethiopian News

ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ የመንግስት ፈላስፋ ወይስ የMorality ጠበቃ? ( በያሬድ ጥበቡ)

Posted in Ethiopian News

በእስር ለመቆየታቸው የፌድራል መንግስቱ እጅ አለበት ብለን እናምናለን ሲሉ እነ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ ተናገሩ።

Posted in Ethiopian News

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንግስነት (ሸገር ትዝታ ዘአራዳ)

Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአገሪቱ ችግሮች መነሻ በተወሰነ ደረጃ አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ-መንግስት መሆኑን ኢዜማ አስታወቀ፡፡

የአገሪቱ ችግሮች መነሻ አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ-መንግስት ነው፦ ኢዜማ የአገሪቱ ችግሮች መነሻ በተወሰነ ደረጃ አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ-መንግስት መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ አስታወቀ፡፡ ችግሮቹ በዘላቂነት የሚፈቱት በህገ-መንግስቱ ውስጥ አሉ የሚባሉ ችግሮች ሲሻሻሉ እንደሆነ ፓርቲው እንደሚያምን ነው የገለፀው፡፡ ፓርቲው ዛሬ በአገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫው በደቡብ ክልል እየተነሳ ባለው የክልልነት ጥያቄ እንዲሁም በሰላምና መረጋጋት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ከቀናት በፊት ከሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በዞኑ በሚኖሩ የተለያዮ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ እጅግ አሳዛኝ ጉዳት መድረሱን የገለፀው ፓርቲው በዚህም የሰው ህይወት መጥፋቱን፣ በርካታ ንብረት መውደሙን እና ቤተ-እምነቶች መቃጠላቸውን ተናግሯል፡፡ ድርጊቱን ያወገዘው የፓርቲው መግለጫ ክስተቱ እንደአገር አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሳችንን የሚጠቁም ነው ብሏል፡፡ መንግስት በሲዳማ ዞን የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ አፋጣኝ ፖለቲካዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ አለበት ያለው ኢዜማ በጥፋቱ ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ አካላትን በማጣራት ለህግ ማቅረብና ለህዝብ ማሳወቅ እንደሚገባው አሳስቧል፡፡ ለተጎጂዎችም ተገቢው ካሳ እንዲከፈል የጠየቀው ፓርቲው በቀጣይ በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ መንግስት የፀጥታ መዋቅሩን በማጠናከር ዜጎችን ከጥቃት የመከላከል ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ፓርቲው በሲዳማ ዞን በተለያዮ ቦታዎች በዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ መንግስት ለሰላምና መረጋጋት ቅድሚያ እንዲሰጥ ከዚያም ለቀጣዮ አገራዊ ምርጫ አስፈላጊውን መደላድል እንዲፈጥር ጠይቋል፡፡
Posted in Ethiopian News

መፈንቅለ ስልጣን ተደረገብኝ ሲሉ የነበረው የድሬዳዋ ከንቲባ ከስልጣን ተነሱ

የድሬዳዋ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ከ3 ወራት በፊት በምክትል ከንቲባነት ተሾመው የነበሩትን አቶ መሀዲ ጌሪን በማንሳት አዲስ ምክትል ከንቲባ ከተማይቱን እንዲያስተዳድሩ ሰይሟል። አዲሱ ተሿሚ አቶ አህመድ ቡህ ናቸው።የከተማው መስተዳደር አፈጉባዬ የነበሩትን አብደላ አሕመድ አውርዶ በ ፋጡማ ሙስጠፋ ተክቷል ። ባለፈው ሳምንት የድሬዳዋ ከንቲባና አፈጉባዬ በስልጣናችን ላይ መፈንቅለ መንግስት ተካሄደብን ሲሉ እንደነበር ይታወሳል። Image Image DireDawa city admin Council replaces D.Mayor Mehadi Gire (1st pic, right), by Ahmed Buh (2nd pic). It also replaced its speaker Abdella Ahmed by Fetum Mustafa (Mss). Mehadi recently claimed “a failed coup attempt” against him. But the Council said both have “resigned”
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዲስ አበባ የመወዛገቢያ ርዕስ ሳትሆን ኢትዮጵያዊያን በጋራ የምንኖርባትና የምናሳድጋት ልትሆን ይገባል – ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ

BBC Amharic : አዲስ አበባ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የምትሆን ከተማ በመሆኗ ለውዝግብና አለመግባባት ምክንያት መሆን እንደሌለባትና የተለያዩ ሃሳቦችን በማቅረብ ልናሳድጋት እንደሚገባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለቢቢሲ ተናገሩ። አዲስ አበባ የሃገሪቱ እምብርት መሆኗን የሚጠቅሱት ምክትል ከንቲባው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫም መሆኗን ጠቅሰው “አዲስ አበባ ሁሉንም የምታቅፍ የሁሉም ከተማ ናት። ከተማዋ የመወዛገቢያ ርዕስ ሳትሆን ኢትዮጵያዊያን በጋራ የምንኖርባትና የምናሳድጋት ልትሆን ይገባል” ብለዋል። አስተዳደራቸው የከተማዋን ነዋሪ ችግሮች ለመቅረፍ የተለያዩ እቅዶች እንዳሉት የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፤ በአዲስ አበባ ውሰጥ ያለው የቤት ችግር በከተማዋ ካሉ ዋነኛ ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑን ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለችግረኞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማዋ ነዋሪዎችን ችግር ለመቅረፍ በቤቶች ልማት በኩል ትልቅ የሚባል ተግባር አከናውኗል የሚሉት ምክትል ከንቲባው፤ የቤቶች ልማት ፕሮጀክትን በተመለከተ እስካሁን የነበረውን አሰራር በመለወጥ፣ በመንግሥት ሲከናወን የነበረውን የቤቶች ግንባታ የሪል እስቴት አልሚዎች እንዲገቡበት ይደረጋል ብለዋል። ለዚህም “የከተማዋ አስተዳደር ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማዘጋጀት የተለያዩ የገንዘብ ተቋማት እንዲሳተፉና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሥርዓት ተግባራዊ ያደርጋል” ብለዋል። በመጪው አዲስ ዓመትም በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለመንግሥት ሰራተኞች በርካታ ቁጥር ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል ያሉት ከንቲባው፤ ግንባታው የሚካሄደው እንደከዚህ ቀደሙ በመንግሥት ሳይሆን በግል ተቋማት ይሆንና መንግሥት የመቆጣጠርና የማስተባበር ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተናግረዋል። በከተማዋ ውስጥ የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ አሳሳቢ ከሆኑት ነገሮች መካከል የሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዕፅ ዝውውር የተጠረጠረችው ናዝራዊት ለመጀመሪያ ጊዜ ቻይና ፍርድ ቤት ቀረበች

BBC Amharic : እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ ቻይና ጉዋንዡ እስር ቤት የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ናዝራዊት አበራ ከወር በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረቧንና የመጨረሻውን ፍርድ እየተጠባበቁ እንደሆነ እህቷ ቤተልሔም አበራ ለቢቢሲ ገለፁ። ናዝራዊት አበራ በቻይና በእፅ ዝውውር ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር መዋሏ ከተሰማ ስድስት ወራቶች አልፈዋል። አንድ ሰው እፅ ሲያዘዋውር ከተገኘ የሞት ፍርድ እንዲበየንበት የሚያዘው የቻይና ህግ በናዝራዊት ላይ ተግባራዊ ይሆናል በሚል በቤተሰቦቿ፣ በቅርብ ዘመዶቿ እንዲሁም በበርካታ ሰዎች ዘንድ ጋትን አሳድሯል። ጉዳዩንም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነም መገለፁ ይታወሳል። በቻይና ጉዋንዡ እስር ቤት የምትገኘው ናዝራዊት ባለፈው ወር ሰኔ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርባለች። 5.2 ኪሎግራም የሚመዝነውን በሻምፖ መልክ የተያዘጋጀ ኮኬይን የተሰኘ እፅ ማን እንደሰጣትና እንዴት ልትያዝ እንደቻለች ለአገሪቱ ፍርድ ቤት አስረድታለች። የቻይና መንግሥት ያቆመላት ጠበቃም ናዝራዊት ከአገር ወጥታ እንደማታውቅ የሚያሳይ የጉዞ ታሪክ ማስረጃ፣ ከወንጀል ነፃ መሆኗን፣ የትምህርቷንና የሥራዋን ሁኔታ -ኢንጂነር እንደሆነች የሚያመለክት ማስረጃ መቅረቡን እህቷ ቤተልሔም አበራ ገልፀውልናል። እህቷ ማስረጃዎቹን የቀረበባትን ክስ ለመከላከል የላኩት መሆኑን በመጥቀስ “የቻይና ሕግ ከባድ ሳይሆን አይቀርም፤ እንዳሰብነው እየሄደ አይደለም ግን ተስፋ አንቆርጥም” ብለዋል። በሌላ በኩል አቃቤ ሕግ ሆነ ብላ ድርጊቱን እንደፈፀመችና የተማረች ሆና ሳለ በስህተት ይህን መቀበል አልነበረባትም ሲል ክሱን ማሰማቱን ነግረውናል። “በድጋሚ መቼ ፍርድ ቤት እንደምትቀርብ ቁርጥ ያለ ቀን አይታወቅም” የሚሉት እህቷ ቤተልሔም በቻይና
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ሐገረ-መንግሥት ግንባታና ብሄራዊ መግባባት በኢትዮጵያ” – ውይይት

VOA Amharic “ሐገረ-መንግሥት ግንባታና ብሄራዊ መግባባት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ውይይት ድሬ ዳዋ ላይ ተካሂዷል። ድሬዳዋ — በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሕፈት ቤት በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ምሁራን የውይይት መነሻ ሃሣቦችና ፅሁፎችን አቅርበዋል። ተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሲዳማ ዞን በተከሰተው ግጭት ከ400 በላይ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

DW : በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሲዳማ ዞን በተከሰተው ግጭት የተፈናቀሉ ከ400 በላይ ነዋሪዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ቦሬ ከተማ መሰደዳቸውን ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ባለስልጣናት ገለጹ፡፡ በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ ከሚገኙት ጭሮ፣ ዶላን፣ ጨልቤ እና ጋኛሬ ከተባሉት የገጠር ቀበሌዎች ተፈናቅለው ወደ ከተማው የገቡት እነዚሁ ተፈናቃዮች በአንድ ቤተ እምነት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ የቤተ እምነቱ አስተዳዳሪዎች ገልጸዋል፡፡ በመንደራቸው የተፈፀመ ጥቃት ብሔርን መሠረት ያደረገ ነው የሚሉት ተፈናቃዮቹ ቤቶቻቸው እንደተቃጠሉባቸው እና ንብረታቸውም እንደተዘረፈ ተናግረዋል። ጥቃት ፈጻሚዎቹም በሌላ አካላት የተላኩ እና የተደራጁ ወጣቶች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። በተፈጸመባቸው ጥቃት በርካታ ነዋሪዎች ለሞት መዳረጋቸውን የገለጹት ተፈናቃዮቹ መውጫ መንገድ አጥተው የቀሩ ብዙዎች መሆናቸውን እንደተናገሩ የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየው ዘግቧል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግስት በሲዳማ ዞን የሟቾችን ቁጥር ለመናገር ተቆጥቧል

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የሟቾችን ቁጥር 60 ገደማ አድርሶታል DW : የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲዓን) ከሐምሌ11 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ወደ 60 ገደማ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል። የሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ደሳለኝ ሰዎች መሞታቸውን ቢያረጋግጡም አጠቃላይ የሟቾቹን ቁጥር ከመናገር ተቆጥበዋል። ሰኞ በሐዋሳ ከተማ ትልቁ ሳምንታዊ ገበያ የሚቆምበት ዕለት ነው። እስከ ዕለተ አርብ ተዘግተው የቆዩት እና ሐዋሳን ከአጎራባች ከተሞች የሚያገናኙ መንገዶች በጸጥታ ኃይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት ትብብር ተከፍተው አገልግሎት መሥጠት ጀምረዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት የሕዝብ መጓጓዣ ተሽከርካሪዎች፣ የመንግሥት እና ማኅበራዊ ተቋማት ወደ ሥራቸው ተመልሰዋል። አሮጌ ገበያ ተብሎ በሚጠራው የከተማዋ የመገበያያ ስፍራ በሥራ ላይ የሚገኙ አንድ ነጋዴ እንደሚሉት ለወትሮው ከከተማዋ አጎራባች አካባቢዎች ለንግድ ወደ ሐዋሳ ብቅ ከሚሉ ዜጎች አብዛኞቹ ቀርተዋል። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/19834AF9_2_dwdownload.mp3 ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን አስራ አንደኛው የኢትዮጵያ ክልል ሊታወጅ በሲዳማ የለውጥ አራማጆች ቀነ ቀጠሮ የተያዘበት ዕለት ነበር። በዕለቱ የደቡብ ክልልንም፣ የሲዳማ ዞንን መቀመጫነት አዳብላ በያዘችው ሐዋሳ የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሌሎች የዞኑ አካባቢዎች ተዛምቷል። ሐዋሳን ጨምሮ በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች እና ግጭቶች የሰው ሕይወት ጠፍቷል። የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ሳርሚሶ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በሐዋሳ ከተማ ብቻ አራት ሰዎች ሲሞቱ 21 ሰዎች ቆስለዋል። ከቆሰሉት ሰዎች መካከል አስራ ሁለቱ አሁን በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ያስረዱት አቶ ዝናው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ እና የሶማሌ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ – ባህር ዳር

ባህር ዳር ላይ በተካሄደ የአማራ እና የሶማሌ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ተገኝተው ተናግረዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ሐገረ-መንግሥት ግንባታና ብሄራዊ መግባባት በኢትዮጵያ” – በድሬዳዋ

“ሐገረ-መንግሥት ግንባታና ብሄራዊ መግባባት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ውይይት ድሬ ዳዋ ላይ ተካሂዷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሹመት

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሆኑ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቴሌቶን በመቀሌ ተካሄደ

በትናንትናው ዕለት በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በተዘጋጀው ቴሌቶን ገቢ ማሰባሰብያ መርኃግብር ከግማሽ ቢልዮን ብር በላይ ለትግራይ ልማት ለማበርከት ቃል ተግብቷል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሹመትና የምክር ቤቱ ውይይት

Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሲዳማ ዞን የሚገኙ ሦስት አብያተ-ክርስትያናት መቃጠላቸዉ ታወቀ

DW : በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በሀገረ ሠላም የሚገኙ ሦስት አብያተ-ክርስትያናት መቃጠላቸዉን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሲዳማ፣ የጌዶ፣ አማሮ እና ቡርጂ ሃገረ ስብከት ቢሮ አስታወቀ። በሲዳማ ሀገረ ሠላም አካባቢ የሚገኙት ዶያ ሚካኤል፣ ገሳባ-ገብረክርስቶስ እና ጭሮ አማኑኤል የተባሉት ሦስት አብያተ ክርስትያናት መቃጠላቸዉን የሃገረ ስብከቱ ምክትል ስራ አስኪያጁ መጋቢ ሐይማኖት ቀሲስ ነፃነት አክሎግ ለዶይቼ ቬለ «DW» ዛሬ ገልፀዋል። በተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ለመከላከል ምዕመናን ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸዉን የተናገሩት የሃይማኖት አባት፤ በርካታ ዲያቆናት ከአካባቢዉ ሸሽተዉ በኦሮሚያ ክልል ቤተ-ክርስትያን ተጠልለዋል ብለዋል። ከ450 በላይ የሚሆኑ የሀገረ ሰላም ተፈናቃዮች በኦሮሚያ ዞን ቦሬ ከተማ በሚገኝ ቤተክርስትያን ተጠልለዉ ይገኛሉ። ከተፈናቃዮቹ መካከል ቤተ-ክርስትያናቸዉ የተቃጠለባቸዉ ዲያቆናትም ይገኙበታል»በአሁኑ ሰዓት ግን የመረጋጋቱ ሁኔታ በመሻሻሉ፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ነገ ስፍራዉ ላይ ተገኝቶ ሁኔታዉን ለማጣራት ቀጠሮ መያዙን መረጃ ደርሶኛል ሲሉ አስረድተዋል። የሃገረ ስብከቱ ሊቀ-ጳጳስ አካባቢዉ ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የፀሎት መርሃ-ግብር እንዲደረግ አዝዘዉ ከትናንት ጀምሮ ምህላ መጀመሩን ተናግረዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሐሙስ እስከ ሰኞ በሲዳማ ምድር ምን ሆነ?

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲዓን) ከሐምሌ11 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ወደ 60 ገደማ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል። የሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ደሳለኝ ሰዎች መሞታቸውን ቢያረጋግጡም አጠቃላይ የሟቾቹን ቁጥር ከመናገር ተቆጥበዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቤተ-ክርስትያን ቃጠሎ በሀገረ ሠላም   

"በሲዳማ ሀገረ ሠላም አካባቢ የሚገኙት ዶያ ሚካኤል፣ ገሳባ ገብረክርስቶስ እና ጭሮኔ አማኑኤል የተባሉት ሦስት አብያተ ክርስትያናት ላይ ቃጠሎ ደርሷል። አብያተ ክርስትያናቱ እንዳይቃጠሉ ሲከላከሉ ከነበሩ ምዕመናን መካከልም የሞቱ ይሁንና ይህን መረጃ በእርግጠኝነት ለማጣራት ቦታዉ ላይ መሄድ ይጠበቅብናል"...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ በኤች አይቪ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ

በዓለም ላይ በኤች-አይቪ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ መከላከያ ድጋፍ በምህፃሩ «UNAIDS» ገለጸ። የኢች-አይቪ ስርጭት በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ስርጭቱ «ወረርሽኝ» ሊባል በሚችል ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሲዳማ ዞን የተፈናቀሉ ወገኖች

በሲዳማ ዞን በተከሰተው ግጭት የተፈናቀሉ ከአራት መቶ በላይ ነዋሪዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ጉጂ ዞን ቦሬ  ከተማ መግባታቸውን ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ባለስልጣናት ገለጹ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው ኢዜማ በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው

በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው ኢዜማ በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው ኢዜማ በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። ማክሰኞ ሐምሌ 16 ቀን ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው የኢዜማ ጽሕፈት ቤት በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን እንዲገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን።የሚል ማስታወቂያ በማሕበራዊ ሚዲያውዎች አሰራጭቷል። Image
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጀጎል ግንብ እየደረሰበት ባለው ጉዳት ከዓለም ቅርስነት ሊሰርዝ ይችላል ተባለ

የጀጎል ግንብ እየደረሰበት ባለው ጉዳት ከዓለም ቅርስነት ሊሰርዝ ይችላል የሚል ሥጋት ማሳደሩን የሐረሪ ክልል ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ። ካጋጠው ጉዳት እንዲያገግም እየሠራ መሆኑን የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ እዮብ አብዱላሂ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳሉት ቅርሶቹ በተፈጥሮ የሚደርስባቸውን አደጋ ለመከላከል እና ለመጠበቅ ተብሎ ዩኔስኮ በሚልከው በጀት ይጠገናሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ህገወጥ ቡድኖች በቅርሱ ዙሪያ እና ውስጥ ወረራ በማድረግ በቅርሱ ውስጥ ሊሠሩ የማይገባቸውን ግንባታ እየገነቡ ነው። ከዚህ ቀደም በጀጎል ግንብ ውስጥም ሆነ ውጭ ማንኛውም ግንባታ ሲካሄድ በአካባቢው ያለው ቀበሌ ለባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ደብዳቤ ጽፎ ይሁንታ ሲያገኝ ግንባታ ይካሄድ እንደነበር አቶ እዮብ አስታውሰው አሁን ግን ወረራ ሊባል በሚችል መልኩ ቤቶች መገንባታቸውን ገልፀዋል፡፡ እንደ ቢሮ ኃላፊው ገለፃ ወረራው በጣም በተደራጁ ሕገ ወጥ በሆኑ ሃይሎች የተከናወነ ሲሆን ከጀጎል ግንብ ባሻገር በዩኔስኮ የተመዘገቡ የሃይማኖት ስፈራዎች ሳይቀር በእነዚሁ የሕገ ወጥ ቡድኖች መዘረፋቸውን ጠቅሰዋል፡፡በቅርስ ውስጥ የሚገኘው እና የሐረሪ ክልል መለያ የሆኑ አገር በቀል ፍራፍሬዎች የሚተከልበት ጥብቅ ስፍራ ሳይቀር ቤቶች የተገነቡበት ሲሆን የተቀረው መሬት ደግሞ እየታራሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ እዮብ እንደሚሉት ቅርሱን ለማዳን በፌዴራል የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ተደጋጋሚ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱም ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ ጽፏ ል። ሆኖም ግን የተጻፈውን ደብዳቤ ተከትሎ ተግባራዊ የሚያደርግ አካል አለመገኘቱን ገልፀዋል፡ ፡ ጀጎል ማለት የሐረሪ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን ቅርስ ነው ያሉት አቶ እዮብ ስለዚህም ማንኛውም
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሱዳን አማጺ መሪ አዲስ አበባ ላይ እየተደረገ ካለ ድርድር ተይዘው ሊባረሩ እንደነበር ተነገረ

የሱዳን አማጺ መሪ አዲስ አበባ ላይ እየተደረገ ካለ ድርድር ተይዘው ሊባረሩ እንደነበር ተነገረ። በዳርፉር ዋነኛው አማጺ ቡድን የሆነው የፍትህና እኩልነት እንቅስቃሴ መሪ የሆኑት ጂብሪል ኢብራሂም በአፍሪካ ሕብረት ጣልቃ ገብነት ለሱዳን መንግሥት ተላልፎ ከመሰጠት ድነዋል ተብሏል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት በእጩነት የቀረቡት የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ሹመት ፀደቀ

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ። የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል። ምክር ቤቱ በጉባኤው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት በእጩነት የቀረቡትን የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ሹመት አፅድቋል። አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር የአማራ ክልል ህዝቦች ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በአብሮነትና መተሳሰብ መንፈስና ለዘመናት ሲኖሩ የቆዩ መሆኑን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ስንከተለው በነበረው የተዛባ የፖለቲካ አስተምህሮ ምክንያት ዛሬ ላይ አንድነታችንና ሰላማችን አደጋ ተደቅኖበታል ብለዋል። ይህንን ለሁለት አስርት አመታት ሲሰበክ የነበረውን የተዛባ የፖለቲካ አስተምህሮ ለማስተካከል እና በአማራ ክልል ህዝብ ላይ የሚሰራን ማንኛውንም የፖለቲካ ሴራ ለማስወገድ ከክልሉ ህዝብ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ በርካታ ወቅታዊ ተግዳሮቶች መኖራቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ እነዚህን ፈተናዎች በብቃት ለመወጣት ቁርጠኛ አቋም ያላቸው መሆኑንም አስገንዝበዋል። ለዚህም በክልሉ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለማስወገድ የፀጥታ ሃይሉን አቅም የማሳደግና የመገንባት ስራ ይሰራል ነው ያሉት። የአማራ ክልል በርካታ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት ነው ያሉት አቶ ተመስገን፥ ክልሉን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በተጨማሪም የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ለግጭት ምክንያት ሳይሆኑ በሕግ አግባብ እንዲመለሱ ለማድረግ የሚሰራ መሆኑን ነው የገለጹት። ከዚህ ባለፈም በክልሉ ያለውን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል፣ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና አዳዲስ የቱሪስት ማስህቦችን ለማስተዋወቅ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶሮ ማነቂያ እና ትዝታዎቿ በፒያሳ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የላስቲክ ቤታችን ፈርሶ ዝናብ እየመታን ነው – በዝናብ የተደረገ ቆይታ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

መንግስት በደነገጠ ቁጥር ሚዲያውን ዝም በሉ አይበል – አቶ ገለታ ዘለቀ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በጎፋ በአከባቢው አመራሮችና በሕዝቡ መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ

ኢትዮ 360 – በጎፋ ዞን የጥምቀተ ባህርና የመስቀል ደመራ በአል የሚከበርበትን ቦታ የአካባቢው አመራሮች እንወስዳለን ማለታቸውን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ (ኢትዮ 360 ) በጎፋ ዞን መሎ ወረዳ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የጥምቀተ ባህርና የመስቀል ደመራ በአል የሚያከብሩበትን ቦታ የወረዳው አስተዳደር በሃይል ለመውሰድ ካደረገው ሙከራ ጋር ተያይዞ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ። የለሃ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋ በመሆን ከ1962 ጀምሮ የጥምቀተ ባህርንና የደመራ በአልን ሲያከብር የነበረው በዚህ ቦታ ላይ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ይህን ያህል አመት ቤተክርስቲያኒቱ ስትገለገልበት የነበረውን ቦታ የወረዳው አስተዳደር ድንገት እወስዳለሁ ማለቱ ከእምነቱ ተከታዮች ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል ብለዋል ለኢትዮ 360። አመራሩ ታቦተ ህጉ የሚያርፍበትን ድንኳን በማፍረስ ንዋየ ቅድሳቱን ለመውሰድ ያደረገው ሙከራ ከምዕመናኑ ጋ ግጭት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል ይላሉ። በዚህ ግብግብ መሃልም የቤተክርስቲያኒቱን ንዋየ ቅድሳት ለመስረቅ የተደረገውን ሙከራም ሕዝበ ክርስቲያኑ ለመከላከል ባደረገ ሙከራ ወደ 23 ሰዎች መታሰራቸው ታውቋል።-በግጭቱ የተጎዳ ሰው ስለመኖሩ ግን የታወቀ ነገር የለም። የፌደራል ፖሊስና የወረዳው የጸጥታ ሃይል ህዝበ ክርስትያኑን የተነሳውን ግጭት ለማስቆም ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ወደ ህዝቡ ሲተኩስ እንደነበርም የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። በሐምሌ 11/2011 በወረዳው አስተዳደር ቦታው በግዴታ ተወስዷል የሚሉት ነዋሪዎች ይህንን ለመከላከል የሞከሩ ግለሰቦችን አፍነው ወስደው እስር ቤት አጉረዋቸዋል ብለዋል። በቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ አባቶች ላይ ማንገላታትና ድብደባ መፈጸሙን ነው ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከልም 13ቱ እዛው መለኮዛ ወረዳ እንዲታሰሩ ሲደረግ ቀሪዎቹ 10ሩ ደግሞ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሲዳማ ዞን በነበረው አለመረጋጋት ከተቃጠሉ ንብረቶች መካከል ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል።

በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ቀናት በነበረው አለመረጋጋት ከተቃጠሉ ንብረቶች መካከል ተሽከርካሪዎች እንደሚገኙበት የደቡብ ክልል ቴሌቪዥን አሳይቷል። Image Image Image Image
Posted in Ethiopian News

ሁለት ዜግነት ያላቸው ሰዎች በፖለቲካችን ውስጥ ገብተው ሲጫወቱ እናዝናለን ፤ (ሊያዳምጡት የሚገባ )

ሊያዳምጡት የሚገባ ፤ ሁለት ዜግነት ያላቸው ሰዎች በፖለቲካችን ውስጥ ገብተው ሲጫወቱ እናዝናለን ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዘር አወቃቀሩና ፖለቲካው ከቀጠለ አገር ትፈርሳለች፣ ደም ይፈሳል #ግርማካሳ

የክልሉ ባለስልጣናት ከተናገሩትና እንደ ቢቢሲ፣ ሮዮተርስ ያሉ የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ፣ እንዲሁም እንደ ኢሳት ያሉ ሜዲያዎች ከዘገቡት ለመረዳት እንደሚቻለው፣ ኢጄቶ የተባለው ቡድን፣ ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም፣ በጀመረውና ባልተሳካለት የሲዳማ ክልልን በጉልበት የማወጅ እንቅስቃሴ፣ ከሃያ በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአዋሳ አንድ ወጣት ግንባሩ ላይ በጥይት ተመቶ ወዲያው እንደሞተ፣ ሶስት ቆስለው የሕክምና እርዳታ ቢደረግላቸው መትረፍ እንዳልቻሉ ኢሳት ዘግቧል። ቢቢሲ በወንዶ ገነት ሶስት ፣ ሮይተርስ ደግሞ በዋተራ ካሳ አስራ ሶስት ኢትዮጵያውይን መገደላቸውን ዘግበዋል። እነዚህ በግልጽ የታወቁና የተረጋገጡ ሲሆኑ የሟቾች ቁጥር ከመቶ ፣ የቆሰሉ ደግሞ ከአራት መቶ በላይ እንደሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሃገረ ሰላም 26፣ በወንዶገነት 8፣ በዳሌ 5፣ በላኮ 6፣ በአገታ ጉኮ 5፣ በአፋራራ 2፣ በአለታ 2 ዜጎች መገደላቸውን ሲዳማ ፔጅ የተሰኘው ገጽ አስፍሯል። የተወሰኑት ሕይወታቸው ያለፈው ከታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ሲሆን፣ ኤጄቶዎች በግፍ የገደሉዋቸው የሌሎች ማህበረሰባት አባላትም ቁጥር ብዙ ነውና በንዴትና በበቀል፣ በጥላቻ፣ ሲዳማ ባልሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የደረሰውም ዘር ተኮር ጥቃት ጥቃት በጣም አስከፊ ነበር። ለምሳሌ በሃገረ ሰላም አቶ የንዬ የሚባሉ ግለሰብ በኤጀቶዎች በተፈፀመባቸው ድብደባ ተጎድተው ጤና ጣቢያ ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ በነጋታው፣ ልጃቸው ሊጠይቃቸው ሄዶ ሳለ፣ አጄቶዎች በድንገት ጠያቂ መስለው፣ ጤና ጣቢያ ውስጥ ገብተው አባትና ልጅን በቀርቀሃ ዱላ ቀጥቅጠው መግደላቸውን ከስፍራው የደረሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በድንጋይ ተወግረው የሞቱም ብዙ ናቸው። በዜጎች ሕይወት ላይ ከደረሰው አሳዛኝ ጥፋት በተጨማሪ በርካታ ሱቆች፣
Posted in Ethiopian News

ሕገ-መንግሥቱ በምክክር ስላልመጣ ችግር አምጥቶአል። DW ዉይይት

ዉይይት፤ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄና ተግዳሮቶቹ DW – «በሲዳማ እስካሁን አስር ብሔር ብሔረሰቦች የክልል ጥያቄን አቅርበዋል። ሕገ-መንግሥት ፈቀደ ማለት፤ ሕገ-መንግሥትን መሠረት አድርጎ የሚያፈርስ ኃይል መኖር የለበትም። መንግሥት ይሄን ካላደረገ ክልል አዉጃለሁ ማለት ከሕግ አኳያ ጥያቄ ዉስጥ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም። ለተከሰተዉ አደጋ በሲዳማ ሕዝብ ይቅርታን እንጠይቃለን» ተወያዮች የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ፤ ማወዛገቡ ቀጥሎአል። የዞኑ ምክር ቤት ከአንድ ዓመት በፊት ያፀደቀዉ ክልል የመሆን ጥያቄ ላይ ለመወሰን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢያቀርብም ጥያቄዉ ምላሽ ባለማግኘቱ የሲዳማ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ አቀንቃኞች ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ሲዳማን አስረኛ ክልላዊ መንግስት ስንል እናዉጃለን ሲሉ ዝተዉ ነበር። የክልሉ ገዥ ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ባወጣዉ መግለጫ ግን የሁሉንም ህዝቦች ተጠቃሚ ያረጋገጠ ውሳኔ ማስተላለፉን ገልፆ ነበር። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ጥያቄዉ የደረሰዉ ህዳር 12 ቀን 2011 መሆኑን በማሳወቅ በቀጣዩቹ 5 ወራት ህዝበ ውሳኔ ለማከናወን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታዉቋል። የቦርዱ መልስ የሲዳማ ልሒቃንን አቋም ከደኢሕዴን መግለጫ ይልቅ ያለዘበ መስሎአል ተብሎአል። ቀደም ሲል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለፓርላማ የመንግሥታቸውን የአፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የክልል እንሁን ጥያቄ ጥናት እየተደረገ ነዉ፣ ጠያቂ ብሔር ብሔረሰቦች በትዕግሥት ሕጉን ተከትለው ማቅረብ እንዳለባቸው ማሳሰባቸዉ ይታወሳል። ኤጄቶዎች በበኩላቸዉ ደኢህዴንም ይሁን ምርጫ ቦርድን አናምንም የሲዳማ ክልልነት ይታወጅልን ሲሉ መጠየቃቸዉ ተሰምቶአል። በሲዳማ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን ) መላው የሲዳማ ብሔር እንዲረጋጋ ጠይቆም ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ ክልል 14 ሰዎች ሲገደሉ መመልከታቸውን የዓይን እማኞች ገለጹ

DW : በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ሶስት አካባቢዎች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 34 መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ተቃዋሚው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፓርቲ ገለጹ። አንድ የዓይን እማኝ በሁላ ወረዳ ሀገረ ሰላም ከተማ 14 ሰዎች ሲገደሉ መመልከታቸውን ተናግረዋል። ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሁላ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ከትላንት በስቲያ አርብ ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ወደ ፌደራል ፖሊሶች የሄዱ የከተማይቱ ነዋሪዎች ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። በጥይት የተመቱት አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን የተናገሩት የዓይን እማኙ ወዲያውኑ ወደ ሁላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢወሰዱም አስራ አራቱ ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል። “ከትላንት ወዲያ እዚህ ሆስፒታል አስገብተው ያወጧቸውን ወደ 14 ሰዎች ነው ያየሁት። ያው እነርሱ የሞቱት በፌደራል ፖሊስ ነው። ግጭት አልነበረም። ህዝቡ ለመጠየቅ ወደ እነርሱ ሲሄድ ወደ ህዝቡ ተኮሱ። በዚያ ሰዓት በመትረየስ ሲመቱ አስሩ በአንድ ጊዜ ወደቀ። ከዚያም [ሌሎችም] ወደቁ። አንዳንዶቹ ቆሰሉ። ወደ 14 የሆኑት ሞቱ” ብለዋል የዓይን እማኙ። የፌደራል ፖሊስ አባላት ሐሙስ ምሽት ወደ ሀገረሰላም መግባታቸውን የሚናገሩት ነዋሪው በነጋታው አንድ ወጣት ልጅ መገደሉን ተከትሎ ነዋሪዎች ለጥያቄ መሄዳቸውን ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። በከተማይቱ ፖሊስ ጣቢያ ሰፍረው የነበሩት ፖሊሶች ነዋሪውን ሲመለከቱ መተኮሳቸውን ገልጸዋል። “በዚህ የሆኑ ልጆች ሞተው ʻእኛ ሰላማዊ ነን። የጠየቅነው ጥያቄ አልተመለሰም። እኛ የፈለግነው ክልሉ ባለፈው የተጠየቀው እርሱ አልተመለሰም። እኛ ውጊያ አልፈልግንም። እናንተ በእኛ ላይ ለምንድነው የምትተኩሱትʼ እያሉ ለመጠየቅ ሲሄዱ ነው። ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ነበር። ባጃጆች የሚቆሙበት አለ። እነርሱም የቆሙበት እዚያ ነበረ። እዚያ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መሪን የምናበላሸው እኛ ነን ። – ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

$bp("Brid_132683_1", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2019/07/dawit-weldegiorgis.mp4", name: "መሪን የምናበላሸው እኛ ነን ። – ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2019/07/Dawit-weldegiorgis.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ቴዲ አፍሮና ደራርቱ ቱሉ በዲሲ ተሸለሙ

Image በታላቁ የ አፍሪካውያን ሩጫ በዲሲ አዘጋጅ የሆነው ኮሚቴ ቴዲ አፍሮንና ደራርቱ ቱሉን መሸለሙን ከዋሽንግቶን ዲሲ ተሰማ። Image   አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከኦሎምፒክ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ከአፍሪካ ቀደምት ተብላ የተሸለመች ሲሆን አትሌት ደራርቱ በተወዳደረችባቸው ሩጫዎች ሰላሳ አምስት ወርቅ አስራ ሁለት ብርና አስራ አምስት የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ይህ ደግሞ አትሌት ደራርቱን ከ አፍሪካ ብቸኛና የመጀመሪያዋ የሜዷሊያዎች አሸናፊ አድርጓታል ። ኮሚቴው ለዚህ ላበረከተችው አስታውጾ ውቅናና ሽልማት ሰጥቷታል። Image ሌላኛው ተሸላሚ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ምርጥ የ አፍሪካ ሙዚቀኛና ወጣቶችን ለበጎ ምግባር በሙዚቃው መልእክት በመቅረጽ እንዲሁም ለ አፍሪካውያን ያደረገው በጎ ተግባርና የተሳካ እንቅስቃሴ እውቅናና ሽልማት ተሰጥቶታል። Image
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮችና በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ አሳሳቢ ውጥረት ውስጥ ገብታለች።- የኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን

ኢዜአ – በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የዜጎችን ደህንነት እና ሰላም ለማስጠበቅ የህግን የበላይነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ጉዳይ በመሆኑ መንግስት፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፡ የሲቪክ ማህበራት እና መላው ህዝብ በጽናትና በጋራ እንዲቆሙ የኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዛሬ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ዛሬ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮችና በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ አሳሳቢ ውጥረት ውስጥ ገብታለች። እነዚህን ችግሮችና ግጭቶች በአፋጣኝ ለማስወገድ፣ የዜጎች ደህንነትና ሰላም ለማስጠበቅ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባር ነው። ለዚህም መላው ህዝብ፣ መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ፀንተው በጋራ ሊቆሙ ይገባል። በአሁኑ ወቅት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የመጣውን የሰላም እጦት ለማርገብና ለህዘቦች የአርምሞ ፋታ ለመስጠት እንዲቻል መላው ህዝብ ለእርቅና ሰላም እንዲቆም ጥሪ ያቀረበው ኮሚሽኑ፤ ችግሮቹ በዘላቂነት እንዲፈቱ የእርቅና ሰላም መንፈስ በኢትዮጵያ የመስፈን አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥቶታል። ህዝቡ “በአገሪቷ ዘላቂ ሰላም ያሰፍናል” በማለት ያመነበትን ወቅታዊ የለውጥ ሂደት ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በነቂስ በመውጣት የተሰማውን ደስታና ድጋፍ የገለጸበት በርካታ አጋጣሚዎች እንደነበሩት አስታውሶ፤ በአንድ ዓመት ውስጥ ተስፋ ሰጪ የሆኑ ሁለንተናዊ ለውጦችን ለማስተዋል እድል ማግኘቱንም አመልክቷል። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥም የታዩትን የተስፋ ወጋገን የሚያጨልሙ ተግባራት መስተዋላቸውን መግለጫው ጠቁሞ፤ ለሰላም እጦት መንስኤ የሆኑትን በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በአብነት ጠቅሷል። ዛሬ የሲዳማን የክልል ጥያቄ ተከትሎ የታየው አሳዛኝ ክስተትም ሆነ በተለያዩ ጊዜያትና አካባቢዎች እየተስተዋሉ ያለው የዜጎች የእርስ በእርስ ግጭትና መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል። የሃይማኖት መሪዎች ፡ የሀገር ሽማግሌ የሆኑ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቋንቋና የጎሣ ማንነትን መሠረት አድርጎ በኢትዮጵያ የተዘረጋው የፌዴራሊዝም ሥርዓት ወደ እርስ በርስ ግጭት ያመራል፤ ሃገሪቱ እንድትበተን ያደርጋል

VOA : “ቋንቋና የጎሣ ማንነትን መሠረት አድርጎ በኢትዮጵያ የተዘረጋው የፌዴራሊዝም ሥርዓት ወደ እርስ በርስ ግጭት ያመራል፤ ሃገሪቱ እንድትበተን ያደርጋል” የሚሉ በርካቶች ናቸው። ሀገሪቱ ውስጥ “የማንነት ጥያቄ አለ” የሚሉ ወገኖች ደግሞ የፌዴራል ሥርዓቱ ማንነትን መሠረት ማድረጉን ይደግፋሉ። ሰሞኑን እንደሚዘገበው እስካሁን የቋንቋን ወይም የጎሣን ማንነት መሠረት አድርገው ያልተካለሉ ብሄረሰቦች በ “ክልል ደረጃ እንዋቀር” የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው። የሃገሪቱን አንድነት አስጠብቆ የሕዝቧን መብቶች የሚያስከብር ፌዴራል ሥርዓት ላይ እንዴት ይደረሳል? ዶ/ር አሰናቀ ከፍአለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለምቀፍ ግንኝነት ትምህርት መምህር እና ዶ/ር ኢታና ኃብቴ በኦሃዮ የኦበርሊን ኮሌጅ የአፍሪካ ታሪክ መምህር ለአድማጮቻችን ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የአማራ ወጣቶች ማህበራት መግለጫዎች አወጡ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በወንዶ ገነት በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሦስት ወጣቶች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

ቢቢሲ በወንዶ ገነት ከተማ በተነሳ ተቃውሞ ላይ በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሦስት ወጣቶች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ገለጡ። የወንዶ ገነት ከተማ ከንቲባ አቶ ዓለሙ ጉበሌ ተቃውሞው የጀመረው ትናንት ከሰዓት መሆንን ጠቅሰው፤ በተቃውሞው ላይ የተሳተፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣና ግርግሩ ያልተፈለገ አቅጣጫ ሊይዝ ሲል መከላከያ ሠራዊት ገብቷል ብለዋል። የወንዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ሌዳሞ በበኩላቸው ለግጭቱ መነሻ የሆነው በሐዋሳና በሌሎች አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎች መሆናቸውን ገልፀዋል። በከተማዋ የተቃጠለ ንብረትም ሆነ የወደመ ሀብት አለመኖሩን የተናገሩት አቶ ዳዊት፤ አስር ግለሰቦች በተቃውሞው ላይ በደረሰ ግጭት ተጎድተው በሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆኑን ጠቅሰዋል። የተጎዱት ወጣቶች ህክምና እያገኙ ያሉት በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታልና አዳሬ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ከንቲባው ናቸው። በተጨማሪም ወንዶ ገነት በንግድ እንቅስቃሴዋ የምትታወቅ ከተማ መሆኗን ጠቅሰው፤ ከተማዋን በማረጋጋት ወደነበረበት ለመመለስ ከአገር ሽማግሌዎችና ከሐይማኖት አባቶች ጋር እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል። ትናንት ተቃውሞ ከነበረባቸው የሲዳማ ዞን ወረዳዎች መካከል አንዷ የሆነችው የሀገረ ሰላም ከተማ የገቢዎች ባለሥልጣን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን፤ በከተማዋ በነበረው ተቃውሞ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ ቁጥራቸውን ይፋ ለማድረግ መረጃው በእጃቸው እንደሌለ ገልጠዋል። ትናንት ማታ 3 ሰዓት ላይ ወደ ከተማዋ የመከላከያ ሠራዊት መግባቱን ያረጋገጡት ኃላፊው፤ አሁን የተዘጉ ሱቆችን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የማስከፈት ሥራ እየሠሩ እንደሆነና የአከባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር እየተወያዩ መሆኑን አረጋግጠዋል። ከሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከሐምሌ 11 ቀን 2011
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21ደረሰ

DW በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ። የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሾዳ በሐዋሳ ከተማ በነበረው ግጭት አራት ሰዎች መሞታቸውን አስታውቀዋል። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ኔሳ ዛሬ ለDW እንደተናገሩት በሲዳማ ዞን ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በነበረ ግጭት 21 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። በሲዳማ ዞን ስር ባለው ወተረሬሳ 12 ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ በሞሮቾ ሶስት እና በሀገረሰላም ደግሞ ሁለት ሰዎች በግጭቱ ህይወታቸው እንዳለፈ አስረድተዋል። የሲዳማ ዞን በክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ በይፋ እንዲታወጅ የአካባቢው ወጣቶች እና ነዋሪዎች መጠየቃቸውን ተከትሎ ባለፈው ሐሙስ በሐዋሳ ከተማ የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሌሎች ቦታዎችም ተዛምቷል። በሐዋሳ በነበረው ግጭት አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በፅኑ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሾዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በግጭቱ የተጠረጠሩ 150 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከንቲባው ጠቁመዋል። ግጭቱን ተከትሎ የክልል እና የፌደራል አካላት ባደረጉት የማረጋጋት ስራ በሐዋሳ ከተማ እና በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን አቶ ስኳሬ መግለፃቸውን የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዘግቧል። በሐዋሳ በዛሬው ዕለት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደሚታይ እና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች ተከፍተው ስራ መጀመራቸውን ዘጋቢያችን አክሏል። የኢንተርኔት አገልግሎት እና የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ግን አሁንም ዝግ እንደሆኑ ነግሮናል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ከማንም ልዩ ጥቅም አንፈልግም፤ ለማንም ልዩ ጥቅም አንፈቅድም” – አክቲቪስት አበርቱ ቢጠና

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማስተላለፍ የወጣው መመርያ  የሕገ መንግሥቱን መርሆዎች እንደሚቃረን ተገለጸ

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማስተላለፍ የወጣው መመርያ  የሕገ መንግሥቱን መርሆዎች እንደሚቃረን ተገለጸ ታምሩ ጽጌ Sun, 07/21/2019 - 14:35
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጭነት ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው መመርያ እያወዛገበ ነው

የጭነት ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው መመርያ እያወዛገበ ነው ሻሂዳ ሁሴን Sun, 07/21/2019 - 14:22
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሲዳማ ዞን በተለያዩ ሥፍራዎች በተፈጸሙ ጥቃቶችና ዘረፋዎች ከባድ ጉዳት ደረሰ

በሲዳማ ዞን በተለያዩ ሥፍራዎች በተፈጸሙ ጥቃቶችና ዘረፋዎች ከባድ ጉዳት ደረሰ ዮናስ ዓብይ Sun, 07/21/2019 - 14:19
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፖሊስ ጋዜጠኛውን ለምን እንዳሰረውና እንደማይፈታው ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ተሰጠ

ፖሊስ ጋዜጠኛውን ለምን እንዳሰረውና እንደማይፈታው ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ተሰጠ ታምሩ ጽጌ Sun, 07/21/2019 - 14:15
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የከተማ አስተዳደሩ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ የሚወጣባቸው ፕሮጀክቶችን ለውጭ ኮንትራክተሮች ሰጠ

የከተማ አስተዳደሩ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ የሚወጣባቸው ፕሮጀክቶችን ለውጭ ኮንትራክተሮች ሰጠ ውድነህ ዘነበ Sun, 07/21/2019 - 14:07
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አስታወቀ

ኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አስታወቀ ነአምን አሸናፊ Sun, 07/21/2019 - 14:04
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሙገር ሲሚንቶ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በምርታማነቱ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረበት ገለጸ

ሙገር ሲሚንቶ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በምርታማነቱ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረበት ገለጸ ቃለየሱስ በቀለ Sun, 07/21/2019 - 13:56
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአካባቢ ተቆርቋሪዎችና በኢንዱስትሪ አቀንቃኞች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ የሶዳ አሽ ፋብሪካ ሥራ አቆመ

በአካባቢ ተቆርቋሪዎችና በኢንዱስትሪ አቀንቃኞች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ የሶዳ አሽ ፋብሪካ ሥራ አቆመ ውድነህ ዘነበ Sun, 07/21/2019 - 13:55
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለአማራ ሕዝብ መብትና ጥቅም ስብሰባ በፍራንክፈርት ከተማ

“ለአማራ ሕዝብ መብትና ጥቅም መከበር በሰላም የሚታገሉ ግለሰቦችን መግደል ማሰር ማዋከብ እና ማሳደድ መቆም አለበት” ሲሉ በጀርመን የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የአማራ ብሔር አደረጃጀቶች ጠየቁ። አደረጃጀቶቹ ዛሬ በፍራንክፈርት ከተማ በወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ ላይ ስብሰባ አካሂደዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ የምንነታረክበት ሳይሆን በጋራ ሆነን ችግሮቻችን የምንፈታበት ጊዜ ላይ መሆናችንን መገንዘብ አለብን – አቶ ሙስጠፌ ኡመር

” ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ የምንነታረክበት ሳይሆን በጋራ ሆነን ችግሮቻችን የምንፈታበት ጊዜ ላይ መሆናችንን መገንዘብ አለብን።” አቶ ሙስጦፋ ሙሀመድ ዑመር – የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ፀደንያ ገብረማርቆስ እና ሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች ስለሜሪ ጆይ የተናገሩት

Ethiopia: Tsedenia Gebremarkos and other celebrities discuss Mary Joy Foundation -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For inquiry or additional...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በፖለቲካ ታማኝነት ተይዘው ውዥንብር የሚነዙ የመገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ – ሸገር

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

‘ታዛቢ ያጣው’ የደቡብ ወሎ ሎጎ ሐይቅ

'ታዛቢ ያጣው' የደቡብ ወሎ ሎጎ ሐይቅ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የታሰሩ ግለሰቦች በምግብ እጥረትና አያያዝ ጉድለት እየታመሙ መሆናቸውን ገልፁ፡፡

በሰንቀሌ ፖሊስ ማሰልጠኛ የሚገኙ አንዳንድ የታሰሩ ግለሰቦች በምግብ እጥረትና አያያዝ ጉድለት እየታመሙ መሆናቸውን ገልፁ፡፡መንግሥት በቶሎ ይልቀቀን እስኪለቀንም አያያዛችንን ያሻሽልልን ሲሉ አመልክተዋል፡፡ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አባላቶቹ መታሰራቸውንና ስለ ሰብዓዊ አያያዛቸው ለማወቅ መቸገሩን አስታውቋል፡፡የኦሮሚያ ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የእስረኞቹ ሰብዓዊ አያያዝ ላይ ስለሚነሳው ቅሬታ አስተባብለዋል፡፡  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ

[የዛሬ 43 ዓመት ገደማ ነው። ሀሊማ ሀሰን በ20ዎቹ እድሜ ክልል የምትገኝ ወጣት ሳለች ከአጋሯ ጋር ልጅ ወለዱ። ሀሰን የሚባል። ጥንዶቹ ብዙም ባይጣጣሙም ሁለተኛ ልጅ ወለዱ። ኑኑ ተባለ። ኑኑ አሁን የሚጠራው ማንስ ክላውዘን ተብሎ ነው። ሀሊማ ታሪኳን እንዲህ አካፍላናለች።] BBC Amharic https://www.bbc.com/amharic/49027647 ሀሊማ ሀሰን እና ማንስ ክላውዘን ከ43 ዓመት በኋላ ሲገናኙ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ከተፈናቀሉ ተፈናቃዮች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ ቀደመው ቀያቸው ተመልሰዋል።

በአማራ ክልል ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ከተፈናቀሉ አብዛኛዎቹ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ክልሉ አስታወቀ። የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ለዶቼቬለ «DW» እንዳስታወቀው በአማራ ክልል ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ከተፈናቀሉ 73 ሺህ ተፈናቃዮች መካከል 63 ሺህ ሚሆኑት ወደ ቀደመው ቀያቸው ተመልሰዋል። የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ እሱ መስፍን በተለይ ለዶቼ ቬለ «DW» እንደተናገሩት 63 ሺህ ተፈናቃዮች ወደ ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች ተመልሰዋል፡፡ ኃላፊው ከዚህ ሌላ እስካሁን 3ሺህ 400 ቤቶች መገንባታቸውንና ቀሪ 10ሺህ ተፈናቃዮችም በቅርቡ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ ተናግረዋል። ከሌሎች ክልሎች የተፈናቀሉ 24 ሺህ ዜጎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ከየክልሉ ኃላፊዎች ጋር እተወያዩ እንደሆነም አቶ እሱ ተናግረዋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሐገራት በኤቦላ ምክንያት በኮንጎ ላይ የጉዞ እቀባ እንዳያደርጉ የአፍሪቃ ህብረት አስጠነቀቀ።

ሐገራት በኤቦላ ምክንያት በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ላይ የጉዞ እቀባ እንዳያደርጉ የአፍሪቃ ህብረት አስጠነቀቀ። DW : የአፍሪቃ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከሎች ኃላፊ ዶክተር ጆን ኤን ንኬንጋሶንግ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የአፍሪቃ ህብረት አባል ሃገራት ወደ ኮንጎ በሚሄድ እና ከኮንጎ በሚወጣ ተጓዥ ላይ እገዳ እንዳያደርጉ እርግጠኛ መሆን እንፈልጋለን ብለዋል። ለዚህ የሰጡት ምክንያትም እገዳው ኤቦላን የሚያስከትለውን ቫይረስ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ያደናቅፋል የሚል ነው።የዓለም የጤና ድርጅት «WHO» ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳለው እስካሁን ከኮንጎ ውጭ በኤቦላ የተያዘ ሰው አልተገኘም። በኮንጎዋ በሰሜን ኪቩ ዋና ከተማ ጎማ አንድ ሰው በበሽታው እንደተያዘ ከተደረሰበት በኋላ ጉዳዩ እያሳሰበ ነው። ለሩዋንዳዋ ኪሴኒ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ጎማ ከኮንጎዋ ከተማ ቡካቩ እና ከደቡብ ኪቩ ክፍለ ሃገር ጋር የሚያገናኛት ወደብ አላት። ከዚህ ሌላ ከከተማይቱ እና ወደ ከተማይቱ ከኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ወደ ኡጋንዳዋ ኢንቴቤ እና ወደ ኢትዮጲያ ዋና ከተማ አዲስ አበባም በረራዎች ይደረጋሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

Yohana – Mircha Alat (Ethiopian Music)

Presented by Hope Entertainment. Ethiopia is a country of traditional music. The music of Ethiopia is extremely diverse, with each of Ethiopia's ethnic groups being associated with unique sounds. Ethiopian music uses a distinct modal system that is ...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ ክልል በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት ማለፉን እና ንብረትም መውደሙን የዓይን ምስክሮች ተናገሩ

ዶቼቬለ – በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት ማለፉን እና ንብረትም መውደሙን የዓይን ምስክሮች ተናገሩ። የዓይን ምስክሮቹ በተለይ በሞሮቾ በሃገረ ሰላም በአለታ ወንዶ እና በይርጋለም ከተሞች የሲዳማ ክልልነት በይፋ እንዲታወጅ በሚጠይቁ ወጣቶች እና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ከትናንት ጀምሮ በተፈጠረው በዚሁ ግጭት በተለይ በሞርቾ እና በሃገረ ሰላም ከተሞች ከሞቱት መካከል አብዛኛዎቹ ታዳጊ ወጣቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል።በግጭቱ የግለሰቦች እና የመንግሥት መኪናዎች መቃጠላቸውንም ተናግረዋል። እንደ ዓይን እማኞቹ በተለይ በሞሮቾ አውራ ጎዳናዎች በድንጋይ በመዘጋታቸው ከሃዋሳ ወደ ይርጋለም ፣አለታ ወንዶ እና ሃገረ ሰላም የሚያገናኙ የትራንስፖርት አገልግሎቶች መቋረጣቸውንም የዓይን እማኞች ገልጸዋል።በሃገረ ሰላም ከተማም ወጣቶች የግለሰቦች እና የመንግሥት ንብረት ሲሰብሩ እና ሲቃጥሉ እንደነበርም እነዚሁ የዓይን ምስክሮች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። አለመረጋጋቱ በተስፋፋባቸው የሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች እስካሁን በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት መጠን ከክልሉም ሆነ ከሲዳማ ዞን የፀጥታ አካላት ማረጋገጥ አልተቻለም። ዶቼቬለ DW ያነጋገራቸው የሲዳማ ዞን የስራ ሃላፊዎች በከተሞቹ ሰዎች መሞታቸውን እና ንብረት መውደሙን ቢያረጋግጡም ዝርዝር መረጃ እየጠበቁ መሆናቸውን እንደተናገሩት ዶቼቬለ ዘግቧል። An armed security officer roams on an empty street during a clash between a Sidama youth and securities after they declared their own region in Hawassa, Ethiopia July 18, 2019. ተጨማሪ ዘገባ Read More https://www.telesurenglish.net/news/Four-Killed-As-Protests-Spread-in-Southern-Ethiopian-City-20190719-0015.html
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሲዳማ ዞን ወጣቶች በየከተማዉ ከሰፈረዉ የፀጥታ አስከባሪ ጋር እየተጋጩ ነዉ።

DW : የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ የቀረበዉ ጥያቄ አፋጣኝ አወንታዊ መልስ እንዲሰጠዉ ግፊት የሚያደርጉ የሲዳማ ፖለቲከኞች በተለይ ወጣቶች በየከተማዉ ከሰፈረዉ የፀጥታ አስከባሪ ጋር እየተጋጩ ነዉ። ነዋሪዎች እንደገለፁት በግጭትና ሁከቱ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል።መኪኖች፤ መኖሪያና መስሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። መደብሮች ተመዝብረዋልም። የተለያዩ ከተሞችን የሚያገናኙ የመኪና መንገዶች ሲዘጉ፤ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በከፊል ተቋርጧል። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/E2E26781_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዋሽንግተን ዲሲው የተቃውሞ እና ድጋፍ ሰልፍ – ወቅታዊ ጉዳዮች በመረጃ ቲቪ (19 July 2019)

Wektawi Gudayoch (Ethiopian Current Affairs) 19 July 2019 -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For inquiry or additional information, visit Mer...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ በተዋናይነት ስለተሳተፈበት የአምለሰት ሙጬ ፊልም የተናገረው

Ethiopia: Haile Gebreselassie during the screening of Amleset Muchie film, Minalesh -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For inquiry or additio...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግስት የሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ጅምሩን ለዉጥ ያደናቅፈዋል የሚል ስጋት አሳድሯል።

DW : የኢትዮጵያ መንግስት «መፈንቅለ መንግሥት» ካለዉ ከሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ በኋላ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሰራቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፈዉ ዓመት የፈነጠቀዉን የሠላምና የዴሞክራሲ ተስፋ ሊያጨናጉለዉ እንደሚችል የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ።ኢሰመጉ ሰሞኑን ባወጣዉ መግለጫ እንዳለዉ እምና መጋቢት የተጀመረዉ ለዉጥ በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ ዘንድ ከፍተኛ ተስፋ ሳያደረ፣ ድጋፍም ያተረፈ ነዉ።ይሁንና መንግስት በቅርቡ የሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ጅምሩን ለዉጥ ያደናቅፈዋል የሚል ስጋት አሳድሯል። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/8B2952C8_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የታሰሩ ጋዜጠኞች ምርመራ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር የማይገናኝ፣ እንዲያዉም ከሞያቸዉና ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር የተገናኘ ነዉ ተባለ

DW : በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያና መዘዙ ተጠርጥረዉ የታሰሩ ጋዜጠኞች የእስር ቤት አያያዝ መሻሻሉን ጠበቃቸዉ አቶ ሔኖክ አክሊሉ አስታወቁ።ይሁንና አቶ ሔኖክ ዛሬ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት በደንበኞቻቸዉ ላይ የሚደረገዉ ምርመራ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር የማይገናኝ፣ እንዲያዉም ከሞያቸዉና ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር የተገናኘ ነዉ።አቶ ሔኖክ የሁለት ጋዜጠኞች ጠበቃ ናቸዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት «መፈንቅለ መንግስት» ከሚለዉ ግድያ በኋላ ያሰራቸዉን ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እንዲለቅ የመብት ተሟጋቾች እየጠየቁ ነዉ። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/936FE9D3_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአሃዱ ራዲዮ ጣቢያ ላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ያልተጠበቀው ምላሽ፣ ከስራ አስኪያጁ አንደበት

Ethiopia: Court dismissed the case against Ahadu Radio Journalists -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For inquiry or additional information, ...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዶ/ር አብይ መንግስት ድጋፍ እና ተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን

Ethiopia: Supporters and critics of Abiy's Government hold protests in Washington DC -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For inquiry or additi...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በህብረ – ብሄራዊ ፌዴራሊዝም ላይ ለጥያቄዎ መልስ

“ቋንቋና የጎሣ ማንነትን መሠረት አድርጎ በኢትዮጵያ የተዘረጋው የፌዴራሊዝም ሥርዓት ወደ እርስ በርስ ግጭት ያመራል፤ ሃገሪቱ እንድትበተን ያደርጋል” የሚሉ በርካቶች ናቸው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሲዳማ ወቅታዊ ሁኔታ እና በጠ/ሚር አብይ የኤርትራ ጉብኝት ላይ ያተኮረ ውይይት

Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ የሥራ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኤርትራ ያደረጉትን የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ተመልሰዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብዛኛው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት በከፍተኛ የፀሀይ ቃጠሎ ውስጥ ነው

አብዛኛው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት በከፍተኛ የፀሀይ ቃጠሎ ውስጥ እንደሚገኝ፣ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪዎች /ሚቲዮሮሎጂስቶች/ አስታወቁ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሶማሌና የአማራ ክልልሎች ግንኙነት

ከ100 በላይ ፖለቲከኞችን፣ የመስሪያ ቤት ኃላፊዎችንና የጎሳ መሪዎችን የያዘዉ የሶማሌ ክልል የመልዕክተኞች ጓድ በአማራ ክልል የሚገኙ ተቋማትን ይጎበኛል፤ ከሕዝብና ከባለስልጣናት ተወካዮች ጋር ይነጋገራል፣ በዩኒቨርስቲ ምርቃ ድግስ ላይ ይገኛልም...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ላይ ውይይት

የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ተከትሎ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር፣ ከትናንት ጀምሮ ሃያ የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ ዋና ፀኃፊ ለቪኦኤ ገለፁ፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከበጎ ፈቃደኛ ልዩነህ ታምራት ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ

ልዩነህ ታምራት ወጣቶችን በዘላቂነት ከጎዳና ሕይወት ለማላቀቅ ሥነ-ልቦናዊ እገዛ፣ ፍቅር እና የክኅሎት ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል የሚል እምነት ያለው በጎ ፈቃደኛ ነው። ልዩነህ ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር በመተባበር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አራት የማገገሚያ ማዕከላት የማቋቋም ውጥን ጭምር አለው። ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

BBC Amharic : በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስብሰባ ተቀምጠው በነበረበት ሰዓት የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው የኔትወርኩ የዜናና ፕሮግራሞች አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ብርሀኑ ለቢቢሲ ተናገሩ። የሲዳማ ኔትወርክ አርማ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ጌታሁን ደጉዬ እና ምክትላቸው አቶ ታሪኩ ለማ የሚባሉ ሲሆን ሌሎች የመገናኛ ብዙሀኑ ባልደረቦች ግን ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገልፀዋል። ትናንት ጠዋት ወደ 6 ሰዓት አካባቢ ወደ ቢሯቸው የፀጥታ አካላት መምጣታቸውን እና ጥበቃ ሰራተኞቹ የቢሮውን ቁልፍ እንዲሰጧቸው መጠየቃቸውን ያስታወሱት አስተባባሪው፤ ነገር ግን የጥበቃ ሰራተኞቹ ቁልፍ እንደሌላቸው በመግለፅ እንዳሰናበቷቸው ተናግረዋል። ማታ ወደ 4 ሰዓት የሲዳማ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ ሽማግሌዎችና፣ ኤጀቶዎች በታቦር መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የምርጫ ቦርድን ሃሳብ ለመቀበል በንግግር ላይ ባሉበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ተናግረዋል። እነዚህ ኃላፊዎች ከወጣቶቹ ጋር የተሰበሰቡት ኤጀቶ ውስጥ በነበሯቸው ተሳትፎ ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ ሥራ የጀመረው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ሲሆን እስካሁን የሚገኘው የሙከራ ስርጭት ላይ ነው። የሚዲያ ተቋሙ ፕሮግራሞቹን የሚያስተላልፈው ሐዋሳ ከሚገኘው ቢሮውና ደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ውስጥ ከሚገኘው ማሰራጫው እንደሆነ አስተባባሪው ተናግረዋል። በአሁን ሰዓትም ምንም ዓይነት ስርጭት ከሐዋሳ የማይተላለፍ ሲሆን ነገር ግን ከጆሀንስበርግ የሚተላለፉ ዝግጅቶች ብቻ በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ እንደሚታዩ ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር ውለዋል ስለተባሉት ግለሰቦች የእስር ምክንያትና ስላሉበት ሁኔታ ለመጠየቅ ይመለከታቸዋል የተባሉ የደቡብ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ ፌደራሊዝም እና መቶ ብር … አስቴር በዳኔ

Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር በዜጎች ላይ የነበረው ተጽዕኖ ምን ይመስላል?

Ethiopian Broadcasting Corporation is a national media which disseminates its news and programs world wide via Television,Radio and Website
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የሸቀጦች የዋጋ ጭማሪ እና የዋጋ ግሽበት

Ethiopian Broadcasting Corporation is a national media which disseminates its news and programs world wide via Television,Radio and Website
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊና በሰራዊቱ ውስጣዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

(ኢዜአ) – የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የጸጥታ እና የሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የጸጥታ እና የሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ትናንት ውይይት አካሄደዋል። ከፍተኛ አመራሮቹ በውይይታቸው በቅርቡ በተቋሙ አመራሮችና በአማራ ክልል አመራሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከፍተኛ ቁጭት የፈጠረ መሆን መግለጻቸውንና ማውገዛቸውን የመከላከያ ዋና ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።አመራሮቹ ድርጊቱ በቀጣይ እንዳይደገም እንደሚሰሩ በውይይቱ ማጠቃለያ ባወጡት ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ ማረጋገጣቸውም ተገልጿል። የአገር መከላከያ ሰራዊት የተሰጠውን ሕገ መንግስታዊ ተልዕኮውን በቁርጠኝነትና ህዝባዊነት በተለበሰ መልኩ እንደሚወጣና የተሰጠውንም ተልዕኮ ከማንኛውም ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ጸድቶ ለመወጣት እንደሚሰራም በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። መከላከያ ሰራዊቱ የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ውስጣዊ አንድነቱን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን እንደሚታገልም ተገልጿል። የተሰው ጓዶች ህልፈት የተቋሙን የሰራዊት አባላት ለቀጣይ ስራ የሚያነሳሳ እንጂ የማይዳክም እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነም ተጠቁሟል። በውይይቱ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሐመድን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እንደተገኙበትና መድረኩ ከምንግዜውም በላይ ከፍተኛ መግባባትና የአንድነት መንፈስ የተፈጠረበት መድረክ እንደነበርም በመግለጫው ተመልክቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሲዳማ ህዝብ በክልል ደረጃ የመደራጀት ጥያቄ

የሲዳማ ህዝብ በክልል ደረጃ የመደራጀት ጥያቄ A Originally published at - https://amharic.voanews.com/a/activists-from-sidama-ethnic-group-delay-declaring-new-region-7-19-2019/5007177.html
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጦፋ ሙሀመድ ዑመር የተመራ የልዑካን ቡድን ባሕር ዳር ገባ፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት ተስማሙ፡፡ የመንግስት ሰራተኞች ለምርጫ የሚወዳደሩ ከሆነ ሥራቸውን የይለቃል፤ ለምን? እነዚህና ሌሎችን ዘገባዎች ይከታተሉ፡፡...
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራው ልዑክ በባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል

በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራው ልዑክ በባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

እውቀት ምንድን ነው?

LTV News
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ከሐዋሳ ተነስቶ በሌሎች አካባቢዎች ጉዳት ያደረሰው ሁከት

ሐሙስ በሐዋሳ ከተማ ተቀስቅሶ ወደ ሌሎች የሲዳማ ዞን አካባቢዎች የተዛመተው ሁከት ከባድ የንብረት ውድመትን ማስከተሉ የተረጋገጠ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ እስካሁን ከገለልተኛ አካል የተረጋገጠ አሃዝ አልተገኘም።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“የሰኔ 15ቱን ጥቃት ሰበብ በማድረግ ህዝብን ማዋከብ ተቀባይነት የለውም።” አዴፓ

"አማራ በመሆናቸው ብቻ ዜጎች ጥቃት ሲደርስባቸው ነበር፤ ዛሬም መሰል ድርጊቶች የሚፈጥሙ አካላትን በዝምታ አይመለከትም።"አዴፓ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

“7 ዓመቴ ነው ክርክር ከጀመሩ፤ እስካሁን ግን ውሳኔ አልተሰጠኝም።” ፍትሕ ያጣች እናት

ምሽት 12፡00 ዜና ሙዳይ ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 11/2011 ዓ.ም (አብመድ)
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ኤርሚያስ ለገሰ – ዶ/ር አብይ ወደህዝበኝነት መመለስ አለበት ለውጡን ማሳካት ከፈለገ

Ermias Legese with Abebe Belew - Addis Dimts on Mereja TV -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For inquiry or additional information, visit Mer...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እነጄ/ል ተፈራ ማሞ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተዘገበ

Ethiopia: General Tefera Mamo and others who have been arrested in Amhara Region go on hunger strike -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For i...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የደኢህዴን መግለጫ መለስ የሞቱ ጊዜ የወጣውን ይመስላል – ግርማ ሰይ

Ethiopia: Former parliamentarian Girma Seifu on Sidama political crisis -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For inquiry or additional informat...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኤጄቶ የተደበደበው ጋዜጠኛ ስለሀዋሳ ሁኔታ የተናገረው

Ethiopia: Journalist attacked in Hawassa town by Ejeto youth -- Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL Get the latest news and information about #Ethiopia and Ethiopians from #Mereja For inquiry or additional information, ...
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት እነ ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ፍትህ ይሰጠን ሲሉ ምግብ በማቆማቸው ለህመም ተዳረጉ።

Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለአማራ ሕዝብ ጥቅም የሚታገሉትን ማሰርና ማዋከብ ሊቆም እንደሚገባ የባሕርዳር ነዋሪዎች ጠየቁ።

Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ለአማራ ሕዝብ ደሕንነት ዘብ እንቆማለን፣ ሕዝባችን ሲሞት ቆመን አናይም” – የአማራ ልዩ ሃይል አባላት

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በየሰበቡ ዜጎችን ማሰር ሊቆም እንደሚገባ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አሳሰበ።

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ክልል ለመሆን በኃይልና በዛቻ ለማስፈጸም የሚደረገውን እንቅስቃሴ ብዙዎች እየተቃወሙት ነው

DW : በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ አቀራረብ፣ እና በምርጫ ቦርድ መልስ እንዲሁም በጥያቄው አተገባበር ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰማሉ። ክልል የመሆን ጥያቄ ማቅረብ መብት ስለ መሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ።ሆኖም ጥያቄውን በኃይል እና በዛቻ ለማስፈጸም የሚደረገውን እንቅስቃሴ ግን ይቃወማሉ።አስተያየት ሰጭዎቹ ጥያቄ አቅራቢዎቹ ሃገሪቱ የምትገኝበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ታግሰው እንዲጠብቁ ይመክራሉ። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/9A68861D_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ ክልል ከተሞች ግጭት እና ዘረፋ እንዳለ ተሰማ

DW : ግጭትም እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ጸጥታ አስከባሪዎች ከተማይቱን ሲቆጣጠሩ ነው የዋሉት።በሌሎች ከተሞችም ግጭት እና ዘረፋ እንደነበረ ተዘግቧል።የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ርዕሰ ከተማ ሃዋሳ  ውጥረት ሰፍኖ ነው የዋለው።ግጭትም እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ጸጥታ አስከባሪዎች ከተማይቱን ሲቆጣጠሩ ነው የዋሉት።በሌሎች ከተሞችም ግጭት እና ዘረፋ እንደነበረ ተዘግቧል።የሃዋሳ እና የሌሎች የደቡብ ክልል ከተሞች ውሎ … https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/76D23972_2_dwdownload.mp3 የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ለዛሬ ለማወጅ መቀጠሩን ተከትሎ በሐዋሳ እና አካባቢዋ ግጭት ተቃውሞ መከሰቱ እየተነገረ ነው። የጥያቄ አራማጆች ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደገለፁት የሲዳማ ሽማግሌዎች እና ወጣት የጉዳዩ አቀንቃኞች ዛሬ ጠዋት ሊያካሂዱት ያቀዱት ስብሰባ አካባቢውን በዘጉት በፀጥታ ኃይሎች ተደናቅፏል። ባለሥልጣናት ወደዚያ ባለመምጣታቸው፤ እና ወደ መሰብሰቢያው ስፍራም እንዳያልፉ ያገዷቸው የፀጥታ ኃይሎች ላይ ወጣቶቹ ድንጋይ መወርወራቸውንም ዘገባው አመልክቷል። ሐዋሳ ከተማ ላይ በቁጣ ወደ ጎዳና የወጡት ዜጎች ጎማ በማቃጠል ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭትም ቢያንስ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱን ሌሎች ደግሞ መጎዳታቸውን የሆስፒታል ምንጮች ለዶይቼ ቬለ «DW» ገልጸዋል። የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ሳርሚሶ ጭንቅላቱን በጥይት መመታቱ የተገለፀው ተጎጂ ወደ ሐኪም ቤት ከሄደ በኋላ ሕይወቱን ማጣቱን ለሐዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ገልጸዋል። «መጀመሪያ ላይ ትንሽ ጭንቅላቱ ላይ የቆሰለ ሰው ገብቷል። እሱ የመጀመሪያ ርዳታ ሰጥተን ወደ ቤቱ ሄዷል። ከዚያ ቀጥሎም ደግሞ አንድ ሴት ነበረች የመጣችው። ባጠቃላይ አራት ወንድ እና አንድ ሴት ነበር የመጡት። አንደኛው ከአዳሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመጣ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሐዋሳ ከተማ በወጣቶችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት ተከሰተ

በሐዋሳ ከተማ በወጣቶችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት እሰከአሁን አንድ ሰው ሲሞት ሌሎች ሦስት ሰዎች መቁሰላቸውን የሆስፒታል ምንጮች አስታውቀዋል። ሟቹ ዛሬ ቀትር ላይ የራስ ቅሉ ላይ በጥይት ተመትቶ ወደ ሆስፒታሉ ከመጣ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን የሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ሳርሚሶ ለዶቼ ቨለ ( DW ) ተናግረዋል።የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ለዛሬ ለማወጅ መቀጠሩን ተከትሎ በሐዋሳ እና አካባቢዋ ግጭት ተቃውሞ መከሰቱ እየተነገረ ነው። የሲዳማ ሽማግሌዎች እና ወጣት የጉዳዩ አቀንቃኞች ዛሬ ጠዋት ሊያካሂዱት ያቀዱት ስብሰባ አካባቢውን በዘጉት በፀጥታ ኃይሎች ተደናቅፏል። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/AE685710_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook