Blog Archives

ራሴን ነኝ ( ድምጻዊትሐመልማል አባተ) አዲስ ሙዚቃ

Source – https://www.youtube.com/channel/UCddm4ePEJcTZ1lxGNIzsLfA/videos
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Poem, Video

የፈረንሳይ የባህል ሚኒስትር ለጃዝ ሙዚቃው ንጉስ ሙላቱ አስታጥቄ እውቅናና ሽልማት አበረከቱ

Image may contain: 5 people, people standing, suit and indoor የክብር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ሥራዎች ላበረከቱት አስተዋፅኦ የፈረንሳይ መንግሥት በባህል ዘርፍ የሀገሪቱን ከፍተኛ ሽልማት አበረከተላቸው። እውቅናው የተበረከተላቸው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ውስጥ በአምባሳደሩ መኖሪያ ሲሆን ሽልማቱን ያበረከቱት የፈረንሳይ የባህል ሚኒስትር ፍራንክ ራይስተር ናቸው። Image may contain: 1 person, smiling, standing, suit and indoor ሚኒስትሩ “አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ ሥራዎቻቸው የታዳሚዎችን የሙዚቃ ጥም ከማርካት ባለፈ አፍሪካ እና ቀሪውን ዓለም ያገናኙ አምባሳደር ናቸው” ሲሉም ገልጸዋቸዋል። አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በበኩላቸው ለተሰጣቸው እውቅና እና ሽልማት አመስግነዋል። EBC  
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music

አሊ (ታንጎ) አብደላ ኬፋ ከደረጀ ኃይሌ ጋር (ካለፈው የቀጠለ)

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Video

በበርካታ ፊልሞች ላይ በትወና የሚታወቀው አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

Image may contain: 1 person, beardበበርካታ ፊልሞች ላይ በትወና የሚታወቀው አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። አርቲስት ተዘራ ለማ ትናንት ምሽት ቤቱ ውስጥ እያለ በድንገት ህመም ካጋጠመው በኋላ በአካባቢው ወደሚገኝ የህክምና ማዕከል ቢወሰድም ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። “ውሳኔ ፊልም” ላይ መጀመሪያ የትወና ስራውን የሰራው አርቲስት ተዘራ ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከ20 በላይ ፊልሞች ላይ የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ተጫውቷል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፥ ፍቅር ባጋጣሚ ፣ ታስጨርሽኛለሽ፣ ፍቅር በይሉኝታ፣ አልወድሽም፣ ወንድሜ ያቆብ፣ ኢንጂነሩ እና ጥቁር እና ነጭ ተጠቃሽ ናቸው። አርቲስት ተዘራ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር። ነብስ ይማር!
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music

በሰላሳ ቀናት ውስጥ ሲኖዶስ መልስ ካልሰጠን አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን ሲል የኦሮሚያ ቤተክህነት ገለጸ

BBC Amharic የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት በክልል ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ቅዱስ ሲኖዶሱ በ30 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቃቸው ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን አስታውቀዋል። በዛሬው ዕለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሚቴው ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ክልላዊ ፅህፈት ቤቱን ጥያቄ የሚቀበለው ከሆነ የሰው ኃይል አመዳደቡም ሆነ አፈፃፀሙ ይህ አደራጅ ኮሚቴና ጠቅላይ ቤተ ክህነት በጋራ የሚወስኑት እንደሚሆን ተገልጿል። በተጠየቀው መሰረት አስቸኳይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ የምዕመኑን ጥያቄ ለመመለስ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚቴው አስጠንቅቋል። እርምጃው ምን እንደሆነ በዚህ ወቅት ግልፅ ባያደርጉም ከዚህ ቀደም እንደተናገሩት በራሳቸው ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት እናቋቁማለን ማለታቸው የሚታወስ ነው። ቀሲስ በላይ በዚህ ወቅት እንደገለፁት ጉባኤው እምነቱ አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አንድ ፓትርያርክና አንዲት ቤተ ክርስቲያን መሆኑን አምነው የቤተ ክርስቲያኗን ሌላ ህግ ማውጣት እንደማያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት የማቋቋም ጥያቄ የቤተ ክርስቲያኗ የዶግማና የቀኖና ትውፊት ለውጥ ሳይኖር አስተዳደራዊ ችግሮችን ለመፍታት መዋቅር የማበጀት ጥያቄ መሆኑንም ገልፀዋል። ጥያቄው አዲስ እንዳልሆነና ታሪካዊ ዳራ ያለው መሆኑን ተናግረው ቤተክርስቲያኗ በአፄ ኃይለ ስላሴ አገዛዝም ወቅት በጠቅላይ ግዛት በአውራጃና በወረዳ ደረጃ የመንግሥት አደረጃጀት ተከትላ ትሰራ እንደነበርና እንዲሁም በደርግ ወቅትም ይህ አሰራር እንደቀጠለ ገልፀዋል። በኢህአዴግ አገዛዝም ወቅት የፌደራል አደረጃጀቱን ተከትሎ ኃገረ ስብከቶች መቋማቸውንና በክልል ደረጃ ፅህፈት ቤት
Posted in Amharic News, Music

ድምጻዊ ዘቢባ ግርማ ከዐመታቶች በፊት በኢትዮጵያ አይዶል

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Poem, Video

ወፌ ቆመች – ሙሉ ፊልም

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Video

“ልጃችሁን ምን መሆን ትፈልጋለህ ብላችሁ አትጠይቁ?” ፌቨን ሰይፉ

Posted in Ethiopian News, Funny, Music, Psychology

ቴዲ አፍሮ ከአፍሪካ ህብረት የዲሲ ፅ/ቤት ሽልማት ሊበረከትለት ነው ተባለ

በአፍሪካ ህብረት የዋሽንግተን ዲሲ ፅህፈት ቤት አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለወጣት አፍሪካዊያን ታላቅ አርአያ በመሆን ላበረከተው አሰተዋትፅዎ የእዉቅና ሽልማት ሊበረከትለት መሆኑን ዛሬ ተገለፀ። ሽልማቱ የሚሰጠዉ በመጪው ሃምሌ በዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄደው በታላቅ የአፍሪካ ሩጫ ጋር ተያይዞ በሚሰናዳዉ ዝግጅት ላይ ነው። ታላቅ ሩጫ በዲሲ፣ በየአመቱ የሚካሄድ ብዙሃኑን የሚያሳትፍ የጎዳና ላይ ሩጫ ሲሆን የመጀመሪያው ዝግጅት በመጪው ሃምሌ 14፣ 2011 ወይም በፈረንጆቹ አቆታተር ጁላይ 21፣ 2019 እንደሚካሄድ ሲገለፅ፤ ዝግጅቱ የሚዘጋጀዉም በዋሽንግተን ዲሲ የአፍሪካ ህብረት ፅህፈት ቤት፣ ኖቫ ኮኔክሽንስ በሚባል የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ከኢትዮጵያ ኢምባሲ፣ እና በዋሽንግተን ዲሲ የከንቲባ ፅህፈት ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ክፍል ጋር በመተባበር መሆኑን ተገልፆል። ዝግጅቱ ለቤተሰብ እና ለህፃናት ምቹ ሆኖ የተሰናዳና በሺህ የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ከተጋባዥ ታዋቂ የአፍሪካ አትሌቶች ጋር የሚሳተፉበት ነው።በዋሽንግተን የአፍሪካ ህብረት ፅህፈት ቤት ዋና ተጠሪ የሆኑት ዶክተር አሪካና ችሆምቦሪኮ ሽልማቱን አስመልክተዉ እንደተናገሩት፣አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከኢትዮጵያም አልፎ ለአፍሪካ ወጣቶች በአርዓያነትና ተግቶ በመስራት ዙሪያ ያበረከተዉ ሚና የጎላ እና እዉቅናዉም ትርጉም ያለዉ ነዉ ብለዎል። አክለዉም፣ አርቲስቱ የመድረክ ላይ ስራዎቹ እና የበጎ አድራጎት ክንዉኖቹ ፣ የአፍሪካ ህብረት ዝግጅቶቹን ተጠቅሞ ለማጉላትና ለማክበር ከተነሳባቸዉ ዓላማዎች ዋነኞቹ መሆናቸዉን ጠቁመዋል። የውድድሩ ዋና አዘጋጅ የሆኑት ዶክተር ጋሻው አብዛ ሽልማቱ ወቅታዊ፣ ምክኒያታዊና አኩሪ ሲሉ ገልፀዉታል። ዶክተር ጋሻው፣ ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የተሠጠዉ እዉቅና ከአበረከተው ተምሳሌታዊ ሚና ባሻገር የአህገር ኩራትም ነዉ ብለዉታል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music

የጌትሽ ማሞ አዲስ ነጠላ ዜማ ሳቢው (ተቀበል)

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Video

ማራኪዬ ከመድረክ ላይ ፡ በቴዲ አፍሮ

Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Ethiopian News, Music

ቴዲ አፍሮ – ሰምበሬ – በሚሊኒየም መድረክ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Video

ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ) ከኤርትራዊቷ ድምጻዊት ሚለን ሃይሉ ጋር የተጫወተው ዜማ ፦ ኮኸበይ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Video

“ሰላሳ የሆነው በምክንያት ነው” ~ቴዲ አፍሮ (ያሬድ ሹመቴ)

“ሰላሳ የሆነው በምክንያት ነው” ~ቴዲ አፍሮ (ያሬድ ሹመቴ) ሚልንየም አዳራሽ በታሪኩ እንዲህ የሙዚቃ ድግስ ሰምሮለት አያውቅም። የባንዱ ውህደትና ፍቅር የተሞላበት ጉልበት፤ ከቴዲ የማይነጥፍ ብቃት ጋር ተደምሮ ልዩ ምሽት ነበር። ወትሮ የሙዚቃ ድግስ ላይ ሲታደሙ እምብዛም ታይተው የማይታወቁ ብዙ ሰዎችን አስተውያለሁ። በእድሜ የገፉ አዛውንቶች፤ አባትና ልጅ፤ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጥለት የባህል ልብስ የዘነጡ ጎልማሳ እንስቶች፤ ከነጠባቂዎቹ ከማረሚያ ቤት የመጣ ታራሚ፤ የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ ጉዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች በአንድ ላይ እጅግ ትኩረት የሚስቡ ታዳሚዎች ነበሩ። ከድምፃዊያን መሐል ተወዳጁ የሂፕሆፕ አቀንቃኝ ልጅ ሚካኤልን አገኘሁት። “ይህንን የመሰለ ልዩ ኮንሰር በአካል ተገኝቼ ዊትነስ በማድረጌ በጣም እድለኛ ነኝ። እኔ ኢንስፓየርድ መሆን እና መማር የምፈልገው ከዚህ ግዙፍ የመድረክ ስራ ነው። በአንድ ምሽት ሁሉም ነገር ስኬታማ ሆኖ ማየት በጣም ያስደስታል። መብራቱ፣ ድምፁ፣ የባንዱ ኤነርጂ፣ የቴዲ ፐርፎርማንስ፣ በእውነት እኔ እንደዚህ የተሳካ ዝግጅት አይቼ አላውቅም።” አለኝ ልጅ ሚካኤል። ጓደኛዬ ደቻሳ አንጌቻ ሳልሰማ ተዘለልኳትን በሳቅና በጭብጨባ የታጀበውን የቴዲ የመድረክ ላይ አጭር ንግግር ነገረኝ። ታዳሚው በጋራ “ጃ ያስተሰርያል!” እያለ ቴዲ እንዲዘፍን ይጠይቃል። ጃ ያስተሰርያልን ቀድሞ ለመዝፈን ያቀደ በመሆኑ እና በሙዚቃዎቹ ቅደም ተከተል አደራደር መሰረት የሚያቀርብበት ግዜ ገና ባለመድረሱ በጨዋ እና በቀልድ አዋዝቶ አንድ ቃል ጣል አደረገ “30 የሆነው በምክንያት ነው። ተረጋጉ” ይህ አባባሉ ብዙውን ሰው ማሳቁን እና ማስጨብጨቡን ምስክር ነኝ። በሚልንየም አዳራሽ ዙሪያ የነበረው የፀጥታ ጥበቃ በእጅጉ የሚያስደስት ነበር። ምንም እንኳን
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music

በለዛ ሽልማት የዚህ አመት የኢትዮጵያ ምርጥ ዘፈን ተሸላሚ – ይመልከቱ

Posted in Music

በሥራው ዓለም ዋነኛው በልዩነት መግባባት መቻል ነው- የጃኖ ባንድ አባላት

ከጃኖ ባንድ አባላት ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ «በሥራው ዓለም ዋነኛው በልዩነት መግባባት መቻል ነው። ሁሉም የራሱ የሆነ ተፈጥሮ የለገሰችው ቅላጼና ችሎታ አለው። እንደ ሕብረ ቀለም በአንድ ሲዋሀድ ውበትን ያደምቃል። የአንዱ ክፍተት በአንዱ ይሞላል። የአንዱ ስህተት በአንዱ ይሸፈናል። ለዚህም በጥንድ መሆኑ እጅጉን አስተዋጽኦ አለው» የጃኖ ባንድ አባላት።
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Video

አርቲስት መስከረም ወንድማገኝ አረፈች

አሳዛኝ ዜና – አርቲስት መስከረም ወንድማገኝ አረፈች ሥርዓተ ቀብሯ ነገ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2010ዓ.ም. በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በ8፡00 ሰዓት ይፈፀማል ቤተሰቦቿ – መገናኛ 24 ቀበሌ፣ የነገው ሰው ትምህርት ቤት ፈለ ፊት በሚገኘው ማኅበር ቤት የሀዘን ዳስ ተጥሏል፡፡ የ28 ዓመቷ መስከረም … • ከ10 በላይ ፊልሞች ላይ ተሳትፋለች • ምንሼ ፊልም ላይ መሪ ገፀ ባህርይ ተጫውታለች • አልተኛም እና በቅርብ የሚወጣው ላመስግንሽ ፊልም ላይ ተውናለች • የዳይሬክተር መሐመድ ዳውድ ‹‹ያነገስከኝ›› ፊልም ላይም ፕሮዳክሽን ማናጀር ነበረች • የሰው ለሰው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ – ተዋናይ፣ ፕሮዳክሽን ማናጀር እና ኮንቲኒቲን መርታለች • የተቀበረው – ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ እንዲሁም የደራሲና መምህር ሀይሉ ፀጋዬ ‹‹የደወል ድምጾች›› የሬዲዮ ድራማ ላይ ተጫውታለች መስከረም – ለተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ቀረጻ ደብረሲና ከተማ ነበረች፡፡ አመመኝ ብላ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች፡፡ በተለያዩ ሆስፒታሎች ለስድስት ቀናት አልጋ ይዛ ሕክምናዋን እየተከታተለች ነበር፡፡ ይሁንና ዛሬ ጠዋት ሆስፒታል እያለች አርፋለች፡፡ ሥርዓተ ቀብሯ ነገ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2010ዓ.ም. በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በ8፡00 ሰዓት ይፈፀማል ነፍስ ይማር!
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music

ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ለአዲስ አመት ዋዜማ በመስቀል አደባባይ ኮንሰርት ታቀርባለች።

ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ለአዲስ አመት ዋዜማ  ላይ ኮንሰርት ታቀርባለች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music, Video

የቴዲ አፍሮ ዘፈን ‘ቴዎድሮስ’ የባህር ዳር ህዝብ ለጠ/ሚ አብይ ባካሄደው የምስጋና ሰልፍ ላይ – ቪዲዮ

Subscribe to mereja.com YouTube channel: https://goo.gl/YZcLT1 የቴዲ አፍሮ ዘፈን ‘ቴዎድሮስ’ በባህር ዳር ስታዲዮም
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Music

እያዩ በሌ – የቁርጥ ቀን ለታ – አዲስ ባህላዊ ዜማ

Tagged with: ,
Posted in Ethiopian News, Music, Video

የልጅ አስተዳደግዎ ምን ይመስላል? በ ዶ/ር አማኑኤል ኃይሌ፥ ዶ/ር ማስተዋል መኮንን እና ፌቨን ሰይፉ

Posted in Music, Psychology
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook