Blog Archives

ጠ/ሚ አብይ ኦነግ ሸኔን ለመደምሰስ ወደ ግንባር ዘምተዋል ተባለ

የመንግስትን መረጃ ከፈለክ ስዩም ተሾመን አዳምጥ ይባላል። ስዩም ተሾመ ውስጥ አብይ አሕመድን ስለምታገኝ መንግስት ነገ ምን እንዳሰበ ታውቃለህ፤ ትገምታለህ፤ መላ ምትም ታስቀምጣለህ ። ስዩም ተሾመ እንዳለው ጠ/ሚ አብይ ኦነግ ሸኔን ለመደምሰስ ወደ ግንባር ዘምተዋል። በማሕበራዊ ሚዲያው ከታች ያለውን መረጃ አስቀምጧል። በቀጣይነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጀግና የጦር መሪ የሚል ስዕል ይሰጣቸዋል። ቀጭን ሚስጥራዊ መረጃ! ================ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የት ጠፉ?” በሚል ልጠይቃችሁ በሙሉ ምላሽ የምትሆን አንዲት ቀጭን ሚስጥራዊ መረጃ ደርሳኛለች! ይኸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ልማዳቸው ወደ ግንባር ዘምተዋል። የወያኔን እብሪት ባስተነፈሱበት ክንዳቸው ሸኔ ላይ ለመድገም ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በመዝመት በሽብርተኛው ቡድን ላይ የሚካሄደውን ልዩ ኦፕሬሽን በመምራት ላይ እንደሚገኙ ቅርበት ካላቸው ምንጮች የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። አብቺ እንደ ልማዱ ኦፕሬሽኑን በድል አጠናቅቆ እንዲመጣ እንመኛለን አዲስ መረጃ ብሎ ማስተላለፍ ሲገባው ይፋ ካደረገው በኃላ ምስጢራዊ ማለቱ ግርምትን ፈጥሮ አስቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመንግስት ሚዲያዎች ይልቅ በርካታ ሃገራዊ ጉዳዮችን በሚከፍሏቸው በማሕበራ ሚዲያ አክቲቪስቶቻቸው በኩል ማስተላለፍን ይመርጣሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ አብይን ሰይጣናዊ የማድረግ ደባ | ምዕራባውያኑ በኢትዮጵያ ላይ የጠነሰሱት ሴራ እንዳይታወቅ አዲስ የጀመሩት ዘመቻ

ጠ/ሚ አብይን ሰይጣናዊ የማድረግ ደባ | ምዕራባውያኑ በኢትዮጵያ ላይ የጠነሰሱት ሴራ እንዳይታወቅ አዲስ የጀመሩት ዘመቻ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ለጅግና ሰው ህይወት እና ሞት አንድ ናቸው ! – ስዩም ተሾመ

ለጅግና ሰው ህይወት እና ሞት አንድ ናቸው‼️ እንዲህ ያለው ጀግና መሪ “አንድ ለእናቱ ሺህ ለጠላቱ” ይባላል። አብይ እንደ ማንኛችንም አንድ ሰው ነው። ጠላቶቹ ሺህዎች ናቸው። ነገር ግን አንድ ብቻውን ሆኖ ሺህዎችን ያርበደብዳል። በዓለም ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ ከያሉበት ተጠራርተው አብረውበታል። እኛም እውነትን እንዳንናገር፣ ኢትዮጵያዊነትን እንዳንዘምር ታፍነናል። ይልቅስ ወዳጄ አንድ ሚስጥር ልንገርህ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ጀግንነት አንድ ላይ የተቆራኙ ናቸው። ለሀገር መሞት ጌጥ የሚሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። ይሄ አፈታሪክ አይደለም። በገሃድ የሚታይ ሃቅ ነው። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር መኖሯ በራሱ ምስክር ነው። ሌላ ልጨምርልህ፣ እስኪ ከላይ ያለውን ቪዲዮ ለአፍታ ተመልከተው። “እኛ ወደ ግንባር የዘመትነው ኢትዮጵያን ለመታደግ አሊያም ኢትዮጵያ ለመሆን ነው” ስማኝ’ማ የሀገሬ ልጅ አቢቹ ሰኔ 16/2010 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ላይ “እኛ ስንኖር ኢትዮጵያዊ፣ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን” ብሎ ሲናገር አጉል ጉራ መስሎህ ነበር እንዴ? አይደለም! ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ዘመናትን ተሻግራ መኖሯ በራሱ እማኝ ነው። ኢትዮጵያ እንደ ማንኛውም ሀገር አይደለችም። እንደ ቡርኪናፋሶ፣ ኬኒያ አሊያም ናይጄሪያ በቅኝ ገዢዎች ተጠፍጥፋ የተሰራች ሀገር አይደለችም። ኢትዮጵያ ሁለት ናት፦ መስዕዋትነት እና ነፃነት! እነዚህ ሁለቱ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት በተለየ ሉዓላዊነቷን ሳታስደፍር የኖረችው ጀግኖች ልጆቿ በከፈሉት መስዕዋትነት ነው። አባቶቻችን በመስዕዋትነት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ጠብቀው ያስረከቡን እኛ ልጆቿ በነፃነት እና እኩልነት እንድንኖር ነው። የወያኔ ክፋቱ/ጥፋቱ ምንድነው? አባቶቻችን በመስዕዋት ባቆሟት ሀገር ላይ በነፃነት ፋንታ ፍርሃት፣ ከእኩልነት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአሜሪካ ጦር በፍፁም ከኢትዮጵያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ውስጥ አይገባም። – ስዩም ተሾመ

May be an image of outdoors and text that says 'CNN Africa CNN AFRICA The US military has positioned special operations forces in Djibouti to be ready to provide assistance to the US Embassy in Ethiopia if the situation worsens, according to one military official and two sources familiar with the movements. US has positioned special ops near Ethiopia for potential US embassy assistann'የአሜሪካ መንግስት ከወያኔ ጋር ማበሩ ምንም ጥርጥር የለውም። ነገር ግን በሁለቱ መካከል ያለው ጥምረት ምን ደረስ ነው? ለዚህ ደግሞ የአሜሪካ የስለላ እና የጦር መስሪያ ቤቶች የሚመሩበትን የልዩ ሃይል ኦፕሬሽን የተግባር መመሪያ (Special Forces Operations (SFO) Field Manual) ማየት ያስፈልጋል። በዚህ መሠረት የአሜሪካኖች ጣልቃ-ገብነት ፍፁም ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ መከናወን አለበት። በምንም አግባብ ቢሆን የአሜሪካ ወታደሮች ወይም ቅጥረኞች እጅ ከፍንጅ መያዝ የለባቸውም። ለምሳሌ በአንጎላ የCIA ቅጥረኞች፣ የአሜሪካ ልዩ ኮማንዶዎች በኢራን፣ እንዲሁም በሶማሊያ የአሜሪካ ወታደሮች በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት በአሜሪካን ላይ ያስከተለው ተፅዕኖ ይታወሳል። በሁሉም አጋጣሚዎች በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት እንዲወገድ ምክንያት ሆነዋል። ሁለተኛ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ እያካሄደ ያለው መደበኛ ያልሆነ ጦርነት (Unconventional Warfare) ነው። በዚህ የጦርነት ስልት የሚደረጉ ነገሮች በሙሉ ከቀጥተኛ ውጊያ (የጦር ፍልሚያ) መለስ ናቸው። በእርግጥ በዚህ ሁለገብ ጦርነት (Hybrid Warfare) ሁሉንም ነገር ይላሉ። ነገር ግን የሚሉት ነገር ከቀጥተኛ ወታደራዊ ጥቃት ወይም ግጭት መለስ ነው። በአጭሩ የአሜሪካ ጦር በፍፁም ከኢትዮጵያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ውስጥ አይገባም። ከታች የምታዩት CNN Africa ዘገባ ልክ ከዚህ ቀደም “የግብፅ ጦር ታንኮችና ጀቶችን ላከ፣ የጦር ልምምድ አደረጉ፣ Nato ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ነው” የሚሉት ዓይነት ነው። ከወሬ ያለፈ አይደለም። ይህም ሆኖ “ጅቡቲ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ጣልቃ ቢገባስ?” የሚለውን ጥያቄ ማስቀረት አይቻልም። ለዚህ ደግሞ ከኢትዮጵያ የሚጠበቀው አንድ ነገር ብቻ ነው። ይህ አንድ ነገር ምንድነው? አንድ (1) የአሜሪካ ወታደርን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከዲያስፖራ ኤጀንሲ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሰው ራሱን የዲያስፖራ ተግባር ምክር ቤት ያለው ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ እገዳ የተጣለበት መሆኑ ተሰማ

ከዲያስፖራ ኤጀንሲ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሰው ራሱን የዲያስፖራ ተግባር ምክር ቤት ያለው ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ እገዳ የተጣለበት መሆኑ ተሰማ የሚዲያ ተቋማት ለወንጀለኛ ድርጅት ሽፋን እንዳይሰጡ ስለመጠየቅ! ከታች በተጠቀሰው መሰረት CEDA የሚባለው ድርጅት በስሙ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ በካሊፎርንያ አቃቤ ህግ እገዳ የተጣለበት ነው። ለዝርዝሩ የእግድ ደብዳቤዎችን ይመልከቱ ! No description available. Image Image Image No description available.    
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ችጋር የጦርነት ስልት መሆኑን የሚያውቁት ርሃብን ፈጥረው፣ የእርዳታ ስንዴ ሸጠው እና ጦር መሣሪያ ገዝተው የመጡት ወያኔዎች ብቻ ናቸው

በህወሓቶች ዘንድ ርሃብና ችጋር ችግር አይደለም። ከዚያ ይልቅ ወደ ስልጣን መወጣጫ እርካብ ነው። በእነሱ ዘንድ ችጋርን ለመፍጠር ያቅዳሉ፣ በዕቅዱ መሠረት ችጋሩን ይፈጥራሉ፣ በዚህ ምክንያት ሚስኪኖች ይሞታሉ። በእርግጥ ችጋር የጦርነት ስልት መሆኑን የሚያውቁት ርሃብን ፈጥረው፣ የእርዳታ ስንዴ ሸጠው እና ጦር መሣሪያ ገዝተው የመጡት ወያኔዎች ብቻ ናቸው። አሁን እነ አምዶም የጀመሩት ነገር የህወሓትን የጦርነት ስልት ዳግም ተግባራዊ ማድረግ ነው። በሌላ አነጋገር ወደ ስልጣን ተመልሰው ለመምጣት ሲሉ በትግራይ ህዝብ ላይ የዘርማጥፋት እየፈፀሙ ይገኛል። ወልቃይትና ራያ ወደ ትግራይ እንዲመለሱ ተወስኗል? በትግራይ ርሃብ እንዲፈጠር የትግራይ ፖለቲከኞች የፈለጉበት ሚስጥር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጅቡቲ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚበላ ጅብ ገብቷል! – ( ስዩም ተሾመ )

ጅቡቲ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚበላ ጅብ ገብቷል! ( ስዩም ተሾመ ) ይህ ጅብ የመሸገው ጅቡቲ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ካምፕ ውስጥ ነው። በቀጣዩ ምርጫ የጅቡቲው ጅብ ወደ ሶማሌ ክልል ዘልቆ በመግባት የኢትዮጵያዊያንን ህይወት ለመቅጠፍ አሰፍስፎ ሲጠባበቅ ነበር። በክልሉ የሚካሄደው ምርጫ ወደ ጳጉሜ ወር የተዛወረው በዚህ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ የኢኮኖሚ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ወደ ጅቡቲ ሲመላለሱ ከርመዋል። ከመጠጥ ውሃ በተጨማሪ መብራት ለማቅረብ፣ እንዲሁም ከአዳማ-አዋሽ ያለውን Expressway በመጀመር እና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመርን በማቀላጠፍ ጉሌን ለማባበል ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ የግብፁ ፕረዚዳንት ጅቡቲ ደርሶ ከተመለሰ በኋላ የኢትዮጵያ ኢታማዦር ሹሙ ጄ/ል ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የፌዴራል ፖሊስ ዳይሬክተር ጄኔራሉ አቶ ደመላሽ ገ/ሚካኤል ተንደርድረው ጅቡቲ ሄደዋል። በዚሁ ዕለት የምርጫ ሰብሰቢዋ በሱማሌ ክልል የሚደረገው ምርጫ ወደ ጳጉሜ መሸጋገሩን ተናገሩ። ትላንትና የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ቡርቴ ከስደት ተመልሳ በሀገሯ የዴሞክራሲ መሰረት እንድትጥል የሾሟትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እየረገመ ተሿሚዋን አሞካሽቷል። ይሄ ስልት በ1977 ዓ.ም ጓድ መንግሥቱን እየረገሙ ሺ/አ ዳዊት ወልደጊዮርጊስን ሲያሞግሱት እንደነበረው ሁሉ በጅቡቲ የመሸገው ጅብ ጠ/ሚ አብይን ለመብላት አሊያም ተቀባይነት አሳጥቶ እንደ መንግሥቱ ሃይለማርያም በወጣበት ለማስቀረት አበክሮ እየሰራ መሆኑን ይጠቁማል። “ጠዋት ያደናቀፈህ ድንጋይ ማታ ላይም ደግሞ ካደናቀፈህ እንቅፋቱ አንተ እንጂ ድንጋዩ አይደለም” እንደሚባለው ሁሉ የኢትዮጵያን ዕድገትና ህልም ያጨናገፉት ሴረኞች ዳግም ካደናቀፉን ድንጋዮቹ እኛ ነን። የኢትዮጵያን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዩንቨርስቲዎች ሰላም አስተማማኝ ስላልሆነ የመንግስት ሃላፊዎች የልጆቻቸውን ደህንነት እየጠበቁ ነው ተባለ

ይህ የሚያሳየው የክልሉ ደህንነት ቢሮ በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሰላም እንደሚሆኑ ማስተማመኛ መስጠት እንደማይችል ነው። የመንግስት ሃላፊዎች የልጆቻቸውን ደህንነት በዚህ መልክ ያስጠብቃሉ። ሌላውስ ምን ዋስትና አለው? የጎሹ እንዳለማው ልጅ በወልዲያ ዩኒቨርስቲ ይማራል ወይም ሁሉም ተማሪዎች ወደ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ይዛወራሉ❗️ ======================================= የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት አማካሪና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጎሹ እንዳላማው የደህንነት ስጋት አለ በሚል ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደበው ልጃቸው ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንዲዛወርላቸው ጠይቀዋል። የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ የከፍተኛ ሃላፊውን ጥያቄ በማፅደቅ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዝውውር ጥያቄውን አቅርቧል። ይህ የሚያሳየው የክልሉ ደህንነት ቢሮ በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሰላም እንደሚሆኑ ማስተማመኛ መስጠት እንደማይችል ነው። የመንግስት ሃላፊዎች የልጆቻቸውን ደህንነት በዚህ መልክ ያስጠብቃሉ። ሌላውስ ምን ዋስትና አለው? No photo description available.
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጌታቸው ረዳ የሆነው እና የሚናገረው በሙሉ ጉግማንጉግ ነው

ጌታቸው ረዳ የሆነው እና የሚናገረው በሙሉ ጉግማንጉግ ነው! እሱ የተናገረው አንዱ እንኳን ትክክል ቢሆን ኖሮ፤ May be an image of 3 people, people standing, outdoors and text==================================== 👉 ወያኔ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ አይፈረጥጥም ነበር 👉 ኢህአዴግ ፈርሶ ብልፅግና ፓርቲ አይመሰረትም ነበር 👉 ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት አይኖርም ነበር 👉 ኢትዮጵያ እንደ ሱማሊያ በጦር አበጋዞች ትመራ ነበር 👉 ኢትዮጵያ 1 ጀት እና የጦር ብርጌድ አይኖራትም ነበር 👉 V8 መኪናውን ጥሎ በአህያ አይፈረጥጥም ነበር 👉 የስዩም፥ አባይ እና አስመላሽ ግንባር አይበረቀስም ነበር 👉 መላው የስብሃት ነጋ ቤተሰብ ለፍርድ አይቀርብም ነበር 👉 የጌታቸው አሰፋ ሬሳ መቃብር ቤት ውስጥ አይገኝም ነበር 👉 ፊቱ ከድቡሼ-ገላነት ወደ ቡሃ-ዕቃነት አይቀየርም ነበር 👉…… ጌታቸው ረዳ ከተናገረው ውስጥ አንዱ እንኳን ትክክል ቢሆን ኖሮ ሁሉም ነገር ጉግማንጉግ ይሆን ነበር። ነገር ግን እሱ የተናገረው ነገር በሙሉ ውሸት ወይም ሰህተት ስለሆነ ከነገሩ ይልቅ ተናጋሪው ራሱ ጉግማንጉግ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ችግሩ የጉግማንጉግ መናገር ሳይሆን እሱን እንደ ሰው ቆጥረው በቁምነገር የሚያዳምጡ ጉግማንጉጎች መኖራቸው ነው❗️
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት የሰሜን ዕዝን ለመዝረፍ የሞከረው ተወንጫፊ ሚሳይሎች ለመቀማት ነበር

ሕወሓት የሰሜን ዕዝን ለመዝረፍ የሞከረው ይህን ዘመናዊ መሣሪያ ለመዝረፍ ነበር። ከሰሜን እዝ ወታደራዊ ደሕንነቶች የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ይህ መቀሌ ላይ ሆኖ አዲስ አበባን መምታት የሚችል ሲሆን በ2007 ዓ.ም ኤርትራን ምድረ በዳ ለማድረግ በቀድሞ የሜቴክ ዳይሬክተር ጄ/ል ክንፈ ዳኘው የተገዛ ነው። ይህ መሣሪያ በተገዛበት ወቅት ኤርትራ የካናዳ ኩባንያ በኤርትራ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ጀምሮ ነበር ። ሕወሓት ከዚህ የወርቅ ማውጫ የሚገኘው ገንዘብ የሻዕቢያ መንግስትን ያጠናክረዋል በሚል በሀገሪቱ ላይ ማዕቀብ እንዲጣልባት ሲወተውት ነበር።ከተወሰነ ግዜ በኋላ ግን የወርቁ ነገር ጨርሶ ተረሳ። ምክንያቱ ደግሞ ወያኔ ከገዛቸው ስምንት (8) ተወንጫፊ ሚሳይሎች ውስጥ አንዱን ብቻ ወደ ትግራይ በመላክ የወርቅ ማውጫውን ዶግ አመድ አድርጎት ነበር። ይህ መሳርያ በ24 ተሽከርካሪዎች ላይ ተጠምዶ ከ82 ጥይት ጋር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢፊድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ በተመረጠ በንጋታው ሳይረጋጋ ሀገሪቱን የሚመሩ ጀኔራሎች መሳርያው ካለበት አምቦና ሆለታ (ወልመራ) ከሚገኘው ህዳሴ ክፍለ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ሄዶ ሰሜን እዝ ስር እንዲተዳደር ተደረገ ። ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆኖ በተመረጠ ማግስት በድብቅ ወደ መቀሌ በመውሰድ በሰሜን ዕዝ ስር አስቀመጡት። ከትላንት በስቲያ የሰሜን ዕዝን ለመዝረፍ የሞከሩት ይሄን ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ለመቆጣጠር ነበር። መከላከያ ሰራዊቱ እንደምንም ብሎ ሚሳይሎቹን መከላከል ባይችል ኖሮ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ አብቅቶላቸው ነበር። ምክንያቱም ሕወሓትች መቀሌ ላይ ቁጭ ብለው ይዘውት የሄዱትን ሚሳይል በመተኮስ፦ አዲስ አበባን፣ አስመራን፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ድሬዳዋና አዳማን ዶግ አመድ ማድረግ ይችሉ ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከወያኔዎች ክፋትና ተንኮል በላይ የሚያቃጥለኝ የእኛዎቹ ቅሽምና ነው። ( ስዩም ተሾመ )

ከወያኔዎች ክፋትና ተንኮል በላይ የሚያቃጥለኝ የእኛዎቹ ቅሽምና ነው። በእርግጥ የወያኔዎችን ሴራና ተንኮል አንድ በአንድ ለማወቅ ጠንቋይ መቀለብ ያስፈልጋል። ነገር ግን የዶ/ር አብይ መንግስት ይህን ማድረግ አይጠበቅበትም። ከዚያ ይልቅ እኔ በየቀኑ የኔ ትንታኔ ላይ የምናገረውን ነገር ማዳመጥ ብቻ በቂ ነው። በተደጋጋሚ “ወያኔዎች በቀጣይ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?” የሚለውን በትክክል እናገራለሁ። የተናገርኩትን ነገር ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት ሆኑ የፖለቲካ ልሂቃን በቀላሉ ሊያገኙት ይችላሉ። መረጃው አጠራጣሪ ከመሰላቸው ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ። ይሁን እንጂ እየተናገርኩ፣ በተጨባጭ ማስረጃ አስደግፌ በቀጣይ የሚያደርጉትን እየጠቆምኩ፣ ቅድመ-ዝግጅት እና ጥንቃቄ ሳያደርጉ ለጥጥጥ… ብለው ከርመው አሁን ላይ ” ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ” አይነት ጨዋቴ ሲጫወቱ ያበሳጫል። ልብ አድርጉ… ወያኔዎች ትላንት ያደረጉትን ጋጥወጥ ተግባር ጨምሮ በቀጣይ የሚያደርጉትን ወይም እንዲሆን የሚፈልጉትን አራት ቀን ቀደም ብዬ በዝርዝር ተናግሬአለሁ። ሙሉ ትንታኔውን ለመመልከት ይሄን ሊንክ ይጫኑ፦ https://youtu.be/HFe_Mh552Nw
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለጠ/ሚ አብይ አህመድ፦ ከህወሓትና አማራ አንዱን ይምረጡ!

ለጠ/ሚ አብይ አህመድ፦ ከህወሓትና አማራ አንዱን ይምረጡ! =========================================== ከላይ በተገለፀው መሰረት እርስዎ የሚመሩት መንግስት ሁለት አማራጮች አሉት። እነሱም የአማራን ህዝብ እያስገደሉ መቀጠል ወይም ህወሓት የሚባለውን የአማራ ጠላት ማጥፋት። ከዚህ በኋላ ህወሓት አማራን እያስገደለ እንዲቀጥል የሚፈቀድለት በአንድ ምክንያት ብቻ ነው። ህወሓትን ለማስወገድ የሚከፈለው ዋጋ ውድ ሆኖ ወይም አላስፈላጊ ኪሳራ ስለሆነ አይደለም። ከዚያ ይልቅ ህወሓት መቀሌ የመሸገው አማራን ለማስነከስ፣ ለማስፈራራት እና በእጅ አዙር ለመግዛት የታሰረ ውሻ ከሆነና ከሆነ ብቻ ነው። – ህወሓት በእርስዎ እና በመንግስትዎ ላይ የሚያነሳው ጥያቄ በዋናነት ከስልጣንና ጥቅም ጋር የተያያዘ ነው። በአማራ ህዝብ ላይ የጋረጠው ግን የህልውና አደጋ ነው። እነዚህ ሰዎች ልክ እንደ  ሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳይ አላቸው፣ ወገን ዘመድ አላቸው፣ ሰብዓዊ ክብርና መብት አላቸው። እነዚህ በግፍ የተገደሉት ሰዎች እንደ እኔና እርስዎ ነፍስና ተስፋ ነበራቸው። – ከዚህ በስተጀርባ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የወያኔ እጅ ያለበት መሆኑ አልጠራጠርም። አንድ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ ስንት አማራ ተገደለ? በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል፣ አስተማማኝ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ስንት አማራ መገደል አለበት? ኢትዮጵያ እንድትኖር ስንት አማራ መታረድ አለበት? – እርስዎም ሆኑ መንግስትዎ የመጨረሻው ጥጋት ላይ ደርሰዋል። ከዚህ በኋላ ወይ የአማራን ገዳይ ይገድላሉ ወይም ከገዳዮቹ ጎን ቆመው አማራን እያስገደሉ መሆኑን በተግባር ያረጋግጣሉ። ስለዚህ ከህወሓት ማፍያዎች እና ከአማራ ህዝብ አንዱን መምረጥና ሌላውን ለማጥፋት የሚወስኑበት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሰዋል። – ልክ እንደ ዛሬ ነገም ህወሓት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙት የቀድሞ የደህንነት ሃላፊዎችና ሰራተኞች 24/7 የሞባይል ስልክ እንደሚጠቀሙ ተሰማ

በመተከል ጥቃት ያደረሱትን ታጣቂዎች በመመልመል፣ በማሰልጠን፣ በማስታጠቅና ተልዕኮ በመስጠት ተሳታፊ የሆኑት እነማን ናቸው? – ስዩም ተሾመ – በመተከል የሚገኙትን ታጣቂዎች ከመመልመል ጀምሮ ጥቃት እንዲፈፅሙ በማድረግ ረገድ በቀጥታ ተሳታፊ የሆነው አቶ  ጌታቸው ታክሲ የተባለ ግለሰብ መሆኑን ከታማኝ ምንጭ መረጃ ደረሰኝ። ይሄ ግለሰብ በህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ስር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የደህንነት ሃላፊ የነበረ ነው። አቶ ጌታቸው ታክሲ ትዕዛዝና መመሪያ የሚቀበለው ደግሞ የቀድሞ የአማራ ክልል የደህንነት ኃላፊ የነበሩና የጥበቃ ዋና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ሃይሌ እንደሆነ ተረዳሁ። ነገር ግን “አቶ ተሾመ ሃይሌ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት የቀድሞ የደህንነት ሃላፊዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን በመተከል ዞን የሚፈፀመውን ጥቃት እንዴት ማስተባበር ይችላል?” የሚል ጥያቄ አነሳሁኝ። ከውስጥ አዋቂው የተሰጠኝ ምላሽ ግን ከመጀመሪያው የባሰ አስደነገጠኝ። – የተጠቀሰው የደህንነት መረጃ ምንጭ ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙት የቀድሞ የደህንነት ሃላፊዎች እና ሰራተኞች 24/7 የሞባይል ስልክ እንደሚጠቀሙና እንደ አቶ ጌታቸው ታክሲ ካሉ በሁሉም ክልሎች ከሚገኙ የደህንነት ሰራተኞች ጋር በስልክ እንደሚገናኙ አረዳኝ። ይባስ ብሎ በተመሣሣይ መንገድ ከቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊ ጋር እንደሚገናኙና የብጥብጥና ሁከት አጀንዳ፣ አቅጣጫና መመሪያ እንደሚቀበሉ ለማወቅ ተችሏል። በዚህ መልኩ በተዘረጋው የሽብር ኔትወርክ ተሳታፊ የሆኑትና በወንጀል ተጠርጥረው በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊዎች ስም ዝርዝርን ከታች መመልከት ይቻላል። – አሁን ባለው አደረጃጀት መሠረት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን የመሳሰሉት ተጠሪነታቸው ለሰላም ሚኒስቴር ነው። የሰላም ሚኒስቴሯ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የህወሓት ሰዎች ወደ አዲስ አበባ ሽማግሌ ላኩ !

ህወሓት ሲለምኗት እምቢ ብላ ሲከሽፍባት መጣች⁉️ – Seyoum Teshome – Image may contain: people sitting and outdoorባለፈው በሀገሪቱ ውስጥ አሉ የተባሉ የተከበሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና እንደ ሃይሌ ገብረስላሴ ያሉ ታዋቂ ሰዎችን ለሽምግልና ተብሎ ህወሓት ጋር ሲላኩ “ሽምግልና እና እርቅ ከብሔር፥ ብሔረሰቦች ጋር እንጂ ከእኛ ጋር አይደለም” ብለው ያሽካኩት ሰዎች አሁን “ወደ አዲስ አበባ ሽማግሌ ላኩ ነው” እ.ያ.ሁ.ያ። ሃይሌን የመሰለ ዕንቁ እንደ ተራ ሰው እጁን አስዘርግተው እየፈተሹ በራሳቸው ላይ የተሳለቁ ሰዎች ትላንት ሽማግሌ ልከው አማልዱን ማለታቸውን ESAT ዘግቧል። – መልካም፣ መጀመሪያ ላይ ለሀገር ሽማግሌዎች ያሳዩት ንቀትና የሰጡት ምላሽ “ያው የተለመደ የማፊያ እብሪትና የሞራል ዝቅጠት ነው!” ብዬ አልፌው ነበር። የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ሲያደርጉትና ሲናገሩት የነበረውን ሁላችንም እናውቃለን። ያ… ሁሉ እልቂትና ውድመት ከደረሰ በኋላ “እርቅና ሽምግልና ከእኛ ሳይሆን ከብሔር፥ ብሔረሰቦች ጋር ነው!” ማለታቸው ሳያንስ “እዩት ዶ/ር አብይ አህመድ ሲጨንቀው፣ ማጣፊያው ሲቸግረው እኛ ጋር ሽማግሌ ላከ” እያሉ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ ሲታትሩ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ድንገት እርቅና ሰላም ሰባኪ ሆነው ሽማግሌ የላኩበት ምክንያት ምንድነው❓ – በመጀመሪያ ደረጃ የነበረው ሁኔታ፣ ሲናገሩት፣ ሲያደርጉትና ሲያራግቡት የነበረውን ነገር ለሚያውቅ ከሃጫሉ ግድያ በስተጀርባ የወያኔዎች እጅ እንደነበረበት መገመት ቀላል ነው። ሁለተኛ በፊት ለእርቅና ሰላም ሲለመኑ አሻፈረኝ ሲሉ የነበሩ ሰዎች ሃጫሉን በመግደል ሊፈፀም የነበረው መፈንቅለ መንግስት መክሸፉን ተከትሎ ሽምግልና መላካቸው የሴራው ጠንሳሾች መሆናቸውን እና ሴራው በመክሸፉ የተሰማቸውን የተስፋ_መቁረጥ ስሜት ይጠቁማል። “ሲፋጅ በማንኪያ፣ ሲበርድ በእጅ!” ማለት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቃል ሲነገረው ያልሰማ ህዝብ በመከራ ሊማር ወስኗል

ሚላን…ኒውዮርክ….ቀጥሎ አዲስአበባ ============================== እሺ እባካችሁ…. የትላንቱ ገበያ እንዴት ነበረ? ዛሬስ አውዳመቱ እንዴት እያለፈ ነው? መልካም… ልክ የዛሬ ሁለት ወር (February 19/2020) በሰሜን ኢጣሊያ ሎምፓርዲ ግዛት Bergamo ከተማ የተመሠረተው የአትላንታ ክለብ ከስፔኑ ቫሌንሺያ ጋር ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ነበራቸው። ከብዙ አመታት ጥበቃ በኋላ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጫወት ዕድል ያገኘው የአትላንታ ክለብ ደጋፊዎች ደስታቸው የተለየ ነበር። በቤርጋሞ ከተማ የሚገኘው ስታዲየም በቂ ባለመሆኑ በሚላኑ ሳንሴሮ ስታዲየም እንዲካሄድ ተወሰነ። ይህን ጨዋታ ለመመልከት የቤርጋሞ ከተማ ነዋሪዎች ነቅለው ሚላን ከተማ ገቡ። ከተወሰኑ ቀናት በኋላ በጨዋታው ከታደሙት 44ሺህ ተመልካቾች ውስጥ 40ሺህ የሚሆኑት ተመልካቾች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። ጨዋታውን የኢጣልያኑ አትላንታ ቫሌንሺያ 4 – 1 አሸነፈ። የአትላንታ ደጋፊዎች በደስታ ጮቤ ረገጡ፣ በደስታ ጨፈሩ፣ አንገት ለአንገት ተቃቅፈው የክለባቸውን መዝሙር ዘመሩ። የአትላንታ እና ከቫሌንሺያ ጨዋታ በሚካሄድበት ዕለት (February 19/2020) ኢጣሊያን ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ብዛት ሦስት ብቻ እንደነበር Wall Street Journal ዘገባ ያስረዳል። ከ20 ቀን በኋላ (March 10/2020) የቤርጋሞ ከተማ ነዋሪዎች እንደ ቅጠል ይረግፉ ጀመር። ከተጠቀሰው እግር ኳስ ጨዋታ ቀጥሎ ባሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በሚላን ከተማ አቅራቢያ ወደ 100 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ የሚገኝበት ቬስትቫል ነበር። በሳንሴሮ ስታድየም በተካሄደው ጨዋታ ላይ እንደ እንኩቤተር የተፈለፈለው የኮሮና ቫይረስ በዚህ ቬስትቫል ላይ በከፍተኛ ፍጥነት ተስፋፋ። ከዚያ በኋላ የተጠቀሱት ቦታዎች በሚገኙበት በሰሜናዊ ኢጣሊያ የሚገኘው የሎምፓርዲ ግዛት ስንት ሺህ የኢጣልያ ዜጎች በገፍ እንደረገፉ ሁላችንም የአይን እማኞች
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢጣሊያ ሚላን፣ ስፔን ማድሪድ እና እንግሊዝ ለንደን በረራውን ያላቋረጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ማመላለሻ ሆኗል ተባለ

Why Were Two Ethiopian Airlines 777s In Miami? የኢትዮጵያ  አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ማመላለሻ ሆኗል። ይሄው አሜሪካ ሚያሚ ድረስ ሄዶ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መልህቋን እንዳትጥል የተከለከለች መርከብ ተሳፋሪዎችን በድብቅ ጭኖ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ ከዚያ ወደ ቪሊፒንስ ይዟቸው ሄዷል :: File this under “that’s kind of cool as an aviation geek,” rather than “that’s useful” (but nowadays I feel like the former is more fun than the latter, given that all the useful news lately seems to be bad news). Two Ethiopian Airlines 777s stopped in Miami At least compared to most other global airlines, Ethiopian Airlines seems to be running a relatively normal operation at the moment, as many of their US flights continue to operate (I’m not exactly sure where the demand is for these flights, though?). I have to imagine that these flights have mostly been pretty empty, and one reason I suspect that is because Ethiopian Airlines has been operating many of their westbound flights to North America nonstop. Ordinarily these flights have refueling stops in Dublin, because the distance of a nonstop from Addis Ababa to the US, combined with the altitude of the airport, make it almost impossible to fly nonstop. However, clearly the
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ፤ “እንኩቶ” ብለው የናቁት “አሻሮ” እንዳያደርግዎት!

ለብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ፤ “እንኩቶ” ብለው የናቁት “አሻሮ” እንዳያደርግዎት!በብዙ ሰዎች ውትወታ ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ አውሎ ሚዲያ ለተሰኘ የዩቲዩብ ቻናል የሰጡትን አስተያየት ተመለከትኩት። ውይይቱ በሁለት አጫጭር ክፍሎች የቀረበ ሲሆን ሁለቱንም ክፍሎች ደጋግሜ አየሁት። አንድን ቃለምልልስ ደጋግሞ የመመልከት ልማድ ባይኖረኝም ያለወትሮዬ ይሄን ቃለምልልስ ደጋግሜ ተመለከትኩት። በመጀመሪያ ደረጃ አውሎ የተሰኘው ቻናል በወያኔዎች የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ነው። ሁለተኛ ቃለምልልሱን ያደረገው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ከያየሰው ጋራ አፍና ጭንቅለቱን ለወያኔ አሳልፎ የሸጠ አገልጋይ ነው። በመሆኑም ሚዲያውም ሆነ ጋዜጠኛው በአማራ ክልል አመራሮች መካከል ያለው ክፍተት ይበልጥ ለማስፋት ጥረት ማድረጋቸው ያለ፣ የነበረና ወደፊትም የሚኖር ነገር ነው። በመሆኑም የብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ ቃለምልልስ በአማራ ልሂቃን መካከል አለመግባባትና ግጭት ለመፍጠር ያለመ ነው። በእርግጥ ከ15ቱ ግድያ በኋላ መታሰራቸው፣ ከእስር ከወጡም በኋላ በክልሉ መንግስት በተሰጣቸው የሥራ ቦታ ደስተኛ አለመሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል። ሆኖም ግን በውስጣቸው የታመቀውን አጉል እልህና ስሜታዊነት ለመግለፅ የወያኔዎች ሚዲያ ጋር መሄዳቸው ያስገምታቸዋል። በቃለምልልሱ የተናገሩትን በጥሞና ላጤነ ደግሞ ጄኔራሉ በራሳቸው ላይ ሌላ ጣጣና መዘዝ እንዳያመጡ ያሰጋል። ከመጀመሪሪው ጀምሮ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ፣ ብ/ጄኔራል አሳምነው ፅጌ እና የብ/ጄ ከማል ከልቹ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የፀጥታ ቢሮ ውስጥ በሃላፊነት ሲሾሙ ተቃውሜያለሁ። ምክንያቱም ለጦርነት የሰለጠኑ ሰዎች የፖለቲካ ኃላፊነት መስጠት ፈፅሞ ትክክል አይደለም። የጦር ጄኔራል የክልል ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ሲሾም የክልሉ ነዋሪ በሙሉ ወታደር ይመስለዋል። ሁሉም የፀጥታ ችግር በወታደራዊ ጉልበት ለመፍታት ጥረት ያደርጋል። ይህ ደግሞ በተለይ በአማራ ክልል ምን እንዳስከተለ በተግባር አይተናል። ብ/ጄኔራል ተፈራ ካለፈው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የባልደራስ እና መኢአድ ቅንጅት በህጉ መሠረት ህገወጥ ነው – ( ስዩም ተሾመ )

የባልደራስ እና መኢአድ ቅንጅት ህገወጥ ነው ጥር 04/2012 ባልደራስ የተባለው አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ማግኘቱን አስታውቋል። በህጉ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲው የተሰጠው ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ፣ የፖለቲካ ፓርቲውን ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፤ የአገልግሎት ጊዜውም ሦስት ወራት ብቻ ነው። በሌላ በኩል የካቲት 27/2012 ዓ.ም «ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፖርቲ» እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በምህጻሩ (መኢአድ) ቅንጅት መፍጠራቸውን አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ በህጉ መሠረት ምርጫ ቦርድ ለባልደራስ የሰጠው ፍቃድ ፓርቲውን “ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ብቻ የሚያገለግል ነው። ከሌላ ፓርቲ ጋር ቅንጅት መፍጠር ፓርቲውን ለማስመዝገብ የሚከናዎን ተግባር አይደለም። ከዚያ ይልቅ አንድ ፓርቲ ከሌላ ፓርቲ ጋር ጥምረት፥ ውህደት፥ ቅንጅት ለመፍጠር በቅድሚያ በአዋጅ መሠረት በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሲያገኝ ብቻ ነው። ባልደራስ ደግሞ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ብቻ የሚያገለግል “ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ” እንጂ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አልተሰጠውም። በመሆኑም የሁለቱ ፓርቲዎች ቅንጅት ህጋዊ እውቅና የሌለው ከመሆኑም በላይ ባልደራስ የተሰጠው ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ያለ አግባብ ጥቅም ላይ በማዋሉ በምርጫ ቦርድ ቅጣት ሊተላለፍበት ይችላል እንግዲህ እነዚህ የተሰጣቸውን ህጋዊ ፍቃድ ትርጉምና ፍቺ ጠንቅቀው የማያውቁ ሰዎች ናቸው ሀገርና ህዝብ እንመራለን የሚሉት።  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኮሮና ቫይረስ ከያዛቸው ሰዎች አብዛኛዎች ድነዋል እንጂ አልሞቱም! ~ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ)

ኮሮና ገባ ብሎ ፍርሃት፣ ድንጋጤና ጭንቀት አያስፈልግም! ኮሮና ቫይረስ ከያዛቸው ሰዎች አብዛኛዎች ድነዋል እንጂ አልሞቱም! ~ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ) እንደዚህ አይነት አዳዲስ በሽታዎች በተከሰቱባቸው የታሪክ አጋጣሚዎች ከበሽታው እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ ሰዎችን የጎዳው የስነ-ልቦና ዝግጁነት አለመኖር ነው። ለዚህም ማግለልና መድሎ ለኤች አይ ቪ መ ስፋፋት የተጫወተውን ሚና ማስታወስ በቂ ነው። እናም ህዝባዊ ፍርሃትና ጭንቀት የሚፈጥሩ መልዕክቶችን ችላ በማለት በእውቀትና በእርጋት ነገሮችን ማስተናገድ ይገባናል። በሽታውን በስፋት ያጠኑት የዉሃን ተመራማሪዎች ቀጣዮቹን ወሳኝ ነጥቦች አስቀምጠዋል፤ – ኮሮና ቫይረስ አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ (አክታ ኣልባ) ሳል የሚያስከትል ሲሆን ከፍተኛ ትኩሳትና ላብ፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ወይም ለመተንፈ ስ መቸገር ዋና ዋናዎቹ መለያዎቹ ናቸው። – ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ …ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣትን ብዙሀኑ መክረዋል፡፡ (ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡) – በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/Snow አትመገቡ! ( ባገራችን ልጆች ዘንድ የተለመደው ጀላቲም አይመከርም።) – የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡ – ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡ (ማስኩ ግን በተለይ የሚያስፈልገው ምልክቱ ላላቸው ሰዎች ነው!) – በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጃዋር የተፈፀመው የሰነድ ማጭበርበር!

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የጃዋር ህልም መለስ ዜናዊን መተካት ነው!

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ከሥራ የተባረሩት የህወሓት ደህንነቶች ተማሪ መስለው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ገብተዋል

ከሥራ የተባረሩት የህወሓት ደህንነቶች ተማሪ መስለው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ገብተዋል :: ===================================== በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሱት እነማን ናቸው? በመሠረቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያለ ምንም ምክንያት እርስ በእርስ አይገዳደሉም። በእርግጥ በመካከላቸው ፀብና ግጭት ይኖራል። ነገር ግን በተማሪዎች መካከል የሚፈጠር ግጭት ቡጢ ከመሰናዘር አያልፍም። በአጠቃላይ የተማሪዎች ፀብና ግጭት ከስድብና ድብድብ አያልፍም። ካለፈው አመት ጀምሮ ግን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚታየው ተማሪዎች እርስ በእርስ በጭካኔ ሲገዳደሉ እያየን ነው። ዩኒቨርስቲዎቻችን ከመማሪያነት ወደ ሽብር ቀጠና ከተቀየሩ ሰነባብተዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ህወሓት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ከስራና ሃላፊነታቸው የተነሱ የደህንነት ሰራተኞች ጓዛቸውን ጠቅልለው ዩኒቨርስቲ ውስጥ ገብተዋል። እነዚህ የህወሓት ደህንነቶች ዩኒቨርስቲ ውስጥ የገቡት የሀገሪቱን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁከትና ብጥብጥ ለማተራመስ ነው። በዚህ መልኩ በ2011 ዓ.ም የጀመሩትን እኩይ ምግባር ዘንድሮ ይበልጥ አጠናክረው መቀጠላቸውን ከጥቅምት 30/2012 ጀምሮ በተግባር አይተንዋል። ይህን ተረድቶ አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር በቀጣዩ ሴሜስተር ደግሞ ከዚህ የባሰ ሁከትና ብጥብጥ ሊከሰት ይችላል። ሙሉ ዝግጅቱን ለማዳመጥ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፦
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

አማራን በማተራመስ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራ !!

አማራን በማተራመስ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራ !! ================================== በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚቀሰቅሰው ግጭትና አለመረጋጋት፣ የተማሪዎች እና ህፃናት እገታ፣ የቤተክርስቲያንና መስኪድ መቃጠል፣… ወዘተ ሁሉም የአማራ ክልል ህዝብና መንግስት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። የሰራ ፖለቲካ መነሻና መድረሻው አማራን በማተራመስ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው። ለምን? እንዴትና መቼ ለሚሉት ፕሮግራሙን ያድምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የታገቱት ተማሪዎች መከራ እና ድራማ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሳው መንግስት ራሱ ነው ‼

Image may contain: 4 people, people sitting and indoorሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሳው መንግስት ራሱ ነው‼ ይሄ መጥረቢያና ገጀራ ይዞ ሐረርና ድሬዳዋን ሲበጠብጥ የሚውለው ጎረምሳ ከጃዋር መሃመድ ጋር ተቃቅፎ ስታዩ የተገረማችሁ በሙሉ በሉ አሁን እርማችሁን አውጡ። ምክንያቱም ከታች በምስሉ ላይ እንደምታዩት ይሄ በጥባጭ ጎረምሳ የወጣቶች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ እስክንድር ከተባለ ግለሰብ ጋር ቢሮ ስብሰባ ተቀምጧል። በዚህ መሠረት ከግብረአበሮቹ ጋር በቀጣይ ተግባራዊ ስለሚደረገው የብጥብጥ ስትራቴጂ ይወያያል። ከዚህ የምንረዳው ነገር፤ 1ኛ) ሐረርና ድሬዳዋ ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት የብሔርና ሃይማኖት ግጭት የሚቀሰቅስው በመንግሥት ፍቃድና በጀት ነው። በመሆኑም የአከባቢው ህዝብ ዘወትር በሽብር ሰቆቃ ከሚኖር ከነጭራሹ “ መንግስት የለም” ብሎ እርሙን ያውጣ‼ ወይም ደግሞ 2ኛ) የጃዋርና አህመዲን የሽብር ቡድን ሐረርና ድሬዳዋ ላይ የመንግስትን ስልጣንና መዋቅር በበላይነት ተቆጣጥሯል። ስለዚህ የአከባቢው ነዋሪዎች ጓዛቸውን ጠቅልለው ይሰደዱ አሊያም ከአሸባሪዎች ጋር አብሮ መኖር ይለመዱ‼ ከዚህ በተረፈ የማንም ጎረምሳ በመንግስት ፍቃድና በጀት ህዝብና ሀገር እያሸበረ መስኪድና ቤተክርስቲያን በእሳት ሲቃጠል፣ ንፁሃን ዜጎች በግፍ እየተገደሉ ዳግም ከህዝብ ጋር አብሮ ማልቀስ፣ በዚህ እኩይ ተግባር የተሰማሩ ሰዎችን ከተጎጂዎች ጋር ሆኖ መርገምና ማማረር አይቻልም። “ሞኝን እባብ ሁለቴ ነክሰው፤ አንዴ ሲያይ ሌላ ግዜ ሲያሳይ” እንደሚባለው ሁሉ ህዝብ ሰላምና ደህንነቱን ማጣቱ ሳያንስ በፍትህ እጦት መሰቃየት የለበትም። ከዚህ በኋላ በተጠቀሰው አከባቢ ሁከትና ብጥብጥ ቢነሳ በመንግሥት ፍቃድና በጀት የተፈፀመ መሆኑን አውቃችሁ ያለ ማንም ድጋፍና እርዳታ ሰላምና ደህንነታችሁን በራሳችሁ ለማስከበር ከወዲሁ ተዘጋጁ‼ይህ በጥባጭ ጎረምሳ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ለፍርድ እስካልቀረበ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ ጃዋር መሃመድ የአሜሪካ ዜግነቱን መተውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ሳያቀርብ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጠው ለዜግነት ኮሚቴ ጠየቀ

የጃዋር ወጥመድ‼ =============== አቶ ጃዋር መሃመድ አሜሪካዊ ዜግነቱን መተውን የሚያረጋግጠው ይሂቺን ሰርተፊኬት ማቅረብ ሲችል ነው። የሰርተፊኬቱ ስም “ CERTIFICATE OF LOSS OF NATIONALITY OF THE UNITED STATES” ይባላል። የሰርተፊኬቱን ይዘት አስተያየት (Comment) መስጫ ቦታው ላይ ታገኙታላችሁ። ጃዋር ይህቺን ሰርተፊኬት ፈፅሞ አያገኝም። ሌላው ቀርቶ የአሜሪካ  Homeland Security መስሪያ ቤትን እንዲሰጠው ለመጠየቅ አይደፍርም። ምክንያቱም አሜሪካ ውስጥ ምን ሰርቶ እንደመጣ ያውቃል። ይሄ ሰርተፊኬት የሚሰጠው ያለበትን ታክስ በአግባቡ ከፍሎ ማጠናቀቁ ከተረጋገጠ በኋላ የአሜሪካ ዜግነቱን መተውን የሚያረጋግጥ ነው። ይህን ሰርተፊኬት ሳያቀርብ የሌላ ሀገር ዜግነት እንዲሰጠው የጠየቀ አሜሪካዊ ዜጋ ቀድሞ በአሜሪካ መንግስት ላይ የታክስ ማጭበርበር እየፈፀመ እንደሆነ ይታወቃል። ጃዋር ደግሞ አሜሪካ ውስጥ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የታክስ ማጭበርበር ፈፅሟል። በመሆኑም የአሜሪካ ዜግነቱን መተውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ሳያቀርብ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጠው ለዜግነት ኮሚቴ ጠይቋል። ኮሚቴው ደግሞ ያለ ሰርቴፍኬቷ ኢትዮጵያዊ ዜግነት መስጠት አይችልም። ስለዚህ ይህቺ ሰርተፍኬት የጃዋር ወጥመድ ናት። (ቪዲዮውን ይመልከቱ)
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የጃዋር ቅሌት ሲጋለጥ ‼ አስገራሚ የሰነድ ማስረጃ !

የጃዋር ቅሌት ሲጋለጥ‼ ጃዋር መሃመድ ምርጫ የሚለው ምክር ቤት በመግባት ያለመከሰስ መብት ለማግኘት ነው። ================== ላለፉት 15 ቀናት አድፍጠን የቆየነው የአቶ  ጃዋር መሃመድ ቅሌት ስንቆፍር ነው። ከአሜሪካ እስከ ኢትዮጵያ፣ ከOMN እስከ LTV፣ ከአሜሪካን የሀገር ውስጥ ገቢ (Internal Revenue Service) እስከ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ ከአሜሪካ የዜግነት አዋጅ እስከ ኢትዮጵያ የዜግነት አዋጅ፣… በአጠቃላይ ምንም የቀረ ነገር የለም። ሰውዬው እልምምም ያለ  ሞላጫ ሌባ ነው። ለካስ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ታክስ አጭበርብሮ ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣው? ለማንኛውም ጃዋር ምርጫ ምናምን የሚለውን ምክር ቤት በመግባት ያለመከሰስ መብት ለማግኘት ነው። እያንዳንዷን ሚስጥር በሰነድ አስደግፌ 50 ደቂቃ በሚፈጅ ዶክመንተሪ እቅጯን እንሆ ብያለሁ። ቪዲዮ ይመልከቱ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የቀን ጅብ ከሚበላኝ እሱን በልቼ ብቀደስ ይሻለኛል‼ (ስዩም ተሾመ)

የቀን ጅብ ከሚበላኝ እሱን በልቼ ብቀደስ ይሻለኛል‼ (ስዩም ተሾመ) ========≥============================ የዶ/ር አብይ አመራር ከሚገባው በላይ ትዕግስተኛና በውይይት የሚያምን ለዘብተኛ የፖለቲካ ቡድን ስለመሆኑ ህወሓት በራሱ ህያው ምስክር ነው። አሁን መቀሌ ላይ ተወሽቆ የሚደነፋውን ህወሓት፤ መለስ ዜናዊ የሚመራው የኢህአዴግ መንግስት ለአንድ ወር እንኳን ይታገሰው ነበረ? እንዲህ ያለ እብሪተኛ ቡድን ትግራይ ውስጥ ተወሽቆ ደርግን ሲተናኮሰው መንግሥቱ ሃይለማርያም ምን እንዳደረገ ይታወቃል። አፄ ሃይለስላሴም ቢሆኑ እንዲህ ያለን የዘራፊዎች ስብስብ መታገስ አይችሉም። የኤርትራው ኢሳያስማ ከኢትዮጵያ ጋር ላለማጣት ብሎ እንጂ ለአንድ ቀን እንኳን ብቻቸውን ቢያገኛቸው ጥንብ-እርኩሳቸውን ያወጣላቸው ነበር። በአጠቃላይ የየትኛውም ሀገር መሪ ወይም መንግስት እንደ ህወሓት ያለ የማፊያ ቡድን በነፃነት እንዲደነፋ አይፈቅድለትም። ሌላው ቀርቶ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቡድን በሌላ ሰው የሚመራ ቢሆን ኖሮ አሁን ያለውን የህወሓት አመራር ከምድረ ገፅ ያጠፋው ነበር። እንደ እኔ ያለው እብድ ደግሞ የኢትዮጵያን ጦር ሃይል የማዘዝ ስልጣን ቢያገኝ እ..ያ..ን..ዳ..ን..ዱ.. የህወሓት አመራር እንደ እባብ ተቀጥቅጦ እንዲገደል ካደረኩ በኋላ አፈር ልሰው እንዳይነሱ የሁሉንም ሬሳ ዛፍ ላይ አንጠለጥለው ነበር። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በህወሓት የፌስቡክ ገፅ ላይ <<“እቲ ሕዚ ሃገር ዝመርሕ ዘሎ ሓይሊ ዘድሐርሐረ ሓይሊ ስለዝኾነ ሽግር ክፈጥር ይኽአል እዩ ዝበልክምዎ ትኽክል እዩ፡፡ ኮይኑ እውን ግን ተወዲብና ነዚ ሓይሊ ምድሕርሓር” ንስኻ ሓይሊ ምድሕርሓር ኢኻ፣ ንህዝቢ ኣይትጠቅምን እናበልና፣ እናተቓለስናዮ መፂእና ኣለና>> ብላለች (ይህን ትግሪኛ አንብቦ መረዳት የማችል ሰው አማርኛ አይችልም ማለት ነው) ምን ለማለት ነው፤ ህወሓት ለሚባለው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዩኒቨርስቲዎቻችን፦ ከስርዓት ለውጥ ወደ ነውጥ ማዕከልነት

ዩኒቨርስቲዎቻችን፦ ከስርዓት ለውጥ ወደ ነውጥ ማዕከልነት ዩኒቨርስቲዎቻችንን ከስርዓት ለውጥ ወደ ነውጥ ማዕከልነት የተቀየሩበት ምክንያት ምንድነው? ከችግሩ በስተጀርባ ያለው ስውር እጅ የማን ነው? ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መወሰድ ያለበት የመፍትሔ እርምጃስ ምንድነው? ባለፉት አራት አመታት በዩኒቨርስቲዎቻችን ውስጥ እየታየ ያለውን የለውጥ እና ነውጥ ንቅናቄ አስመልክቶ የቀረበውን ትንታኔ ያዳምጡ። በጉዳዩ ዙሪያ ሃሳብና አስተያየት ይስጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ይህ ሰምቶ በቸልታ ማለፍ ሽብርተኝነትን በተግባር መደገፍ ነው!

ይህ ሰምቶ ማለፍ አሸባሪዎችን መደገፍ ነው! (ስዩም ተሾመ) ከአስር አመት በፊት “የኢህአዴግ መንግስት ጨቋኝና አምባገነን ነው!” ብሎ መናገር ልክ እንደ ሃጢያት ይታይ ነበር። “ጭቆና እና አምባገነንነት መጨረሻው ውድቀትና ውርደት እንጂ ልማትና እድገት ሊሆን አይችልም” የሚል ምክር አዘል ተግሳፅ የተናገሩ ልሂቃንን በጠላትነት ያድኑ ጀመር። ከአምስት አመት በኋላ “የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሠረታዊ ችግር የኢህአዴግ ጨቋኝነትና አምባገነንነት” እንደሆነ በይፋ የሚናገር አዲስ ትውልድ መጣ። ይህን ግዜ የኢህአዴግን ጨቋኝነት እና አምባገነንነት አምነው ተቀብለው የህወሓትን የበላይነት መቃወም ጀመሩ። ከሁለት አመት በፊት ደግሞ የችግሩ መሠረት “የብሔር፣ ቋንቋና ሃይማኖት ልዩነትን መሰረት በማድረግ በዜጎች መካከል ጥላቻና ቂም የሚሰብከው፣ ያለመግባባት እና ጥርጣሬ ምንጭ የሆነው የአፓርታይድ ስርዓት ነው” ሲባል እንደ ወራሪ ጠላት ጨርቄን-ማቄን ሳይል ፈርጥጦ ወደ መቀሌ በመሄድ ሆቴል ውስጥ መሸገ። ህወሓትን ከስልጣን ለማስወገድ የተደረገው ትግል ብዙ አመት የወሰደው፣ አላስፈላጊ መስዕዋት ያስከፈለው በሌላ ምክንያት ሳይሆን በራሱ በኢትዮጵያ ህዝብ መዘናጋትና ቸልተኝነት ነው። በእርግጥ ይሄ በሁሉም የህይወት ዘርፍ የሚስተዋል መሠረታዊ ችግር ነው። የህወሓት ጉዳይ ደግሞ ከሁሉም የባሰ ነው። ከመጥሪያ ስሙ ጀምሮ እስከ የዕለት መግባሩ የሚያሳየው ሌላ ሆኖ ሳለ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ከምሁራን ምክር ይልቅ የህወሓቶችን ምክር ያዳምጣል። “የትግራይ ነፃ-አውጪ ግንባር (ትህነግ) ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ይሰራል?” ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ “መንግስታዊ ስርዓቱ ፌደራላዊ ወይስ አሃዳዊ ነው?” እያለ ይጨነቃል። የህወሓት ባለስልጣናት መቀሌ ከገቡበት እለት አንስቶ ሆቴል ውስጥ የሚያድሩት ውሏቸው እንጂ መቀሌ ህልማቸው ተመልሶ መምጣት እንደሆነ መረዳት የተሳነው
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ከህወሓት ጋር ውህደት አስክሬን አቅፎ እንደ መተኛት‼

ከህወሓት ጋር ውህደት አስክሬን አቅፎ እንደ መተኛት‼ ስለ ህወሓት የሆነ ነገር በተባለና በተፃፈ ቁጥር “በትግራይ ህዝብ ላይ የተቃጣ ጥቃትና መገለል ነው!” በማለት እሪሪሪ ያላሉ። ይሄን የሚሉት ደግሞ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የህወሓት አባላት እና በሀገር ውስጥ እስከ ውጪ የሚገኙ የድርጅቱ ደጋፊዎች ናቸው። ስለ አንድ ማፊያ ቡድን በተናገርክ ቁጥር በስሙ የሚነግዱበትን ህዝብ ተሳደብክ ይሉሃል። በእርግጥ እነሱ እንዳሉት ተሳድበህ ቢሆን እንኳን ወልዶ ባሳደገ ህዝብ ከመነገድ አይብስም። እውነት ለመናገር ህወሓትን አምርረው የሚጠሉት ሰዎች ለትግራይ ህዝብ ከህወሓቶች አስር እጥፍ የሚበልጥ ፍቅርና ክብር ያላቸው ናቸው። የትግራይን ህዝብ ምንም ያህል ብትጠላው የህወሓትን ያህል ጠላት አታፈራለትም። ይህ የማፊያ ቡድን ለትግራይ ህዝብ ያተረፈለት ነገር ቢኖር ጥላቻና ጠላት ነው። አሁንም ቢሆን ህወሓት በህዝብ ላይ ጦርነትና ዕልቂት እንዲመጣ እየፀለየ ነው። ህወሓት ወደ ስልጣን የመጣው የሃውዜንን ህዝብ አስጨፍጭፎ ነው። የኤርትራን ጦር ያሸነፈው የኣይደር ህፃናትን አስጨፍጭፎ ነው። ባድመ ላይ 70ሺህ ወታደሮች የሞቱበትን የደም መሬት ለወራሪው ሃይል በነፃ ያስረከበ ከሃዲ ነው። በጎንደር፣ ቆቦና ወልዲያ የትግራይ ተወላጆች ላይ ብሔር ተኮር ጥቃት ተፈፅሟል እያለ የአዞ እምባ ሲያነባ የነበረው ራሱ ገድሎና አፈናቅሎ ነው። አሁን ላይ እያደረገ ያለው በተመሣሣይ መንገድ ህዝብን ጨፍጭፎና አስጨፍጭፎ ስልጣን መቆጣጠር ነው! በእርግጥ ከህወሓት ጋር መደመር ከፋሽስት ኢጣሊያ ጋር አብሮ እንደመስራት ይቆጠራል። ከህወሓት ጋር ጥምረት ለመመስረት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖች ሀገራቸውን ከከዱ ባንዳዎች አይለዩም። ከህወሓቶች የሚደርስበትን በደልና ጭቆና በመፍራት አንገትን ደፍቶ መኖር በጠላት ወረራ ግዜም
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለኦሮሞ ተወላጅ ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ሊታደል ነው

(ስዩም ተሾመ) ለኦሮሞ ተወላጅ ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ሊታደል ነው!! ብሔርተኛ ሲባል “ራስ ወዳድ ጥቅመኛ ነው” የምላችሁ ለዚህ እኮ ነው። በአርከበ ዕቁባይ ዘመን የትግሬ ብሔርተኛ ከትግራይ ትምህርት ቢሮ ነቅሎ መጥቶ አዲስ አበባ መስተዳድር ውስጥ ከተሰገሰገ በኋላ የከተማውን ነዋሪ ግጦት ሄደ።  በታከለ ኡማ ዘመን ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኛ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች መልሶ ለመጋጥ እንዲህ አሰፍስፏል። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ባወጣው ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ላይ “የታደሰ የአ/አ መታወቂያ መያዝ” እንደ መስፈርት ተቀምጧል። ከታች በምስሉ ላይ ያለው በኦሮምኛ የተፃፈ መልዕክት በተጠቀሰው ክፍት የሥራ ቦታ ለሚያመለክቱ የኦሮሞ ተወላጆች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ለማደል በስልክ ቁጥር 0921879712 ላይ እንዲደውሉ ጥቆማ ይሰጣል። የዚህን ስልክ ባለቤት ጨምሮ በዚህ ህገወጥ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ተጠያቂ ካልሆኑ ከከንቲባ ፅ/ቤት እስከ ቀበሌ ድረስ እየተሰራ ያለው ወያኔን ለመተካት መሆኑን በተጨባጭ ያረጋግጣል። ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ በሚስጥር ሲተላለፍ የነበረው መልዕክት የአማርኛ ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል። ************************************************ No photo description available.የአ/አ (የፊንፊኔ ) ከተማ አስተዳደር በሁሉም የትምህርት መስክ አምስት ሺህ ሰዎችን አወዳድሮ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሥራ ማስታወቂያ በማውጣት ገልጿል፣ የምዝገባ ቀን 2/3/2012 መመዝገቢያ ቦታ አዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ አስፈላጊ መመዘኛዎች — በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ — በ2010 እና 2011የተመረቃችሁ ብቻ — የሥራ ልምድ 0 ዓሠት አንድ ተወዳዳሪ ይዞ መገኘት ያለበት የ10ኛና 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት የ8: 10 12ኛ ክፍሎች ካርድ ኦርጅናልና
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከባድ ሚስጥራዊ መረጃ፡- ጄ/ል ሳሞራ ዬኑስ በሱዳን 8ሺህ ወታደር እያሰለጠኑ ነው!

በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ከሚፈፀሙ የተቀናጁ የወንጀል ተግባሮች፣ የብሔር ግጭቶች፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ወዘተ በስተጀርባ የህወሓቶች እጅ እንዳለ ስንናገር ለአንዳንዶች ውሸት ይመስላቸዋል። በእርግጥ ለህወሓት አባላትና ደጋፊዎች በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ መረጃ ማቅረብ ቀርቶ ድርጊቱ ከዓይናቸው ስር የተፈፀመ ቢሆን እንኳን አምነው ለመቀበል ይቸግራቸዋል። ምክንያቱም እንዲህ ያለ የማፍያ ቡድን አባልና ደጋፊ መሆንን አምኖ ከመቀበል ይልቅ በተግባር ያዩትን እውነት መካድ ይቀላቸዋል። ነገር ግን ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል ቢሆን በተደጋጋሚ የህወሓቶችን እኩይ ተግባራት የሚያሳዩ መረጃዎች ሲቀርቡለት በሙሉ ልብ አምኖ ለመቀበል ይቸግረዋል። ምክንያቱም ህወሓት ጨቋኝና ዘራፊ የሆነ የፖለቲካ ቡድን እንጂ የተደራጀ የማፍያ ቡድን እንደሆነ በግልጽ መገንዘብ ተስኖታል። ሆኖም ግን በተደጋጋሚ የሚደርሱን ሚስጥራዊ መረጃዎች የሚያሳዩት ቢኖር ህወሓት ትክክለኛ የማፍያ ቡድን መሆኑን ነው። ዛሬም የደረሰን ሚስጥራዊ መረጃ ይህንን እውነት የሚያረጋግጥ ነው። በዛሬው ዕለት የደረሰን ሚስጥራዊ መረጃ አንድ ማንነቱ ያልተገለፀ የደህንነት ሰራተኛ የህወሓቶችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ያዘጋጀው ሪፖርት ነው። በዚህ መሰረት ህወሓት ሱዳን ውስጥ ወታደራዊ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ ከፍተው ወደ 8ሺህ ሰራዊት በድብቅ እያሰለጠኑ እንደሆነ፣ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖችን መቀሌ ላይ በመሰብሰብ እየሸረቡት ያለው ሴራ፣ መቀሌ ላይ የመሸገው የህወሓት ማፊያ ቡድን በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማደናቀፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም አንዳንድ የደቡብ ልሂቃን ከህወሓት ጋር በመመሳጠር በተለይ በወላይታ ዞን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት እየሰሩት ያለው ስራ በሪፖርቱ ተካትቷል። ይህ ሪፖርት በአጠቃላይ ሰባት ገፆች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ አምስቱ ገፅ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጃዋር እና ህወሓት: ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር “አለማወቅ” ነው። ይህን ስል ለአንዳንዶች ንቀት አሊያም እብሪት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ስለ እኔ የሚኖራችሁ ስሜት ያነሳሁትን ሃሳብ ቅንጣት ያህል አይቀይረውም። ምክንያቱም እዚህ ሀገር ያለው መሰረታዊ ችግር አላዋቂነት ነው። አዋቂ ማለት ጠያቂ ነው። ምንም ነገር ሲሆን “ምን? የት? እንዴት? ለምን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ያነሳል። ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ሲያገኝ እርምጃ ይወስዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ጥያቄ የሚጀምረው ከድርጊት በኋላ ነው። በተለይ የዛሬ ትውልድ የፊት ገፅታሀን የሚያጣራው አንገትህን በሜንጫ ቆርጦ ከጣለ በኋላ ነው። ለምሳሌ አቶ ጃዋር መሃመድ በፌስቡክ ገፁ ላይ “ተከብቤያለሁ” ብሎ ሲፅፍ በዚያ ውድቅት ሌሊት ወጣቱ ድንጋይና ፌሮ ይዞ መሮጥ ከመጀመሩ በፊት “ጃዋር ማንና የት ነው? ጃዋር ለምንና እንዴት ነው የተከበበው?” ብሎ መጠየቅ ነበረበት። ይህን ቢያደርግ ኖሮ ያ ሁሉ መከራና ሁከት አይከሰትም። የ86 ሰዎች ህይወት በከንቱ አይቀጠፍም ነበር። ጥያቄ መጠየቅ ስንጀምር እውነታው ይፋ ይወጣል። የጃዋር አጋች-ታጋች ድራማ ውሸት መሆኑን ካወቅን ሁከትና ብጥብጥ የሚነሳበት ምክንያት የለም። ምክንያቱም ጃዋር መሄመድ ትውልዱ ኢትዮጵያ ይሁን እንጂ ዜግነቱ አሜሪካዊ ነው። የተከበበው ደግሞ ባሌ ወይም ነገሌ ሳይሆን አዲስ አበባ ቦሌ ነው። ቀጣዩ ጥያቄ “ማን ከበበው? ለምንና እንዴት ተከበበ?” የሚል አይደለም። ከዚያ ይልቅ ጥያቄው መሆን ያለበት “የአሜሪካ ኢምባሲ ከአቶ ጃዋር መኖሪያ ቤት ምን ያህል ይርቃል?” የሚል ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ ኢትዮጵያ እንደገባ በማንኛውም አግባብ የማይቋረጥ ወይም የማይጠለፍ ቀጥተኛ የስልክ መስመር ይሰጠዋል። ይህ ስልክ ለአደጋ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በእነ ጃዋር መሃመድ የተዘረጋው ስውር እጅ !

በእነ ጃዋር መሃመድ የተዘረጋው ስውር እጅ ! በአዲስ አበባና በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የሚደርሱትን ጥቃቶች የተመለከተ ሰው በስውር ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች እንዳሉ ይታዘባል። አቶ ታዬ ደንደዓ አምቦን ለመበጥበጥ ከ 10 በላይ ሙከራዎች መደረጋቸውን የጠቀሰበት ጽሁፍ፣ ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ ባወጡት መግለጫ “ይህ ሁሉ ለምን እንደመጣብን እናውቃለን። ከዚህ የበለጠ ፈተና ቢያጋጥመንም እንኳን የጀመርነውን ጉዞ አናቋርጥም” ማለታቸው፣ በተደጋጋሚ በባልደራሱ ሊ/መንበር እስክንድር ነጋ ላይ የሚደርሰው ጥቃት፣ ጃዋር ሙሃመድ “በሃይልም ቢሆን አያሸንፉንም” በማለት በትዕቢት የተናገረው ንግግር፣ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባል “ ሲ ኮማንዶ በሚል የመከላከያ አባላት መደረጀታቸውን መግለጹ እንዲሁም በመሳሪያ ሃይል የታገዘ ተደጋጋሚ ዘረፋ መፈጸሙና የመሳሰሉት ድርጊቶች፣ በስውር የሚንቀሳቀስ ( ሱ) ጸረ-መንግስት የሆነ ( ኑ) የኦሮሞ ድርጅት (ቶች) መኖሩን ወይም መኖራቸውን የሚያመልክት ነው። ይህ ስውር ሃይል በአንድ የዕዝ ሰንሰለት የሚመራ ይሁን አይሁን ማወቅ ባይቻልም ጸረ-አብይ፣ ጸረ-ኢዜማ፣ ጸረ-አማራ እና በአጠቃላይ ጸረ አንድነት አቋም እንዳለው ከንግግሩና ከድርጊቱ መታዘብ ይቻላል ። በዚህ ስውር ሃይል ውስጥ የተወሰኑ የደህንነት፣ የመከላከያ፣ የፖሊስ እንዲሁም የኦዴፓ አባላት እንዳሉ፣ ጃዋርን የመሳሰሉ አክቲቪስቶችም እንደ አገናኝ ድልድይና ማዕከል ሆነው እያገለገሉ እንደሆነ እረዳለሁ። ይህን ስውር ሃይል በስውር የሚከታተልና የሚያዳክም፣ ምናልባትም በመንግስት ደህንነት ስር የተዋቀረ ሌላ ስውር ሃይልም እንዳለ ይሰማኛል። ለሁለቱም ስውር ሃይሎች የሚሰሩ 5ኛ ረድፈኞች እንዳሉም ማየት ይቻላል። መረጃዎችን ከአንዱ ወስደው ለሌላው ስለሚያቀብሉም አንደኛው ሃይል አሸንፎ እንዳይወጣ እንቅፋት የሆኑበት ይመስለኛል። ጸረ መንግስት የሆነው ስውር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሽብር ፖለቲካ፡- “እኔ ትክክል ነኝ፣ አንተ ሟች ነህ!”

የሀገራችን ፖለቲካ ጭምልቅልቅ ብሏል። ሁሉም በራሱ እንደ መጣከት ይናገራል፤ በእውን ከሆነው ይልቅ የመሰለውን ይፅፋል። ነባራዊ ሁኔታውን ሳያገናዝብ በቢሆን ዓለም እሳቤ ይጠይቃል፣ ያስባል፣ ይወስናል፣ ይመራል፣… ሁሉ ነገራችን መላ-ቅጡ ጠፍቷል። ይሁን እንጂ ነባራዊ እውነታን ከመቀበል ውጪ ሌላ ምርጫና አማራጭ የለንም። ምክንያቱም እውነትን በራሳችን ፍላጎትና ምርጫ መቀየር ሆነ ማስቀረት አንችልም። በእርግጥ ቀድሞ የነበረው፣ አሁን ያለውና ወደፊት የሚኖረው ነገር አንድና ተመሳሳይ ነው። ሁለትና ሦስት ዓይነት እውነት የለም። በተጨባጭ የነበረው፣ ያለውና የሚኖረው አንድ ዓይነት እውነት ነው። ልዩነቱ በእኛ ሃሳብና አስተሳሰብ፣ ባለን ዕውቀትና ግንዛቤ፣ በምናራምደው አቋምና አመለካከት ምክንያት የተፈጠረ ነው። በጋራ መነጋገርና መግባባት ካለብን፣ ሰላምና መረጋጋት ከፈለግን፣ ለውጥና መሻሻል ካስፈለገን፣… ሌላ ሳይሆን እኛ ነን መቀየር፥ መለወጥ ያለብን። በዚህ መሰረት ከራሳችን አልፈን የሌሎችን ሃሳብና አስተሳሰብ ለመረዳት ጥረት ማድረግ፤ ያለንን ልምድና ዕውቀት ለሌሎች ማካፈል፤ የሌሎችን አቋምና አመለካከት በትዕግስት ማስተናገድ፣ የራሳችንን አቋምና አመለካከት በኃይል ለመጫን ከመሞከር ይልቅ በምክንያት ማስረዳት አለብን። ለዚህ ግን በቅድሚያ ነባራዊ ሁኔታን መገንዘብ፣ የራሳችንን አቋምና አመለካከት መፈተሸ፣ ማዳበርና ማሻሻል፣ እንዲሁም የሌሎችን ሃሳብና አመለካከከት በዝርዝር ማጥናትና መረዳት ይኖርብናል። የሀገራችን ፖለቲካ ውጥንቅጡ የወጣው እዚህ ጋር ነው። በእውን ስላለው ነባራዊ ሁኔታ በቂ ግንዛቤ የለንም፣ ያለንን ሃሳብና አመለካከት በምክንያታዊ ዕውቀትና በተጨባጭ ማስረጃ ለማስደገፍ ሆነ ለማሻሻል ጥረት አናደርግም። በዚህ ላይ ደግሞ የሌሎችን ሃሳብና ጥያቄ ከመረዳት ይልቅ በጅምላ ለመፈረጅና ለማጣጣል እንጣደፋለን። በእንዲህ ያለ ሁኔታ ታዲያ እንዴት መነጋገርና መግባባት ይቻላል? ሰላምና መረጋጋት ከወደዬት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የውስኪ ቤት ወሬ:- ጌታቸው ረዳ እና የሲዳማው እስረኛ – ስዩም ተሾመ

ህወሓቶችን በቀዳዳ አጮልቀን ማየታችንን ቀጥለናል። ከወትሮው በተለየ መልኩ የህወሓቶች ቅጥር ግቢ በጣም ተረብሿል። ከሁሉም በላይ ደግሞ አንድ የቤተሰቡ አባል ክፉኛ ተሸብሯል። ዝም ብሎ ይቆዝምና በድንገት ብስጭት ያላል። እንደ እብድ ብቻውን ማውራት ጀምሯል። ዝም ብሎ ይቆዝማል። በቆዘመበት ለብቻው ያጉተመትማል። ከዚያ በድንገት እጁን ካወራጨ በኋላ በአቅራቢያው እብደቱን የሚታዘብ ሰው አለመኖሩን ለማረጋገጥ ዙሪያ ገባውን ይቃኛል። ከዚያ ተመልሶ መቆዘም ይጀምራል። ለዚህ የዳረጉትን ሰዎች በስም እየጠራ ይሳደባል። ወዲያው ደግሞ ሃፍረት ይሰማዋል። መሃል አደባባይ ላይ እርቃኑን የቆመ ይመሰልል፤ በአንድ እጁ ሃፍረተ-ስጋውን በሌላኛው ደግሞ ዓይኑን ለመሸፈን ይጥራል። በዙሪያው ቆመው ከሚሳለቁ ሰዎች ሃፍረተ-ስጋውን ለመሸፈን የሚያደርገው ጥረት ሰማይን በነጠላ እንደ መሸፈን ይሆንበታል። ሰውዬው ሁለት ዓይኑን በእጁ ሲሸፍን ማየት የማይፈልገው ነገር ቀድሞ የባሰ እየጨመረና እየሰፋ፣ ይበልጥ እየጎላና እየገዘፈ ይመጣል። ዓይኖቹን ሰሸፍን ከሚሸሸው ስሜት ጋር ፊት ለፊት ይጋፈጣል። ለካስ የፊት ዓይን ሲጨፈን የኋላ ዓይን ይከፈታል። የኋላ ዓይን በውስጣችን ያለውን ጥሩና መጥፎ ስሜት የምናይበት ዓይነ-ህሊና ነው። ስለዚህ ሰውዬው የፊት ዓይኑን ሲጨፍን ቅሌትና ውርደቱን በዓይነ-ህሊናው ማየት ይጀምራል። ከምንግዜውም በላይ የፀፀትና ሽንፈት ስሜት አጥንቱ ድረስ ዘልቆ ይሰማዋል። እንደ ቁርጥማት የሚያደርገውን ያሳጣዋል፤ እንደ ጎን ውጋት ቀስፎ ይይዘዋል። ከዚያ የቀኝ እጁን አይበሉባ በኃይል በማወናጨፍ ሰቅዞ የያዘውን ውጋትና ቁርጥማት ለማስወገድ ይሞክራል። ከዚያ የሚታዘበው ሰው መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ዙሪያ ገባውን ይቃኛል። ወዲያው ደግሞ ተመልሶ መቆዘም ይጀምራል። ለብቻው ያልጎመጉማል። ይሄ ሁሉ ሲሆን እኛ አጮልቀን እያየን ነው። አጮልቀን ካየነው በመጠኑ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር አብይ Vs ኦቦ ጃዋር ነው : “ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ” ወይም እንደ ድንጋይ ስትቀጠቀጥ ትኖራታለህ !

ዶ/ር አብይ Vs ኦቦ ጃዋር ነው : “ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ” ወይም እንደ ድንጋይ ስትቀጠቀጥ ትኖራታለህ ! (ስዩም ተሾመ) አሁን ያለን አማራጭ ሁለት ናቸው፤ ወደፊት መራመድ ወይም ባለንበት መርገጥ። እንደ ሀገር ለወደፊት መራመድ የሚቻለው የሀገሪቱን ሰላምና አንድነት ማስከበር እና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመዘርጋት መሰረት ሲጣል ነው። ባለንበት መርገጥ ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብና ታሪክ አምርሮ የሚጠላ ፅንፈኛ ቡድን የብሔር ግጭትና ብጥብጥን እንደ መሳሪያ ተጠቅሞ የፖለቲካ ስልጣኑን በመቆጣጠር እና ልክ እንደ ህወሓት የራሱን የበላይነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው። በዚህ መሰረት የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም በማስከበር በእኩልነት መርህ ላይ የተመሰረተ መንግስታዊ ስርዓት የመዘርጋት ህልም ያለው የኦሮማራ ጥምረት በአንድ በኩል፣ አሁን ያለውን የብሔር አፓርታይድ በማስቀጠል የራሱን የበላይነት ማረጋገጥ የሚያሻው የህወሓት-ኦነግ/ጃዋር ጥምረት በሌላ በኩል ሆነው ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል። ሁለቱም ወገኖች ፈፅሞ የማይታረቅ ህልምና ዓላማ ያላቸው ናቸው። ፍጥጫው፤ በእኩልነትና የበላይነት፣ በአብሮነትና የበላይነት፣ በሰላምና ጦርነት፣ በአፓርታይድና ዴሞክራሲ፣ ለውጥን በማስቀጠልና በመጥለፍ፣ በዶ/ር አብይ እና በኦቦ ጃዋር መካከል ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ፍጥጫው በድርድር አሊያም በሽምግልና የሚፈታ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በብዙሃኑ ዘንድ ድጋፍና ተቀባይነት ያገኘው ወገን አሸናፊ በመሆን የፖለቲካ ስልጣኑን ይቆጣጠራል። ብዙሃኑ የሕብረተሰብ ክፍል ማለት ደግሞ ሌላ ሳይሆን እኔ፣ አንተ፣ አንቺ፣ እኛ ነን። እኛ ድጋፍና ይሁኝታ የሰጠነው ወገን የፖለቲካ ስልጣኑን ይይዛል። እኛ በቸልታ ዳር ቆመን ስናለምጥ፣ የሌሎችን ውትወታ ስንጠበቅ አሊያም ደግሞ እንደ ከዚህ ቀደሙ በማንአለብኝነት ስናለምጥ በጃዋር የሚመራው ፅንፈኛ ቡድን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ ውህደት እና የህወሓት “አጥፍቶ-መጥፋት”

(ስዩም ተሾመ) ባለፉት 45 አመታት ህወሓት የአቅም እንጂ የአቋም ለውጥ አላደረገም። እንደ ኢዲዩና ኢህአፓ ካሉ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች ቀርቶ እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ እና ኢ/ር ግደይ ዘርዓፂዮን ካሉ የድርጅቱ መስራቾች ጋር የነበረውን የሃሳብ ልዩነት በሰላም መፍታት አልቻለም። ጠፍጥፎ ከሰራቸው የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር ሆነ ራሳቸው ጠፍጥፈው ከሰሩት ኢህአዴግ ጋር ያላቸውን የአቋም ልዩነት በውይይትና ድርድር ለመፍታት አልሞከሩም። በአጠቃላይ ህወሓቶች የተለየ ሃሳብና አመለካከት ያለውን ግለሰብ፣ አመራር ወይም ቡድን በእስር፣ ስደት ወይም ሞት ደብዛውን ከማጥፋት ባለፈ ሌላ ዘዴ ወይም መፍትሄ አያውቁም። ኢህአዴግ ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ የውህደት ጥያቄ ሲያነሱ የነበሩ መሆናቸው ዘንድሮ ውህደቱን ከመቃወም አላገዳቸውም። እንደ አንድ የፖለቲካ ቡድን ካየነው የህወሓትን አቋምና አመለካከት መረዳትና መገመት በጣም አስቸጋሪ ነው። የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ሆኖ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድር፣ በጠላትነት የፈረጀውን ህዝብ ለመምራት የሚጥር፣ በከባድ ጦርነት ከፍተኛ ዋጋ ተከፍሎበት ያስመለሰውን ሉዓላዊ መሬት ለወራሪው ኃይል አሳልፎ የሚሰጥ፣ የራሱን ወደብ ለጎረቤት ሀገር አሳልፎ ሰጥቶ በውድ ዋጋ የሚከራይ፣ ሐዋሳ ላይ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ የመረጠውን የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሳይውል-ሳያድር በጠላትነት የሚፈርጅ፣ አሁን ደግሞ ላለፉት 30 አመታት ሲጠይቅ የነበረውን የኢህአዴግ ውህደት የህልውና አደጋ ነው በሚል አምርሮ የሚቃወም ነው። በዚህ መሰረት የህወሓት አቋምና ውሳኔ ፍፁም የተደበላለቀና እርስ-በእርስ የተጠላለፈ እንደመሆኑ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት አቋምና አመለካከቱን ማወቅ ሆነ መገመት አስቸጋሪ ነው። እንደ ህወሓት/ኢህአዴግ ያለ ወጥ የሆነ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት የሌለው ቡድንን መቃወም ሆነ መደገፍ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አስደንጋጭ ሚስጥራዊ መረጃ፦ በህወሓቱ ጌታቸው ረዳ እና በግብፁ የደህንነት ኃላፊ የተዘጋጀው ፕሮፖዛል! (ስዩም ተሾመ)

አስደንጋጭ ሚስጥራዊ መረጃ፦  በህወሓቱ ጌታቸው ረዳ እና በግብፁ የደህንነት ኃላፊ የተዘጋጀው ፕሮፖዛል! (ስዩም ተሾመ) Image may contain: 4 people, people standing and suit በምስሉ ላይ የሚታዩት አራት ሰዎች ስም፤ ከግራ ወደ ቀኝ፡- 1ኛ- የግብፅ ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ ካሊድ ፋውዚ (khalid Fawzy)፣ 2ኛ- ፍልስጤማዊው መሃመድ ዳህላን (Mohammed Dahlan)፣ 3ኛ- ለግዜው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ፣ 4ኛ- የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆነው አቶ  ጌታቸው ረዳ ካሕሳይ ናቸው። መሃመድ ዳህላን የግብፅ ድህንነት መስሪያ ቤት ቅጥረኛ ሲሆን ነዋሪነቱን በተባበሩት አረብ ኢሜሬት ነው። ይህ ግለሰብ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበረበት ወቅት አደራዳሪ መስሎ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ነበር። በዚህ አጋጣሚ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የፈጠሩት ወዳጅነት ከዱባይ ከተማ እስከ ካሪቢያን ደሴቶች ድረስ ለሽርሽር እስከመሄድ አድርሷቸዋል። በሁለቱ መካከል ያለው ወዳጅነት ከራሳቸው አልፎ በምስሉ ላይ ከምታዩት የግብጹ ደህንነት ኃላፊ ካሊድ ፋውዚ (khalid Fawzy) ጋር ወዳጅነት እንዲመሰርቱ አስችሏቸዋል። የአራቱ ሰዎች ምስል ያለበት ፎቶ የተነሳው እዚሁ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ውስጥ ነው። ……. …..ከጥንት ዘመን ጀምሮ አንድ ያልተቀየረ የግብፃዊያን ታሪክ ቢኖር ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ያደረጉት ሙከራ በሙሉ በሽንፈት መጠናቀቁ ነው። ህወሓቶች ከግብፃዊያን ጋር በመመሳጠር የኢትዮጵያን ጥቅምና ሉዓላዊነት የሚፃረር ፕሮፖዛል ማዘጋጀታቸው ግን ሀገርን ከመሸጥ ተለይቶ አይታይም። በተለይ የህወሓት/ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆነው አቶ ጌታቸው ረዳ ከውጪ ሀገር ደህንነት ኃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ለፈጸመው አሳፋሪ ድርጊት በሀገር ክህደት ሊጠየቅ ይገባል።(ስዩም ተሾመ)
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና ጋዜጠና እስክንድር ነጋ ተገናኝተው የአዲስ አበባን ጉዳይ ሊወያዩ ነው – ስዩም ተሾመ

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት/ባልደራስ ዛሬ በራስ ሆቴል ሊያደርግ ያቀደው ሰብሰባ እንዳይካሄድ መከልከሉን አስመልክቶ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አንዲት ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ነገር ግን ወዲያው ለጠ/ሚኒስትር ቢሮ ቅርበት ያለው አንድ የመንግስት ሃላፊ ስልክ ደውሎ ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ ሰጥቶኛል። በስልክ የነገረኝን መረጃ በፌስቡክ እንዳወጣው ጠይቄው ፍቃደኛ በመሆኑ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ ዛሬ በራስ ሆቴል ሊያካሂድ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲቀር የተደረገው በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ትዕዛዝ ነው። ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ አካላዊ ጥቃት ለማድረስ የተጠነሰሰ ሴራ መኖሩ በደህንነት መስሪያ ቤቱ ስለተደረሰበት ነው። ባለፈው ሳምንት በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ፊርማ በማሰባሰብ የሀገሪቱ መንግስት ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ልዩ ጥበቃ እንዲያደርግለት መጠየቃቸው ይታወሳል። በዛሬው እለት ሊካሄድ በታሰበው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ደግሞ ህጋዊ እውቅና እና ፍቃድ ያላቸው ጋዜጠኞች ብቻ የሚታደሙበት አይደለም። ከዚያ ይልቅ ማንኛውም ግለሰብ በቦታው ተገኝቶ ለመታደም ይችላል። ይህ ደግሞ በእስክንድር ነጋ ላይ ጥቃት ለማድረስ ዓላማ ላላቸው ሰዎች ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። በዚህ መሰረት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ሊቃጣ የሚችለውን አደጋ ለማስቀረት ሲባል የዛሬው መግለጫ እንዲሰረዝ መደረጉን ከላይ የተጠቀሱት የመንግስት ኃላፊ ነግረውኛል። ከዚሁ ጋር አያይዤ “በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ በመንግስት በኩል ምን ለማድረግ ታቅዷል?” በሚል ላቀረብኩላቸው ጥያቄ ሃላፉው ምላሽ ሰጥተውኛል። በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት/ባልደራስ በየትኛውም ግዜና ቦታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሆነ ስብሰባ የማድረግ መብት እንዳላቸው ገልፀዋል። ነገር ግን ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው፣ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቁም ነገሩ የብሮድካስት ባለስልጣኑ እንደ ቀድሞ ማስፈራራት እንደማይችል ማወቁ ላይ ነው (ስዩም ተሾመ)

ከብሮድካስት ባለስልጣን ለLTV እና ቤቲ ታፈሰ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያና የቪዲዮ ምስሉን ከኢንተርኔት ላይ እንዲያወርዱ መደረጋቸውን የሰማሁት ከሌላ ሳይሆን ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከተው የጣቢያው ሰራተኛ ነው። ይህ ሰራተኛ ዛሬ ልክ ከቀኑ 8፡41 ላይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንደከሰሳቸውና የጣቢያውን ኃላፊ ወደ ቢሮ ጠርቶ ቃለ-ምልልሱ “ለአንድ ወገን ያደላ ነው! የቪዲዮ ምስሉ በአስቸኳይ ይውረድ” ብሎ እንዳዘዘው ነገረኝ። እኔም “በቀጥታ እንዲመጡ ንገሯቸው! ለጣቢያው ጉዳዩን አስመልክቶ በደብዳቤ ያሳውቋችሁና እናንተም በደብዳቤ ምላሽ ስጡ” የሚል ምክር ሰጠኋቸው። ይህን ያልኩበት ምክንያት እንዲህ ያለ በእብሪት የተሞላ ትዕዛዝና ማስጠንቀቂያ በጓሮ በር ያስተላለፈው የብሮድካስት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ኃላፊ ጉዳዩ አደባባይ ሲወጣ አንዳች ነገር ትንፍሽ እንደማይል እርግጠኛ ስለነበርኩ ነው። አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ኃላፊ በጣቢያው ሥራ ላይ በቀጥታ ጣልቃ-ገብቶ እንዲህ አድርጉ፣ ያንን ቪዲዮ አውጡ ሌላኛውን አውርዱ የማለት ስልጣን የለውም። በመስሪያ ቤቱ መደበኛ አሰራር እንዲህ ያለ ትዕዛዝ ሆነ ማስጠንቀቂያ አይሰጥም። ስለዚህ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ የጣቢያውን ሰራተኛ ቢሮ ጠርቶ በወረቀት ላይ ማስፈር የማይችለውን ትዕዛዝና ማስጠንቀቂያ በቃሉ ተናገረ። በዚህ የተደናገጡት የጣቢያው ኃላፊዎች የቃለ-ምልልሱን ቪዲዮ ከኢንተርኔት ላይ አወረዱት። ነገሩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ወጥቶ የብዙዎች መነጋገሪያ ሲሆን ግዜ ቀድሞ በማንአለብኝነት ሲያስጠነቅቅና ሲያስፈራራ የነበረው ሰውዬ ወደ ጣቢያው ደውሎ “የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እስካልደረሳችሁ ድረስ የብሮድካስት ባለስልጣን ማስጠንቀቂያ ሰጠን ብላችሁ መናገር አትችሉም” ብሎ ሊለማመጥና ሊያስፈራራ እንደሚችል የታወቀ ነው። የጣቢያው ኃላፊዎች ይህን በፍርሃት ተቀብለው “ማስጠንቀቂያ አልተሰጠንም” ብለው ለቢቢሲ ቢናገሩም የቃለ-ምልልሱን ቪዲዮ ከኢንተርኔት ላይ ማውረዳቸውን ግን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብይ ተመርጧል፣  ለማ አሸንፏል! (ስዩም ተሾመ)

አብይ ተመርጧል፣  ለማ አሸንፏል! (ስዩም ተሾመ) ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሲሆን ያሸነፈው ለማ መገርሳ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የህዝባዊ ንቅናቄው ባለቤት የኦሮሚያ ቄሮዎች ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎ በኢህአዴግ መንግስት ውስጥ የለውጥ ንቅናቄ የተጀመረው በለማ ቡድን (Team lemma) አማካኝነት ነው፡፡ ስለዚህ በፖለቲካና ኢኮኖሚው ረገድ ስር-ነቀል ለውጥ እንዲመጣ እየጠየቀ ያለ ማህብረሰብ እና ይህን ጥያቄ ተቀብሎ ለማስተናገድ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ያለው አመራር አለ፡፡ ነገር ግን የለማ አመራር የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ሁለት መዋቅራዊ ችግሮች ነበሩበት፡፡ አንደኛ፦ በማንኛውም አግባብ የለውጡን ንቅናቄ ለመቀልበስ ጥረት የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ የሆነ የፖለቲካ ቡድን (ህወሓት) የለማን እጅ ጠምዝዞ ይዞት ነበር፡፡ ሁለተኛ፦ በአገልጋይነት እና ኪራይ ሰብሳቢነት መስፈርት ተመርጠው በክልሉ የሲቪል ሰርቪስ መዋቅር እና በድርጅቱ ኦህዴድ ውስጥ የተሰገሰጉ ካድሬዎች የሚፈለገው ለውጥ የሞት ያህል ያስፈራቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ በክልሉ ውስጥ ካሉት 500ሺህ ሲቪል ሰርቫንቶች 100ሺህ (20%ቱ) በተጭበረበረ የትምህርት ዶክመንት ተቀጥረው የሚሰሩ ናቸው፡፡ አንደኛ ላይ የተጠቀሰው እንቅፋት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የለማን ቡድን ለማስወገድ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል የለማ አመራር ሁለተኛውን እንቅፋት ለመፈንቀል ሙከራ ሲያደርግ ካድሬዎቹ ከወላጃቸው ህወሓት/ኢህአዴግ ጋር በመመሳጠር ለማን እጁን ጠምዝዘው ለመጣል ይሞክራሉ፡፡ የዶ/ር አብይ መመረጥ ከማንም በላይ የለማን አመራር ጠቅሞታል፡፡ ምክንያቱም የለማ ቡድን እጁን ከፀረ-ለውጥ ቡድኑ አስለቅቋል፡፡ በመሆኑም አሁን በነፃነት መወሰን፣ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይችላል፡፡ በአገልጋይነት እና ኪራይ ሰብሳቢነት መስፈርት ተመርጠው በክልሉ መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉትን ሆድ-አደሮች መንጥሮ ማስወገድ ይችላል፡፡ በዚህ መሠረት፣ በክልሉ ህዝብና መንግስት መካከል
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News