Blog Archives

ጠ/ሚ አብይ ለሕዝብ የገቡትን ቃል በማጠፋቸው ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የመቀጠል ብሔራዊ ህልውናዋ አደጋ ላይ ነው

አቶ ዮም ፍሰሃበቁጥር ከደርዘን በላይ የሆኑ ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊ የዳያስፖራ ድርጅቶች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ የገቡትን ቃል አክብረው ዜጎችን ለመጠበቅ እና ቅሬታዎችን ለመፍታት ቆራጥ የማስተካከያ ርምጃዎች እንዲወስዱ ጠየቁ። 15 ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ድርጅቶቹ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የመቀጠል ብሔራዊ ህልውናዋ አደጋ ላይ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉትን የዳያስፖራ ድርጅቶችን ወክለው ያነጋገርናቸው፣ የአሜሪካ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ጉዳይ ኮሚቴ የቦርድ አባል እና ጸሐፊ አቶ ዮም ፍሥሃ እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ወሳኝ መፍትሔዎችን በማስተዋል መውሰድ እና በአፋጣኝ በሥራ ላይ ማዋል ይኖርባዋቸዋል፡፡ ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን፣ ኢትዮጵያ ከዚህ የበለጠ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ እንደምትችል አሳስበዋል። በደብዳቤው ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም ሆነ ከመንግሥት ጉዳዮች ኮምዩኒኬሽንስ ጽ/ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ሆኖም ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽ/ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ ለድርጅቶቹ የሰጠው ምላሽ በዘገባው ተካቷል። /ስለ ደብዳቤው ከአሜሪካ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ጉዳይ ኮሚቴ የቦርድ አባል እና ጸሐፊ እንዲሁም አቶ ዮም ፍሥሓ ጋራ ተከታዩን ውይይት አድርገናል/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በትግራይ የኤርትራ ሰራዊት መንገድ በመዝጋቱ እርዳታ እየደረሰ አይደለም ተባለ

በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ድንበር አንዳንድ አካባቢዎች፣ በተለይም ለኢሮብ ወረዳ ሕዝብ፣ ዛሬም ሰብዓዊ ርዳታ እየደረሰ እንዳልኾነ፣ አንድ የአካባቢው ተወላጅ ለቪኦኤ ገለጹ፡፡ የዚኽም ምክንያት፣ ወደ ወረዳው የሚገባው መንገድ በመዘጋቱ እና በየትኛውም ወገን ትኩረት በመነፈጉ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡ የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ፣ መንገዱን የኤርትራ ሠራዊት ኬላ ስለዘረጋበት የሰብአዊ ርዳታ ለማቅረብ እንደተቸገረ አስታወቀ፡፡ የኤርትራ መንግሥት፣ ከዚኽ ቀደም የሚቀርብበትን የትኛውንም ክሥ አልተቀበለም። የኢሮብ ወረዳን ሕዝብ በተመለከተም፣ እስከ አሁን የሰጠው ምላሽ የለም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጄኔራል ተፈራ ማሞን ሕክምና እንዳያገኙ የከለከላቸው ከፍተኛ ባለስልጣን እንጂ ኢሚግሬሽን አይደለም ተባለ

ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የውጭ ሀገር ሕክምና በመከልከላቸው ሕመማቸው እየተባባሰ እንደኾነ ገለጹ · ባለቤታቸው፣ “ክሥ ለመመሥረት እየተዘጋጀን ነው፤” ብለዋል ከአራት ወራት በፊት ወደ ውጭ ሀገር ሔደው እንዲታከሙ የሐኪሞች ቦርድ ቢያዝም፣ መንግሥት ፈቃደኛ ባለመኾኑ የጤና እክላቸው እየተባባሰባቸው እንደኾነ የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኀይል ዋና አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ተናገሩ። ጀነራሉ፣ በወቅቱ ሕክምና ባለማግኘታቸው፣ በአሁኑ ሰዓት በጽኑ ታመው አልጋ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኀይለ በበኩላቸው፣ ለሕክምና ወደ እስራኤል ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ የመሳፈርያ ቅጹ ላይ ይለፍ የሚል ማኅተም የሚያደርገው ግለሰብ፣ ከበላይ አካል የመጣ ትእዛዝ ነው፤ በማለት እንደ ከለከሏቸው ገልጸዋል፡፡ የከለከለውን አካል ለማወቅ ጥረት ቢያደርጉም እንዳልተሳካላቸውና በቅርቡም ክሥ እንደሚመሠርቱ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ በ1980 ዓ.ም የደርግ ሥርዐተ መንግሥት ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት፣ በቀኝ እግራቸው ላይ ያልወጣ ጥይት እና የቦንብ ፍንጣሪ እንዳለ በሐኪሞች በመረጋገጡና ወደ ውጭ ሀገር ሔደው እንዲታከሙ በሐኪሞች ቦርድ መወሰኑን የጠቀሱት ጀነራሉ፣ ባለፈው ኅዳር ወር፣ ከሀገር መውጣት እንዳይችሉ በመንግሥት መከልከላቸውን ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ ሕክምና ማግኘት ሲገባቸው ባለማግኘታቸው፣ ሕመሙ እየባሰባቸው እንደ መጣ ገልጸዋል፡፡ “ለብዙ ጊዜ የኖሩ ተደጋጋሚ ምቶች እዚያው ውስጥ አሉ፤ ነገር ግን በየጊዜው ሕክምና አላገኘኹም፡፡ በሀገር ውስጥ ለመታከም ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጌ፣ ይህ በውጭ ካልኾነ በሀገር ውስጥ አደጋ ይገጥምሃል፤ ከነርቭኽ ጋራ የተያያዘ ነገር አለው እግርኽ ላይ አደጋ ሊገጥምኽ ይችላል፤ አሉኝ፡፡ እኔም የሰጋኹት እርሱን ነው፤ ምክንያቱም የተሰገሰገው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአንተኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝት ፋይዳ ትንታኔ

የዩናይትድ ስቴትሱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝት፤ የሁለቱን ሀገሮች ያለውን ግንኙነት መልሶ ለማደስና ቀድሞ ወደነበረው ደረጃ የመመለስ አንደምታ እንዳለው አንድ ምሑር ተናገሩ። በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክኒያት የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ሻክሮ ቆቷል የሚል እምነት ያላቸው በኒው ዮርኩ አዮና ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው፤ የብሊንከን ጉብኝ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲያበቃ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ላይ ከተደረገው የሰላም ሥምምነት በኋላ የታየ ለውጥ ነው የሚልም እምነት አላቸው። ዶ/ር ደረሰ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያና የኒዠር ቆይታቸውን አጠናቀው የተመለሱትን የዩናይትድ ስቴትሱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝት ፋይዳ በተመለከተ ትንታኔ ሰጥተውናል። ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የባሌ አባገዳዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መዳ ወላቡ የተባለው ቦታ “የኦዳ ሮባ መገኛ እና የስኮ እና መንዶ መቀመጫ በመሆኑ ወደ ምስራቅ ቦረና መካለል የለበትም” ሲሉ አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አቤቱታ አሰሙ። ቅሬታቸውንም ለፌዴራል እና ለኦሮሚያ ክልል መንግሥት ማቅረባቸውን የገለፁት አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ከመንግሥት አካላት መልስ እየተጠባበቁ እንደሆነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ለብዙሃን መገናኛ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንዲህ ያለ አደረጃጀት በየጊዜው እንደ አስፈላጊነቱ ይከናወናል ሲሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ የጉጂ አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በቅርብ ጊዜ ለፌዴራል እና ክልል መንግሥት ጥያቄ አቅርበው የዞን አደረጃጀቱ እንደማይቀለበስ ከመንግሥት ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ ጌታቸው ረዳ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነት በህወሓት ታጩ

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል በመቋቋም ላይ የሚገኘውን የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ከህወሓት በኩል መታጨታቸውን ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። ዓለም አቀፍ የትግራይ ምሑራን ማኅበር ሌተናል ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ባለፈው ሳምንት በእጩነት ማቅረቡ ይታወቃል:: የአቶ ጌታቸውና ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኒ ኣባላት ሹመት፣ የክልሉ አመራሮች ከፌደራሉ መንግሥት ጋር በጊዜያዊ አስተዳደሩ አወቃቀር ጉዳይ ተወያይተው ካፀደቁት በኋላ አስተዳደሩ ሥራ እንደሚጀምር ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጉራጌ ዞን የም/ቤት አባላትን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ታስረዋል

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ያለመከሰስ መብታቸው ያልተነሳ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ብዝ ሰው መታሰሩን ነዋሪዎችና አንድ የሕግ ባለሞያ ገለፁ። እስሩ ክልል ከመሆን ጥያቄ ጋር ሊያያዝ ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸውም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲም አምስት አባላቱ እንደታሰሩበት አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን 40 ሰው መታሰሩን አረጋግጦ የታሰሩበት ምክኒያት ግን “ብጥብጥ በማስነሳትና በሕገ ወጥ ድርጊት ስለተጠረጠሩ ነው” ብለዋል። [ሙሉውን ዝግጅት ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ መርዛማ ቅራኔዎችንና የጎሳ መከፋፈልን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ብሊንከን ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ ሀገራቸው በኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ጭቆናዎችን እንደምታውቅ ገልጸው፣ እነዚህ ችግሮች በሽግግር ፍትህ እልባት ሊያገኙ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ለዚህም ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እንደምታደርግ የገለጹት ብሊንከን፣ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚውል 331 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍም ይፋ አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና፣ ኢትዮጵያ ወደ አጎአ እድል ተጠቃሚነት እንድትመለስ ስምምነቱን የመፈጸም ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ አንተኒ ብሊንከን፣ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከምክትላቸው ደመቀ መኮንን እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም፣ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ውይይታቸውን በማስመልከት ምሽት ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ብሊንከን፣ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስወገድ መርዛማ ላሏቸው ቅራኔዎችና ለጎሳ መከፋፈል ችግሮች መፍትሔ ማምጣት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ይህም በሽግግር ፍትህ ሊተገበር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ “ኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ የሆነ የሽግግር ፍትህ ሂደት ለማካሄድ በገቡት ቃል መሰረት እንዲያካሂዱ እናሳስባለን። ይህም እርቅንና ተጠያቂነትን የሚያካትት ሊሆን ይገባል፡፡” ያሉት ብሊንከን “መርዛማ ቅራኔዎችን እና የጎሳ መከፋፈልን ማስወገድ፣ በሰሜን፣ በኦሮሚያም ይሁን በየትኛውም አካባቢ ያለውን የፖለቲካ እና ብሄር ተኮር ግጭቶችን ለማስወገድ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ በዚህ ጥረት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ አጋር እንደመሆኗ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋለች፡፡” ብለዋል። ኢትዮጵያ እየተጋፈጠቻቸው ያሉ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ደግሞ፣ ዘላቂ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“የከብቶቻችን ዋጋ ወደቀ” የቦረና አርብቶ አደሮች

ከብቶቻቸውን የሚገዛቸው በማጣታቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን የቦረና አርብቶ አደሮች ገለፁ። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የያቤሎ አካባቢ አርብቶ አደሮች፤ ድርቅ ካስከተለው ጉዳት የተረፉላቸውን ከብቶች እጅግ አነስተኛ በሆነ ዋጋ ለመሸጥ መገደዳቸውን አመለከቱ። የቦረና ዞን የመስኖ ልማት እና አርብቶ አደር ጽህፈት ቤት በበኩሉ አሁን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ድጋፍ ለዚህ ምላሽ የሚሆን መፍትሄ መያዙን ገልጿል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እናት ፓርቲ በጉባዔው መስተጓጎል ምክኒያት ኪሳራ እንደደረሰበት አስታወቀ

እናት ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ እሁድ የካቲት 26/2015 ዓ.ም ሊያካሂደው የነበረው ጠቅላላ ጉባዔ በክልከላ ምክኒያት በመስተጓጎሉ ለ3 ሚልየን ብር ኪሳራ መዳረጉን ገለፀ። ፓርቲው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የጠራቸውን አባላቱን ጨምሮ 700 ሰው መጉላላት እንደደረሰበት አስታውቋል። ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ የአዳራሽ ውል ስምምነት ፈጽሞ የነበረው ቅድስተ ስላሴ ዩኒቨርሲቲ ከተባለ ተቋም ጋር እንደነበር ገልፆ በስብሰባው ሰዓት ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው በሚል ወደ ውስጥ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ከተቋሙ ምላሽ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተወካዮች የፓርቲውን ጉባዔ ለመታዘብ በቦታው እንደነበቱ የገለፀልን ኮምዩኒኬሽን ቦርዱ ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን አስታውቋል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት የሰጠንን ስልጣን አንቀበልም !

በትግራይ በሚቋቋመው የጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋሚያ ሰነድ የካቢኔ ወንበር ከተመደበላቸው ፓርቲዎች ሁለቱ ሥልጣኑን አንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። ሥልጣኑን አንቀበልም ያሉት ሳልሳይ ወያነ ትግራይና ውድብ ናፅነት ትግራይ የተባሉ ፓርቲዎች “የተያዘው መንገድ የሕዝባችንን መከራ የሚያራዝም ነው” ብለዋል፡፡ በክልሉ የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ ክፍፍል ሰነድ ይፋ የተደረገው ለሁለት ቀናት በመቀሌ ከተማ የተካሄደው ጉባኤ ሲጠናቀቅ ነው። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአማራ ክልል ከሦስት ሚሊዮን በላይ ህጻናት የትምህርት ዕድል እንዳላገኙ ተገለፀ

በአማራ ክልል በቅድመ አንደኛ ደረጃ እንዲሁም በአንደኛና መካከለኛ ደረጃ መማር ከሚገባቸው ህጻናት ውስጥ ከ3.2 ሚልዮን የሚልቁት ትምሕርት ቤት መገኘት እንዳልቻሉ የክልሉ ትምሕርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ጨምሮ፣ በተፈጥሮ አደጋ፣ በወረርሽኝና በቂ የትምህርት ተቋማት ባለመኖራቸው በርካታ ተማሪዎች በትምሕርት ዕድሜያቸው ማግኘት የሚገባቸውን ትምህርት እያገኙ አለመሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡ አሁን ያለው የጸጥታ ችግርና መፈናቀል ልጆቻችንን ወደ ትምህርት ቤት እንዳይልኩ እንቅፋት እንደፈጠረባቸው ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየት የሰጡ ወላጆች ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ቤት በመቆያቸው በመጠለያ ጣቢያ መኖራቸው እንደሚያሳዝናቸው የተናገሩም ህጻናት አሉ፡፡ ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዋስ እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው ወንጌላዊ ቢኒያም ከእስር አልተፈቱም

ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከነበረው ችግር ጋራ በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት መሄዱን ጠበቃቸው ገለጹ። ጥር 14/2015 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተፈጥሮ ከነበረው ችግር ጋራ በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የካቲት 3/2015 ዓ.ም የተያዙት ወንጌላዊ ቢኒያም ሽታዬ፣ ፖሊስ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ወንጀል ጠርጥሪያቸዋለሁ በሚል ፍርድ ቤት አቅርቧቸው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ከ33 ጠበቆቻቸው መካከል አንዱ ጠበቃና የህግ አማካሪ ብሩክ ደረጀ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡ የካቲት 17 ቀን ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የ5,000 ብር ዋስትና አስይዘው እንዲወጡ ቢፈቀድም ፖሊስ ይግባኝ በማቅረብ በእስር ላይ እንዳቆያቸውም የገለጹት ጠበቃው፣ ጉዳያቸው አሁን ወደ አዲስ አበባ ፍርድ ቤት ወርዶ እየታየ መሆኑንም አብራርተዋል፡ በተለያዩ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዋስትና ቢፈቀድላቸውም፣ ፖሊስ በፌዴራል ደረጃ ባሉ ፍርድ ቤቶች ያለውን ይግባኝ ካጠናቀቀ በኋላ፣ ዛሬ ጉዳዩን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ምድብ ችሎት ወስዶት እዚያም ዋስትና ተፈቅዶላቸው ፖሊስ ይግባኝ ማቅረቡን ከጠበቆቻቸው አንዱ ጠበቃ ብሩክ ደረጀ ተናግረዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በፈረሱ ቤቶች ላይ የምትመሰረተው “ሸገር” ከተማ

በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ስር የሚገኙ አምስት ከተሞችና አንድ ወረዳ ተጨፍልቀው አዲስ የተመሰረተችው ሸገር ከተማ፡ “ለነዋሪዎች ምቹ ትሆናለች” ሲሉ የክልሉ ፕሬዚዳንት ተናገሩ። ይሁን እንጂ ነዋሪዎች የከተማዋን መመስረት ተከትሎ ለዓመታት የኖሩባቸው ቤትች እየፈረሱባቸው መሆኑን በመግለፅ አቤቱታ እያሰሙ ነው። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት ከአማራ ክልል የማረኩት እንጂ የዘረፍኩት ተሽከርካሪዎች የሉም አለ !

– የተማረኩ እንጂ የተዘረፉ ተሽከርካሪዎች የሉም – ትግራይ ክልል በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተሽከርካሪዎቻቸው እንደተዘረፉባቸው የሚናገሩ ባለንብረቶች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ፡፡ “በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦቻችንን የምናስተዳደርባቸው ተሸከርካሪዎቻችን በመዘረፋቸው ለከፋ ችግር ተጋልጠናል” ሲሉ በአማራ ክልል ኮምቦልቻና ቃሉ ወረዳ የሚኖሩ ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ። “ተሸከርካሪዎቻችን ትግራይ ውስጥ መኖራቸውን አረጋግጠናል” የሚሉት ከ50 የሚበልጡ ቅሬታ አቅራቢዎች መንግሥት የሰላም ሥምምነቱን ከተፈራራመ የተዘረፉ ንብረቶችንም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል። የትግራይ ክልል ትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ ደግሞ “የተማረኩ’’ ሲሉ የገለጿቸውን የግለሰብ ተሸከርካሪዎች ለባለንብረቶቹ መመለስ ፖሊሲው እንደሆነ ጠቅሶ ለዚህም ፌዴራል መንግሥቱና ክልሎች በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው አመልክቷል። በአንፃሩም ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ከትግራይም የተዘረፉ ከስድስት ሺህ በላይ ተሸከርካሪዎች እንዳሉ ቢሮው ገልፆ ለማስመለሱ ፌዴራል እገዛ እንዲያደርግ ጠይቋል። ከ77 በላይ የግለሰብና የመንግሥት ተሸክርካሪዎች በጦርነቱ ተዘርፈዋል የሚለው የአማራ ክልል መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት በበኩሉ የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጥያቄ ለመመለስ የአቅም ውስንነት እንዳለበት ገልጾ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ተቋማት ጉዳዩን እንዲያውቁት ማድረጉን ጠቁሟል፡፡ /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ደቡብ ኦሮሚያ የድርቁ ጫና አሁንም እየከፋ ነዉ

በኦሮሚያ ክልል ደቡባዊ ክፍል ድርቁ ያስከተለው ጫና የከፋ መሆኑን የጉጂ ዞን አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ልቤን ደበሶ በዞኑ በድርቅና በፀጥታ ችግር ምክኒያት ለችግር የተጋለጡ ከአምስት መቶ ሰባ ሺህ በላይ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበርያ ቢሮም፣ በድርቅ የተጠቁ የኢትዮጵያ ክልሎች በኮሌራ ወረርሺኝም እየተጎዱ መሆኑን አስታውቋል። በሌላ በኩል ለአምስት ተከታታይ ወቅቶች ዝናብ ባለመኖሩ ምክኒያት የተባባሳው የቦረና ድርቅ እስካሁን 3.3 ሚልየን እንስሳት መጨረሱን የዞኑ አስተዳደር ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል። ቦረና ውስጥ ድርቅ መበርታቱንና ነዋሪዎቹ በምግብ እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውን ጠቅሰን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። በተጨማሪም ወደ ስምንት መቶ ሺህ የሚሆን ሰው የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገውና ከእነዚህም ውስጥ አዛውንቶችና ሕፃናት በረሃብ እየተጎዱ መሆናቸውና የሚደርሰው የእርዳታ እህልም እጅግ አነስተኛ መሆኑን የቦረና ዞን ድሬ ወረዳ ነዋሪዎችና በአካባቢው የሚሰሩ የጤና ባለሞያ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ድምፅ መናገራቸው አይዘነጋም። የዘገባውን ሙሉ ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Ethiopian News

የኦነግ አባላት እስር “ከሕግ አግባብ ውጭ ነው” ሲል ኢሰመኮ አስታወቀ

በኦሮምያ ክልል ቡራዩ ከተማ እሥር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ አመራር አባላት ሳይፈቱ የቆዩት “ከሕግ አግባብ ውጭ ነው” ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። ከታሳሪዎቹ መካከል የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ከኔሳ አያ እና ከፍተኛ የአመራር አባል ዳዊት አብደታ በጠና መታመማቸውን የጠቆሙት የሕግ ጠበቃቸው ደንበኞቻቸው የሕክምና አገልግሎት መነፈጋቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጥገና የተደረገለት የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ቤት ተመረቀ

በተለምዶ አጠራሩ “አሜሪካን ግቢ” እየተባለ በሚታወቀው የአዲስ አበባ ሰፈር የሚገኘው እና የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ መኖሪያ ኾኖ ያገለገለው ቤት፣ የጥንት ይዞታውንና ቅርጹን በጠበቀ አኳኋን ጥገና ተደርጎለት ተመረቀ። የዳግማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ምኒልክ የጦር ሚኒስትር የነበሩት እና በምክር ዐዋቂነታቸው እና በአመራር ፈሊጣቸው “አባ መላ” በመባል የሚታወቁት ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት፣ በወራሪው ፋሽስት ኢጣልያ ዘመን፣ ከ700 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ሕይወት ከእልቂት የተረፈበት ሥፍራ እንደኾነም አንድ የታሪክ ተመራማሪ ተናግረዋል። የዘገባውን ሙሉ ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለዓመታት የኖሩበት ቤት እየፈረሰባቸው መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

ሸገር ከተማ በሚል እንደ አዲስ እየተዋቀረ በሚገኘው ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ስር በሚገኙ አካባቢዎች ለዓመታት መኖራቸውን የጠቀሱ ነዋሪዎች ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ቤታቸው እየፈረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል። በደረሰባቸው በደል ማዘናቸውን የገለፁ የገጣፎ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች፣ አግባብ ባልሆነና ብሔርን በለየ አካሄድ ያለምንም ማስጠንቀቂያ መንግሥት ቤታቸውን እንዳፈረሰባቸው ተናግረዋል። “በዚህም ምክኒያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል” ብለዋል። ስለጉዳዩ የተጠየቁት የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ “እያፈረስን ያለነው የግንባታ ፈቃድ የሌላቸውን ነው” ብለዋል፡፡ ብሔርን የለየ ቤት ማፍረስ እንዳልተደረገ የገለፁት ዶ/ር ተሾመ ቤቶቹ ከመፍረሳቸው በፊት በቅድሚያ ከነዋሪዎቹ ጋር ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ በሸገር ከተማ ስላለው የቤቶች ፈረሳ ጉዳይ መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በበኩሉ ለነዋሪዎቹ ምትክ ሥፍራ ወይም ጊዜያዊ ማቆያ ሥፍራ ሳይዘጋጅ ቤታቸው መፍረሱ ተገቢነት የሌለው መሆኑን ገልፆ፣ አንዳንዶቹ ፈረሳዎች የሕግ ሥነ ሥርዓትን ያልተከተሉና ከመንግሥት በኩል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ የታከለባቸው ናቸው ብሏል። የዘገባውን ሙሉ ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ተመላሽ ተፈናቃዮች ዳግም የመፈናቀል ስጋት ተጋርጦባቸዋል

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወደ ቀያቸው የተመለሱ የክልሉ ነዋሪዎች በቂ ድጋፍ ባለማግኘታቸው ዳግም የመፈናቀል አደጋ ስጋት እንደተጋረጠባቸው ገለፁ። የክልሉ መንግሥት ተፈናቅለው ከነበሩ መካከል መካከል ከ26 ሺህ ውጪ አብዛኛዎቹ ወደየአካባቢያቸው መመለሳቸውን ቢያስታውቅም ለተመለሱ ተፈናቃዮች ድጋፍ መስጠት እንዳልቻለ አስታውቋል። ዜጎች እየተጎዱ መሆኑንና ጠቅሶ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደርግ ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጥያቄ ማቅረቡን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ትውልደ ኤርትራዊውን የራፕ ሙዚቃ ኮከብ የገደለው ሰው ቅጣት ተፈረደበት፡፡

ፋይል - ራፐር ኒፕሲ ሀስል እ.አ.አ በመጋቢት 29፣ 2018 ኦክላንድ፣ ካሊፎርኒያ ውስጥ የቅርጫት ኳስ ግጥሚያ ሲመለከትእ.አ.አ በ 2019 ዓመተ ምህረት ትውልደ ኤርትራዊውን የራፕ ሙዚቃ ኮከብ በመድረክ ስሙ ኒፕሲ ሀስል ወይም ኤርሚያስ አስገዶምን ሎስ አንጀለስ ከተማ መንገድ ዳር በጥይት የገደለው ሰው ትናንት ረቡዕ የ60 ዐመት እስራት ቅጣት ተፈረደበት፡፡ ኤሪክ ኤ ሆልደር ሎስ አንጀለስ በሚገኘው በራፐሩ የልብስ መደብር ደጃፍ ላይ በፈጸመበት ግድያ እና ወንጀሉንም የፈጸመው በጥይት በመሆኑ በሃምሳ ዐመት እስራት እንዲቀጣ የሎስ አንጀለስ ወረዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ኤች ክሌይ ጃክ ፈርደውበታል፡፡ ግለሰቡ ኒፕሲ ሀስልን ተኩሶ በገደለበት ወቅት በአቅራቢያው የነበሩ ሌሎች ሁለት ሰዎች በጥይት በማቁሰሉ ደግሞ በተጨማሪ የ10 ዐመት እስራት እንዲቀጣ ዳኛው ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡ በአንድ ወቅት የአንድ የወሮበላ ቡድን ተቀላቅሎ እንደነበረ የሚነገረው የራፕ ሙዚቃ ዘፋኙ ኒፕሲ ሀስል የተገደለው በሰላሳ ሶስት ዐመቱ ነው፡፡ በራሱ የልብስ መደብር ፊት ለፊት የተፈጸመበት ግድያ ያደገበትን የሎስ አንጀለስ አካባቢ ማህበረሰብ እና ታላቅ ዝና ያተረፈበትን ሙዚቃ ሙያውን ባልደረቦቹን እና እንዲሁም የመጣበትን ማህበረሰብ በሚጠቅሙ ሥራዎቹ የሚያደንቁትን እጅግ እንዳሳዘነ የሚታወስ ነው ፡፡ ኒፕሲ ሀስል ከህልፈቱ በኋላ እ አ አ በ2020 ዐመተ ምህረት “ራክስ ኢን ዘ ሚድል” እና “ሀየር” በሚባሉት ስየራፕ ስልቶቹ የግራሚ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጥቁር ልብስ ምክኒያት ከሥራ የታገዱ ሰዎችን ጉዳይ የቤተክርስቲያኒቷ ሕግ ቡድን እየተከታተለው ነው

በኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተፈጥሮ ከነበረው ችግር ጋራ በተያያዘ ከሥራ የታገዱ ሠራተኞችን ጉዳይ እየተከታተለ እንደሚገኝ የቤተክርስቲያኗ የሕግ ቡድን አስታወቀ። ከታገዱ ሠራተኞች መካከል አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የሰጡ አንዲት ግለሰብ፣ መፍትሔ ካላገኙ ቤተሰባቸው ለችግር እንደሚጋለጥባቸው ተናግረዋል፡፡ የቤተክርስቲያኗ የሕግ ቡድን አባል ዲያቆን ዘካሪያስ ወዳጅ፣ በሥራቸው ላይ ችግር የተፈጠረባቸውን ሰዎች እያገኙ በማናገር ላይ መሆናቸውንና ችግሩ በአስተዳደራዊ መንገድ ካልተፈታ ወደ ሕግ እንደሚወስዱት ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡ በተያያዘ ዜና፣ ፖሊስ ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ኅብረተሰቡን ለሽብር በማነሳሳት ወንጀል ጠርጥሪያቸዋለሁ ያላቸውን መምህር ምህረተአብ እና ወ/ሪት ፌቨንን ጨምሮ በእነርሱ መዝገብ ስር የነበሩ ሌሎች ሦስት ተጠርጣሪዎችን ከእሰስር መልቀቁም ታውቋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በተከሰተው ድርቅ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ሰብዓዊ ቀውስ ሊያጋጥም ይችላል ተባለ

በአፍሪካ ቀንድ ለስድስተኛ ተከታታይ ወቅት ዝናብ ላይጥል እንደሚችል በመገመቱ በቀጠናው አስከፊው ድርቅ ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት ተቀስቅሷል። የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ እና በቀጠናው የአየር ንብረትን የሚቆጣጠር አንድ ተቋም ባወጡት ማስጠንቀቂያ ይጥላል ተብሎ ከሚጠበቀው በእጅጉ ያነሰ ዝናብ ስለሚኖር አስከፊውን ድርቅ የበለጠ ሊያባብሰው እንደሚችል አመላክተዋል። ከአስር አመት በፊት በሶማሊያ ብቻ 260 ሺህ ሰዎች ከሞቱበት የከፋ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ሲልም ስጋቱን ገልጿል። የአየር ትምበያዎች በዚህ በያዝነው የ2015 ዓ.ም ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባለው የዝናብ ወቅት መጣል የነበረበት ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ እና ከፍተኛ ሙቀት እንደሚኖር ማመላከታቸውን የልማት፣ አየር ትንበያ እና አፈፃፀም ማዕከል በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ICPAC) አስታውቋል። በአብዛኛው የአፍሪካ ቀንድ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለው ወሳኝ የዝናብ ወቅት ከዓመታዊ አጠቃላይ የዝናብ መጠን እስከ 60 በመቶውን የሚሸፍን ሲሆን ፤ ሁኔታው ሚቲኦሮሎጂ ባለሞያዎች እና የእርዳታ ተቋማት በቀጠናው ለረጅም ግዜ በቆየው አስከፊ ድርቅ ሳቢያ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ሰብዓዊ ቀውስ ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ ያስጠነቀቁትን ፍራቻ የሚያረጋግጥ ነው። አይፓክ በመግለጫው “ድርቁ ባጠቃቸው የተወሰኑ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ዩጋንዳ አካባቢዎች ዝናብ ለስድስተኛ ተከታታይ ወቅት ላይጥል ይችላል” ብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲኦሮሎጂ ኢንስቲትዩት በበኩሉ ባለፉት ተከታታይ ወቅቶች በድርቅ ተጠቅተው ከቆዩ አካባቢዎች መካከል አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ከመደበኛ በታች የሆነ የበልግ ዝናብ ሊያገኙ ይችላሉ የሚል ትንበያ አስቀምጧል። በሌላ በኩል አክሽን አጌንስት ሀንገር የተሰኘው በአፍሪካ ቀንድ ረሃብን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“የአፍሪካን ነፃ ገበያ ንግድ ትግበራው ቀላል አይሆንም” አቶ ክቡር ገና

የአፍሪካ ኅብረት በተያዘው የአውሮፓውያን ዓመት ለነፃ ንግድ ቀጣና መተግበር ትኩረት እንደሚሰጥ በአዲሱ ሊቀመንበሩ በኩል አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ሲካሔድ የቆየው የኅብረቱ መደበኛ ጉባዔ ሲጠናቀቅ፣ አዲሱ ሊቀመንበር አዛሊ አሱማኒ በአፍሪካ የነፃ ንግድ እንዲቀላጠፍ በትኩረት እንደሚሠራበት ተናግረዋል። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ባለሞያ ደግሞ “የነፃ ንግድ ትግበራው ቀላል አይሆንም” ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ንግድ ምክርቤቶች ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክቡር ገና ሲናገሩ፣ “በየሀገራቱ ያለው የመገበያያ ገንዘብ ልዩነት፣ የጉምሩክ አሠራር፣ የሎጂስቲክስና የመሰረተ ልማት ችግሮች በአህጉሩ የነፃ ንግድ ቀጣናን ለመተግበር ፈታኝ ያደርጉታል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነቱ የበለጠ ተጠቃሚ የሚሆኑት ትልቅ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገሮች ስለሆኑ፣ አካሔዱ ጥንቃቄ የሚፈልግ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተመድ መርማሪዎች ቡድን የሰላም ጥረቱን ያጨናግፋል ስትል ኢትዮጵያ አስጠነቀቀች

ተመድ ያቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን ውል እንዲቋረጥ ኢትዮጵያ ሐሳብ አቀረበች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት በተደረገው ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር መነሳቱ ባለፈው ጥቅምት ከተፈረመው የሰላም ሥምምነት ወዲህ የታዩ መሻሻሎችን ያስተጓጉላል ስትል ኢትዮጵያ አስጠንቅቃለች፡፡ “በተመድ ለኢትዮጵያ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን በአፍሪካ ኅብረት የተመራውን የሠላም ሂደትና በፕሪቶሪያ የተፈጸመውን የሠላም ሥምምነት በመርዛማ ትርክት የሚበክል ነው” ሲሉ የኢትዮጵያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑ በአገሪቱ ተቋማት እየተደረገ ያለውን ጥረትም ያዳክማል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አዲስ አበባ ላይ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ ኅብረት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ መናገራቸውን ኤኤፍፒ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ትዊተር ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በተመድ የተቋቋመው ኮሚሽን ባለፈው መስከረም ባወጣው የመጀመሪያ ሪፖርት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመፈጸማቸው ማስረጃ እንዳገኘ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚሽኑን ሪፖርት ውድቅ አድርጓል፡፡ ሶስት ዓባላት ያሉት የተመድ ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ኤርትራ እና ህወሓት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን እንዲመረምሩና ጥሰት ፈጻሚዎቹንም ለፍርድ እንዲያቀርቡ መጠየቁ ይታወሳል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ የነበሩ መንገደኞች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገለፁ።

ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ የነበሩ መንገደኞች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገለፁ። ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት ተጓዦቹ “የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነችው ጎሃ ፂዮን አካባቢ ስንደርስ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች እንድንመለስ አድርገውናል” ብለዋል፡፡ የካቲት 2 እና 3/2015 ዓ.ም የአማራ ክልል መታወቂያ የያዙ ተጓዦችን ብቻ ለይተው ይመልሱ እንደነበርና ከአርብ ወዲህ ግን ሁሉንም ተጓዦች መከልከላቸውን መንገደኞቹ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ተጓዦች ደጀን ከተማ ላይ እየተጉላሉነው መሆኑንም አስተያየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከፌዴራል መንግሥት መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ባይሳካም፣ የኦሮሚያ ክልል አተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ፣ “የተዘጋ መንገድ የለም” ብለዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሰመጉ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈፀሙን አስታወቀ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ጋራ በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አስታወቀ። ኢሰመጉ በክልሉ ተፈጽመዋል ካላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መካከል “በሻሸመኔ ከተማ ከመንግሥት የጸጥታ አካላት በተተኮሱ ጥይቶች የሰዎች ህይወት ማለፉን” በመረጃዎች አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ አጠቃላይ ስለደረሰው የጉዳት መጠን አልገለጸም፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ገመቹ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት፣ ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ ስለጉዳት መጠኑ እንደሚገልጹ ተናግረዋል፡፡ በተያያዘ በቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ መሰረት በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ትላንት የተጀመረው ጥቁር ልብስ የመልበስ ተግባር ዛሬም አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች የቀጠለ ሲሆን፣ ኢሰመጉ በዛሬው መግለጫው፣ “ከልብሱ ጋራ በተያያዘ በአንዳንድ አካባቢዎች ምዕመናን እስራት፤ እንግልት እና ወከባ እየደረሰባቸው ነው” ብሏል፡፡ ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ መንግሥታቸው በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ገለልተኛ መሆኑን ቢገልጹም፣ ቤተክርስቲያኗ በበኩሏ መንግት “በሕገወጥነት የፈረጅኩትን አካል” እየደገፈ ነው ስትል ትከሳለች፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በዛሬው መግለጫው፣ “የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅና ያልሰጣቸው አዲስ የተሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት ወደ አብያተክርስቲያናት ሲገቡ በመንግሥት የጸጥታ አካላት ጭምር ታጅበው ነበር” ብሏል፡፡ ኃይማኖት የማኅበራዊ መስተጋብር አንዱ ክፍልና መብት በመሆኑ በመረዳት፣ “መንግሥት በቤተክርስቲያን እውቅና ያልተሰጣቸውን ኤጲስ ቆጶሳት በተለያዩ አብያተክርስቲያናት መመደብ አግባብ አይደለም” በማለት የተቃወሙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ላይ የጸጥታ አካላት የሚፈጽሙትን ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ግድያ፣ አካል ማቁሰል፣ ድብደባ እና እስር፤ አንዲሁም ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎች
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኢትዮጵያ ተፈናቃዮችን ጎበኙ

ፎቶ ፋይል፦ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛው ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኡም ራኩባ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛው ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኢትዮጵያ ስደተኞችን እና ተፈናቃዮችን ጎበኙ። ከትናንት በስተያ ዕሁድ ኢትዮጵያ የገቡት የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛው ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ከኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን ወደትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ተጉዘው በጦርነቱ ሳቢያ የተፈናቀሉ ቤተሰቦችን ጎብኝተዋል። በአማራ ክልል ዓለምዋች የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ያሉ ኤርትራዊያን ስደተኞችንም ጎብኝተዋል። ለሁለት ዓመታት በተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ኤርትራዋያን ስደተኞች የተነጣጠረ ጥቃት ሲደርስባቸው የነበረ ሲሆን ባለፈው ታህሳስ ወር የተባበሩት መንግሥታት የስድተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመተባበር 7 ሽህ ኤርትራውያን ስደተኞችን ከምዕራብ ትግራይ ወደ አለምዋች ካምፕ ማዛወሩን ዘገባው አውስቷል። የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ለማቆም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ የረደዔት ድርጅቶች በጦርነት ወደተጎዱት አካባቢዎች የበለጠ ዕርዳታ ለማጓጓዝ መቻላቸውን የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነሩ ፊሊፖ ግራንዲ በትዊተር ባወጡት ቃል ተናግረዋል። ወደትግራይ ክልል የሚገባው ዕርዳታ አቅርቦት የተሻሻለ ቢሆንም አሁንም ካለው ከባድ ችግር አንጻር በቂ አለመሆኑን አንድ የመንግሥታቱ ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኦነግ ሸኔ ከ800 በላይ የጤና ኬላዎች እና ከ150 በላይ የጤና ጣቢያዎች በላይ አወደመ

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክኒያት ከ800 በላይ የጤና ኬላዎች እና ከ150 በላይ የጤና ጣቢያዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የፀጥታ ችግር ባለበት አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ተገቢውን የጤና አገልግሎት እንደማያገኙ የገለፁ ሲሆን የጤና ባለሞያዎችም ተገቢውን ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት መቸገራቸውን ይናገራሉ። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት ቤተክርስቲያኒቷን ከሚከፋፍል አካሄድ ይታቀብ

ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሪ አባቶችና ምዕመናን ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ፤ “መንግሥት ቤተክርስቲያኒቷን ከሚከፋፍል አካሄድ ይታቀብ” ሲሉ ጠይቀዋል። ቁጥራቸው የበዛ ኢትዮጵያውያን እና ትወልደ ኢትዮጵያ በተሳተፉት በዚሁ ሰልፍ ላይ፤ ጉዳዩ ተካሮ ደም አፋሳሽ እንዳይሆን ከወዲሁ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ አሳስበዋል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ትላንት በጹሑፍ ባወጣው መግለጫ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በውስጣዊ አሠራር መፈታት እንዳለበት መንግሥት ያምናል” ብሏል። ችግሩን ለማባባስ፣ በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ብሎም ሀገርን ወደ ፈተና ለማስገባት ይጥራሉ ባላቸው አካላት ላይ መንግሥት ‘የህግ ማስከበር’ ያለውን ሥራ እንደሚሠራ አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር ሥርዓት ሊመሰረት ነው

ከፌዴራሉ መንግሥት በጀት ለማግኘትና የትግራይ ክልል ፖለቲካዊ ሁኔታ በዘላቂነት ለማሻሻል በቅርቡ አዲስ የሽግግር ሥርዓት እንደሚኖር የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኙትን ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ ዞኖችን ለማስተዳደር የክልሉ አስተዳደሮች ወደ አካባቢዎቹ እየተመለሱ ነው መሆኑን ክልሉ አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተፈናቃዮች ቁጥር በአማራ ክልል መጨመሩን ተመድ አስታወቀ

በአንዳንድ የአማራና የኦሮምያ ክልል አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክኒያት መፈናቀል በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በበኩሉ ከአጎራባች ክልሎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር 1.2 ሚልየን መድረሱን ገልፀዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቡርጂ እና በጉጂ ተወላጆች መካከል የነበረው ግጭት በዕርቅ ተቋጨ

በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶያማ ከተማ ውስጥ ስምንት ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች ሃያ ሰዎች መቁሰላቸውን ተከትሎ በቡርጂ እና በጉጂ ተወላጆች መካከል ለወራት ይሰማ ነበር የተባለው “ቂም ትናንት በተካሄደ እርቅ ተቋጭቷል” ሲሉ የሁለቱ አካባቢዎች ባለሥልጣናትና ነዋሪዎች ገልፀዋል። “ሰዎችን በማንነታቸው እየለዩ ገድለዋል” ተብለው የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሬ አለማየሁ አስታውቀዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ኤርትራን ጎበኙ

በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የተመሩ ከፍተኛ ልዑካን በኤርትራ የአንድ ቀን ጉብኝት ለማድረግ ምጽዋ የገቡ ሲሆን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሚኻዬል ቦግዳኖቭም አብረዋቸው ተጉዘዋል፡፡ ልዑካኑን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳልህ ፕሬዚዳንታዊ አማካሪው የማነ ገብረ መስቀል በኤርትራ የሩስያ አምባሳደር ኢጎር ሞዝጎ እና ሌሎችም ከፍተኛ የኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናት በምጽዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ላቭሮቭ በቆይታቸው ከኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነቶች ስለማጠናከር እንዲሁም የሁለቱ ሀገሮች ትኩረት በሆኑ የቀጣናው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተው የአንድ ቀን ጉብኝታቸውን ማጠናቀቃቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል፡፡ President Isaias Afwerki received at State House today Russian delegation led by Foreign Minister Sergei Lavrov. The discussions centered on the dynamics of the war in Ukraine & enhancement of bilateral ties on sectors of energy, mining, information technology. education & health pic.twitter.com/Ax5Shac3JC — Yemane G. Meskel (@hawelti) January 26, 2023
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኦነግ ሸኔ ደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን ገደብ ከተማ ላይ ጥቃት ፈፀመ

ባለሥልጣናቱ “ኦነግ ሸኔ” የሚሉት “የኦሮሞ ነፃነት ጦር” እንደሆነ የሚናገረው ቡድን “ገደብ ከተማ ውስጥ አድርሶ አምስት ሰው ገድሏል” ሲል በደቡብ ክልል የጌዴዖ ዞን አስተዳደር አስታውቋል። ቡድኑ ባለፈው ዕኩለ ሌሊት “ከተማዪቱ ገብቶ ጥቃት ከፍቷል” ሲሉ የዓይን እማኞች መሆናቸውን የጠቆሙ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ቨርጅንያ፤ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙት የቡድኑ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ለአሜሪካ ድምፅ አፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል በሰጡት ምላሽ ቡድናቸው ፈፅሟል የተባለውን ጥቃት አምነው “እርምጃ የወሰድነው ፌደራልና የክልሉ ኃይሎች በሚጠቀሙበት የወታደር ካምፕ ላይ ነው” ብለዋል። ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፅንስና የሚወለዱ ህፃናት ሞት ተመዝግቦባታል

የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት ደራሽ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ በህፃናት ሞት ላይ ያተኮሩ ሁለት ሪፖርቶችን በቅርቡ አውጥቷል። ባለፈው የአውሮፓ የ2021 ዓ.ም. የህፃናት ሞት አኀዛዊ መረጃዎችን በገመገመበት ሪፖርቱ በዓመቱ ውስጥ በየዘጠኝ ሴኮንዱ ሁለት ህፃናት መሞታቸውንና ወደ ሁለት ሚሊየን የሚጠጋ ቁጥር ያላቸው ደግሞ አንድም ማህፀን ውስጥ ሳሉ ወይም በምጥ ወቅት እንደሚሞቱ ገልጿል። እንዲህ ዓይነት በፅንስና በሚወለዱ ላይ ከሚደርሰው አደጋ ግማሹ የሚደርስባቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት ሀገሮች መሆናቸውን የዩኒሴፍ ሪፖርት ይናገራል። የአዲስ አበባ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የማህፀንና የፅንስ ህክምና መምህር ፕሮፌሰር ድላየሁ በቀለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከተያያዘው ፋይል ያገኙታል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እስካሁን የፖሊስ ኃይል በየትኛውም የኃይማኖት ተቋም ላይ ተመድቦ የሚጠብቅበት አሠራር የለም – የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ሰሞኑን ተሰጠ በተባለው የ”ጳጳሳት ሹመት” ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ውሣኔ ያሳልፋል የተባለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ጀምሯል ። በሌላ በኩል በቤተክህነት በርና በአካባቢው ጥበቃ ላይ ነበሩ ያሏቸው የፖሊስ አባላት መነሳታቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒው ዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ገልፀው መንግሥት ፀጥታ እንዲያስከብር ጠይቀዋል። ይሁን እንጂ “እስካሁን የፖሊስ ኃይል በየትኛውም የኃይማኖት ተቋም ላይ ተመድቦ የሚጠብቅበት አሠራር የለም” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ሥጋት መኖሩን የሚጠቁም መረጃ ከደረሳቸው ግን ወንጀልን ከመከላከል ተግባራቸው ጋር አቀናጅተው እንደሚይዙት ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲዋን ልትቀይር ነው

ላለፉት 28 ዓመታት ሲሠራበት የቆየውን የትምህርት ፖሊሲ ለመቀየር አዲስ ረቂቅ መዘጋጀቱ ተሰምቷል፡፡ ረቂቁ ከፀደቀ አዲሱ ፖሊሲ እስከ 10ኛ ክፍል የነበረውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ 12ኛ ክፍል እንደሚመልሰው ተነግሯል። ተማሪዎች ቢያንስ ሦስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ እንደሚደረግም ረቂቁ ያሳያል። የባለሙያዎችን ትችትና አስተያየት ያካተተውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚልየን መጠጋቱ ታወቀ

ከኦሮምያ ክልል አራቱም ዞኖች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር አንድ ሚልየን መጠጋቱን የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክተር ጌቴ ምህረቱ ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በድጋሚ በተቀሰቀሰው ግጭት ከአራቱም የኦሮምያ ክልል ዞኖች ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር በየዕለቱ መጨመሩን ተናግረዋል። ትናንት ሰኞ ጥር 15/2105 800 ተፈናቃይ ባህር ዳር መግባቱን ገልፀዋል። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች ከሁለት እስከ አራት ሳምንት የፈጀ የእግር ጉዞ አድርገው ባህር ዳር መድረሳቸውን ተናግረዋል። በኦሮምያ ክልል በቀጠለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ንጹሃን ዜጎች በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ ወደ አማራ ክልል እየተፈናቀሉ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ጠቁሟል። ለዝርዝሩ ዘገባው የተያያዘውን ፋይል ይመልከቱ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ፣ ከሚታዩ ለውጦች ጋር ተያይዞ ሊነሳ አሊያም ሊጨምር ይችላል – አሜሪካ

የትግራይ ክልል ም/ቤት የአመራር ለውጥ እንዲደረግ መወሰኑን ክልሉ አስታወቀ፤ ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ክልሉን በፕሬዚዳትነት እየመሩ ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ባቀረቡጥ ጥያቄ መሰረት መሆኑ ታውቋል፡፡ የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ በፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ፤ “የአመራር ለውጥ ያስፈለገው ወቅታዊውን ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለሽግግሩ እና ለሰላም ድርድር የሚስማማ ካቢኔ ማዋቀር አስፈላጊ በመሆኑ ነው” ብሏል። በሌላ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እየወጡ እንደሚገኙ መረጃ እንዳላት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ተናገሩ፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ፣ ከሚታዩ ለውጦች ጋር ተያይዞ ሊነሳ አሊያም ሊጨምር እንደሚችልም ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ስላገረሸው ጦርነት የመቀሌ ነዋሪዎች አስተያየት

ግጭቱ የሰላም መፍትሄ እንዲያገኝ እንደሚፈልጉ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ተፈናቃዮች እና አንዳንድ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። [ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው ።

በአማራና በአፋር ክልሎች የግንባር አካባቢዎች ቁጥሩን አረጋግጦ ለመናገር የማይቻል ብዛት ያለው ሰው እየተፈናቀለ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ማምሻውን ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ተናግረዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል። በአማራ ክልል ደባርቅ፣ ደሴና ወልድያ ላይ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት የሰዓት እላፊ ገደብ በመጣሉ በሲቪሎች እንቅስቃሴ ላይ ጫና ማሳደሩን፣ የህክምናና የንግድ አገልግሎቶችን ለማግኘትም እክል መፍጠሩን ቃል አቀባዩ አክለው ጠቁመዋል። ወደ ትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በየብስ ማድረስ ካለፈው ረቡዕ፤ ነኀሴ 18 አንስቶ የተቋረጠ መሆኑንና ከማግስቱ ነኀሴ 19 አንስቶ ደግሞ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች የአየር አገልግሎት ወደ መቀሌ ለመብረር አለመቻሉን፣ በዚህም ጥሬ ገንዘብ ማድረስና ተለዋዋጭ ሠራተኞችን ማሠማራት አዳጋች እንደሆነበት ዱጃሪክ ተናግረው ድርጅቱ የፀጥታና ደኅንነት ሁኔታው በፈቀደ መጠን መንግሥታዊ ካልሆኑ አጋሮች ጋር በመተጋገዝ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ ለማድረስ መጣሩን እንደሚቀጥል አመልክተዋል። ትግራይ ውስጥ ሰብዓዊ አጋሮች ምግብና ሌሎችም አስፈላጊ አቅርቦቶችን ማከፋፈል እንደገና መጀመራቸውን ቃል አቀባዩ ገልፀዋል። ዛሬም ለስደስተኛ ቀን ቀጥሎ በዋለው የሰሜን ጦርነት “ህፃናት እንዳይጎዱ በከፍተኛ ጥንቃቄና ኃላፊነት ግዳጄን እየተወጣሁ ነው” ሲል ፌዴራል የመከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። የህወሃት ኃይሎች “ህፃናትንና ሴቶችን ከፊት አሰልፈው እየተዋጉ ናቸው” ሲል ከሷል። የህወሓት መሪዎች ህፃናትን ወደ ጦር ግንባር ማሠማራትን አስመልክቶ ከዚህ ቀደምም ይቀርቡባቸው የነበሩ መሰል ውንጀላዎችን በተደጋጋሚ ሲያስተባብሉ የቆዩ ሲሆን አዲስ በቀረበባቸው ክስ ላይ እስካሁን በይፋ የተሰማ ምላሽ የለም። ለጦርነቱ መጀመር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የውጭ የገንዘብ ኩባንያዎችን ለማስገባት የፋይናንስ አዋጅ ማሻሻያ እየተደረገ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

የውጭ የገንዘብ ኩባንያዎችን ለማስገባት የፋይናንስ አዋጅ ማሻሻያ እየተደረገ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓት በኅብረተሰቡ ዘንድ የፋይናንስ ተደራሽነትን እንደሚያሰፋ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በቅርቡ ኢትዮ-ቴሌኮም ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር ያስጀመረው የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትም አነስተኛ ብድር ለሚፈልጉ የንግድ ተቋማት ትልቅ ዕድል ይዞ እንደመጣ ይገልፃሉ። ይህ ሥርዓት በተለመደው የባንክ አሠራር ተጠቃሚ ያልሆኑትን የንግድ ሥራዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለማካተት እንደሚያስችል ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል። ዘርፉ ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገበት ችግር ሊያስከትል እንደሚችል የተነገረ ሲሆን በተጠቃሚው ዘንድም በአገልግሎቱ ላይ ዕውቀት ማስጨበጥ እንደሚያስፈልግ ቪኦኤ ያነጋገራቸው የኢኮኖሚ ባለሙያ ገልፀዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንድ የቡርጂ ተወላጅ ተገደለ ተብሎ ዘጠኝ የጉጂ ተወላጆች መገደላቸውን ተከትሎ ውጥረቱ ተባብሷል።

በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶየማ ከተማ ውስጥ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም በምዕራብ ጉጂ ዞን ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በሃገር ሽማግሌዎች መፍትሔ አለማግኘቱን ገለፁ። በኦሮምያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች አንድ የቡርጂ ተወላጅ ገድለዋል መባሉን ተከትሎ በተጠቀሰው ቀን ዘጠኝ የጉጂ ተወላጆች ከተገደሉ በኋላ በአካባቢው የተፈጠረው ውጥረት እስካሁን አለመብረዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ። ምእራብ ጉጂ ዞን ሱሮ በርጉዳ ወረዳ ወሌና ቦኮሳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ደንቦበ ቅርጫ፤ “የሰው ሕይወት በአካባቢው ከጠፋ ወዲህ የእርስ በእርስ ግንኝነቶች ተቋርጠዋል” ብለዋል። ግብይት በመቋረጡም በሁለቱም በኩል ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸውን ገልፀው፤ ከዚህ ቀደም በተገባላቸው ቃል መሰረት ችግሮቹ በሽምግልና እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የቡርጂ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ ጉዳዩን በቅርቡ እንደሚፈታ ተናግረዋል። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሚሰጠው ድጎማ መቋረጥ በተማሪዎች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዞን ዳህና ወረዳ የሚገኙ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከመንግሥት የሚሰጣቸው ድጎማ በቋረጡ መቃብር ቤት ለማደርና ለምኖ ለመኖር መገደዳቸውን አስታወቁ፡፡ አካል ጉዳተኞቹ “ከአምስት ወር በላይ ሊሰጠን የሚገባው ድጎማ ተቋርጦብናል፡፡ ከመንግሥት አካልም የተሰጠን ምላሽ እስካሁን የለም” ብለዋል። የብሔረሰብ ዞኑ ትምህርት መምሪያ የተፈጠረውን ችግር አምኖ በአዲሱ በጀት ዓመት ክፍያቸውን ለመክፈል እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የእርዳታ እህል የጫኑ የጭነት መኪናዎች የሚተላለፉባት አፋር በመተላለፊያው መንገድ ዳርና ዳር የሚኖሩት ነዋሪዎች የሚበሉት የላቸውም ልጆቻቸው እየሞቱ ነው

ከጅቡቲ ወደ ትግራይ የሚሄዱት የእርዳታ እህል የጫኑ የጭነት መኪናዎች በኢትዮጵያ አፋር ክልል ያልፋሉ፣ ሆኖም በመተላለፊያው መንገድ ዳርና ዳር የሚኖሩት ነዋሪዎች የሚበሉት እንደሌላቸው እና ልጆቻቸው እየሞቱ መሆኑን ይገልፃሉ። በስፍራው የሚገኘው ባልደረባችን ሄነሪ ዊልኪንስ በድርቅ እናጦርነቱ ባሳደረው ተፅእኖ ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ የገቡትን በአፋር ክልል ኢሬብቲ ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎችን እና “አፋር ክልል ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ድርቁ አስጊ ሁኔታ ውስጥ መሆኑመታወጅ አለበት” የሚሉ የእርዳታ ሠራተኞችን አነጋግሮ ያላከውን ዘገባ ነው። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የባይቶናውን አቶ ክብሮምን ጨምሮ 17 ሰዎች ያሉበት እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ገለፁ

ሐምሌ 3/ 2014 ዓ.ም ተይዘው በአቃቂ ቃሊቲ ፖሊስ መምሪያ ታስረው የነበሩት የባይቶና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ክብሮም በርኸ እና ሌሎች 17 ሰዎች የሚገኙበት እንዳልታወቀ ቤተሰቦቻቸው ገለፁ። እስረኞች የሚገኙበትን ቦታ ፖሊስ እንዲያሳውቅ እንዲታዘዝላቸው ለፍርድ ቤት ማመልከታቸውን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናገሩ። የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፖሊስ ስለዚህ ጉዳይ ምንም እንደማያውቁ ሲገልፁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ደግሞ ሁኔታውን እየተከታተለው መሆኑን ገልጿል። /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሁለቱ ወለጋ ዞኖች ከጭፍጨፋ የተረፉት እርዳታ እየጠየቁ ነው

በኦሮምያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በቅርቡ በታጣቂዎች ከተፈፀመ የብሄር ማንነት የለየ ጅምላ ግድያ የተረፉና መቻራ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተናገሩ። ወደ የመንደራቸው እንዲመለሱ የአካባቢው ባለሥልጣናት ቢጠይቋቸውም ተፈናቃዮቹ ግን የበረታ ሥጋት እንዳለባቸውና መመለስ እንደማይፈልጉ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። ጭፍጨፋውን ተከትሎ ከለምለም ቀበሌ ውስጥ በሥጋት ተፈናቅለው ከነበሩ ቁጥራቸው ወደ ሃያ አምስት ሺህ ከሚጠጋ ሰዎች ብዙዎቹ መመለሳቸውን ቀደም ሲል የክልሉ አደጋ መከላከል የነበረውና አሁን ስሙን ወደ ቡሳ ጎኖፋ ግን ገልጿል።  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአፋር ክልል ለተረጂዎች የሚሆን የእርዳታ አቅርቦት እጥረት እንዳለበት ገለፀ

የአፋር ክልል በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን እና ተፈናቃዮችን ለማገዝ የዕርዳታ አቅርቦት እጥረት እንዳለበት ገለፀ፡፡ የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ለቪኦኤ በሰጠው ማብራሪያ፣ ለክልሉ ተረጂዎች እየደረሰ ያለው እርዳታ በብዛትና በጥራት አነስተኛ በመሆኑ፣ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ተገቢውን ምላሽ ካልሰጡ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል በመግለፅ አስጠንቅቋል፡፡ በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩት 336 ሺህ ሰዎች ውስጥ እስካሁን ድረስ ዘጠና ከመቶ የሚሆኑትን ወደ ቀዬያቸው እንደተመለሱ የተናገሩት የጽ/ቤቱ ኃላፊ “እነሱም ቢሆኑ በአካባቢያቸው የነበሩት የአገልግሎት መስጫ ተቋማት በመውደማቸው ትኩረት ይሻሉ” ብለዋል፡፡ /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የደሕንነት ስጋት ቢኖርም ኤፍራታ ግድምና ጅሌ ጥሙጋ እየተረጋጉ ነው

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች አጎራባች አካባቢዎች ሰሞኑን በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል። ይሁን እንጂ “ሸኔ” ሲሉ የጠሯቸው ታጣቂዎች ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሰው የደኅንነት ሥጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጀውና ባለሥልጣናቱ “ሸኔ” የሚሉት “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” እንደሆነ የሚናገረው ቡድን “በሰላማዊ ሰዎች ግድያ ላይ እጁ እንደሌለበት” በዓለምአቀፍ ቃል አቀባዩ መሆናቸው በሚገልፁ ተጠሪው በኩል ሲያስተባብል መቆየቱ ይታወሳል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ ክልል 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ህዝብ ለአጣዳፊ የምግብ እጥረት መጋለጡ ተነገረ

በደቡብ ክልል በድርቅ፥ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክኒያት 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ህዝብ ለአጣዳፊ የምግብ እጥረት ተጋልጡዋል ሲል የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ቪኦኤ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች በዝናብ እጥረት እና በሁከት ምክኒያት ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናግረዋል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“መንግሥት የዜጎችን ግድያ ለማስቆም የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠል አለበት” የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት

የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገሪቱ ሰላም ለማስፈን እና የዜጎችን ግድያ ለማስቆም የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሳስቧል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በበኩሉ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚደረገው ድርድር እና ምክክር ሁሉን አቀፍ ሊሆን እንደሚገባው ገልጿል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሶማሊያው ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ለአራት ቀናት ያደረጉትን ቆይታ አጠናቀው ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 5 ረፋድ ላይ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በጋራ ለመሥራት በሰባት ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አዋሳኝ ቦታዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ሕይወት ጠፋ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረደ አዋሳኝ ቦታዎች ትናንት በተቀሰቀሰው ግጭት ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለፁ። ከሁለቱም አስተዳደር ዞኖች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለግጭቱ መቀስቀስ የተለያዩ ምክኒያቶችን ሰጥተዋል። አንደኛው ወገን መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራውና በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡንድ ነው ሲል ሌላኛው ደግሞ የመንግሥትን ታጣቂዎች ተጠያቂ ያደርጋል። ከመንግሥት በኩል መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የድሬዳዋ ከተማ ወደ ክልልነት ፤ ከንቲባዋም ወደ ርዕሰ መስተዳደርነት ሊቀየሩ ነው

በረቂቅ ሰነዱ ላይ ድሬዳዋ የከተማ አስተዳደር ሳይሆን “ድሬዳዋ አስተዳደር” ተብላ እንድትጠራ የታሰበ ሲሆን መሪዋም “ከንቲባ” ሳይሆን “ርዕሰ መስተዳድር” ይባላል ተብሏል። በገቢ አሰባሰብ በኩልም የፌዴራል መንግሥቱ ከድሬዳዋ ከሚሰበስበው ገቢ የተወሰነው ለድሬዳዋ ገቢ እንዲሆን ታስቧል። በአስተዳደሩ ከማዕከልና ቀበሌ ባሻገር የወረዳ መዋቅርም የሚኖር ሲሆን የፖሊስ ኮሚሽን እና ምርጫ 97ትን ተከትሎ ወደ ፌዴራል መንግሥቱ ተዛውረው የነበሩ የተዛወሩ ተቋማት ተጠሪነታቸው ለድሬዳዋ አስተዳደር እንዲሆን የቻርተሩ ረቂቅ ይጠይቃል። በሌላ በኩል አብላጫውን የአስተዳደር ምክር ቤት ወንበር ከከተማው ነዋሪ በግማሽ ያነሰ ቁጥር ላላቸው የገጠር ቀበሌዎች የደለደለው ነባሩ የምክር ቤት አባላት ቁጥርና አወካከልን በተመለከተ በአዲሱ ረቂቅ ላይ በግልጽ የተባለ ነገር የለም። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/ —
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው” – የትግራይ አርሶአደሮች

በዘንድሮ ክረምት በትግራይ ክልል ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ባለመኖሩ፤ ምርታቸው በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንስ እንደሚችል የሰጉ አርሶ አደሮች በአሁኑ ወቅት ሰላም እንዲመጣ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። በክልሉ ምስራቃዊ ዞን ፀአድ አምባ እና ስቡሃሳሴ በተባሉ አካባቢዎች አግኝተን ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች፤ ጦርነት ቆሞና ሰላም ተፈጥሮ መደበኛ ኑሮአቸውን ለመቀጠል እንደሚናፍቁ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ትግራይ ክልል ዙሪያውን ተዘግቶ ነዋሪዎቿም ጽግር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። /ዘገባው የሮይተርስ ነው ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/
Posted in Ethiopian News

በአፋር ተይዘው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ሞት፣ ሕመም፣ ችግር መቀጠሉ ተሰማ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “ህገወጥና የዘፈቀደ እሥራት” ሲል በጠራው ሁኔታ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች አሁንም በበረታው የወቅቱ ሞቃት የአየር ጠባይና በበሽታ ምክንያት እናቶችና ህፃናት እየታመሙ መሆናቸውንና የሰዎች ሞትም መቀጠሉን ለቪኦኤ ገልፀዋል። ይኖሩበት ወደ ነበረው አካባቢ እንዲመለሱ እንዲደረግም ጠይቀዋል። በሌላ በኩል “የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የውጭ ግንኙነት ፅህፈት ቤት” መሆኑን የሚናገረው ቢሮ በመላ ሃገሪቱ “በማንነታቸው ምክንያት በጭካኔ ተይዘዋል” ሲል የገለፃቸውና “በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ” ያላቸው የትግራይ ተወላጆች እንዲፈቱ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርግ ጥሪ አድርጓል። የፌዴራልና የክልል ባለሥልጣናትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ባይሳካም የአፋር ክልል መንግሥት ባለሥልጣናት በቅርቡ ሰጥተዋቸው የነበሩ አስተያየቶችንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን መግለጫዎች መልዕክት አካትቶ የትግርኛ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረባ ገብረ ገብረመድህን ያጠናቀረውን ሪፖርት ቆንጂት ታየ ታቀርበዋለች። ሙሉውን ከተያያዘው ዘገባ ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኮንሶ በምግብ እጥረት ስምንት ሕፃናት ሞቱ

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በምግብ እጥረት ምክኒያት ስምንት ሕፃናት መሞታቸውን የካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስታወቀ። በምግብ እጥረት የተጎዱ ሌሎች ከአራት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ በሆስፒታሉ የሕክምና እርዳታ እንደተደረገላቸው የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አማረ ገርሞ ተናግረዋል። የዞኑ ግብርና መምሪያ በዞኑ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ለቪኦኤ ተናግረዋል። ሙሉውን ከተያያዘው ዘገባ ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በተለያዩ አካባቢዎች የሚሰሙ ግድያዎች “ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው?” የሚል ስጋትና ፍርሃት አሳድሯል

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ከተፈፀመው የብሄር ማንነት የለየ ጅምላ ግድያ ጨምሮ በየጊዜው በተለያዩ አካባቢዎች የሚሰሙ ግድያዎች “ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው?” የሚል ስጋትና ፍርሃት አዘል ጥያቄ ብዙዎች እንዲጠይቁ እያደረገ ነው። በኢትዮጵያ በሲቪሎች ላይ በተከታታይ የሚፈጸመውን ግድያና የመንግሥትን ኃላፊነት አስመልክቶ አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ኃላፊን አነጋግረናል። በጉዳዩ ላይ የመንግሥት ተወካዮችን ለማነጋገር ያደርገው ጥረት አልተሳክም።
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ብልፅግና እና ሕወሓት በአደራዳሪዎች ጉዳይ ለመግባባት አልቻሉም ተባለ ።

የብልፅግና መንግሥት ከህወሓት ጋር የሚደረግ የሰላም ድርድር “በአፍሪካ ኅብረት ሸምጋይነት መካሄድ አለበት” የሚለውን አቋሙን በዚህ ሳምንት በድጋሚ ቢያስታውቅም ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በበኩሉ በአፍሪካ ኅብረት ላይ እምነት እንደሌለው ገልፆ ድርድሩ “በኬንያ ሸምጋይነት ይካሄድ” በሚለው አቋሙ እንደፀና ነው። የሰላም ንግግር ተስፋና ሁለቱ ወገኖች አሁን የገቡበትን አጣብቂኝ በተመለከተ የቪኦኤው ሪፖርተር ሄንሪ ዊልክንስ አዲስ አበባ ላይ ተንታኞችንና ፖለቲከኞችን አነግሯል። ሙሉውን ከተያያዘው ዘገባ ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በ300 ሰዎች፣ በ 72 የፌዴራል ፖሊስና የልዩ ኃይል አባላትና አራት ባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደራሼ ምክንያት ባለሥልጣናትና ሌሎችም ታሠሩ በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ ውስጥ ለህይወት መጥፋትና ለንብረት ውድመት ምክንያት በሆነ በቅርቡ የተፈጠረ ሁከት ጠርጥሬአቸዋለሁ ብሎ በያዛቸው 300 ሰዎች ላይ የከፈተውን ምርመራ ማጠናቀቁን የክልሉ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል። መደበኛ እንቅስቅሴ እያደረጉ መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ የተናገሩ ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ አመልክተዋል። ልዩ ወረዳውን በዞን ለማደራጀት ከሚቀርበው ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳ ሁከትና በተፈፀመ ጥቃት 72 የፌዴራል ፖሊስና የክልል ልዩ ኃይል አባላትና አራት ባለሥልጣናት መገደላቸውን ቢሮው ለቪኦኤ ገልፆ በምርመራው የደረሰበት ደረጃ ክሥ ለመመሥረት እንደሚያስችለው ጠቁሟል። /ዝርዝሩን ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ውጥረት አለ

ከሁለት ሳምንት በፊት በቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶየማ ከተማ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት የሀገር ሽማግሌዎች በጥረት ላይ መሆናቸው ተነግሯል። አባ ገዳ ጅሎ መንዶ ከአካባቢው ማኅበረሰብ የተውጣጡ የተለያዩ ሰዎችን ተቀብለው ማነጋገራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የቡርጂ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ጥቃቱን ተከትሎ ወስጃለው ባለው እርምጃ ከሰባ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ውሎ ለፍርድ እያቀረበ መሆኑን ቢገልፅም ነዋሪዎቹ ግን አሁንም በአካባቢው ውጥረት እንዳለ ይገልፃሉ። ከሁለት ሳምንት በፊት በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ዘጠኝ ሰዎች በድንጋይና በዱላ ተወግረው ተገደሉ ፡፡ ግድያው የተፈጸመው በልዩ ወረዳው ሶያማ ከተማ በሚገኝ የገበያ ሥፍራ ነው ፡፡ የዶቼ ቬለ DW ታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጡት ከሟቾቹ በተጨማሪ ሃያ አንድ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ

ባለፈው ቅዳሜ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በመጨመር ላይ መሆኑን፣ ከጥቃቱ የተረፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ጥቃቱን በማውገዝ ባወጧቸው መግለጫዎች፣ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በተካሔደ 6 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ዘመቻ ማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ መከላከያ ሰራዊት ከትናንት ጀምሮ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጸው መላው ኅብረተሰብም እንዲተባበር ጠይቀዋል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኤርትራ መንግሥት እስካሁን የትግራይን ክልል አካባቢዎች ተቆጣጥሮ ይዟል ይህንንም ለቆ ሊወጣ ይገባል – ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል

ከፌዴራል መንግሥት ጋር እስካሁን የተጀመረ ድርድር እንደሌለ ትግራይ ክልልን በማስተዳደር ላይ የሚገኙት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ገለፁ። የትግራይ ክልል ሕዝብ ሳያውቅ እና ሳይወስን የሚያካሂዱት ድርድር እንደሌለም ተናግረዋል። ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለትግራይ ክልል መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ “የኤርትራ መንግሥት እስካሁን የትግራይን ክልል አካባቢዎች ተቆጣጥሮ ይዟል” ብለዋል። “ይህንንም ለቆ ሊወጣ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል። ብለዋል። በሌላ በኩል ትናንት ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ሰላምን ማውረድ እንደሚፈልግ ገልፀው ይህንን በስኬት ለማጠናቀቅ የሚረዳ ስለ ጉዳዩ ጥናት የሚያደርግ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። በግንቦት አጋማሽ መግለጫ ያወጣው የኤርትራ መንግሥት በበኩሉ ህወሓት በአፍሪካ ቀንድ ቀውስ ለመፍጠር በኤርትራ ላይ ጦርነት አውጇል ሲል መወንጀሉ ይታወሳል። /ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቡርጂ ውስጥ በጉጂዎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ያወገዘ ሰልፍ ተካሄደ

በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶያማ ከተማ ገበያ ውስጥ ለገበያ በተሰበሰቡ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ያወገዘ ሰልፍ ዛሬ መካሄዱን የወረዳው ነዋሪዎች እና የልዩ ወረዳው ባለሥልጣናት ገለፁ። “ድርጊቱ አስነዋሪና አሳፋሪ ነው” ያሉት የሶሮ በርጉዳ ወረዳ አስተዳደር ድርጊቱን የፈፀሙ ግለሰቦችን ለሕግ ለማቅረብ እና ለተበደሉ ቤተሰቦች ፍትሕ ለመስጠት እየሠራ መሆኑን ገልጿል። /ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በባሌ ዞን መጣል ጀምሮ የነበረው የበልግ ዝናብ በመቆሙ ሰብል ደረቀ

በባሌ ዞን ቆላማና ወይና ደጋ አካባቢዎች መጣል ጀምሮ የነበረው የበልግ ዝናብ በመቆሙ ሰብል እየደረቀ መሆኑን ገበሬዎች ተናግረዋል። ከተቋረጠ አንድ ወር እንደሞላው የተናገሩት የደሎ መና ወረዳ ገበሬዎች እርጥበቱ ካልተመለሰ ሰብላቸውን እንደሚያጡ ሥጋታቸውን የገልፁ ሲሆን ድርቀቱ ከመቶ በላይ የገጠር ቀበሌዎችን እንደሚሸፍን የባሌ ዞን ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አልይ መሐመድ አመልክተዋል። አካባቢውን ተዘዋውሮ የተመለከተው ገልሞ ዳዊት ዝርዝሩን ይዟል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የደረሰውን ድብደባ ጉዳይ እያጣራን ነው – የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

የፍትሕ መጽሔት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለለኝ ዛሬ በፖሊሶች ድብደባ እንደተፈፀመበት እና ፊቱ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ቤተሰቦቹ እና ጠበቃው ገለፁ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ምላሽ፣ ስለሁኔታው ማጣራት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዘገባው የኬኔዲ አባተ ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጉህዴን ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸውን ክልሉ አስታወቀ

– እጅ ከሰጡት ውስጥ የታሰሩት ብዙ ናቸው ብሏል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት በመተከል ዞን ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ከ1200 በላይ የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጉህዴን/ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጥተው ከኅብረተሰቡ ጋር መቀላቀላቸውን አስታወቀ። የክልሉ ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ እንደገለፀው፣ ያለጸጥታ ኃይል እጀባ የመጓጓዣ አገልግሎት በዞኑ ውስጥ መጀመሩንም አስታውቋል። በሌላ በኩል ጉህዴን፣ “በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጥተው የገቡ 110 ታጣቂዎች ታስረውብኛል፤ የመንግሥት ኃይሎች ተኩስ እየከፈቱ ነው እንዲሁም የነዋሪዎችን ቤት እያቃጠሉ ነው” ሲል አቤቱታ ያሰማ ሲሆን የሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ “ይህ ፍረጃ ተገቢነት የሌለው ነው” ሲሉ አስተባብለዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሶማሌ ክልልን የኑሮ ውድነት መንግሥት እንዲመለከተው ነዋሪዎች ጠየቁ

የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የኑሮ ውድነት ከአቅማቸው በላይ መሆኑን በመግለፅ፣ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ። በአብዛኛው በውጭ ምንዛሪ የሚገዙ ሩዝ እና ፓስታ የመሳሰሉ የምግብ ሸቀጦችን ተመጋቢ የሚበዛበት ክልል በመሆኑ፤ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱና የጥቁር ገበያ ዋጋው መናር የክልሉን ሕዝብ ለከፍተኛ ዋጋ ውድነት ተጋላጭ እንዳደረገው ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። የክልሉ ካቢኔ በክልሉ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት ለመከላከል በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ የሚተገበሩ አራት ዋና ዋና ውሳኔዎችን መወሰኑን ያስታወቀ ሲሆን ከውሳኔዎቹም መካከል አንዳንድ በጀቶችን በማጠፍ ለመንግሥት ሠራተኞች እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ድጎማ ማድረግ የሚል ይገኝበታል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአቅርቦት እጥረት ምክኒያት አይደር ሆስፒታል ሥራ ማቋረጡን አስታወቀ

በትግራይ ክልል ትልቁ የጤና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከትናንት ማታ ጀምሮ ሥራ ማቋረጡን ገለፀ። ሆስፒታሉ በሕክምና መሳሪያዎች፣ መድኃኒት እና ነዳጅ እጦት ምክኒያት ሥራውን ማቆሙ አስታውቋል። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገብረስላሴ፤ ሆስፒታሉ በድንገተኛ ሕክምና ለሚመጡ የተወሰኑ ታካሚዎች ካልሆነ በስተቀር ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማይሰጡ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር በሀገሪቱ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ልዩ ልዩ ድጋፎች ማድረጋቸውን ባለፈው ሳምንት ማጠናቀቂያ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጾ ነበር። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ልዩ ልዩ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት የኮሚቴው የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፓትሪክ መጌቫንድ ባለፈው ሳምንት በ5ኛ ዙር በተላከ ድጋፍ መድሃኒት፣ ምግብና ቁሳቁሶች የጫኑ የእርዳታ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባታቸውን ገልፀው ነበር። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሠራተኞች ታስረው እንዲመረመሩ ፍ/ቤት ፈቀደ

የፍትሕ መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ኤዲተር ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ ባለፉት ጥቂት ቀናት በቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የዩቲዩብ ሚዲያ አዘጋጆች ውስጥ የተወሰኑት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ባለፈው ሐሙስ የታሰረው የፍትሕ መጽሔት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ከአስር ቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው “ገበያኑ” የተሰኘ የዩቲዩብ ሚዲያ መስራችና አዘጋጅ ሰለሞን ሹምዬ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ ባለፈው ዓርብ እና ቅዳሜ በቁጥጥር ስር የዋሉት የተለያዩ የዩቲዩብ ሚዲያዎች አዘጋጆች መዓዛ መሐመድ እና በቃሉ አላምረው ለመጀመሪያ ጊዜ መቅረባቸውን ጠበቆቻቸው ገልጸዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሐሙስ አመሻሽ ላይ ከሥራ ስትወጣ በፖሊስ ተይዛ የነበረችው፣ “የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ” ቴሌቪዥን የኦሮምኛ መዝናኛ ዝግጅት አዘጋጅ ሰቦንቱ አህመድ ዛሬ መለቀቋን የጣቢያው ዳይሬክተር ለሚ ታዬ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን በተከታታይ ባወጣው መግለጫ “የሚዲያ ባለሞያዎች እስር የሚዲያ ሕጉን የሚጻረር” መሆኑን በመጥቀስ ባለሙያዎቹ እንዲለቀቁ ጠይቋል፡፡ መንግሥት በበኩሉ የሚዲያ ባለሙያዎች እስር ሕግ የማስከበር እርምጃ አካል መሆኑን ነው የገለጸው፡፡ በሌላ ዜና ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ ሞክረዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው በባሕር ዳር ታስረው የሚገኙት የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ ዛሬ ለሁለተኛ ግዜ ፍ/ቤት ቀርበው፣ ፖሊስ ለምርመራ ተጨማሪ 10 ቀን እንደተፈቀደለት ጠበቃቸው ሸጋው አለበል ገልጸዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከማዕከላዊ ጎንደር የተፈናቀሉ ወደቀያቸው እየተመለሱ መሆኑ ተገለፀ

ባለፈው ዓመት ከማዕከላዊ ጎንደር፣ ጭልጋ ወረዳ፣ አይከል ከተማ ተፈናቅለው ጎንደር አዘዞ የነበሩ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ መጀመሩን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስታወቀ። ተፈናቃዮቹ እየተመለሱ ያሉት ከኃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከምሑራን እና ከሌሎች የኅብረተስብ ክፍሎች ተውጣጥቶ የተቋቋመ ምክር ቤት ከነዋሪዎች ጋር ባደረገዉ ምክክር ከስምምነት ላይ በመደረሱ መሆኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠቅሷል። ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሲመለሱ በከተማው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበልበመደረጉ የተደሰቱት ተፈናቃዮች ተከስቶ የነበረው ግጭት የጥቂት ፖለቲካ ነጋዴዎች ሴራ ነው ብለውታል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በወረቀት ዋጋ መናር እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ኢትዮጵያ ጋዜጣ የሌለባት ሀገር እንዳትሆን ያሰጋል

በወረቀት ዋጋ መናር እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት መንግስታዊው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በህትመት ዋጋ ላይ ከሰማኒያ ከመቶ በላይ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ የጋዜጦች ዋጋ ከእጥፍ በላይ መጨመሩን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አሳታሚዎች እና ጋዜጣ አዟሪዎች ተናግረዋል። የዋጋ ጭማሪው በጋዜጦችና መፅሄቶች የገፅ ብዛት እና የስርጭት መጠንም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ እያደረገ ሲሆን በዚህ ከቀጠለ ሀገሪቱ ጋዜጣ የማይታተምባት ሀገር ለመሆን እንደሚያሰጋት የሙያው ተንታኞች ተናግረዋል። ከአራት አመት በፊት ከፍተኛ ዋጋ ኖሮት ሰባት ብር ከሀምሳ ሳንቲም ይሸጥ የነበረው ሪፖርተር ጋዜጣ በየግዜው ዋጋ እየጨምረ ሄዶ ከሁለት ሳምንት በፊት 20 ብር ገብቷል። 6 ብር ከሀምሳ ሳንቲም የነበሩት ካፒታል እና ፎርቹን ጋዜጣም አሁን ዋጋቸው 20 ብር ነው። ከ15 እስከ 20 ብር ይሸጡ የነበሩ እንደ ፍትህ፣ ሀበሻ እና ግዮን የመሳሰሉ መፅሄቶችም እንዲሁ 25 ብር ገብተዋል። በግል ጋዜጦች እና መፅሄቶች ላይ የታየው ይህ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ዋና ምክንያቱ የመንግስት የህትመት ተቋም የሆነው ብርሃን እና ሰላም በህትመት ዋጋ ላይ ከ80 በመቶ ጀምሮ ጭማሪ ማድረጉን ለአሳታሚዎች በላከው ደብዳቤ በማስወቁ እንደሆነ የቁምነገር መፅሄት ዋና አዘጋጅ እና የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምራት ሀይሉ ገልፀዋል። አቶ ታምራት እንደሚሉት ጋዜጦች እና መፅሄቶች ከእጥፍ በላይ የሆነ የዋጋ ጭማሪ አድርገውም የህትመት ዋጋቸውን ለመሸፈን አይችሉም። የህትመት ዋጋ መናር በሀገር ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጦች እና መፅሄቶች ዋጋ እንዲጨምር ከማድረጉ በተጨማሪ የገፅ ብዛታቸው እና የስርጭት መጠናቸው በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በጦርነት የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ወደ መኖሪያቸው ለመመለስ የሚያስችል ሁኔታ እንደሌለ ተናገሩ

በአብዛኛው የኢትዮጵያ አፋር ክልል አካባቢ ሲካሄድ የቆየው ግጭት ቢቆምም፣ የትግራይ ሀይሎች ክልሉንከተቆጣጠሩ በኃላ ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ የአፋር ተወላጆች ግን ወደ መኖሪያቸው መመለስ አልቻሉም።በዚህ ጦርነት የተጎዱት የትግራይ ተወላጆች ብቻ ሳይሆኑ በአፋር ክልልም የተካሄደው ጥቃት መኖሪያ ቤቶቻቸውን እናመተዳደሪያቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዳወደመው ለስደት የተዳረጉ ሰዎች ይናገራሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በትግራይ ክልል ከሚካሄደው ግጭት ጋር ተያይዞ ወደ 700 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ባስታወቀበት የኢትዮጵያ አፍር ክልል ከሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች – ይህ አንዱ ነው። ከተፈናቃዮቹ የተወሰኑትም በዚህ ከክልሉ ዋና ከተማ ሰመራ በ100 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው መጠለያ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። የአፋር ክልል ከትግራይ ክልል ጋር ረጅም ግዜ የቆየ ቁርኝት ያለው በመሆኑ የህወሃት ሀይሎች ጥቃት ሲያደርሱባቸው፣ ለነዋሪዎቹ ያልጠበቁት ድርጊት ሆኖባቸዋል። ከተፈናቃዮቹ አንዷ ሀሊማ ጣሂር እስማኤል ስለሁኔታው እንዲህ ታስረዳለች። “ተኝተን ነበር። የከባድ መሳሪያ ተኩስ ሰማን። ስንነሳ የጦርነት ቀጠና ውስጥ ነበርን። ባሎቻችን እና ልጆቻችን ተበታተኑ። በመኖሪያችን ላይ በተከፈተው ከፍተኛ ተኩስ ምክንያት ቤታችንን ጥለን ተሰደድን።” ሀሊማ ከአምስት አመት በታች ከሆኑ ሶስት ልጆቿ ጋር ሆና ነው የተሰደደችው። ከጥቂት ልብሶች በስተቀር ምንም ነገር አልያዙም። አሁን ልክ እንደሌሎቹ ተፈናቃዮች የእርዳታ እጅ እየጠበቁ ይኖራሉ። የትግራይ ሀይሎች ጥቃት ባደረሱባቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች የቆዩ አንዳንድ ሰዎች እንደነገሯትም፣ መተዳደሪያዋ የነበረው የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ተዘርፎ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል። ኮናባ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቿ መኖሪያ ቤትም እንዲሁ ወድሟል። “አሁን እንዴት አርገን ወደ ኮናባ እንመለሳለን? ወደ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዲሱ ፕሬዚዳንት የተከፋፈለች እና ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧ በድርቅ የተጎዳባት ሶማሊያን ተረክበዋል

ከሳምንት በፊት በሶማሊያ በተደረገ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ የነበሩት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ትናንት በትረ ሥልጣናቸውን ሲረከቡ በሃገሪቱ ታሪክ በድጋሚ ተመልሰው የፕሬዚዳንትነቱን ወንበር የተረከቡ የመጀመሪያው መሪ ሆነዋል። እአአ ከ2012 እስከ 2017 ሃገሪቱን በፕሬዚዳንትነት መርተው የነበሩት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ትናንት በሃገሪቱ መዲና ሞቃዲሹ ውስጥ በተደረገ አጭር ሥነ ስርዓት መንበሩን በምርጫ ካጡትና “ፎርማጆ” በመባል ከሚታወቁት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ተረክበዋል። በሦስት ዙር በተደረገና ከፍተኛ ፉክክክር በታየበት ያለፈው ሳምንት ምርጫ የቀድሞውን የሃገሪቱ ፕሬዘዳንት ፎርማጆ ያሸነፉት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ በሃገሪቱ ታሪክ ተመልሰው ስልጣን የጨበጡ መሪ ሆነዋል። ሞሃመድ ዳይሴን ለቪኦኤ እንደዘገበው አጭር ግን ደማቅ በነበረውና በመዲናዋ ሞቃዲሾ በተደረገ ሥነ ስርዓት አዲሱ ፕሬዚዳንት መንበረ ሥልጣናቸውን ከተሸናፊው ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ በቅፅል ስማቸው “ፎርማጆ” ተረክበዋል። ፎርማጆ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የሶማሊያ ህዝብ አዲሱን ፕሬዚዳንት እንዲደግፍ ጥሪ አድርገዋል። “የሶማሊያ ህዝብ ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር እንዲሰራ እመክራለሁ፤ ምክንያቱም ምርጫው ተጠናቋል። ሥራቸውንም ይጀምራሉ፤ የሚሰሩት ሁሉ ለሶማሊያ ህዝብ ይሆናል” ብለዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፎርማጆ የሶማሊያ ወታደሮች በኤርትራ እንደሚገኙ ለመጀመሪያ ግዜ ይፋ አድርገዋል። ወታደሮቹ የተላኩት ለሥልጠና ቢሆንም በሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ተሳትፈዋል የሚል ክስ ሲቀርብባቸው ነበር። አዲሱ ፕሬዘዳንትም በሥነ ስርዓቱ ላይ በኤርትራ ስለሚገኙት የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ሲናገሩ “ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው። ሥልጣኑንም ሆነ የመንግሥት ዶሴዎችን በሰላም ተረክቤያለሁ። በኤርትራ የሚገኙ ሰልጣኝ ወታደሮቻችንም ወደ ሶማሊያ እንዲመለሱ እንሰራለን” ብለዋል። በኤርትራ የሚገኙት የሶማሊያ ወታደሮችን ቁጥር በተመለከተ እስከ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሐረሪ ክልል ጋዜጠኛ ሙህዬዲን አብዱላሂ በዋስ መፈታቱን ገለፀ

የሐረሪ ክልል ጋዜጠኛ ሙህዬዲን አብዱላሂሕዝብን በመንግስት ላይ አነሳስተሃል’ በሚል ጥርጣሬ ከሳምንት በላይ ታስሮ የቆየው የሐረሪ ክልል ጋዜጠኛ ሙህዬዲን አብዱላሂ በ2 ሺ ብር ዋስ መፈታቱን ገለፀ። በሀረሪ ቲቪ የኦሮምኛ የመዝናኛ ፕሮግራም አርታዒ ሙሄዲን ጎንደር ውስጥ በሙስሊሞች ላይ ተፈጽሞ የነበረውን ጥቃት በተመለከተ በግል ፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ ምክኒያት እንደታሰረም ገልጿል። እስካሁን ክስ እንዳልተመሰረተበት የሚናገረው ሙህዬዲን የተጠረጠረበት ወንጀል ሕዝብን በመንግስት ላይ ማነሳሳት እንደሆነ እንደተነገረው፣ ሆኖም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ ክሶች እንደቀረቡበት ተደርጎ መዘገቡን ተናግሯል። ለስምንት ቀናት በቁጥጥር ስር የቆዬው ጋዜጠኛው አመራሮች ቢሮ ድረስ ጠርተው የዋስትና ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችል ነግረውት ጥያቄውን ማቅረቡንና በታሰረ በዘጠነኛው ቀን በ2ሺ ብር ዋስ መፈታቱን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጿል። ግንቦት 17 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንዳለው እና የክሱ ሂደትም ገና በምርመራ ላይ እንደሚገኝም ተናግሯል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ደራሼ ውስጥ የጅምላ እስር እና አፈሳ መኖሩን ነዋሪዎች ገለፁ፤ ክልሉ አስተባብሏል

በደቡብ ክልል የደራሼ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የጅምላ እስር እና አፈሳ መኖሩን ገለፁ። እስሩ የኃይማኖት አባቶች እና ሸማግሌዎችን ጨምሮ ንፁህና እና ጥፋተኛውን እንደማይለይ በመግለፅም ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ቆስለው በጊዶሌ እና በአርባ ምንጭ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ የነበሩ ጉዳተኞች ጭምር መታሰራቸውን ጨምረው ገልፀዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በወረዳው በተከሰተው የፀጥታ ችግር እጃቸውን አስገብተዋል የተባሉ 330 ተጠርጣሪዎችን ወረዳውን የተቆጣጠረው ጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዙ ማሰሩን አስታውቋል። በወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉን እንጂ በአፈሳ ያሰሩት እንደሌለም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ገለፀዋል። “ከሕክምናቸውም አስነስተን ያሰርነው ወንጀልኛም የለም” ሲሉም አስተባብለዋል። የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተጨማሪ ዘገባ ልኳል።  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አበርገሌ ውስጥ በተከሰተው በሽታ የሕፃናት ሕይወት ማለፉን አርሶ አደሮች ገለፁ

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ በህወሓት ቡድን ቁጥጥር ሥር ይገኛል በተባለው አበርገሌ ወረዳ 12 ቀበሌ በተለምዶ ፅላሪ ጀርገብ እየተባለ በሚጠራ ቦታ ወረርሽኝ መከሰቱን በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች ገለፁ። በአሁኑ ወቅት በሰቆጣ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙት የአበርገሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ዓለሙ ክፍሌ በሽታው ከተከሰተ አምስት ቀናት ማለፉን ገልፀዋል። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኪዳት አየለ በወረርሽኙ ህጻናት እንደሞቱ ከአንድ ቀን በፊት ሪፖርት እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦነግ አመራሮች ከእስር እንዲፈቱ ኢሰመኮ ጠየቀ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች በሕገወጥ እስር ላይ ስለሚገኙ፣ ‘በአፋጣኝ እንዲፈቱ’ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለን ጠቅሶ መግለጫ ያወጣው ኮሚሽኑ “አመራሮቹ ለረጅም ግዜ ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ በመሆኑ በአፋጣኝ እንዲፈቱ እና ለደረሰባቸው ጉዳት እንዲካሱ” በማለት አሳስቧል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን መግለጫ በተመለከተ ከኦሮምያ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከኦሮምያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ግን ለግዜው አልተሳካም።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የደራሼ ግጭት በመባባሱ መንገድ ተዘጋ ፤ ነዋሪዎች በግጭቱ መስፋፋት ምክንያት ወደ ጫካ እየሸሹ ነው

በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ እና አከባቢው የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በመባባሱ መንገድ መዘጋቱና የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሉን የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እና መንገደኞች ተናገሩ። የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በግጭት ውስጥ የተሳተፉትን እና ያልተሳተፉትን ባልለየ መልኩ ሰዎችን በጅምላ ማፈስ ስለጀመሩ ነዋሪው ሸሽቶ ወደ ጫካ እየገባ መሆኑን ነዋሪዎቹ ጨምረው ገልፀዋል። በመንግሥት ላይ የሚቀረበውን ወቀሳ በተመለከተ ከክልሉ መንግሥትም ሆነ ከጊዜያዊ ወታደራዊ ዕዝ በኩል የተሰጠ አስተያየትም ሆነ የወጣ መግለጫ የለም። ዘገባውን ያሰናዳው ዮናታን ዘብዲዮስ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወደ ትግራይ እየገባ ያለው እርዳታ ከሚያስፈልገው አምስት በመቶ ብቻ መሆኑን ክልሉ ገለፀ

የተኩስ ማቆም ሥምምነት ከተደረገ ወዲህ ወደ ክልሉ 430 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መግባታቸውንንና ይህም የክልሉ ሕዝብ ከሚያስፈልገው 5 በመቶ ብቻ መሆኑን ትግራይ ክልል አስታወቀ። የክልሉ ገጠርና ግብርና ቢሮ አስቸኳም ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ገብረ እግዚያብሔር አረጋዊ፤ በአሁኑ ሰዓት የእርዳታ ፈላጊ ሰዎች ቁጥር መጨመሩንና በቅርቡ በተደረገ ዳሰሳ ጥናትም 6.5 ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ቢሮው ገልጿል። በሌላ በኩል በቅርቡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥናት በትግራይ ያሉ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 5.2 ሚሊዮን እንደሆነ፣ ወደትግራይም በረድዔት ሥራ ላይ የተሰማሩ 92 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዳሉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም የረድዔት ድርጅቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠሩን ተናግረው ነበር። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጀነራል ተፈራ ማሞ እስካሁን የት እንዳሉ ማወቅ አለመቻላቸውን የግል ጠባቂያቸው ተናገሩ

ጀነራል ተፈራ ማሞ እስካሁን የት እንዳሉ ማወቅ አለመቻላቸውን ባለቤታቸውና የግል ጠባቂያቸው ተናገሩ የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ ትናንት እረፋዱ ላይ ሰው ለማግኘት አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መውጣታቸውን የሚናገሩት ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይለማሪያም፤ ከቀኑ 10 ሰዓት በኋላ በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ቢደውሉም እንደማይነሳና ዛሬም ወደ ተለያዩ የፍትህ ተቋማት ቢሄዱም ምላሽ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል። “ትናንት ረፋዱ ላይ ከአቶ ዩሐንስ ቧያለው ጋር ቀጠሮ እንዳለውና እርሱን ለማግኘት እንደሚሄድ ነግሮኝ ነበር ከቤት የወጣው” ያሉት ወ/ሮ መነን “ሁሌ ስብሰባ ወይም ሌላ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ጉዳይ ሲኖረው ስልክ ደውሎ ወይም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ያለበትን ሁኔታ ያሳውቅ ነበት ትናንት ግን ይህን አላደረገም። ሁኔታው አላምር ሲለኝ ስልኬን አንስቼ ደጋግሜ ደወልኩ ስልኩ አይነሳም አቶ ዩሀንስ ጋር ደወልኩ እስከ 10:30 ድረስ አብረው እንደነበሩና ወደ መኪናው አስገብቶት እንደተለያዩ ነገረኝ ማታም የቅርብ ዘመዶቻችን ጋር ስደዋውል አየሁት የሚል ሰው አላገኘሁም” ብለዋል። ዛሬ ጠዋት ፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቢሄዱም ሊያገኟቸው እንዳልቻሉና በኋላም ወደ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ሲሄዱ በነገው ዕለት ወረቀት ጽፈው ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ እንደተነገራቸው ገልፀዋል። ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጦርነት ምክንያት ሻክሮ የነበረው የኢትዮጵያና የምዕራባውያን ግንኙነት በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለተወካዮች ም/ቤት ባቀረቡበት ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ሻክሮ የነበረው የኢትዮጵያና የምዕራባውያን ግንኙነት በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። “መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ፣ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት የሚያስችል እርምጃ በመውሰዱ እና መሰል ተግባራት ምክንያት ከምዕራባውያን ጋር መተማመን እየተፈጠረ ይገኛል” ብለዋል። ይሁን እንጂ ከሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ጋር በተያያዘ መሻሻሎች ቢኖሩም፣ አሁንም ችግሮች እንደሚስተዋሉ የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው። ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በሚል፣ ህወሃት ከአፋር ክልል ታጣቂዎቹን ሙሉ በሙሉ ማስወጣቱን የሚገልጹት የክልል አመራሮች በበኩላቸው ለችግሩ ተጠያቂ የሚያደርጉት የፌዴራሉን መንግሥት ነው፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት ወደ ክልሉ እየገባ ያለው እርዳታ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የትግራይ ክልል የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ መጠኑ ግን እጅግ አነስተኛ መሆኑን መግለፃቸው ይታወሳል። እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም እና ዩኤስኤአይዲ ያሉ ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችም በመንግስት በኩል ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር መሻሻሎች መኖራቸውን እና ወደ ትግራይ ክልል የሚገባው የድጋፍ አቅርቦት መጨመሩን ገልጸው፣ ሁኔታዎች ይበልጥ መሻሻል እንዳለባቸው ማመልከታቸው ይታወቃል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋው ባለው ድርቅ ተስፋ የቆረጡ ወላጆች ህጻናት ልጆቻቸውን እየዳሩ ነው – ዩኒሴፍ

“በኢትዮጵያ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋው ባለው ድርቅ ተስፋ የቆረጡ ወላጆች ህጻናት ልጆቻቸውን እየዳሩ ነው” ሲል የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ በዚህ ዓመት ያለ እድሚያቸው የተዳሩ ልጆች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩንም አስታውቋል፡፡ ይህን እድገት ለመቀልበስና ህጻናት ልጃገረዶችን ለመጠበቅ፣ የረድኤት ድርጅቶች፣ በድርቅ ለተጠቁ ቤተሰቦች፣ በጣም የሚያስፈልጋቸውን ውሃና ሌሎች እርዳታዎችን ለማግኘት እየጣሩ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፣ ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ ያልቻሉ ሰዎች እርዳታ ፍለጋ ወደ ተፈናቃይ ካምፖች እየፈለሱ ነው፡፡ ራሳቸውን በገቢ ደግፈው ለማቆየትም ማናቸውንም ነገር ያደርጋሉ፡፡ ናስቴሆ በኻር አብዲ ያገባቸው በ14 ዓመቷ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የቀደመው ባሏ እሷንና ሁለት ልጆችዋን መደገፍ ስላልቻለ በዚህ ዓመት ደግሞ ሌላ ሰው አግብታለች፡፡ ተፈናቃይዋ ሙሽሪት ናስቴሆ እንዲህ ትላለች፣ “ምን ማድረግ እችላለሁ? እንዳልሰራ ምንም ሙያ የለኝም፣ በዚያ ላይ አልተማርኩም፣ ልጆቼ እየተሰቃዩ ነው፡፡” 18 ዓመት ያልሞላቸው ልጃገረዶች ጋብቻ በባህልም ሆነ በአገሪቱ የተለመደ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት 40 ከመቶ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ሴቶች የተዳሩት 18 ዓመት ሳይሆናቸው መሆኑን ይገልጻል፡፡ ድርቁ ባስከተለው የመተዳደሪያ እጦት ግፊት፣ ያደረባቸው ወላጆች፣ ልጆቻቸውን መዳሩ፣ የአንድ ተመጋቢ አፍ ቀንሶ፣ የጥሎሽም ገቢ ስለሚያስገኝላቸው እንደ እፎይታ ይወስዱታል፡፡ በተባበሩት መንግሥታስት የህጻናት መርጃ ድርጅት፣ የሶማሌ ክልል የመስክ አገልግሎት ኃላፊ ኡትፓል ሞይትራ እንዲህ ይላሉ “ድርቁ እጅግ በጣም ባጠቃቸው አካባቢዎች፣ በወረዳዎቹ አደጋው የከፋ መሆኑን ይነገረናል፡፡ 63 ከመቶ ያህል ጨምሮ እናየው ነበር፡፡ በእርግጥ ይህ አሃዝ ትክክለኛ ላይሆን ይችላል፡፡ ከተለያዩ ወረዳዎች ማህበረሰቡን በማነጋገር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፕሮፌሰር አስመረት አስፋው ሹመት በመወሰኛ ም/ቤት ጸደቀ

ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊት ፕሮፌሰር አስመረት አስፋው የዩናይትድ ስቴትስ ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳይንስ ክፍል ኃላፊነት ሹመት በመወሰኛ ምክር ቤት ጸደቀ። የዩናይትድ ስቴትስ ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳይንስ ክፍል ኃላፊነት የታጩት ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊት ፕሮፌሰር አስመረት አስፋው ሹመታቸው በትናንትናው ዕለት በህግ መወሰኛ ምክር ቤት ጸድቆላቸዋል። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ በዕጩነት የቀረቡት በካሊፎርንያ ዩኒቨርሲቲ መርስድ መምሕርት እና ተመራማሪዋ የባዮኬሚስትሪ ትምህርት ክፍሉም ተተባባቂ ዲን የሆኑት ፕሮፌሰር አስመረት 54 በ45 በሆነ ብልጫ የሴኔቱን ድምፅ አግኝተው ሹመታቸው ጸድቆላቸዋል። ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊት ፕሮፌሰር አስመረት አስፋው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በትምህርቱ ጎራ ያሳደረው ጫና

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፉት አስርተ ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማያውቅ ያለው አፍሪካ ቀንድን የመታው አስከፊ ድርቅ በኢትዮጵያ ብቻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲያፈናቅል፣ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ሕጻናት ከትምህርት ገበታቸው እንዲስተጓጎሉ እና በመቶዎች የሚቆጠሩት ትምህርት ቤቶች ደግሞ እንዲዘጉ ምክኒያት መሆኑ ተዘገበ። ዓለም አቀፉ የረድኤት ድርጅት ሴቭ ዘ ችልድረን እርዳታ ቡድን፣ ያላቸውን ሁሉ ያጡ ወላጆች ከተጠለሉባችው የስደተኛ ካምፖች አቅራቢያ ሕጻናቱን በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚያሰባስቡ ማዕከሎችን ገንብቷል። አርብቶ አደሮችን እና በግብርና የሚተዳደሩትን በተመሳሳይ የነበራቸውን መተዳደሪያ ባሳጣቸው ድርቅ ሳቢያ ከ900 ሺ በላይ አባወራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ለመፈናቀል ተገደዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች በኢትዮጵያ በተለይም በገጠር እና ከከተሞች ራቅ ብለው በሚገኙ አካባቢዎች እጅግ ደካማ ናቸው። እንደ የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ግምገማም ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት የመጀመሪያ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያሸጋግግራቸውን ውጤት አያመጡም። በዚህም የተነሳ ከአጠቃላዩ 54 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ብቻ ናቸው ከስምንተኛ ክፍል የተሻገረ የትምሕርት ደረጃ የሚደርሱት።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደራሼ ወረዳ በተኩስ ልውውጥ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በደቡብ ክልል ደራሼ ወረዳ ውስጥ መሳሪያ ታጥቀው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች እጃቸውን እንዲሰጡና ትጥቃቸውን እንዲፈቱ በአካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የሰጠው ጊዜ ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ በመንግሥት ወታደሮችና በታጣቂዎቹ መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የልዩ ወረዳው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ነዋሪዎቹ ፈርተው ከአካባቢው በመሸሽ ጫካ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በአካባቢው የተቋቋመው ወታደራዊ ዕዝ ጥምር ኃይል ምክትል ሰብሳቢ ሌተናል ኮሎነል ፈጥነ ሲሳይ ታጣቂዎቹ የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ተጠቅመው እጃቸውን የማይሰጡ ከሆነ እዙ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቃቸውን የክልሉ የመንግትሥ ቴሌቪዥኝ ጣቢያ ዘግቧል። ዮናታን ዘብዲዮስ ዘገባ ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጎንደር ውስጥ ግጭት ያነሳሱና የወንጀል ድርጊት የፈፀሙ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ ተጠየቀ

ባለፈው ሚያዚያ 18 በጎንደር ከተማ ለበርካቶች ህይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደም እና ዘረፋ ምክንያት የሆነው ግጭት አስተዳደራዊ መሆኑን የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ። ከአዲስ አበባ ጎንደር የሄደው የልኡካን ቡድን ትናንት ሕዝባዊ ውይይት ያካሄደ ሲሆን ግጭቱ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ምክኒያት የተቀሰቀሰ ስለመሆኑ ከውይይቱ የተገኘው ሐሳብ እንደሚያስረዳ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል። ድብቅ አጀንዳ ያላቸው ቡድኖች ይህንንም ችግር እንደ አንድ መሳሪያ በመጠቀም ግጭቱን ስለማባባሳቸው በውይይቱ ላይ መነሳቱን ምክር ቤቱ ገልጾልናል። ከውይይቱም በኋላ በዚህ ግጭት ውስጥ በመሳተፍ፣ በመግደል በመዝረፍና ሌሎችንም ጥፋቶች በመፈፀም የተጠረጠሩ በሙሉ ለፍድር እንዲቀርቡ፣ ተጎጂ የኅብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸውና በአካባቢው የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ መወሰኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል። የከተማዋ አስተዳደር እስካሁን በድርጊቱ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ 250 የሚደርሱ ሰዎችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጿል። የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮችን፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ እና የከተማዋን ነዋሪዎች ያነጋገረው ዘጋቢያችን መስፍን አራጌ ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በግጭቱ የእስልምና እና የክርስትና ዕምነት ተከታይ የሆኑ የከተማይቱ ነዋሪዎች ተገለዋል – የጎንደር ከተማ አስተዳደር

ትናንት በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰዎች ህይወት፣ አካል ጉዳትና ንብረት ውድመት ምክንያት የሆኑ አካላት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡ በግጭቱ የሞቱና የተገዱ ሰዎችን አጣርቶ ይፋ እንደሚደርግም የክልሉ መንግሥት ትናንት ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር በበኩሉ በግጭቱ የእስልምና እና የክርስትና ዕምነት ተከታይ የሆኑ የከተማይቱ ነዋሪዎች መገደላቸውን አመልክቷል፡፡ በሌላ በኩል በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ቤተ እምነቶች ባስተላላፉት ጥሪ “መንግሥት ለንጹሃን ሞት ምክንያት የሆኑ ህገ ወጥ ተግባራትን ያስቁም” ብለዋል። “‘.. ማንም ይሁኑ ማን ድርጊቱን የፈጸሙ ወገኖችንም ተጠያቂ እንዲያደርግ” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ የመብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ገለፀ

የዩናዩትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው የሃገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በሚተነትነው እአአ የ2021 ዓመታዊ ሪፖርቱ፤ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናትና ታጣቂ ቡድኖች፣ ተፈጽመዋል ያላቸውን የሰብአዊ መብቶች ጥቃቶችን ዝርዝር አቅርቧል። ሪፖርቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት ከአምስት ወር በተካሄደው ግጭት እንዲሁም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በመንግሥት እና በተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ደረሱ ያላቸውን የመብት ጥሰቶችና ጥቃቶችን ዘርዝሯል። ሪፖርቱ በመንግሥት አካላት ደረሱ ካላቸው መሰረታዊ የመብቶች ጥሰቶች መካከል፣ ከሕግ ውጭ በዘፈቀደ በመንግሥት የተፈጸሙ ግድያዎች፣ የሰዎችን ደብዛ ማጥፋት፣ ማሰቃየትና የጭካኔ ተግባራት፣ ክብረ ነክና ኢ – ሰብአዊ ቅጣቶች፣ ለሕይወት አስጊ በሆኑ እስርቤቶች ማሰር፣ የዘፈቀደ አያያዝና እስራትን እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን አስታውቋል። በትግራይ በተካሄደው ጦርነት እንደ ህዩማን ራይትስ ዋች፣ አምነስት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የመሳሰሉ አካላት ባወጧቸው ሪፖርቶች መንግሥት በዘፈቃድ አሰቃቂ ግድያዎችን መፈፀሙን የሚያሳዩ በርካታ ሪፖርቶችን መውጣታቸውን የገለፀው ሪፖርት ፌደራል ፖሊስ የተፈፀሙ ወንጀሎችን ማጣራቱን ውጤቱ ግን ይፋ አለመደረጉን ገልጿል። 53 ገፅ ያለውና ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የታየውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚያትተው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት አካል፣ ከመንግሥት ውጪ ጥቃቶችንና የመብት ጥሰቶችን አድርሰዋል ያላቸውን ቡድኖችም በዝርዝር አካቷል፡፡ “ከመንግሥት ኃይሎች በተጨማሪ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ግጭት የህወሃት ኃይሎች፣ የአማራ ክልል ሚሊሺያ እና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች በንፁሃን ዜጎች ላይ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ በግዳጅ ማፈናቀል፣ ዝርፊያ እና የንብረት ማውደም ፈፅመዋል።” ይላል። ሪፖርቱ አያይዞም “በስም ያልተገለፁ ያላቸው የጉምዝ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እየገቡ አለመሆኑን ክልሉ አስታወቀ

“የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየገቡ አይደለም” ሲል የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ገለጸ። ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ሲባል በሁለቱ በኩል ግጭት ለማቆም ውሳኔ ከተወሰነ ሃያ ቀናት ቢሆነውም እስከ አሁን ወደ ትግራይ ክልል ሃያ ስድስት ተሽከርካሪዎች ብቻ መግባታቸውን ቢሮው ገልጿል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ በደረሰ ጥቃት 25 ሰዎች በጂንካ ሆስፒታል መተኛታቸውን አስተዳዳሪው ገለፁ

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት በጂንካ ከተማ በጋዘር፣ በሁባመር እና በመፀር በሰው እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር በዞኑ የአሪ ወረዳ ወደ ዞን መዋቅር ለማደግ አቅርቧል ከተባለው ጥያቄ ጋር በተያያዘ ተፈፅመ ባሉት በዚህ ጥቃት እጃቸው አለበት ያሏቸውን አራት ፖሊሶችን ጨምሮ 133 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ በሰው እና በንብረት የደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግርዋል። የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጂ ዶ/ር ፍቅረአብ ሉቃስ በጥቃቱ የተጎዱ 25 ሆስፒታል መተኛታቸውን ተናግረዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሮምያ ክልልን ሰላም ለማረጋገጥ እየሠራሁ ነው ሲል ኦፌኮ ከታጣቂዎች ጋር ድርድር እንዲደረግ ጠይቋል

ኦፌኮ ከታጣቂዎች ጋር ድርድር እንዲደረግ ጠይቋል የኢትዮጵያ መንግሥት “ሸኔ” እያለ የሚጠራቸውና እራሰቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በሚል የሚጠሩ የታጠቁ ቡድኖች ይንቀሳቀሳሉ በተባሉ ቦታዎች ያሉትን የሰላም ችግሮች ለመፍታት እየሠራ መሆኑን ክልሉ አስታወቀ። እያከናወነ ያለው ሥራ የሕግ የበላይነት የሚያረጋግጥና የፖለቲካ ሥራዎችንም የጨመረ መሆኑን የክልሉ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ገልፀዋል። በኦሮምያ ክልል እንቅስቃሴ የሚያደርገው የኦሮሞ ፈዴራሊስት ኮንግረስ በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ መንግሥት ከታጣቂዎቹ ጋር ወደ ሰላም ድርድር መግባት አለበት ሲል ጠይቋል። ​ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለአምነስቲና ለህዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት ከባህር ዳርና ከመቀሌ የተሰጡ ምላሾች

አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዋች ምዕራብ ትግራይ ውስጥ ከአንድ ዓመት በፊት በአማራ ክልል ባለሥልጣናትና በክልሉ ታጣቂ ቡድኖች በትግራይ ተወላጆች ላይ “ዘር የማፅዳት ጥቃት ተፈፅሟል” ሲሉ ያወጡትን የጋራ ሪፖርት “ሚዛናዊነት፣ ገለልተኛነትና ተዓማኒነት የሌለው” ሲል የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት እንደማይቀበለውና እንደሚቃወመው ትናንት (ዕሁድ) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሪፖርቱን “የህዝባችንን ጩኸት ለመቀማት ያነገበ” ሲልም የክልሉ መንግሥት ከስሷል። በሌላ በኩል እራሱን “የትግራይ የውጭ ጉዳዮች ቢሮ” ብሎ የሚጠራው አካል ዓርብ፤ መጋቢት 30/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ “የትግራይ መንግሥት (ጋቨርንመንት ኦብ ትግራይ) ሲል የጠራው አካል ቡድኖቹ ላወጡት ሪፖርት ምሥጋና እንደሚያቀርብ አመልክቶች “የተጠቀሱት የጭካኔ አድራጎቶች በትግራይ ተወላጆች ላይ ከተፈፀመው እጅግ ጥቂቱ ናቸው” ብሏል። ሪፖርቱና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አድራጎቶቹን “ዘር ማጥፋት” ብለው እንዲጠሩ መግለጫው ጎትጉቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነርና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ያካሄዱትን ምርመራ ውጤት ይፋ ባደረጉበት ሥነ-ሥርዓት ላይ የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋም ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባሽሌት በሰጡት መግለጫ “ትግራይ ውስጥ የጦር ወንጀሎችና በሰብዕና ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ስለመኖራቸው” ተናግረው “ዘር ማጥፋት ተፈፅሟል ለማለት የሚያበቃ ማስረጃ ግን አላገኘንም” ማለታቸው ይታወሳል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ “ምዕራብ ትግራይ ውስጥ ተፈፅመዋል የተባሉትና በሁለቱ ድርጅቶች ሪፖርት የተገለፁት የጭካኔ አድራጎቶች በብርቱ እንደሚያሳስቡት ጠቁሞ ህይወት አድን እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ያለገደብና ያለማቋረጥ እንዲደርስ እንዲደረግ ማሳሰቡ ተገልጿል። የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀቦችን ከመጣል አንስቶ ከአፍሪካ የዕድገትና የዕድሎች ተጠቃሚነት ህግ (አጎአ) መርኃግብር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ ክልል የተባለው እርዳታ እየደረሰ አይደለም አለ

እኤአ ከመጋቢት 24/2022 ጀምሮ የትግራይ ክልል መንግሥት ለትግራይ ህዝብ አጣዳፊና ዘላቂ ለሆነ የእርዳታ አቅርቦት ተደራሽነት ሲባል ግጭት የማቆም ሥምምነቱን ተግባራዊ ቢያደርግም ባላፉት ሁለት ሳምንታት ከገቡት 26 ተሽከርካሪዎች በስተቀር በቂ እርዳታ ወደ ክልሉ አለመግባቱን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ መግለጫው አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት “ግጭት የማቆም ሥምምነቱን አጋጣሚ የትግራይን ህዝብ እርዳታ እንዳይደርስ ለሚያራምደው የጭካኔት ተግባሩ የተጠቀመበት ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው” ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ወደ ትግራይ እየገባ ያለው ሰብአዊ እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን በሚያወጡት የሀስት መግለጫ በተደጋጋሚ የሚለፍፉ ቢሆንም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡ አንዳንድ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶችም ያለባቸው የህግ የሞራልና የሙያ ግዴታ ወደ ጎን በማለት ወደ ትግራይ የሚገባው እርዳታ እየጨመረ መሆኑን በመግለጽ የዐቢይን መንግሥት የሀሰት ትርክት ያስተጋባሉ ብሏል፡፡ መግለጫው አያይዞም የትግራይ መንግሥት በትግራይ ህዝብ ህይወት ላይ የሚካሄደውን እንዲህ ያለው ቀልድ እንዲቆምና ሰው ሰራሽ የሆነው የሰብአዊ እርዳታ እገዳ እንዲያበቃና የተቋረጡት መሠረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ምስራቅ ወለጋ አባ ገዳ ራሻ ማርቆስ በታጣቂዎች ተገደሉ ተባለ

የጅማ አርጆ ወረዳ አባ ገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ አባ ገዳ ራሻ ማርቆስ ባለፈው ዕሁድ በታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። ከሁለት ሳምንት በፊትም በአባ ገዳ ራሻ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈፀሙንና ተጠርጣሪዎቹ መንግሥት “ሸኔ” የሚላቸው እራሳቸውን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” ብለው የሚጠሩ ሸማቂዎች መሆናቸውን አባ ገዳዎች ተናግረዋል። የታጣቂዎቹ የውጭ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የገለፁ ግለሰብ ደግሞ ክሱን አስተባብለዋል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ የጅማ አርጆ ወረዳ አባ ገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ ራሻ ማርቆስ መጋቢት ቅዳሜ መጋቢት 24/2014 ዓ.ም ለሊት በታጣቂዎች ተገድለው ሰኞ መጋቢት 26/ 2014 ዓ.ም መቀበራቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጋሻሁን ታከለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። “ኦነግ ሸኔ የተባለው ታጣቂ ቡድን በሌሊት ከመኖሪያ ቤታቸው በማሰወጣት የቤተሰቦቻቸውን አባላት እንዳይከተሏቸው እንዲመለሱ በማድረግ ደብድበውና ጀርባቸውን ወግተው ገድለዋቸዋል” በሌላ በኩል የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ጸሐፊና የጉጂ አባ ገዳ ጅሎ ማንዶ ከሁለት ሳምንት በፊት ለሊት ላይ ሸኔ ሲሉ የጠሯቸው ታጣቂዎች በመኖሪያ ቤታቸው ብዙ ጥይት እንደተተኮሰባቸው ተናግረዋል። “የተኮሱትን ጥይት ከመሬት ሰብስበን ስንቆጥረው 47 ሆነ። በአራት ሞተርሳይክል ስለመጡ ስንት እንደሆኑ አናቅም።” ካሉ በኋላ “ቤት ውስጥ የነበሩ 12 ሰዎችን በተኩሱ አልተጎዱም ነገር ግን ቤቱ ተሰባበረ እንዲሁም ቤት ውስጥ የነበረ የቡና ክምር ተበተ።” ብለዋል። አያይዘውም “በወቅቱ ታጣቂዎቹ እኛ “ወቦ” ነን። እናንተ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን በትናችኋል። ጠላት ናቸሁ እያሉ ተኩስ ከፍተው ነው የሄዱት” ብለዋል። የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ፀሐፊና የቱለማ አባ ገዳ ጎበነ ሆላ “ሸማቂዎቹም
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተመድ ዋና ጸኃፊ በእርዳታዎቹ ትግራይና አፋር መድረስ ተደስቻለሁ አሉ

ፎቶ ፋይል፦ ስቴፋን ዱያሪች የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ የሰብአዊ እርዳታ በሮችን ክፍት ለማድረግ መወሰኑን ተከትሎ የእርዳታ ምግብና ነዳጅ የጫኑ ተሽካርካሪዎች ትግራይ እና አፋር የመድረሳቸው ዜና ያስደሰታቸው መሆኑን ቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱያሪች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡ ዋና ጸኃፊ ሁሉም ወገኖች እርዳታውን ለሚፈልጉ ሰዎች ተደራሽነትን ለማመቻቸት የገቡትን ቃል በማክበር የጀመሩትን ጥረት እንዲገፉበት አሳስበዋል፡፡ በትግራይ የባንክ፣ የመብራትና የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን ጨምሮ የንግድ አገልግሎት ተደራሽነት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱም በድጋሚ ጥሪ ማድረጋቸውን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወደፊቷን ሰላማዊና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመርዳት ከዚህ በፊት የገባውን ጽኑ አቋም በድጋሚ እንደሚያረጋግጥ አመልክቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አበርገሌ ውስጥ በተከሰተ የመድኃኒት እጥረት የሰዎች ሕይወት ሕይወት ማለፉ ተገለፀ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አበርገሌ ወረዳ ውስጥ በተፈጠረ የመድኃኒትና የምግብ አቅርቦት እጥረት ምክኒያት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱን የወረዳው አስተዳዳሪ ገለጹ፡፡ የህፃናትና የአዛውንት ሟቾች ቁጥር እንደሚበዛ ተናግረዋል። አብዛኞቹ ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነበረባቸው አስተዳዳሪው ገልፀው፤ የሞታቸው ምክኒያት ግን የመድኃኒት እጥረት መሆኑን ጠቁመዋ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአበርገሌ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደሚገባ የብሔረሰብ አስተዳዳር ዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት አስታውቋል። ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ቁጥር የሚወሰነው በማን ነው?

የትግራይ ክልል ሕዝብን አስቸኳይ የምግብ ፍላጎት ለማሟላት በየቀኑ 300 የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንደሚገባቸው የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁ ሲሆን ወደ ትግራይ ክልል የሚገቡ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ቁጥር የሚወሰነው በለጋሾች አቅም መሆኑን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ወደ ክልሉ በሚገቡ የጭነት ተሸከርካሪዎች መጠን ላይ የተቀመጠ ገደብ እንደሌለ ተናግረዋል። መንግስት ለትግራይ ክልል የእርዳታ ምግብ ገዝቶ የማቅረብ ሚና ሊወጣ ይገባል በሚል የክልሉ ባለሥልጣን ላቀረቡት ክስ በሰጡት ምላሽ ደግሞ፤ መንግሥት በሌሎችም ክልሎች ያለውን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ አቅም በፈቀደ ድጋፍ ማቅረብ ይቀጥላል ብለዋል ሚኒስትሩ። እርዳታው በአግባቡ እንዲደርስ የህወሓት ወገን ግጭት ማቆም አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ፣ ይሁንና ህወሓት የገባውን ቃል በመተግበር ላይ አይደለም ብለዋል። የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል ከገቡ ከ109 ቀናት በኋላ 21 ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ መግለፃቸው ይታወሳል። ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰሞኑ የፈንታሌ ጥቃት የአማራና የኦሮምያ ዞኖች ባለሥልጣናትን እያነጋገረ ነው

በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ማክሰኞ በተፈፀመ ጥቃት ሥምሪት ላይ የነበሩ የኦሮምያ የፀጥታ ጥበቃ አባላትና አንድ የአካባቢ ሚሊሽያ አዛዥን ጨምሮ 26 ሰዎች መገደላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል። ሌሎች 15 ሰዎች መቁሰላቸውን ለቪኦኤ የተናገሩት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ ለጥቃቱ ከአማራ ክልል የመጡ” ያሏቸውንና “የፋኖ ሚሊሽያ” እንደሆኑ የገለጿቸውን ታጣቂዎች በተጠያቂነት ከስሰዋል። በሌላ በኩል በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና ጎጥ ላይ እንደተፈፀመ የተገለፀው ይህ ጥቃት “ማንነታቸው ባልታወቀ አካላት የተቀነባበረ ነው” ሲል የዞኑ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ መምሪያ ገልጿል። “የኦሮምያ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በፋኖዎቹ ተገድለዋል” የሚለውን የኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መግለጫም እንደማይቀበሉት የመምሪያ ኃላፊው መሐመድ አህመድ ተናግረዋል። ለዝርዝሩ የተያያዘውን ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News