Blog Archives

ጠ/ሚ ዓብይ አሕመድ በብሔራዊ መግባባት ላይ ያጠነጠነ የውይይት መድረክ ላይ አልተገኙም

የ”ብሔራዊ መግባት” ጉባኤ ተጠናቀቀ – በዛሬው ዕለት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሲካሄድ የዋለው በብሔራዊ መግባባት ላይ ያጠነጠነ የውይይት መድረክ መጠናቀቁን በስፍራው የነበረው የኢትዮጵያን ዳይጀስት ባልደረባ ዘግቧል። – በአገራችን ባሉ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የነበረው ይህ የውይይት መድረክ ሦስት የፖለቲካ አመራሮች ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፍ መሰረት በማድረግ የተካሄደ ሲሆን የኦፌኮ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ አገረ መንግሥትና የጋራ መግባባትን አስመልክቶ ያቀረቡት ጽሑፍ በተወያዮቹ ሰፊ ክርክር አስነስቷል። – ፕ/ር መረራ ከአጼ ምኒልክ የአገር ምስረታና አርሲ ውስጥ አኖሌ በተባለው ስፍራ በወቅቱ ተፈጽሟል በሚል በመታሰቢያነት ስለቆመው ሐውልት ያነሱት ሐሳብ በተወያዮቹ ከአገራዊ መግባባት ይልቅ አፍራሽ ነው በሚል ትችት ቀርቦበታል። – ሌላው ጥናት አቅራቢ የኢዜማ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ በሕገመንግሥት ሥርዓትና አገራዊ ሁነት የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን ተወያዮቹ በአገራዊ መግባባት ዙርያ የሚቀርቡ ጥናቶች ከነባራዊው አገራዊ እውነታ እንጂ ከፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ተነስተው መቅረብ አይገባቸውም የሚል ሃሳብ ተሰንዝሯል። – የውይይት መድረኩ በማጠቃለያው፤ በቀጣይ ጊዜ በመሰል አጀንዳ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይሆኑ ገለልተኛ ወገኖች የመወያያ ጥናት ቢያቀርቡ የተሻለ መሆኑን አቅጣጫ አስቀምጧል። – በዕለቱ ከመድረኩ ጠ/ሚ/ር ዓብይ አሕመድ ይመጣሉ ተብሎ የተገለጸ ቢሆንም “በአስቸኳይ የሥራ ጉዳይ” ሊመጡ ያለመቻላቸው ተገልጿል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፈንቅል መሪ አቶ የማነ ንጉሥ ድንገተኛ የግድያ ሙከራ ተቃጥቶባቸዋል።

በ’ፈንቅል’ መሪ ላይ የግድያ ሙከራ ! “የትግራይ ሕዝብ የነፃነት ጥያቄ በታጋይ ልጆቹ መገደል የሚቆም አይደለም” አቶ የማነ ንጉሥ *********************** Image may contain: 1 personየፈንቅል መሪ፤ አቶ የማነ ንጉሥ በዛሬው ዕለት እኩለ ቀን በተለምዶ 22 ጉላጉል ሕንጻ ጀርባ፥ ድንገተኛ የግድያ ሙከራ ተቃጥቶባቸዋል። – የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ድርጊቱ የተመራው በአንድ የቀድሞ ደህንነት አባል ሲሆን ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል። – ከአደገኛው ሙከራ በኋላ አቶ የማነ ንጉሥ እንደገለጹልኝ፤ ‘የነፃነት ንቅናቄው ከነገ በስቲያ እሁድ በአዲስ አበባ በጠራው ልዩ ጉባኤ ሕወሓትን በአጭር ጊዜ የማስወገድ አዲስ የትግል ምዕራፍ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነበርን’ ብለውኛል። – አቶ የማነ ጥቃት ሊፈጸምባቸው ሲል አብሯቸው የነበረው ‘የቄሮ ፋኖ ለአገራዊ ግንባታ’ አስተባባሪ አቶ ስለሺ ደቻሳ እና በአከባቢው የነበረው ማሕበረሰብ ሕይወታቸውን ለማዳን ላደረጉት ፈጣን እንቅስቃሴ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተጨማሪም፤ የትግራይ ሕዝብ የነፃነት ጥያቄም “በታጋይ ልጆቹ መገደል የሚቆም አይደለም” ብለዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጄኔራሎቹ ቃለ ምልልስ !

የጄኔራሎቹ ቃለ ምልልስ ! (የመጀመርያ ክፍል) በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት እቤት ስንውል ጊዜያችንን በተለያዩ ጠቃሚ ነገሮች እንደምናሳልፋቸው ይገመታል፡፡ ለዚሁ ዓላማ በሚል ከዛሬ ሰባት ዓመታት በፊት በዝዋይ እስር ቤት ቃለ መጠይቅ አድርጌላቸው ሃሳባቸውን በመጀመርያ መጽሐፌ(የነፃነት ድምጾች ላይ) ለንባብ ካበቃሁላቸው የእስር አጋሮቼ ሁለቱ ብ/ጄ/ል ተፈራማሞ እና ብ/ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ናቸው፡፡ ጊዜው የቆየ ቢመስልም በወቅቱ የተነሱት ነገሮች ምን ያህል መሰረታዊ እንደሆኑ ያስተዋልኩት መለስ ብዬ ጽሑፎቹን የመመርመር እድል ባገኘሁበት በዚህ ወቅት ነው፡፡ በተለይ መጽሐፏን ማንበብ ያልቻላችሁ ወገኖች አጋጣሚውን ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ በጽሑፉ ርዝመት እንዳትሰለቹ በሚል የሁለቱንም ጄኔራል መኮንኖች ቃለ ምልልስ በሁለት በሁለት ክፍል አቀርብላችኋለሁ፡፡ ሌሎችም ወደፊት በተከታታይ የማቀርብላችሁ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ወገኖች ሃሳብና ተሞክሮ ይኖራል፡፡ (ታዲያ ርቀታችንንና ንጽናችንን እየጠበቅን) **********//********** ⨳“የሆነው ሁሉ ብዙሃኑን ሕዝብ ይጠቅማል ብለን ጊዜ ወስደንና አስበንበት ያደረግነው በመሆኑ፣ ከሕዝቡ ምንም ነገር መሸሸግ የለበትም ብዬ አምናለሁ፡፡›› በማለት ነበር ስለ 2001ዱ ‹‹የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ›› የሚል ስያሜ፣ የተሰጠው ክስ ላነሳሁላቸው ጥያቄ መመለስ የጀመሩት፡፡ *“እስኪ ስለራስዎ በአጭሩ ያጫውቱኝ፤ ወደ ትግል መቼ፣ እና እንዴት ገቡ? ከእነማን ጋር ነበሩ? የትግል ሜዳ ልዩ ትውስታዎችዎ ምንድናቸው?” አልኳቸው፡፡ ⨳የትግል እንቅስቃሴዬ የተጸነሰው በ1967 ዓ.ም ነበር፡፡ በወቅቱ የትውልድ አካባቢዬ በነበረው ላስታ አውራጃ ውስጥ የደርግን መምጣት ተከትሎ፣ ዓላማቸው የተለያየ ሆኖም ተመሳሳይ መገለጫ ያላቸው የዐመፅ እንቅስቃሴዎች ይካሄዱ ነበር፡፡ ብርሃነመስቀል ረዳ በአየር መንገድ ላይ ጥቃት የሰነዘረውም ያኔ ነበር፡፡ ደርግ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዓለ ጥምቀቱ እና የደበኞቹ ነገር !

በዓለ ጥምቀቱ እና የደበኞቹ ነገር ! በዓለ ጥምቀቱ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሚካኤል ታቦትን አጅቦ በማስገባት ይጠናቀቃል። እንኳን አደረሳችሁ ተባብለን መልካም ምኞት ተለዋውጠናል። በበዓሉ አከባበር ወቅት ጎንደር ላይ ምዕመኑ የተቀመጠበት ርብራብ ተደርምሶ የወገኖቻችን ውድ ሕይወት ጠፍቷል፣ አካላዊ ጉዳት ደርሷል። እግዚአብሔር የሞቱትን ነፍስ ይማር፣ ቤተሰብን ያበርታ፤ የተጎዱትንም ይዳብስልን። ከተፈጥሮ አደጋው መለስ ስንል ግን ዛሬም ሰው ሠራሽ አደጋዎች ቀጥለዋል። የመዲናችንን አንዳንድ አከባቢዎች ጨምሮ በሐረርና ድሬዳዋ… ደግሞ ከሕግና ስርዓት በላይ የሆኑ አካላት የፈለጋቸውን አድርገዋል። ዜጎች የዕምነት ሥርዓታቸውን እንዴት ማክበር እንዳለባቸው፣ የቤተ ዕምነታቸው ንዋየ ትውፊታትና ሌሎች የበዓሉ ማድመቂያ ዕሴቶች በፖሊስ ሃይል፣ ስፖንሰር በሚደረጉ የየአካባቢው ጎረምሶችና ለኢትዮጵያ ጥፋት 24 ሰዓት እየሠሩ ባሉ አካላት እየተወሰነ እንዳለ በአደባባይ ታይቷል። በመንግሥት በኩል ችግሮችን ለማስወገድ የአቅም ሳይሆን ዝቅ ሲል ቁርጠኝነት፤ ከፍ ሲል ፈቃደኝነት ያለመኖሩ በይፋ ተጋልጧል። (ከወር በፊት ከፍተኛ መጠን ያለው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ሲመረቅ ችግሮች ሁሉ የሚወገዱ፤ ቢያንስ በእጅጉ የሚቀንሱ መስሎኝ ያልተሟገትኩት አልነበረም። አፉ በሉኝ !) በቤተ ክርስቲያናችን ቃለ አዋዲ(ስርዓተ ቤተክርስቲያንንና ሌሎች) መሰረት ቤተክርስትያኗ የራሷ አርማ ያላት ሲሆን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ መሰረቱ በመጽሐፍ ቅዱስ (በዘፍጥረት መጽሐፍ 9:1-17) እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በቀስተደመና ተምሳሌት ዘለዓለማዊ የምህረት ቃል ኪዳን የገባበት መሆኑን የገለጸበት ነው። ሃይማኖታዊና የሕግ ዝርዝር ሳያስፈልገው ግን ዜጎች በአገራቸው፤ የሌሎችን ዕምነትና ማሕበራዊ ዕሴቶች እስካልነኩ ድረስ ዕምነታቸውን በፈለጋቸው መንገድ የማክበር የማይገሰስ መብት አላቸው። እንዴት ዕምነታችንን ማራመድ እንዳለብን፤ አንድ ቀን እንኳ የፈጣሪን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሰበር ዜና፦ የገዛኸኝ ነብሮ ቤተሰቦች የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው

የገዛኸኝ ነብሮ ቤተሰብ ትናንት በተካሄደው የቀድሞው አየር ወለድ አመታዊ ክብረ በአል ላይ የታጋዩ ምስል ያለበት የክብር መታሰቢያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የነብሮ ቤተሰቦች ሽልማቱን ሲረከቡ የገዛኸኝ ነብሮ በሰለጠነ ቅጥረኛ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ) ውስጥ ከተገደለ ሁለት ዓመቱ ሊመጣ ጥቂት ወራት ብቻ የቀሩት ሲሆን ወደ አገሩ አጽሙን አምጥቶ በክብር ለማሳረፍ የተገባው ቃል እስካሁን አእንዳልተተገበረ ቤተሰቦቹ በተለይ ለመረጃ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ሕዝብ በሚበዛበት ካርልና ፖሊ ጎዳና የነበረ ሲሆን ፖሊስ ግን የደረሰው ከአርባ ደቂቃ በላይ #ሆን ብሎ በመዘግየት እንደነበር ሁኔታውን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ። የምርመራው ሂደትም ሽስካሁን ሸልተጠናቀቀም መባሉ ቅሬታ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ጀግናው ከመገደሉ በፊት በነበረው ቀን በስፍራው በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በነበረ ዝግጅት ላይ ተጠርቶ ሳይሆን ለመቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንደተለመደው በተቃውሞ የአጋርነት ድምጹን ለማሰማት ተገኝቶ ነበር። በቀጣዩ ቀን መገደሉም ይታወሳል፡፡ ነብሮ የቀድሞው 102ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አባል ሲሆን በተገደለባት ደቡብ አፍሪካ ከሃያ አመታት በላይ መኖሩ የሚታወቅ ሲሆን የቀድሞውን አየር ወለድ በመወከል ሽልማቱን የሰጡት የ102ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጄ/ል ተስፋዬ ሃብተማርያም ናቸው፡፡
Tagged with:
Posted in Amharic News

ገዛኸኝ ነብሮን ለማሥረሳት ?! ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ለኢትዮጵያውያን ክብርና ነፃነት ነበር !

ገዛኸኝ ነብሮን ለማሥረሳት ?! ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ለኢትዮጵያውያን ክብርና ነፃነት ነበር ! … *****//*****//***** Image may contain: 1 person ገዛኸኝ ነብሮ በሰለጠነ ቅጥረኛ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ) ውስጥ ከተገደለ ሁለት ዓመቱ ሊመጣ ጥቂት ወራት ብቻ ቀሩት ! ነብሮን ለማስረሳት እየተደረገ ያለው ነገር ግን በእጅጉ የሚያስቆጭ ነው። ይህን ያልኩበትን ምክንያት በኋላ ላይ እመለስበታለሁ። ነብሮ የተገደለው በሰለጠነ ቅጥረኛ ብቻ ሳይሆን ጊዜ በሚፈታው ውስብስብ ደባ ነው። በደባው ከአንድ አገር በላይ እንደተሳተፈበት ብዙ ማሳያዎች አሉ። አንዱ ጀግናው የአገር ልጅ ሕዝብ በሚበዛበት ካርልና ፖሊ ጎዳና ተገድሎ ፖሊስ ግን የደረሰው ከአርባ ደቂቃ በላይ #ሆን ብሎ በመዘግየት ነው። የምርመራው ሂደትም የባሰ ቁጭትና መንገብገብ የሚፈጥር ነው ! ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ለኢትዮጵያውያን ክብርና ነፃነት ነበር ! … *****//*****//***** ጀግናው ከመገደሉ በፊት በነበረው ቀን በስፍራው በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በነበረ ዝግጅት ላይ ተገኝቶ ነበር። ተጠርቶ ሳይሆን ለመቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንደተለመደው በተቃውሞ የአጋርነት ድምጹን ለማሰማት ! አደረገውም ! ይህ ተቃውሞ የተለመደ ተግባሩ ነበር። ኢትዮጵያ ነፃ እስክትወጣ እቀጥልበታለሁም ይላቸው ነበር። ነብሮ የቀድሞው 102ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አባልም ነበር። ባለነጠላጫማዎቹ አዲስ አበባን ተቆጣጥረው ባለብዙ ፎቆች ሲሆኑና ብዙዎችን በአደባባይ መግደል ሲጀምሩ ከአገር ወጥቶ ለሁለት አስርታት ያህል በተሰዋባት ደቡብ አፍሪካ ኖሯል። ገዛኸኝ ነብሮ ከአገሩ እንደወጣ በደሙ ፍሰትና በሕዝብ ልጆች ሁለንተናዊ ትግል የአገሩ ነፃነት ቢረጋገጥም ለስንቱ ወንበዴ የተረፈች ቅድስት አገር አጽሙን በክብር ማሳረፍ አልቻለችም። ቤተሰቦቹ ልጃቸው እንዲረሳ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት የኢትዮጵያውያን ኮሙኒቲ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሰበር ዜና:- የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አዲሱን የጸረ-ሽብር ሕግ አጸደቀ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ጉባኤው በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፤ የሕግ ማሻሻያ ም/ቤት ተሻሽሎ የቀረበለትንና ለመንግስታዊ አፈና ውሏል በሚል ከፍተኛ ነቀፌታ ሲቀርብበት የነበረውን የጸረ ሽብርተኝነት ሕግ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ፡፡ የኢፌዴሪ የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 ተብሎ የሚታወቀው የአፈና ሕግ ከወጣ በኋላ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሲቪክ ማሕበረሰብ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ሌሎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የዚህ ክስ ሰለባ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በተለይ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ነፃነትን ለማፈን በሚል የአዋጁ አንቀጽ 6 ቁጥር 3 ላይ የጸሐፊዎቹ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በአንባቢው ላይ ሊፈጥር ይችላል ብሎ በሚገምተው በማንኛውም የተለጠጠ ትርጓሜ ሲያስቀምጠው ‹‹አንባቢዎቹ የሚያነቡት ነገር ድርጊቱን እንዲፈጽሙ፣ ወይም ለመፈጸም እንዲዘጋጁ፣ ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ የሚገፋፋቸው እንደሆነ አድርገው ይረዱታል ተብሎ ሊገመት የሚችል መልዕክት እስከ 20 ዓመት ጽኑ እስራት ያስቀጣል›› ማለቱ በሕጉ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለት በጸደቀው በዚህ ሕግ ላይ አቶ አበበ ጎዴቦ ስለሽር ሕጉ አስፈላጊነት ሲዘረዝሩ የሽብር ድርጊት በሰው ህይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ የሚፈጥረውን ምስቅልቅል አስቀምጠዋል፡፡ በዚህም ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን እና ለረቂቅ አዋጁ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች መገኘታቸውን አውስተዋል። በመጨረሻም አዋጅ ቁጥር 652/2001 በ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ ብቻ መጽደቁን ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘግቧል፡፡ —
Tagged with: ,
Posted in Amharic News

ሰበር ዜና: በትግራይ ድብደባና እስር ተጀመረ

በሕወሃት ተጠርቶ የነበረውና ‹‹የትግራይ ሕዝባዊ ኮንፍረንስ›› የተሰነው ጉባኤ ከተጠናቀቀ በኋላ በክልሉ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ከህግ አግባብ ውጪ የእስር እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የአረና ትግራይ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ በተለይ ለመረጃ ቲቪ ገለጹ፡፡ እንደ አቶ አብርሃ አገላለጽ በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ የሕወሃት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል ምክትል መስተዳድር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ‹ድርጅታችንን በሚቃወሙ ሁሉ ላይ እርምጃ እንወሰወዳለን› ሲሉ ባወጁት መሰረት ድብደባና እስሩ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ እስካሁን 21 የትግራይ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ ድብደባ የተፈጸመ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ደግሞ አቶ ሃደራ ወሉ እና አቶ መሀሪ ተክሌ በተባሉ ሁለት የአረና አባላት ላይ ድብደባ ከተፈጸመ በኋላ ለእስር እንደተዳረጉ ተገልጧል፡፡ ህወሃትን የሚቃወም በሙሉ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ ጫና እየተደረገ መሆኑንም ሊቀ መንበሩ ተናግረዋል፡፡ አቶ አብርሃ የትግራይ ሕዝብ በአሁኑ ሰዓት በፍርሃት ተሸብቦ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመበት እንደሆነ አስታውስው ከቀጣዩ ምርጫ ጋር በተያያዘ ፓርቲያቸው ዝግጅት እያደረገ ቢሆንም በተጨባጭ በትግራይ ምርጫ መደረጉ አጠራጣሪ እንደሆነባቸው ለመረጃ ቲቪ ገልጸዋል፡፡ _ _ _
Tagged with:
Posted in Amharic News

ሰበር ዜና ፡ የአዲስ ጊዜ መጽሄት ዝግጅት ክፍል ተዘረፈ

በኒው ኢንተርቴይመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር ስር በየሳምንቱ እየታተመች የምትወጣው የአዲስ ጊዜ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ባልታወቁ አካላት ዝርፍያ እንደተፈጸመበት የዝግጅት ክፍሉ ባልደረቦች ለመረጃ ቲቪ ገልጸዋል፡፡ ዝርፍያው የተፈጸመው ከትናንት ወዲያ ሌሊት ላይ ሲሆን የዝግጅት ክፍሉን በር በመስበር የመረጃ ቋት የያዘውን ኮምፒውተር ብቻ በመምረጥ መወሰዱን ለማረጋገጥ እንደተቻለ ታውቋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ በትናንትናው ዕለት በስፍራው ተገኝቶ አስፈላጊውን የአሻራና የቴክኒክ መረጃዎች ያሰባሰበ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሦስት የጥበቃ ሠራተኞች ተይዘው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Tagged with:
Posted in Amharic News

የኦነጉ ከፍተኛ አመራር ስለጠ/ሚ/ር ዓብይ የሰጡት አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ

ላለፉት 11 ወራት በእስር ላይ ቆይተው በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦነግ ከፍተኛ አመራር አባል ኮሎኔል ገመቹ አያና ስለጠ/ሚ/ር ዓብይ አሕመድ የሰጡት አስተያየት አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ኮሎኔል ገመቹ ከኦሮሚያ ኒውስ ኔትዎርክ ጋር በአፋን ኦሮሞ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስለጠቅላይ ሚ/ር ዓብይ አሕመድ፣ የፌዴራል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ስለሆኑት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ ከሰኔ 15ቱ የባሕርዳር ክስተት ጋር ተያይዞ በእስር ስለቆዩት ስለእነ ጄ/ል ተፈራ ማሞ እና ስለ እነ ክርስቲያን ታደለ ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ዓብይን የማውቀው ከልጅነቱ ጀምሮ ነው፡፡›› የሚሉት እኒህ አመራር ‹‹ከሰው ጋር ተግባብቶ ለመኖር የሚቸግረው ሰው አይደለም፡፡ በባድመ ጦርነት ወቅት አብረን ስለነበርንና ታናሻችንም ስለነበር እንልከው ነበር፡፡ እንደባሕላችን ታላቁ ስለሆንኩ ልኮኝ አያውቅም፡፡ እሱም ሲበሳጭ ሃሳቡን የሚከፍለው እኛጋ መጥቶ ነበር፡፡›› ካሉ በኋላ በዙርያው እየተደረጉ ባሉ ነገሮች ላይ ሙሉ መረጃ አለው ብለው እንደማያምኑ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል፡፡ ኮሎኔል ገመቹ ‹‹ይህን የምልበት ምክንያት አለኝ፡፡›› ይላሉ ‹‹ይህን የምለው ከወር በፊት መስርያ ቤቱ አስጠርቶ አነጋግሮኝ ነበር፡፡ እኔ የታሰርኩበት ጉዳይና ለእሱ የተነገረው አይገጥምም፤ አይመሳሰልም፡፡ ከዓመታት በፊት ጀምሮ አብረን ብዙ እንዳሳለፍን ከጠቀሰልኝ በኋላ ‹‹ገመቹ ይህን አደረገ ሲባል ከማውቀው ማንነትህ አኳያ በጣም ገርሞኛል›› ሲለኝ ፍርሃት ተሰማኝ፡፡ የፈራሁት እሱ የማያውቀውና ያላጤነው መንግስት አጠገቡ ይኖር ይሆን እንዴ? ብዬ ነው፡፡ ለእሱ የተሳሳተ መረጃ የሚሰጥ ይኖራል ያሰኛል !›› ብለዋል፡፡ የፌዴራል ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ስለሆኑት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ደግሞ በቃለ ምልልሳቸው ሲገልጹ፤- ‹‹እኔ ከጨለማ ክፍል የወጣሁ ቀን የጨለማ ክፍሉን ማፍረስ ጀመሩ፡፡ ምንድነው ስንል
Tagged with:
Posted in Amharic News

በሸካ ዞን ተቃውሞው ቀጥሏል (በውብሸት ታዬ)

-ሆቴሎችና ባንኮች ተዘግተዋል -የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል -ተቃውሞው አራተኛ ቀኑን ይዟል ከሁለት ሳምንት በፊት አንድ የ’መንጃ’ ብሔረሰብ አባል በአንድ ከፊቾ(የከፋ ብሔረሰብ አባል) ላይ ግድያ ፈጽሟል በሚል መነሻ በተቀሰቀሰ ግጭትና የበቀል እንቅስቃሴ በርካታ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን በሰው አካል ላይም ጉዳት መድረሱን በቦታው የተገኘው ባልደረባችን ዘግቧል። የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከሳምንት በፊት የተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል በየኪ ወረዳ ቴፒ ከተማ በመገኘት በከተማው አዳራሽ የማሕበረሰቡን ተወካዮች ያነጋገሩ ሲሆን፤ በውይይቱ ወቅት የተወሰኑ አካላት ተደራጅተው ወደአዳራሹ በመሄድና እየደረሰብን ነው ያሉትን ጥቃት በተቃውሞ በሚገልጹበት ወቅት የተጠቀሙባቸው ቃላት የአከባቢውን ቀደምት ማሕበረሰቦች ክብር የሚነካ በመሆኑ ለችግሩ እዚህ መድረስ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል። የአሁኑ የተቃውሞ እንቅስቃሴም ይህን ሆን ተብሎ የተደረገ ግጭት ቀስቃሽ መፈክር ሲያሰሙ የነበሩ ወገኖች ለፍርድ ይቅረቡልን የሚል መሆኑን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሌላ በኩል ስብሰባው በዞኑ ዋና ከተማ በማሻ መደረግ ሲኖርበት በቴፒ መደረጉ የራሱ መልዕክት አለው የሚሉት ነዋሪዎቹ የሚመለከተው የመንግስት አካል ጉዳዩን መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል። በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለት ለችግሩ መፍትሔ ለማፈላለግ በሚል ተቃውሞው ከተቀሰቀሰባቸው ሶስት ወረዳዎች አንዷ ወደሆነችው የአንድራቻ ወረዳ ከተማ ጌጫ ከተለያዩ የማሕበረሰብ አባላት የተውጣጡ የሽምግልና ቡድን አባላት ሄደው እንደነበር ከቡድኑ አባላት አንዱ የገለጹልን ቢሆንም ይህ ዘገባ እስከሚጠናቀርበት ጊዜ ድረስ ሁኔታው ተመሳሳይ መሆኑን በሃዘኔታ ገልጸዋል። ከክስተቱ ጀርባ አሁን እየታየ ያለውን ለውጥ ማደናቀፍ የሚፈልጉ አካላት ግፊት አለበት ብለው እንደሚያምኑም ያላቸውን ግምት አስቀምጠዋል። መንገድ በመዘጋቱም የትራንስፖርት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News